uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ውጤታማ የፋይናንስ ሥርዓትን በመተግበር እና ሀብትን ለተፈለገው ልማት በማዋል ረገድ በአፍሪካ ምሳሌ ከሆኑ ከተሞች ውስጥ አዲስ አበባ ግንባር ቀደም ናት - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ,AMN-Addis Media Network ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇?Addis Ababa City Manager's OfficeceGER1 Telgram:- ??👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...&

የሀሰተኛ ማንነት ማስረጃ የሚያዘጋጅ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሀሰተኛ ማስረጃ እያዘጋጀ ለተለያዩ ግለሰቦች ሲሰጥ የነበረ ግለሰብ በተሰጠ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን አሳወቀ፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ወደ ኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት ሃሰተኛ መታወቂያ እና ያላገባ ማስረጃ በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የመጣች ተገልጋይ በሰጠችው ጥቆማ መሆኑን የኤጀንሲው የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስናቀች ሙህዬ አስታውቀዋል፡፡ ከግለሰቧ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት ሀሰተኛ ሰነድ በሚያዘጋጀው ግለሰብ በተሰራ ኦፕሬሽን በብር 20,000 መታወቂያና ልደት እንዲያዘጋጅ በመደራደር መረጃው የሚያዘጋጅላት ግለሰብ ፎቶና ሌሎች መረጃዎችን እንዲሁም የቀብድ ክፍያ 10,000 ብር በሚቀበልበት ወቅት ከለሚ ኩራ ፖሊስ መመሪያ ጋር በመተባበር ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኤጀንሲው ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡ ግለሰቡ በፖሊስ ዝርዝር ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

አዲስ እንደ ስሟ ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ በሃብት ማመንጨት፣ ማስተዳደርና መቆጣጠር የተሻለ አፈጻጸም ያላት አፍሪካዊት ከተማ መሆኗ በጥናት ተመላከተ አዲስ አበባ በሃብት ማመንጨት፣ ማስተዳደርና መቆጣጠር አኳያ የተሻለ አፈጻጸም ያላት አፍሪካዊት ከተማ መሆኗን በመንግስታቱ ድርጅት በተደረገ ጥናት ተመላከተ። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ ከዩኤን ሃቢታት እና ከኢምፓክት ካፒታል ፎር ዴቨሎፕመንት ጋር በመተባበር ስድስት የአፍሪካ ከተሞች ሃብት የመፍጠርና የማስተዳደር አቅምን በተመለከተ ያካሄደውን ጥናትበትናንትናው እለት ታህሳስ 10 / 2017 አ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በናይሮቢ፣ ሉሳካ፣ ኪጋሊ፣ ዳሬሰላም እና ያሁንዴ ከተሞች የተደረገ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር የጥናት ውጤትም የአዲስ አበባ፣ ናይሮቢ እና ሉሳካ ከተሞች ሁኔታ ይፋ ተደርጓል። ጥናቱ ባካተታቸው ስድስት መስፈርቶችም አዲስ አበባ በአምስቱ የተሻለ ደረጀ ላይ እንደምትገኝ ተጠቁሟል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት፤ አዲስ አበባ በሃብት ማመንጨት፣ ማስተዳደር፣ መፍጠር እና ሃብት ከማከማቸት አኳያ እንዲሁም በሌሎችም መሥፈርቶች የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኗ በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የመሰረት ልማት ግንባታዎችን በማከናወን ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ፤ የልማት ስራዎቹንም በራሷ አቅም በማከናወን ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡ ከተማዋ ከምትሰበስበው ገቢ 65 በመቶ የሚሆነውን ለልማት ፕሮጀክቶች በማዋል ላይ እንድምትገኝ ጠቁመው፤ በተለይም በኮሪደር ልማቱ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ጤናማ የፋይናንስ ስርዓት በማረጋገጥ እና ዜጎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በመመለስ እንደተቻለም ጠቁመዋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የከተማ እና ልማት ዋና ክፍል ኃላፊ አትኬልሽ ፒርሰን (ዶ/ር) በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ በመስፈርቶቹ መሠረት በጥናቱ ከተካተቱ ከተሞች የተሻለ አፈጻጸም ያላት ከተማ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ከተማዋ በራሷ ገቢ በማመንጨት ራሷን የምታስተዳደር ከተማ መሆኗን ጠቅሰው፤ የነዋሪዎቿን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሏንም ጠቁመዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስትራቴጂክ ፕሮግራሞች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር እሸትአየሁ ክንፈ(ዶ/ር( እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ ተቋማቱ ባከናወኑት ጥናት መሰረት አዲስ አበባ ከተማ ሃብት ከማመንጨት አኳያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኗ መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ ሃብቱን ለማመንጨት የተጠቀመችው ሃብት አነስተኛ መሆኑም ከሌሎች ከተሞች የተሻለች እንድትሆን ማስቻሉን ጠቁመው፤ የሃብት መረጃዎችን ከማቀናጀት አኳያም እመርዊ ስራዎች መሥራቷን ጠቁመዋል፡፡ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አሥራት በዚሁ ወቅት፤ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር ከተማዋ ከፍተኛ ገቢ እንድታገኝ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የመሠረተ ልማት ግንባታዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ይበልጥ ከማነቃቃት አኳያ ትልቅ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውንም ነው ያነሱት፡፡ በሌላ መልኩም ከፍተኛ የሥራ ዕድልን ከመፍጠር ባሻገር ለኦኪኖሚ ዕድገት ልማት ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይ የኪጋሊ፣ የዳሬሰላም እና ያሁንዴ ከተሞች ጥናት ይፋ እንደሚደረግም በዚሁ ወቅት ተጠቁሟል፡፡ Ethiopian News Agency ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ የማንሰራራት ጉዞ - የፒያሳ አዲስ ገጽታ

በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ዘላቂ አገልግሎት መስጠትን ታሳቢ አድርገው እየተገነቡ ነው- በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ዘላቂ አገልግሎት መስጠትን ታሳቢ ያደረጉ፣ ጥራታቸውን የጠበቁና የከተማዋን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያልቁ ሆነው እየተገነቡ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ፡፡ ከመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት የተገኘውን የተሻለ አፈጸጻም በሁለተኛውም ለመተግበር ስራው ከመጀመሩ ቀደም ብሎ መሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ስራው መጀመሩን ኢ/ር ወንድሙ አስታውሰዋል፡፡… See more

ጥራታቸውን የጠበቁና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ሆነው እየተገነቡ የሚገኙት የኮሪደር ልማት የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች AMN-Addis Media Network ታኀሣሥ 10/2017 ዓ.ም… See more

መዳናችን አዲስ አበባ የፋይናንስ ስርአት በመተግበር የሚሰበሰብ ገቢ ፤ የገባውን ሀብት ለተፈለገው ልማት በማዋል ረገድ ውጤታማ እንቅስቃሴ እና ፈጣን ለውጥ ከታዩባቸው የአፍሪካ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ ቀዳሚ ስፍራ መያዟን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ ዪኤንሲዲኤፍ (UNCDF)፣ ዩኤን ሃቢታት እና አለምአቀፍ ተቋማት ጋር ባካሄዱት ጥናት ውጤት ይፋ አድርገዋል። በዛሬው እለት ታህሳስ 10 / 2017 አ.ም ጥናቱ ይፋ በተደረገበት መድረክ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥናቱን ለመሩ፣ላስተባበሩ እና በጥናቱ ለተሳተፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል። የእውቅና ሰርቲፊኬት የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ ሃላፊዎችና በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ጋር በመሆን ነው። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et