cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
4 961
Obunachilar
-424 soatlar
-47 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#KebriDeharUniversity ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የሁሉም የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ወይም የ2015 ዓ.ም መደበኛ ሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 13 እና 14/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። ጥሪው በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በሪሚዳል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ2014 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተርን ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች withdrawal የሞላችሁ ተማሪዎችን ይመለከታል። https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

🔥 2👍 1
ማስታወቂያ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ካምፓሶቹ በሚሰጡ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ በማታና በረዕፍት ቀናት ተማሪዎችን ተቀብሉ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ⚡️የማመልከቻ መስፈርቶች፡-  ፨12ኛ ክፍል አጠናቀው የብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የዘመኑን መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ እና ፈተናውን ከወሰዱ አምስት አመት ያልበለጣቸው፤  ፨በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ትምህርቱን/ቷን የተከታተለና/ችና የማለፍያ ነጥብ ያገኘ/ች (የተፈጥሮ ሳይንስ 200 እና ከዚያም በላይ ሶሻል ሳይንስ 150 እና ከዚያም በላይ እንዲሁም ለአይነስውራን 100 እና ከዚያም በላይ)፤  ፨በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ያጠናቀቁና COC ያለፉ በሙያው ቢየንስ ሁለት ዓመት ያገለገሉ እና ዩኒቨርሲቲው የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ፤  ፨በቀድሞ የትምህርት ስርዓት 12+ 2 ዲፕሎማ ያላቸው ወይንም በማንኛውም የት/ት ዓይነት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፤  ፨የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት ከኢፌድሪ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤ 💥ማሳሰቢያ፡-  ➡️ምዝገባው የሚከናወነው በኦንላይን ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከት ይቻላል፡፡ ➡️አመልካቾች ጥቅምት 27-ሕዳር 19 /2016 ዓ.ም ማመልከት ይችላሁ፡፡ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

👍 3👏 1
" በጦርነቱ ምክንያት ወደኃላ ባልቀር አሁን የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ " - ተማሪ ሙሴ ኪዳነ በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 657 በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው የቀላሚኖ ት/ት ተማሪ ሙሴ ኪዳነ " መድረስ ከነበረብኝ የትምህርት ደረጃ ባለመድረሴ ዓመታት ከእድሜ ላይ ተሰርቋል " ሲል ገልጿል። የትግራይ #ሃውዜን ነዋሪ የሆነው ተማሪ ሙሴ አሁን ላይ እድሜው 22 ሲሆን ፤ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደስ መሰኘቱን ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግሯል። አስከፊው ጦርነት በይከሰትና ወደኃላ ባይቅር ኖሮ አሁን ላይ የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደነበርም ገልጿል። ሙሴ ኪዳነ ፥ " አሁን የመጣው የፈተና ውጤት ጥሩ ነው። ደስም ብሎኛል ከውጤቱ ጋር አያይዤ ማለት የምፈልገው ሁሉም ሰው ያሰበውን ደረጃ ለመድረስ የሚያስችለውን ጥረት ካደረገ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው። " ብሏል። መድረስ ከነበረበት የትምህርት ደረጃ ባለመድረሱ ዓመታት ከእድሜው እንደተሰረቀበት የሚገልፀው ተማሪ ሙሴ አሁን የሚገባውን ሁሉ የሚማርበት እድል ሊመቻች ይገባል ሲል ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግሯል። በትግራይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል። #Tikvah https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

👍 1🔥 1
የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል። ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 255 ያመጡ ☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 234 ያመጡ ☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 218 ያመጡ ☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 200 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 224 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 192 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ ☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ ☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል። መረጃውን ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኤፍ ቢ ሲ ነው። https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

