uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የኢትዮዽያን ፈጣን ለዉጥ ሊገታዉ የሚችል ምድራዊ ሀይል የለም! ከሁሉ በፊት የረዳን ፈጣሪ ይመስገን! አምና በዚህ ወቅት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ ዘንድሮ ደግሞ በሀገራችን የመጀመሪያ፣ ግዙፍ እና አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ "አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል" ግንባታን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን። ይህ አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኮንቬንሽን እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ትላልቅ አህጉር አቀፍ እና አለምአቀፍ ኹነቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገምግመናል:: ቀሪ ዉስን ስራዎችንም በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ ተግተን በመስራት ላይ እንገኛለን። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለህዝብ የገባውን ቃል እና የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱን መሰረት ባደረገ መ… See more

03/06/2017 የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት አዲስ ለተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አሰተዳደር ባለስልጣን ሰራተኞች የአገልገ‍ይነት ሰነልቦና በማላበስና የባለሰልጣን መሰሪያ ቤቱን ተግባር እና ሀላፊነት ተረድተው ተልእኳቸውን ለመፈፀም እንዲያስችል እየሰጠ የሚገኘው የግንዛቤ የሚፈጥር የአቅም ግንባታ ሰልጠና ሁለተኛ ዙር መሰጠት ጀመረ። በዛሬው የሰልጠና መርሀ-ግብር ባለሰልጣን መስሪያቤቱ በተግባር አፈፃፀም ሂደቱ የመደገፋ በቅንጅት የመምራት እና የማሰተባበር ሚና ያለው የአዲስአበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት መዋቅር የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ። ሰልጠናውም በወጣለት መርሀ ግብር መሰረት በተቋሙ ተግባር፣ሀላፊነት እና ተልእኮ ላይ የባለስልጣን መሰሪያቤቱ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ አበራ ቱራ ተሰጥቷል ። ሰልጠናው ቀጥሎ በእቅድ እና በጀት አዘገጃጀት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ የሰልጠና ባለሙያ በአቶ ደስታ ፋንታ እየተሰጠ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለህዝብ የገባውን ቃል እና የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱን መሰረት ባደረገ መልኩ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡ See less

አፍሪካ ህብረት ጉባዔን በፅዱ አዲስ አበባ ማክበርን ታሳቢ ያደረገ የፅዳት ዘመቻ በቂርቆስ ዛሬም እንደቀጠለ ነው *********************** የካቲት 02/2017 ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን በፅዱ አካባቢ እንዲካሄድ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን ስትሰራ ቆይታለች። ከነዚህ ስራዎች አንዱና ዋናው የፅዳትና ውበት ስራ ሲሆን ለባለፉት ሶስት ወራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ ቆይቷል። ቂርቆስም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ የፅዳትና ውበት ስራዎችን ስትሰራ የቆየች ሲሆን የዛሬው የፅዳት ዘመቻም የዚሁ አካል ነው። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮዽያ ለሚያደርጉት ጉብኝት እንኳን ደህና መጡ! አይኤምኤፍ ለኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራማችን የሚያደርገውን የቀጠለ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ የእርስዎንም የግል ጥረት እና አስተዋፅዖ ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጠዋለን። በአይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ታላላቅ የድጋፍ መርሃግብሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም በሀገር በቀል ርዕይ እና የለውጥ አጀንዳ ላይ የተመሠረተ የእድገት እና የልማት ህልሞቻችንን በሚገባ ቀርፆ የያዘ ነው። ለረጅም ጊዜ የቆዩ የማክሮኢኮኖሚ ፈተናዎችን ለመሻገር የለውጥ ሥራዎቻችንን በጠንካራ ትኩረት እና ባለቤትነት በመያዝ ቆራጥ፣ ሁሉን አቀፍ እና ታሪካዊ ርምጃዎችን ወስደናል። በፕሮግራሙ እስካሁን የታዩ ውጤቶችም ቀና እና አበረታች ናቸው። እየተካሄዱ ያሉ የትግበራችን ሥራዎችም የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት፣ እድገትን ማፍጠን፣ የዜጎች ኑሮ ደረጃን ማሻሻል ሲሆኑ በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻል ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ ር አቢይ አህመድ A warm welcome to IMF Managing Director Kristalina Georgieva on the occasion of your visit to Ethiopia! We value the IMF’s continued technical and financial support for our economic reform program and appreciate immensely your personal involvement and contributions. Ethiopia’s macroeconomic reform program, which is supported by one of the IMF’s largest financing programs, is based on a Home-Grown Vision and Reform Agenda that clearly articulates our growth and development aspirations. As such, we have strong ownership of the reforms and have been able to undertake bold, comprehensive, and historic measures to address long-standing macro challenges. The results of the program so far are positive and very encouraging. Our on-going implementation will bring macro stability, unleash growth, improve living standards, and help establish Ethiopia as an African Beacon of prosperity.

