Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና ተጠሪ ተቋማቱ የተከናወኑ አበይት የስራ አፈፈፃፀሞችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ በዛሬው እለት የተካሄደውን ጋዜጣዊ መግለጫ ዘገባ በፋና ሚዲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ይከታተሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት ዉጤት እያስመዘገቡ እንደሆነ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በስሩ ያሉ ተጠሪ ተቋማት እየሰጧቸዉ ባሉ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በመግለጫዉ ላይ እንደተናገሩት በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቱ ስር ባሉና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉት የጽዳት እስተዳደር ፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፣ የኤሌክትሪክ ተቋማት የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያዎችን በማድረግና ወደ ተግባር በመግባታቸዉ አበረታች ለዉጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አብራርተዋል።
አያይዘዉም በተቋማቱ በተከናወኑ አገልግሎቶች ከጽዳት አንጻር የከተማዋን ገጽታ መቀየር ያስቻለ ተግባር ስለመከናወኑ ፣ ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት አንጻርም በተለይም ከዲጂታል የማንነት መለያ ( Digial Identity) ጋር ተያይዞ የነዋሪዎችን ከወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች ማለትም ከመታወቂያ አገልግሎቶች እና ሌሎችንም ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር እንደዚሁም ከተማዋን ከአደጋ ስጋት ለመጠበቅ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ረገድ የተመዘገቡ ወጤቶች የሚጠቀሱ እንደሆነ አብራርተዉ የተመዘገቡት ዉጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸዉ የከተማዉ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በመግለጫዉ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች በተጠሪ ተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
“ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ቢኖሩም እስከዛሬ ሶስት አመት በፊት ድረስ ከውጭ በማስገባት ላይ ተመስርታ ቆይታለች። አሁን ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ የማምረት አልፎም ወደውጭ የመላክ አቅም አሳድጋለች።”
Kanaan dura rasaasawwan dhuka'an biyya keessatti homishuuf yaaliiwwan kan turan ta'us, hamma waggaa sadan darbaniitti biyyattiin alaa galchuurratti hirkattee turteetti. Amma garuu Itoophiyaan biyya keessatti dhukaatuuwwan homishuu bira darbitee humna alatti erguu horatteetti.
Although there were previous attempts to manufacture bullets domestically, the country relied on imports until three years ago. Now, Ethiopia has developed the capability to produce ammunition locally and even export it.
በከተማዉ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል ወቅቱን መሰረት ያደረገ ጥንቃቄ እንዲደረግ ተገለጸ።
የኮልፌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በክፍለ-ከተማዉ ከሚገኙ ልዩ ልዩ ማህበራትና የህብረተሰረብ ክፍሎች እንዲሁም ከነዋሪዎች ለተዉጣጡ 700 ተሳታፊዎች በአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመርሀ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ-ከተማዉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልማ እንደተናገሩት በከተማ ደረጃም ሆነ በክፍለ-ከተማዉ የእሳት አደጋዎች እያጋጠሙ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሱ መሆኑን አስታዉሰዉ እነዚህ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና አደጋዉ በሚያጋጥም ጊዜ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የሚያስገነዝብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሰጥ ከኮሚሽን መ/ቤቱ ጋር በመተባበር መርሀ-ግብሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
አቶ ዳኛቸዉ አበበ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ የዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ኃላፊ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የአደጋ መከላከል ስራ ለኮሚሽን መ/ቤቱ ብቻ የሚተዉ አለመሆኑን ጠቅሰዉ የስልጠና ተሳታፊዎች ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዉ ያገኙትን ዕዉቀትና መረጃን መሰረት በማድረግ በአካባቢያቸዉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎች እንዲከላከሉ አሳስበዋል።
የኮሚሽን መ/ቤቱ ም/ኮሚሽነርና የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ፉፋ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በከተማዋ እና በአካባቢዉ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎች የአብዛኛዎቹ የአደጋ ምክንያት በጥንቃቄ ጉድለትና በቸልተኝነት የሚደርሱ በመሆኑ የጥንቃቄ ባህልን በማሳደግ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል የሚቻል በመሆኑ የዛሬዉ አይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ጠቀሜታቸዉ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
አያይዘዉም የኮልፌ ክፍለ-ከተማ አስተዳደር የስልጠና ተሳታፊዎችን በመለየትና ጥሪ በማድረግ እንዲሁም ለስልጠናዉ ያስጠየቀዉን ወጪ በመሸፈን ላደረገዉ አስተዋጾኦ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በቀጣይ አንድ ወር ወስጥ ከ450 ሺህ በላይ ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) አገልግሎት ምዝገባ እንደሚከናወን ተገለፀ።
ስራዉን ለማከናወን በቂ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ተሰማርቷል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የከተማ አስተዳደሩ በ2018 አ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ ይዘዉ በትምህርት ገበታቸዉ ላይ መገኘት እንደሚገባቸዉ ላሳለፈው ውሳኔ ተግባራዊነት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን አውስተዋል።
የብሔራዊ መታወቂያው የመመዝገብ ተግባሩ ከትምህርት ቤቶች ባለፈ በተለያዩ የመንግስትና የግል ባንኮች፣በኢቲዮ ቴሌኮም፣በሲቪል ምዝገባና በነዋሪነት አገልግሎት ተቋም የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዉ ተማሪዎች በእነዚህ ተቋማት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉም አስገንዝበዋል።
ለዝርዝሩ ቀጣዩን ቪዲዩ ይመልከቱ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ የፋይዳ መታወቂያ በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ከማድረግ ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የገለጿቸው አንኳር ነጥቦችን ይከታተሉ።
ቀልጣፉ ግልጽና ተጠያቂነትን የተላበሰ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እንዲሰጥ እንሰራለን _
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት "ቀልጣፉ ግልጽና ተጠያቂነትን የተላበሰ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እንዲሰጥ እንሰራለን" በሚል መሪ ሃሳብ ከሚመለከታቸው የወረዳና የክ/ከተማ ባለድርሻ አካላት እና ከጽ/ቤቱ ጋር በቅንጅት ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በ2017 የመጀመሪያው 6 ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሞ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ሰጥቷል።
ውይይቱን የመሩት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታደሰ ባለፉት 6 ወራት ከተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው የተቀናጀ አሰራር
ከጎርፍ አደጋ ስጋት ቅነሳ፣ ከእሳት አደጋ እና ህብረተሰቡን የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ውጤታማ የሆነ ስራ መስራቱን ገልጸው
በቀጣይም ከተማዋን ውብ፣ጽዱና ንጹህ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ከግብ ለማድረስ ሰፊ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ስራዎችን በቅንጅት መስራት፣ ከጎርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ተግባራት ላይ ርብርብ ማድረግ፣ የመንገድ ዳር መብራት ችግሮችን መቅረፍ፣ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ ባሉ የሴክተሩና የተጠሪ ተቋማት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እንዲወጡ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በመጨረሻም ጽ/ቤቱ ባለፉት 6 ወራት ባሳዩት የላቀ አፈጻጸም ከ1 እስከ 3ኛ ለወጡ የወረዳ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለሙያዎች የእውቅና ሽልማት ሰጥቷል።
#ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
የካቲት 25/2017