👍 4
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ማለፊያ ነጥብ ያመጡትንና ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችል አስታውቋል። በዩኒቨርሲቲው የሪጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር ገዛኸኝ አሰፋ (ዶ/ር ) ፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ዋሴ እና በዩኒቨርሲቲው የቤተ ሙከራዎች አደረጃጀት ኮሚቴ ሰብሳቢና የኬሚስትሪ መምህር ዶ/ር ፈቃዱ ቸኮል እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል በሰው ሃይል፣ በቤተ ሙከራ፣ በቤተ መጻህፍት፣ በአይሲቲ መሰረተ ልማት እና በዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችን ዝግጅት ለመማር ማስተማሩ ምቹ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ጠቅሰው አዲስ ተማሪዎች ወሎ ዩኒቨርሲቲን ቢመርጡ ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንደሚወጡ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ታምራት አበበ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል በተማሪዎች መኝታ ክፍል፣ በምግብ ቤት እና በተማሪዎች ክሊኒክ በኩል አደረጃጀቱን በሰው ሃይል፣ በቁሳቁስና በአሰራር የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ዩኒቨርሲቲው የተግባር ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ተማሪዎችን ለመቀበል ሲዘጋጅ በሰው ሃይል፣ በቤተ ሙከራ፣ በቤተ መጻህፍት፣ በመማሪያ ክፍል ዝግጅትና በሌሎችም አደረጃጀቶች የተሟላ መሆኑን ገልጸው ተማሪዎች በእውቀትም በክህሎትም ብቁና ተውዳዳሪ እንዲሆኑ በሚያስችል ደረጃ ላይ ያለ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቁመዋል። https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

👍 1💯 1
2023 የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ የሆነው የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሔማን በቀለ 25,000 ዶላር ተበረከተለት። በአሜሪካ ቨርጂንያ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ ሔማን ሽልማቱን ያገኘው የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያስችል ሳሙና በመፍጠሩ ነው። ሳሙናው በአነስተኛ ዋጋ ($.50) ለገበያ የሚቀርብ መሆኑ ተመልክቷል። "ታዳጊዎች በዓለም ላይ መልካም ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ አምናለሁ" የሚለው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪው ሔማን፤ ለባዮሎጂ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት አይነቶች ሁሌም ልዩ ፍላጎት እንደነበረው ይገልፃል። ውድድሩ የፈጠራ ሃሳቡን ለማውጣትና ውጤታማ እንዲሆን ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረለት ገልጿል። ላለፉት አራት ወራት በውድድሩ ለመጨረሻ ዙር ከደረሱ ሌሎች ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ጋር America’s Top Young Scientist ለመባል ብርቱ ፉክክን ሲያደርግ ቆይቷል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የፈጠራ ውጤቱን የበለጠ በማበልፀግና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በማቋቋም ሳሙናውን ለሚፈልጉ ሰዎች በአነስተኛ ዋጋ ለማቅረብ እንደሚፈልግ ተናግሯል። USA Today በሔማን በቀለ ላይ የሠራውን ሰፊ ዳሰሳና የምስል ዘገባ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ https://www.usatoday.com/story/news/health/2023/10/23/virginia-teenager-heman-bekele-america-top-young-scientist/71288776007/?fbclid=IwAR0HNycYzn2ii4gAg4iIYSHQ5gm7yUh1oRW7hWTHNPYEiAUQMKYfX-OV-2I ፎቶ፦ ሔማን በቀለ እና መካሪ (Mentor) ከሆነችው የፕሮዳክት ኢንጂነሪንግ ስፔሻሊስት https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
14-year-old who invented soap to treat skin cancer named America’s Top Young Scientist