የ6 ወራት የስራ ዕቅድ አፈጻጸማችንን ግምገማ አጠናቅቀናል፡፡ በግምገማችን ባለፉት ስድስት ወራት መገንባት የጀመርነዉን ጠንካራ የስራ ባህል የአመራር ቁርጠኝነትንና ቅንጅትን በማጠናከር እንዲሁም የገቢ አሰባሰብን በማሳደግ በርካታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በጥራት አጠናቅቀን ለህዝባችን ግልጋሎት ክፍት አድርገናል:: የሀገርን ክብርን በሚመጥን መልኩ ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ አዲስ አበባን አለም አቀፍ የስበት ማዕከል ከማድረግ በተጨማሪ ለነዋሪዎቻችን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እና ሰፊ የስራ እድል የፈጠሩ፣ አገልግሎትን የሚያሳልጡ ተግባሮች ተከናዉነዋል፣ የተቀሩትንም በቀሪ ወራት በፍጥነት የምናጠናቅቅ ይሆናል። በቀጣይም የአፈፃፀም ዉስንነትን በማስተካከል፣ ማዘመን የጀመርነዉን አገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር ቀልጣፋ እና ፈጣን እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተደራሽ በማድረግ፣ ብልሹ አሰራር እና ጉቦኝነትን በመታገል እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት የምንሰራ ይሆናል:: ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ድክመቶቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው ተነቅሰው እንዲታረሙ እያደረግን ለላቅ ውጤታማነት መትጋታችንን የምንቀጥል ይሆናል:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት በአዲስ ለተቋቋመውና ለጽ/ ቤቱ ተጠሪ ለሆነው የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አሰተዳደር ባለስልጣን ሰራተኛች በመጀመሪያ ዙር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ። ካለፈው ሐሙስ ጥር 28 ቀን ጀምሮ ለሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና በተቋም የሰራ ባህል ግንባታ ፣በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በማይንድሴት እና ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ፣ በእቅድና በጀት ዝግጅትና ሌሎችም የሰልጠና ርእሶች ላይ በሰነድ የተደገፈ ሰልጠና ተሰጥቷል ። የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመዲናችን የመንገድ መብራት መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች በማከናወን በአገልግሎቱ የህዝቡን እርካታ የማረጋገጥ ተልእኮውን በብቃት ለማከናወን በሚያደርገው ጥረት ይህን መሰል ስልጠና የሰራተኞች አቅም በማጎልበትና የመፈፀም አቅም በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ተመላክቷል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸማችንን መገምገም ጀምረናል። ባለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማችን ከተማችንን ከነዋሪዎቿ ኑሮ እና አኗኗር ጋር አስተሳስረን ውብ እና አበባ የማድረግ እንዲሁም የቱሪስት መተላለፊያ ሳትሆን መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ አቅደን እየሰራን ያለነውን ስራ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ማድረግ እና ውጤታማነቱን ማስጠበቅ ችለናል። አስተዳደራዊ ወጪን እና ብክነትን በመቀነስ ከህዝብ ከሰበሰብነው ግብር 70 % የሚሆነውን የነዋሪዎቻችንን እንግልት ለሚቀንሱ እና ህዝብን ለሚጠቅሙ ተግባራት እንዲሁም ለዘላቂ ልማት በማዋላችን የፈጣን ለዉጦቻችንን ቀጣይነት አስጠብቀናል። አገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ እና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት አሰራራችንን ዲጂታላይዝ ለማድረግ አቅደን የሰራናቸው ስራዎችም ለውጦችን አሳይተዋል። የግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማችን ባስመዘገብናቸው ስኬቶች ሳንረካ አቅደን ያልፈፀምናቸዉን እና ድክመቶቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው ለይተን በመገምገም ለቀጣይ ውጤታማነት የምንዘጋጅበት ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