Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
አብሮነት!
ወንድማማችነት!
እህትማማችነት!
ህብረብሔራዊ አንድነት!
በመዲናችን አዲስ አበባ
ጥምቀት 2017
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን/ አደረሳችሁ እያልኩ በአሉ የሰላም፣የጤናና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ!
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ!!
ጥምቀት በዓለም ካስተዋወቁን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓሎቻችን አንዱ ነው። የኅብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነው የጥምቀት በዓል ኢትዮዽያዊያን በባህላዊ አልባሳት ደምቀዉ በተለያዩ ቋንቋዎች ሀይማታዊ እና ባህላዊ ትዕይንቶችን የሚያሳዩበት የእኛነታችን መገለጫ በዓል ነው።
በርካታ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዚህ በዓል ላይ የሚታየውን ሀይማኖታዊ ትዕይንት፣ ባህላችንን፣ ዉበታችንን፣ ድምቀታችንን፣ አብሮነታችንን እንዲሁም እሴቶቻችንን ተመልክተዉ ይደነቁበታል።
ጥምቀትን ስናከብር፤ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት፣ ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር፣ ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት እና ለሀገር ገፅታ ግንባታ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ በማጉላት፣ ዉብ እና ደማቅ በሆነ ሁኔታ ሊሆን ይገባል።
በዓሉ አብሮነት ሚጎለብትበት፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የደስታ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
መልካም የጥምቀት በዓል ይሁን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ አሁን ጎንደርን ጨምሮ በመላው ሀገራችን በ11 ከተሞች ተስፋፍቷል።
ይኽ ሰፊ በጎንደር ላይ ያለው ሥራ የፋሲል ግቢ እድሳትን ጨምሮ ለማዕከላዊው የፒያሳ አካባቢ የተደረገ የፍሳሽ ሥርዓት ማሻሻያ፣ የአስፋልት መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራዎች ልማት የተካተቱበት ነው።
ታሪካዊዋ ከተማ ለአመታዊው የጥምቀት በዓል ጎብኝዎችን ለመቀበል በተሰናዳችበት ሁኔታ የታደሰውን የፋሲል ግቢና ከባቢውን የሚያሳይ ምስል እነሆ እንላለን።
The corridor development project that begun in Addis Ababa has now expanded to 11 cities across the country, including Gondar.
This extensive initiative in Gondar includes the restoration of Fasil Ghebbi, upgrades to its center Piassa, improvements to drainage systems, asphalt roads, walkways, and the development of green spaces.
As the historic city prepares to welcome visitors for the annual Timket celebration, here’s a glimpse of the restored Fasil Ghebbi and its newly upgraded surroundings.
#PMOEthiopia
እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ጥምቀት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ኅብረ ብሔራዊ በዓላችን ነው። በሃይማኖታዊነቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት ወርዶ፣ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ እናስብበታለን። ይሄም የጠፋውን አዳም ለመፈለግ የተደረገ ጉዞ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳም በወደቀበት በእያንዳንዱ ዱካ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ ተከትሎ ዋጅቶታል። በዚህም አዳምን ወደ ጥንት ክብሩ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከጥንቱ የበለጠ ክብር ሰጥቶታል።
ይሄም ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚያስተምረን ብዙ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ የወደቀችበት ብዙ ነው። በእያንዳንዱ በወደቀችበት ውድቀት ተከትለን ማንሣት አለብን። የትርክት፣ የሀገረ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የመግባባት ውድቀቶቿን ወደ ትንሣኤዋ መቀየር አለብን።
ክርስቶስ አዳምን ሲያድነው እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ አለብህ አላለውም። አዳም ዐቅም እንደሌለው ያውቃልና። መዳኑን እርሱ ራሱ ሊያደርገው እንደማይችል ያውቃል። ስለዚህ ክርስቶስ ተገብቶ ፈጸመለት።
ኢትዮጵያችን በዘመናት መከራዎች ደክማለች። በዘመናት ድህነትና ኋላ ቀርነት ተጎድታ ዐቅም አጥታለች። እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ ነበረባት የሚለው አሁን ለውጥ አያመጣም። መደረግ ያለበትን እኛ ልጆቿ ዛሬ እናድርገው። ስለ ሀገራችን እኛ ቤዛ እንሁን። ቤተልሔም መወለድ ካለብን እንወለድ። በባሕር መካከል መቆም ካለብን እንቁም። መሰደብ ካለብን እንሰደብ፣ መሰቀል ካለብንም እንሰቀል። ነገር ግን ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያመጣ ይሁን። ዛሬ እያደረግነው ያለነውም ይሄንኑ ነው።
ጥምቀት ባህላዊ በዓላችንም ነው። የኢትዮጵያ የመስክ ላይ ትዕይንት ማቅረቢያ በዓል ነው። መስኩና ወንዙ ይታይበታል። ልብሳችን እና የወግ ዕቃዎቻችን ለዓለም እናሳያለን። የፀጉር አሠራራችንን እና ዜማዎቻችንን እናቀርባለን። ጥምቀት የኢትዮጵያ ባህል የአደባባይ ሙዝየም ነው።
ብዙ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ይሄንን ወቅት ከሚመርጡበት ምክንያቶች አንዱ ይሄ የአደባባይ ሙዝየም ነው። ከገጠር እስከ ከተማ ፤ ከዳር እስከ መሐል፤ ከውጭ እስከ ሀገር የጥምቀት በዓል የእኛነታችን መገለጫ ነው።
ጥምቀት ኅብረ ብሔራዊ በዓልም ነው። የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች ለማየት የፈለገ ሰው አንዱ አማራጩ የጥምቀት አደባባይ ነው። በአንድ አደባባይ ሺህ ዓይነቱን ኀብረ ብሔራዊ ማንነታችንን ማየት ይቻላል። የክት የተባለው የባህል ልብሳችን ይወጣል፤ ታይተው የማያውቁ ጌጣጌጦች ብቅ ይላሉ፤ በጥምቀት የኢትዮጵያን መልከ ብዙ ገጽታ ማየት ይቻላል።
እነዚህን የመሰሉ ዕሴቶቻችንን ስላስረከቡን ቀደምቶቻችንን እናመሰግናቸዋለን። ጥምቀት ከተማን ከገጠር ያገናኛል። ብዙዎች ወገኖቻቸውን ለማግኘት ገጠር ይወርዳሉ። የውጭውንም ከሀገር ቤት ያስተሣሥራል። ሚልዮን ወገኖቻችን ጥምቀትን አብረውን ለማክበር ከውጭ ገብተዋል። ይሄም ኅብረ ብሔራዊ ትሥሥራችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።
የጥምቀትን አስተምህሮ ለሀገር ግንባታ በመጠቀም፤ ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት እና ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር በዓሉን እንድናከብር አደራ እላለሁ።
በድጋሚ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
ጥር 10፣ 2017 ዓ.ም
Boost this post to get more reach for Addis Ababa City Manager's Office.
የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ታቦታት የሚያድሩባቸው ስፍራዎች ላይ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
ጥር 10/2017 ዓ.ም
*****************
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ታቦታት የሚያድሩባቸውና የሚያልፉባቸው ስፍራዎች ላይ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
በዕለቱም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣ የሀይማኖት አበቶችና ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የጥምቀት በዓል ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በአደባባይ የሚያከብረው በዓል መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመዋል። ታቦታቱ የሚያልፉባቸውንና የሚያድሩባቸውን ስፍራዎች ለማፅዳት በቦታው ለተገኙ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
በተጀመረው አግባብ መጨረሻው እንዲያምርና ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ የሚቻለው እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራና በትብብር መስራት ሲቻል መሆኑንም ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ የጥምቀት በዓል ኢትዮጵያዊያን ብቻ የሚሳተፉበት ሳይሆን ከመላው አለም የሚመጡ ቱሪስቶች የሚታደሙበት በመሆኑ እሱን የሚመጥን ተግባራት ማከናወንና በጋራና በትብብር በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ ሁሉም አካል ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው በዓሉ በሰላምና በድምቀት ተከብሮ እንዲውል ለማድረግ ታቦታቱ የሚያድሩባቸውንና የሚያልፉባቸውን ቦታዎች ማፅዳትና ምቹ ማድረግ ተገቢነት እንዳለው ገልፀዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት መርሐ ግብር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
በጃን ሜዳም "የጥምቀት በዓል በፅዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሀሳብ የፅዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፥ የሁሉም ሃይማኖቶች ተወካዮች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፥ የጥምቀትና የከተራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም የታቦት ማደሪያ ቦታዎች የማጽዳትና ምቹ የማድረግ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
በዓሉን ለማክበር ወደ ከተራና ጥምቀት ለሚጓዙ እግረኞችና ለተሽከርካሪዎች መንገዶችን የማስተካከል ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል።
አዲስ አበባን ውብና ፅዱ የማድረግ ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም ነው የገለጹት።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ፥ የጥምቀት በዓል ፍቅርንና አብሮነትን የሚያስተምር ነው ብለዋል።
የጥምቀት በዓል የሚከበርበትን ስፍራ በአብሮነት በማጽዳት የተባበሩትን የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮችና የህብረተሰብ ክፍሎች አመስግነዋል።
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፥ ሃይማኖታዊ በዓላት ሁሉም ህብረተሰብ አንድነቱንና ትብብሩን የሚያጠናክርባቸው መልካም እሴቶቻችን ናቸው ብለዋል።
ይህም በዓላቱ ደምቀውና አምረው እንዲከበሩ በማድረግ የሀገር ገፅታ እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለትም የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች አንድነታቸውን ለማሳየት በጥምቀት በዓል የታቦታት ማደሪያ የፅዳት ዘመቻ ላይ በመሣተፋቸው ምስጋና አቅርበዋል።
#Ethiopian_News_Agency
#Ethiopia
#ጥምቀትበዓል
የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጃንሜዳ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
************************************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር "ጥምቀትን በጽዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሃሳብ የከተራና የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጃንሜዳ የጽዳት ዘመቻ አካሄደ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ከተማ አስተዳደሩ የጥምቀት በዓልን በጽዱ ሥፍራ እና በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓል።
የጥምቀት በዓል ኢትዮጵያ ካሏት የአደባባይ በዓሎች አንዱ መሆኑን የገለጹት ኢንጅነር ወንድሙ፤ የጽዳት ዘመቻው መካሄዱ የሕዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መላከህይወት አባ ወልየሱስ ሰይፉ በበኩላቸው፤ በዓሉ የፍቅር መሆኑን ገልጸው በዓሉ በአዲስ አበባ 66 ቦታዎች ይከበራል ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያን የጥላቻ እና መለያየትን ሃሳብን ከአዕምሮ ማጽዳት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በዓሉ በሰላም እንዲከበር እያደረገ ላለው ድጋፍ መላከህይወት አባ ወልየሱስ አመስግነዋል።
በጽዳት ዘመቻው ከተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች፣ ወጣቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
የከተራ፣ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ በዓላት የፊታችን ጥር 10፣ 11 እና 12 በተከታታይ በድምቀት ይከበራሉ።
በአማን ረሺድ
ጥር 9 ቀን 2017 ዓም
