cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

በአሸዋ ሜዳ የደብረ መንክራት መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርሰቲያን የፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ የመማማሪያ ቻናል

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። "የሠማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባርያዎቹም ተነስተን እንሰራለን "ነህ 2፥20 ይህ ቻናል የአሸዋሜዳ ደብረ መንክራት መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርሰቲያን የፍሬ ሀይማኖት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ የመማማሪያ ቻናል ነው።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
207
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
"መከራውን ቤቴ ሁኜ ልቀበል ብለው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስ ይላታል፤ ሌሎችም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከእኛ ጋ ናቸው ተብላችሁ ተታላችሁ የሄዳችሁ፤ ፀፀት ውስጥ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሌሎች ለመምጣት እየፈለጉ ቁልፍ ተይዞባቸው እንደተቸገሩም ሰምተናል:: " ብፁዕ አቡነ አብርሃም ብፁዕ አቡነ አብርሃም ይህንን የተናገሩት በሕገ ወጥ መንገድ ከተሾሙት "ኤጲስ ቆጶሳት" መካከል በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ አካሉ የይቅርታ ደብዳቤ በአስገቡ ሰዓት ነው፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ሰበር ዜና +++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት "አባ" ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል። በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ። በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሆኔን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል። "መከራውን ቤቴ ሁኜ ልቀበል ብለው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስ ይላታል ፤ ሌሎችም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከእኛ ጋ ናቸው ተብላችሁ ተታላችሁ የሄዳችሁ፤ ፀፀት ውስጥ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሌሎች ለመምጣት እየፈለጉ ቁልፍ ተይዞባቸው እንደተቸገሩም ሰምተናል::" ብፁዕ አቡነ አብርሃም ይህንን የተናገሩት በሕገ ወጥ መንገድ ከተሾሙት "ኤጲስ ቆጶሳት" መካከል በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ አካሉ የይቅርታ ደብዳቤ በአስገቡ ሰዓት ነው፡፡ ++++++++++
Hammasini ko'rsatish...
ቅዳሜ 04/06/2015 ህጻት _____ ይህሰቆች ሒሳብ (4-7) አብርሞች ሒሳብ (4-7) ቀደማይ ክፍል ት/ተ ሃይማኖት ከዕለይ " የማቴ አንድምታ ሰልሰይ " የቤ/ክ ታሪክ በዓለም ኦሮምኛ " _____ እሁድ 05/06/2015 ህጻት  _የጨዋታ መዝሙር ይህሰቆች መ/ቅዱስ ጥነት አንደኛ አብርሞች  መ/ቅዱስ ጥነት ሁለተኛ ቀደማይ ክፍል  ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ከዕለይ     "       7ቱ ምሥረታ ቤ/ክ ሰልሰይ     "       የቤተክርስቲያን ታሪክህጻት  _____ ይህሰቆች  ሒሳብ (4-7) አብርሞች  ሒሳብ (4-7) ቀደማይ ክፍል  ት/ተ ሃይማኖት ከዕለይ     "       የማቴ አንድምታ ሰልሰይ     "        የቤ/ክ ታሪክ በዓለም ኦሮምኛ     "        _Barumisaa Amanitta
Hammasini ko'rsatish...
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አባለት እንደምን ቆያችሁ!! በወቅታዊ ጉዳይ ብዙ ስጋት አድሮብን ብሆንም አሁን ከአባቶቻችን እንደሰማነው መልካም ዜና ሁለችንም የተለመደውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንድትቀጥሉ ታላቅ አከብሮት እንገልጻለን ። ቅደሜ እና እሁድ መደበኛው የሰ/ት/ቤት አገልገሎት ይቀጥላል ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ት/ት ክፍል
Hammasini ko'rsatish...
#ሞዓ ተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን አሸንፋለች ክብር ሁሉ በአርያም በግርማ ለተቀመጠው የተገፉትን እንባ ለሚያየው የምስኪኑንም ጩኸት ለሚሠማው ንጉሳችን ኢየሡስ ክርስቶስ ይሁን። አንድ ሲኖዶስ አንድ ፓትርያርክ አንዲት ቤተክርስቲያን
Hammasini ko'rsatish...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ያወገዘቻቸው የቀድሞ የሐይማኖቱ አባቶች፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንና ልዩ ሀይል  በየትኛውም  የቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ቅቢ እንዳይደርሱ  ፍርድ ቤቱ ጊዜያዊ እግድ ጥሏል።
Hammasini ko'rsatish...
#ቅዱስ_ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አጭር መግለጫ ከተናገሩት የተወሰደ ፦ " ... ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በደንብ አውርተናል። በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን መሪነት በመንፈሳዊ ግርማ ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ክብር ሆነን እግዚአብሔርም አክብሮን ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል እነዛን አጠቃላይ ነገ ነው የምንገልፀው። የነበረን ጥያቄ አጠቃላይ በመንግስት ፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዲሁም በሌሎች እዛ ባሉት ተገቢ ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝበዋል። ስለዚህ ጉዳይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን። የተገኘውን ውጤትም አጠቃላይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን። ዛሬ ይሄን አጭር መግለጫ ለመስጠት የወደድነው ምእመናኖቻችን ህዝባችን ስለሚጠብቅ ፤ ህዝባችን ምንም ከቆምንበት ዓላማ ወደኃላም ሆነ ወደፊት እንዳላልን ሁል ጊዜ የህገ ቤተክርስቲያን አቋም የፀና እንደሆነ፣ የቀኖና ቤተክርስቲያን የፀና እንደሆነ ይሄንን ለማረጋገጥ ነው። ይሄ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ስለዚህ ምእመናንን ወገኖቻችን ስለምታደርጉ የፀሎት ፣ የምክር አጠቃላይ የሞራል ድጋፍ በቤተክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን። በፀሎት ትጉ፣ በምዕላ ትጉ ፤ እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሰምቷል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አንዳንድ የምሰማቸው እና የምናያቸው ነገሮች ስላሉ ነው ዛሬ ጠቅላላ መግለጫ ያላወጣነው። ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ መግለጫ እንሰጣለን። " @EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery
Hammasini ko'rsatish...