Heman Bekele, a ninth grader from Virginia, was named \

👏 4👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#BongaUniversity ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ፣ ማታ እና ሳምንት መጨረሻ መርሐግብር የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 29 እና 30/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ ስለሆነም በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ተብሏል፡፡ https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 2
🧜‍♂️Vitamins_Deficiency🧜‍♂️ 1- Vitamin “A”: Night blindness 2- Vitamin “B1”: Beriberi 3- Vitamin “B2”: Ariboflavinosis 4- Vitamin “B3”: Pellagra 5- Vitamin “B5”: Parestheia 6- Vitamin “B6”: Anemia 7- Vitamin “B7”: Dermititis and enteritis 8- Vitamin “B9” - “B12”: Megaloblastic anemia 9- Vitamin “B17”: Cancer 10- Vitamin “C”: Scurvy and swelling of gums 11- Vitamin “D”: Rickets and Osteomalacia 12- Vitamin “E”: less fertility 13- Vitamin “K”: Non-Clotting of blood https://t.me/ethiolearn
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

🔥 1👏 1
የትኩሳት አንጎል ንዝረት፡Febrile seizure የአንጎል ንዝረት የአንጎል ህዋሳት በሚያሳዩት የተዛባና ያልተገባ ከመጠን ባያለፈ ውስጣዊ መነቃቃት አማካኝነት የሚፈጠር የጤና እክል ነው።በህክምና አጠራሩ /seizure/ ተብሎ ይጠራል።ማንቀጥቀጥ(convulsion ) አንዱ የSeizure ምልክት ነው።ንዝረት በማያንቀጠቅጥ ምልክት ሊገለጥ ይችላል። የሚጥልና የማይጥል ንዝረት አለ። Epilepsy " የሚጥል" የሚለውን ስያሜ ገላጭ ነው። በእምቦቀቅላ ህፃናት ላይ ትኩሳትን ተተርሶ ስለሚከሰተው የአንጎል ንዝረት/ Febrile seizure/ በሚከተለው መልኩ አቀርብላችኋለሁ። የውስጥ የሰውነት ትኩሳት መጨመርን ተተርሶ የሚከሰት የአንጎል ንዝረት Febrile seizure ይባላል።ከአንድ ወር -5ዓመት ባሉ ህፃናት ይከሰታል።ንዝረቱ በዋናነት ትኩሳትን ተከትሎ ስለሚመጣ ስያሜውም ያንን ተመርኩዞ የተሰጠ ነው። በህፃናት ላይ ከሚታዩ ንዝረቶች ቀዳሚ ነው።በኛም ሀገር ይህ ችግር በብዙ ህፃናት ላይ የሚታይ ነው። febrile seizure ለማለት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አሉ።እነሱም:- 1) የእድሜ ክልል ከ አንድ ወር-5 ዓመት መሆን አለበት 2) የትኩሳት መጠናቸው 38 እና ከዚያ በላይ መመዝገብ አለበት፤ 3) ካሁን በፊት ያለ ትኩሳት የተከሰተ ንዝረት መኖር የለበትም፤ 4) ለንዝረት የሚያጋልጡ የአንጎል ችግሮች(ማጅራት ገትርና ሌሎች ችግሮች) እና ተጓዳኝ የንዝረት መንስኤዎች(የስኳር ማነስ፤የንጥረ ነገሮች መዛባት) መኖር የለባቸውም። እንደዚህ አይነት ችግር ከመቶ እስከ አራት ህፃናት ላይ ሊከሰት የሚችል ሰፊ የልጆች ችግር ነው።