Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እሳቤዎች ዕውን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እሳቤዎች ዕውን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ መገኘታቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአፍሪካ የከተማ ልማት ችግሮች አህጉራዊ፣ የፖሊሲ እና ስልታዊ መፍትሄዎች የሚመክረውን ይህን መድረክ ሀገራችን እንደ መልካም ዕድልና አፍሪካዊ ሃላፊነት አድርጋ ትወስዳዋለች ብለዋል፡፡
ይህ ፎረም በአፍሪካ ዕድገት ላይ እንድናሰላስል፣ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ እና በአህጉራችን ውስጥ ዘላቂ፣ አካታች እና የበለፀጉ ከተሞችን ወደፊት ለመፍጠር ዕድል ይፈጥርልናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት የጋራ ጥንካሬዎቻችንን መጠቀም አለብን ያሉት አቶ ተመስገን፤ ለዘመናችን ፈተናዎች ከተለመዱት ምላሾች በተለየ ከፖለቲካዊ ስልቶቻችን ጋር የሚጣጣሙ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን መፍጠር ይገባናል ብለዋል፡፡
EBC
ከቻይና-አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ጎን ከጀኔራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ባለፈው ሐምሌ ካደረግነው ውይይት የቀጠለ ውይይት አድርገናል። በቆይታችንም ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመረ።
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ፣ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአቻ አፍሪካ ሀገራትና የአለማቀፍ ተቋማት ሚኒስትሮች በተገኙበት የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓናፍሪካኒዝም አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል።
በፎረሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም የፓን አፍሪካኒዝም መጸነሻ ስፍራ በሆነችው ኢትዮጵያ እንዲሁም በጥቁር ህዝቦች የነጻነት ታሪክ ውስጥ የማይፋቅ አሻራ ባሳረፈው የአድዋ ድል መታሰቢያ ማእከል በፓን አፍሪካኒዝም አዳራሽ መካሄዱ ልዩ እና ታሪካዊ ድምቀት እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡
ከንቲባዋ አክለውም ፈጣን እድገትና ለውጥ እየታየበት ባለው የግሎባላይዜሽን አለማቀፋዊ ሁኔታ በተለይ የአህጉራችን አፍሪካ ሀገራት ፈጣን የከተሞች እድገት ሊከሰት እንደሚችልና ይህን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸው፣ የሁሉም ሃገራት ከንቲባዎች የአረንጓዴ ልማትን እና ለትውልድ የሚሻገሩ ምቹ የመኖርያ ከተሞችን በመገንባት ሂደት ውስጥ ሰርቶ ማሰራትን መርህ ያደረገ የበሰለ አመራር በመስጠት ቁልፍ ሚና መጫወት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡
የመዲናዋ እድገት መሰረቱ የህዝብን ፍላጎትና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አካታች የልማት እቅድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማችን ነዋሪዎች ያሉባቸውን ችግሮች መፍታት ብቻ ሳይሆን ከምንጩ ማድረቅ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ እና የቀዳማዊ ልጅነት ፕሮግራሞች፤ እንዲሁም የነገዋ የሴቶች ስብእና መገንቢያና የስራ ፈጠራ ማእከል በዋነኝነት የሚጠቀሱ መሆናቸውንና አዲስ አበባ ወደ አለማቀፋዊ ተወዳዳሪ ከተማነት በፍጥነት እያደገች እንደምትገኝ ጭምር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል፡፡
ፎረሙ ከነሃሴ 29 ለተከታታይ ሶስት ቀናት የአፍሪካ ከተሞችን ለዘላቂ ልማት መለወጥ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በተለያዩ የከተሞች መሰረተ ልማት መስፋፋት ፣ ኢንቨስትመንት፣ በአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎም ይጠበቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤፍኤም 97.1 ሬድዮ ጋር በመተባበር የሚቀርበው ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ሁለተኛ ምእራፍ ሁለተኛዉ ክፍል ፕሮግራም እንድትከታተሉት ተጋብዛችሁዋል።
See less
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ መከናወን ጀምሯል::
ውይይቱ ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን በሚል መሪ ቃል የሚከናወን ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ከ30 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል::
በአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመከናወን ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከመላው አለም የተውጣጡ እንግዶችም በመታደም ላይ ይገኛሉ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በቻይና አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ላይ ይሳተፋሉ::
#PMOEthiopia
በከተማችን አዲስ አበባ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከነገ ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ በመሆኑ ደስታችን የላቀ ነው ።
የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በማዘጋጀት ከአፍሪካ ወንድሞችና እህቶቻችን ጋር ከተሞቻችንን በማዘመን፣ ለነዋሪዎች ምቹ የለውጥና የብልፅግና ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ እና እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ የምንመክርበት ወሳኝ መድረክ ሲሆን ለፎረሙ ስኬታማነት በርካታ ዝግጅቶችን አድርገናል::
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን እድል ማግኘታችን ትልቅ ትርጉም አለው ፤ ተባብረን በጋራ ሰርተን ከተማችንን ለዚህ አይነት ፎረም፣ ኮንቬንሽንና የስበት ማዕከል ማድረግን አጠናክረን ይበልጥ መስራት ይኖርብናል::
እንዲህ ያሉ ሁነቶች ለከተማችን በቱሪዝም ተጨማሪ ገቢ በማስገኘትና በማስተዋወቅ በኩል ጥቅም ያላቸው በመሆኑ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በፍፁም ትህትና ፣ አፍሪካዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት በማድርግ እንግዶችን በመቀበል ፣ በማስተናገድ እና በተለያዩ የግብይት ስፍራዎችም ይህንኑ ክብር እንድትሰጡ እና ፍቅራችሁን እንድትገልፁላቸው በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ቢል ጌትስ ከ2010 ዓመተ ምህረት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ እንኳን ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ። ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፤ በጤና እና የፋይናንስ ዘርፉን አካታች ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ለሚያደርግልን ያልተቋረጠ ድጋፍ በጣም እናመሰግናለን። የዛሬው በስንዴ ክለስተር ልማት እና የዶሮ ርባታ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን በመቻል ጥረት መንገዷን አጽንታ ባለበት ወቅት የተጠናከረውን ትብብራችንን የበለጠ የሚያጠናክር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ፍቅርን ፣ክብርን ለሰጠን እና እምነቱን ለጣለብን ህዝብ ፤በታማኝነትና በቅንነት እንዲሁም በላቀ ትጋት በማገልገል ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
See less
"አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ ይገባል! "
የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳ 1 ያስገነባውን የደረቅ ቆሻሻ ማቆያና የቅብብሎሽና ጣቢያ በዛሬው ዕለት በይፋ አስመረቀ።
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በፍቃዱ ሃይሉ ቆሻሻ ሀብት መሆኑን በመረዳት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ ቆሻሻን በአግባቡ መሰብሰብና ማስወገድ እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ሶስት ወረዳውችን (4፣9 እና10) ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ አዲስ አበባ በቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቷ ስሟን የሚመጥን አይደለም የሚለውን አመለካከት ለማስቀረት ይህ ፕሮጀክት ሰፊ አስተዋጽኦ ስላለው ሁሉ ባለድርሻ አካል ቆሻሻን ከመሰብሰብ ጀምሮ እስከ አወጋገዱ ድረስ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈን ጨምሮ የተለያዩ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
