Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
በሀሰተኛ መታወቂያ የጋብቻ እና የልጃቸው ልደት ሰርቲፊኬት ለማግኘት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው እንደገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ቤት በቀን 29/1/2017 ዓ.ም በሀሰተኛ መታወቂያ የጋብቻ እና የልጃቸውን ልደት ሰርቲፊኬት ለማግኘት የሞከሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት በከፊል ተመልሷል
***********
በለገጣፎ ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት አምባሳደር ሪል ስቴት፣ አያት ዞን 1፣ ዞን 2 እና ዞን 8፣ መሪ 40/60 ኮንድምኒየም፣ ሰባ ሁለት፣ ከሸገር ዳቦ ወደ ጥሩ መናፈሻ፣ ሳራ አምፖል ፋብሪካ፣ ካራ ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት የተመለሰ ሲሆን፤ በቀሪዎቹ አካባቢዎች ማለትም በለገጣፎ ከተማ፣ 44 ማዞሪያ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ገዋሳ እንዲሁም የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል ኃይል ለማገናኘት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
ኤሌክትሪክ ለተመለሰላችሁ ደንበኞቻችን በትዕግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋና እያቀረብን፤ አሁንም የኃይል አቅርቦቱ ባልተመለሰባቸው አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ጥገናው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አቅርቦቱ ወደቦታው እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎትተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት በከፊል ተመልሷል
***********
በለገጣፎ ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት አምባሳደር ሪል ስቴት፣ አያት ዞን 1፣ ዞን 2 እና ዞን 8፣ መሪ 40/60 ኮንድምኒየም፣ ሰባ ሁለት፣ ከሸገር ዳቦ ወደ ጥሩ መናፈሻ፣ ሳራ አምፖል ፋብሪካ፣ ካራ ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት የተመለሰ ሲሆን፤ በቀሪዎቹ አካባቢዎች ማለትም በለገጣፎ ከተማ፣ 44 ማዞሪያ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ገዋሳ እንዲሁም የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል ኃይል ለማገናኘት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
ኤሌክትሪክ ለተመለሰላችሁ ደንበኞቻችን በትዕግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋና እያቀረብን፤ አሁንም የኃይል አቅርቦቱ ባልተመለሰባቸው አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ጥገናው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አቅርቦቱ ወደቦታው እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ። ዛሬ ማለዳ በጽህፈት ቤታችን ተቀብያቸው በተለያዩ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዛሬ ምሽት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን(CAF) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ፤ምክትል ፕሬዝዳንቱን እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ተቀብለን የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን አስጎብኝተናቸዋል::
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መመስረት የአንበሳውን ድርሻ የተጫወተች፣ በዓለም እግር ኳስ መድረክ የአፍሪካ ውክልና እንዲጨምር ትርጉም ያለው ጥረት ያደረገች ሲሆን አፍሪካውያን እንዲሰባሰቡ እና ድምጻቸው ጎልቶ እንዲስማ አፍሪካዊ ወንድማማችነት እንዲያብብም ታሪክ የማይረሳው አስተዋጽዖ አበርክታለች::
አዲስ አበባችን ጽዱና ውብ ምቹ የመኖሪያና የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዲና ለማድረግ እየሰራናቸው ያሉ ስራዎች ፍሬያማ ሆነው መዲናችን የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻነትን ጨምሯል::
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች እንግዶቹን በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንድታስተናግዱ እያልኩ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የጉባኤው ተሳታፊዎች ቆይታቸው ፍጹም ያማረ እና ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን(CAF) 46ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የሚገኙት የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የጉባኤው ተሳታፊዎችን በዓድዋ ድል መታሰቢያ አቀባበል አድርገውላቸዋል::
የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የጉባኤው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአቀባበል መርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል::
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመገኘት እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ስራዎችን
ጎብኝተናል።
በዛሬ ጉብኝታችን የከተማችንን ቁመና የሚመጥን በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ እና በሎጀስቲክ የተደራጀ፤ ከነዋሪዎች ጋር በቅርበት የሚሰራ የፖሊስ ተቋም ለማደራጀት የጀመርነው ስራ ዉጤታማ መሆኑን ተመለከተናል።
እስካሁን ለተገኘው ውጤት በራሴና በከተማዉ ህዝብ ስም እያመሰገንኩ፣ በቀጣይም የሪፎርም ስራው እስከታችኛው መዋቅር እንዲደርስ እና የአገልጋይ ፖሊስ ዲሲፕሊን እየተጠናከረ እንዲሄድ የተጀመረውን ስራ የምንቀጥል መሆኑን ማሳወቅ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ አጠናቆ አስረከበ።
በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን በመከላከልና ለህብረተሰቡን ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ባለሀብቶችን በማስተባበር የአቅመ ደካማ ቤት ማጠናቀቅ ማስረከቡ የሚደነቅ ተግባር ነው ሲሉ ገልጸዋል። ለዚህ በጎ ተግባር ድጋፍና ክትትል ያደረጉና አስተዋጽዖ ያበረከቱ አካላትንም አመስግነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ እንዳሉት ዛሬ የተመረቀው የአቅመ ደካማ ቤት ከዚህ ቀደም ስራዉ የተጀመረዉ የመኖሪያ ቤት ለኑሮ ምቹ ያልነበረ ከመሆኑም በላይ ለአደጋ ተጋላጭና ስጋት የነበረ ቦታ እንደነበረ ጠቅሰዉ በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ ችሏል የቤት ዕድሳት ስራዉ አደጋን ማስቀረት የሚያስችል እንደሆነ አብራርተዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን አንዱዓለም በክፍለ ከተማው በርካታ በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለሀብቶችን በማስተባበር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳትን አጠናቆ በማስረከቡ ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ ኒቆዲሞስ ቡቼ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በዛሬዉ ዕለት ለምርቃት የበቃው የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት የሚያስጠይቀዉን ወጪ ሀብት በማፈላለግ ረገድ ኮሚሽን መ/ቤቱ ላደረገዉ ጥረት እንዲሁም የቤት ዕድሳቱን ወጪ ለሸፈኑት ባለሀብት ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የከተማ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በመገኘት የቤት ምርቃት መርሃ ግብሩን ተገኝተዋል።
Gullele communication-ጉለሌ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከምሁራን እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የተደረገ ውይይት
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
AMN - ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም
ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በለሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 3 መቆዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ማህበር እያስገነባ ባለዉ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።
ለኮሚሽን መ/ቤቱ በደረሰዉ ጥሪ መሰረት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታዉ ፈጥነዉ በመድረስ እሳቱ ሳይስፋፋ በፍጥነት መቆጣጠር ችለዋል።
በእሳት አደጋዉ በመጋዘን ዉስጥ የነበሩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሰዉ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