በጊዜ ማሳከም ከተቻለ ደግነቱ በአካላዊ እድገታቸውም ሆነ በአእምሮ ብስለታቸው ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ የለም። የትኩሳቱ መንስኤ በአብዛኙ በቫይረስ የሚመጣ ኢንፌክሽን ሆኖ ቶንሲልና ጉረሮ ኢንፌክሺን አልያም ጉንፋንም ሊሆን ይችላል።በተለይ የቶንሲል ኢንፌክሺን በነዚህ የህፃናት እድሜ ተሰራፍቶ መገኘቱና የሚያስከትለው ሙቀት ከፍ ያለ በመሆኑ ብዙ ግዜ የዚህ ችግር መነሻ ይሆናል። የችግሩ ምልክት? ሙቀት ያለው ህፃን ድንገት ለአጭር ግዜ ራስ መሳት/መንቀጥቀጥ ወዲያው ወደነበረበት መመለስ ተዘውትሮ የሚከሰት መታያ ነው።በጣም ጥቂት ህፃናት ላይ ይኸ ምልክት ከአስር ደቂቃ በላይ ሊቆይ ይችላል(በጣም አስቸኳይ ህክምና የሚሻ ነው) ። የትኞቹ ህፃናት ተጠቂ ናቸው? በቤተሰብ በትኩሳት የተከሰተ ንዝረት ታሪክ ከነበረ፣ የአንጎል እድገት ችግር ያላቸው ለዚህ ችግር ተጋላጭ ይሆናሉ። ህክምናው? ዋና ህክምናው ትኩሳት ማብረድ ላይ ያነጣጠረ ነው።በፓራሲታሞል ይኸ እስከሚገኝ በረዶ/ቀዝቃዛ ዉኃ በማድረግ ሙቀቱን በመቀነስ ቢያንስ ተደጋግሞ እንዳይመጣ ያደርጋል።በመሰረቱ በሙቀት የሚመጣ ንዝረት ቢበዛ 2/3 መደጋገም ነው የሚኖረው። የመደጋገም ቁጥሩ ብዙ ከሆነ ችግሩ ጠንከር ያለ መንስኤ እንደ ማጅራት ገትር ሊሆን ስለሚችል በጥንቃቄ መመርመር ያሻል። ወላጆች ልጆቻቸው የዚህ አይነት ችግር ሲያጋጥማቸው ማድረግ የሚገባቸው ተረጋግቶ ህፃኑን በአመቺ አያያዝ መያዝና ቀዝቃዛ ውኃ ማድረግ፤ፓራሲታሞል ካለ መስጠት በመቀጠል ወደ ሐኪም ቤት መውሰድ ነው። ወደፊት ወደ የሚጥል ህመም የመቀየር እድሉስ? ተደጋግሞ የሚጠየቅ ጥያቄ ነው።በዚ የተጠቁ ህፃናት ሌላ ግዜ ትኩሳት ሲያጋጥማቸው ተመልሶ ሊመጣ ይችላል።በአሐዝ ከ20-40% በሚሆኑት ላይ የመመለስ እድል አለው። ከአምስት አመት በኋላ ወደ ሚጥል ህመም የመከሰት እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው።እንደማንኛውም ህፃን ተቀራራቢ የመጠቃት እድል ነው ያላቸው። በተረፈ ይኸንን ንዝረት ለማከም ፀረ-ንዝረት መድሐኒት መውሰድ አያስፈልጋቸውም።ትኩሳቱን ና የትኩሳቱን መንስኤ በማከም ሙሉ በሙሉ ማከም ይቻላል። ሌላው ጉዳይ የጀርባ ፈሳሽ መቀዳት አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ነው? ይኸ የሚሰራው የማጅራት ገትር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ነው።ውሳኔው በእያንዳንዱ ህፃን ምልክት የተቃኘ ይሆናል።ከማቀጥቀጥ በኋላ ንቃተ ህሊና የመዛባት ችግር ካለ፤የራስ ምታት፤የአንገት ህመም፣ተስፈንጣሪ ተደጋጋሚ ትውከት፣ማንቀጥቀጡ ተደጋጋሚና የቀጠለ ራስን መሳት ካለ ብቻ የጀርባ ፈሳሽ መቅዳት ሒደት/lumbar puncture /መስራት ግዴታ ይሆናል።እነዚህ በሌሉበት መስራት አያስፈልግም። በትኩሳት የሚከሰት ንዝረት ወላጆችን ሊያስጨንቃቸው አይገባም፤ ዶር መስፍን በኃይሉ CR-HakimEthio https://t.me/+3EGHwc0EqhM1MTY0
Hammasini ko'rsatish...
Ethio_E_learning_Center

https://t.me/+SVSIDQoTv92qjcjA

👍 4😁 1
Is their any one who can manage this channel @Abdu3313
Hammasini ko'rsatish...
🔥 2 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.