Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎትን ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጅ አሰራር የማሸጋገር ሂደትን በሙሉ አቅም በማፋጠን የስማርት አዲስ አበባን ግንባታ አጠናክሮ ማስጠቀል እንደሚገባ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ5ቱን ተጠሪ ተቋማት፣የክፍለ ከተሞች እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መዋቅሮችን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ መድረክ ላይ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በሁሉም መስክ የተከናወኑ ስራዎች መልካም የሚባል አፈፃፀም እንደተመዘገባባቸው ገልፀው ከዚህ ጋር በተያያዘ ግን የአገልግሎት አሰጣጡን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የማድረግና በቴክኖሎጂ በማዘመን ፍትሀዊ አገልግሎትን በማረገጋጥ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል። በዚህ ረገድ የሰው ኃይሉ ዘመኑን የዋጀ፣ እውቀትና አቅም የተላበሰ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራ መስራት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘውም መዲናችን በፅዳቷ እምርታዊ ለውጥ ያስመዘገበችበትና እንደ አህጉርም በአለምዓቀፍ ደረጃም ሞዴል የሆነችበት ስራ መከናወኑን አውስተው ከቅድመ አደጋ መከላከል ጋር በተያያዘም ባላፈው የክረምት ወራት ከነበረው ከፍተኛ የዝናብ ሁኔታ አንፃር በከተማችን ከክረምቱ በፊትና በክረምቱ ወቅትም በተከናወኑ ሰፊ የአደጋ ልየታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ነዋሪዎቻችንን ከከፋ አደጋ መታደግ ችለናል ሲሉም ተናግረዋል።
ይሁንና ይህን አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያ የአደጋ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ተለይተው የተፈቱትን መልሶ በማየት፤ አዲስ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት፤ በዘላቂነት አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማስፋትና የአመለካከት ለውጥ ላይ መስራት በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል አንደሚገባም አስምረውበታል፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም አዲሱ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋም የሆነው የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የመንገድ መብራት አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ በአንድ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ቀደም ብሎ በእርጅና፣ ስርቆት፣ ግጭት፣ የመሰረተ-ልማት አለመሟላትና በሌሎች ምክንያቶች ጨለማ የነበሩትን መንገዶች ብርሀን እንዲሰጡ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ስራ በመስራቱ ከተማችን የወንጀል ስጋት የቀነሰባት፣ በቀንና በሌሊት የሚሰራባት ብርሐናማ ምቹና የንግድ እንቅስቃሴዎች ያደገበትን ሁኔታ መፍጠር መቻሉንም አስረድተዋል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ ከዚህ ጎን ለጎን መሰረተ ልማቱን በቴክኖሎጂ ታግዞ በአንድ ማዕከል ከማስተዳደር፣ የከተማውን የመብራት ሽፋን የደረስንበትን ደረጃ ለይቶ ከማጥናትና የመንገድ መብራቶች ከዘመናዊ ከተማ መገለጫነት ባለፈ ከተማችን ባገኘችው በቂ የመንገድ ብርሀን የተገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን ለህዝብ ማሳወቅና ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ ከከተማችን የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ጋር ተያይዞ የሃይል አቅርቦት ተቋርጦ የሚቆይበት ጊዜ ማጠሩንና አገልግሎቱን ሪፎርም በማድረግ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸው ይሁን እንጅ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከከተማችን ነዋሪዎች ህይወት ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ ከዚህ አንፃር አገልግሎቱን ከማዘመንና የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ፈጣን ምላሽ ከመስጠት አኳያ ያሉ ቀሪ ስራዎችን በልዩ ሁኔታ መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ በከተማችን በ 2ኛዉ ምዕራፍ ተጀምረዉ በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ለ አራቱ ማለትም (1) ከመስቀል አደባባይ መገናኛ - ሳዉዝ ጌት፣ (2) ከአንበሳ ጋራዥ -ጎሮ ፣ (3) ከአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል ፣ ጎሮ ፣ቦሌ ቪ አይ ፒ ተርሚናል እንዲሁም ከሳር ቤት -ጀርመን አደባባይ ፣ጋርመንት ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ አካላትን አመስግነናል ።
በዚህም በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት ሌት እና ቀን ሲሰሩ ለነበሩ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪዎች ፣ማህበራት ፣በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎችም ለነበራቸዉ ከፍተኛ አስተዋፆ እና ትዉልድ ተሻጋሪ ስራ አመስግነናል ።
በተለይም መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ለሚነዙ ሀሰተኛ አሉባልታዎች ጆሮ ሳይሰጥ የልማት ተነሺ ሆኑትም ያልሆኑትም ለጋራ ልማት በመተባበር ፣ ቡና እያፈላ ፣ ዉሃ እያቀረበ ለልማት ስራዉ ዉጤታማነት ላሳየዉ ከፍተኛ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለዉ ።
በ 1ኛ እና በ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተጠናቀቁ መሰረተ ልማቶች መካከል 342 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣ 185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ ፣241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣ ዘመናዊ የመንገድ መብራቶች ፣ በርካታ የህዝብ መገልገያ እና መዝናኛ ቦታዎች ፣ በርካታ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ፣ 101 የህፃናት መጫወቻዎች ፣ 155 የስፓርት ማዘዉተሪያዎች ፣ 153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች እንዲሁም 210 የሕዝብ መፀዳጃዎች ተገንብተዉ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ፣
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዞቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ ኮሪደር
Sar Bet - German Square - Garment Factory - Furi area corridor
#PMOEthiopia
የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ ኮሪደር - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት… See more
ከካዛንቺስ ኮሪደር ቀጥሎ በመዲናዋ ሁለተኛው :ረጅሙ እና ሰፋ ያለ አካባቢ የሚሸፍነዉ ከሳርቤት - ጀርመን አደባባይ- ጋርመነት ፉሪ የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት - በምስል
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከሳርቤት - ጀርመን አደባባይ- ጋርመንት ፉሪ የሚዘልቀውን የኮሪደር ልማት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ
#ebcdotstream #addisababa #corridor #ወንድሙ #ኮሪደር
ማንንም ወደ ኋላ ያልተወ ፍትሃዊ ልማት!!
የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!!
Eenyuyyuu dubatti kan hin dhiisne misooma haqa-qabeessa!!
Jiraattonni magaalaa keenyaa baga gammaadan!!!
በአዋሽ ፈንታሌ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ዛሬ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል,ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በዩኒቨርሲቲው የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር)፥ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አረጋግጠዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ አካባቢ መከሰቱን ገልጸዋል።
የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትም አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎች ድረስ መሰማቱን ነው የገለጹት።
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
