cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

እግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ ( ፩ ተሰሎ ፭÷ ፳፭ ) ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ትክክለኛ አድራሻዎቼ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል። ቴሌግራም 👉 -https://t.me/hamernoah My -email ☞[email protected] መካነ ድር፡https:hamernoah.wordpress.comሁላችሁም ተሳታፊ ሁኑ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 410
Obunachilar
+124 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
EOTC TV | ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን | ክርስቲያናዊ ሥርዓተ ሐዘን | ክፍል 2

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++

https://youtu.be/Wqgq1KebrOo

🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹 📡 የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት 🎥 📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻 ለመረጃ 📞 +251985585858 ➽ የዩቲዮብ ገጻችን http://www.youtube.com/c/eotctv ➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን

https://www.facebook.com/eotctvchannel

➽የቴሌግራም ገጻችን

https://t.me/eotctvchannel

➽ የቲክ ቶክ ገጻችን

https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/

➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2

https://youtu.be/Wqgq1KebrOo

➽የትዊተር ገጻችን

https://twitter.com/EotcT/

➽የኢንስታግራም ገጻችን

https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=

https://www.youtube.com/watch?v=rQMNdD9hmkY ተንቀሳቃሽ ስልክ በቅዳሴ ሰዓት መጠቀም
Hammasini ko'rsatish...
MK TV || ዜና ተዋሕዶ || ከቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠው የሥርዓተተክሊል ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

#መጻሕፍትን ባለማወቅ ትስታላችሁ " ከሥር ወደ ተጠቀሱት ሀገራት በአንድም በሌላም ተደራሽ ሆኗለች።": #እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም።(መ.ኢዮብ ፴፫፥፲፬) በውጭ ሀገራት እና በሀገር ውስጥ ●ስዊዘርላንድ ● አዳማ ●ኖርዌይ ● ይርጋጨፌ . ዋሽንግተን ● ሚዛን ● ኢጣሊያን ●ጎንደር ● ካናዳ ● አጣዬ ●ግሪክ ●ቦንጋ ●አፋር ● ጅማ ●ቬርጂኒያ ●ወረታ ●እንግሊዝ ● ጂንካ ●ሜሪላንድ - ●ጋምቤላ ●ውርጌሳ ●ቢጣ(ከፋ) ●ቻግኒ ● ሐዋሳ ●ሳንኩራ መድኃኔዓለም ●ዲላ ●ነቀምቴ ●ቡታጅራ ማርያም ●ባቴ ደብረ ማኅቶት ● አሰላ ●አሶሳ ●ሆሣዕና ●ደሴ " መጻሕፍትን ባለማወቅ "መጽሐፌ በአንድም በሌላም መንገድ ለአንባቢያን ደርሳለች። 👉ከላይ በተጠቀሱ ሀገራት የምትኖሩ ክቡራን አንባብያን መፍቀርያነ መጻሕፍት መጽሐፉን ለመውሰድ በውስጥ መስመር ጻፉልኝ!!! ●በቅርቡ በሌሎች ሀገራት 3ኛው ዕትም ተደራሽ ትሆናለች።
Hammasini ko'rsatish...
#መጻሕፍትን ባለማወቅ ትስታላችሁ " ከሥር ወደ ተጠቀሱት ሀገራት በአንድም በሌላም ተደራሽ ሆኗለች።": #እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም።(መ.ኢዮብ ፴፫፥፲፬) በውጭ ሀገራት በሀገር ውስጥ ●ስዊዘርላንድ ● አዳማ ●ኖርዌይ ● ይርጋጨፌ . ዋሽንግተን ● ሚዛን ● ኢጣሊያን ●ጎንደር ● ካናዳ ● አጣዬ ●ግሪክ ●ቦንጋ ●አፋር ● ጅማ ●ወረታ ●እንግሊዝ ● ጂንካ ●ሜሪላንድ - ●ጋምቤላ " መጻሕፍትን ባለማወቅ "መጽሐፌ በአንድም በሌላም መንገድ ለአንባቢያን ደርሳለች። 👉ከላይ በተጠቀሱ ሀገራት የምትኖሩ ክቡራን አንባብያን መፍቀርያነ መጻሕፍት መጽሐፉን ለመውሰድ በውስጥ መስመር ጻፉልኝ!!! ●በቅርቡ በሌሎች ሀገራት 3ኛው ዕትም ተደራሽ ትሆናለች።
Hammasini ko'rsatish...
↳ ✍️ " እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ "✍️↲ (ማቴ .፭÷፲፬) ༺ ༻ ቅዱስ ዳዊት "#ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ ፣ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ"ብሏል ። (መዝ.፲፰÷፫_፬) ቅዱሳን ሐዋርያት እየተባሉ የሚጠሩት በቁጥር፲፪ ናቸው። ሐዋርያት ማለት ደጃዝማች፣ ቀላጤ ፣ምጥው፣ፍንው፣ሂያጅ ማለት ነው ።ስማቸውና ሥልጣናቸው በቅዱስ ወንጌል የተገለጠነው። ጌታ በመጀመሪያ በይፋ ያስተማራቸው ሥራውን ሲጀምር የመረጣቸው ከባዱም ኃላፊንት ይጥልባቸው ዘንድ የሾማቸው ናቸው።ይህ ዕለት አበው ሐዋርያት ሰማዕትነት የተቀበሉበት ዕለት ነው። #የክርስትና እምነት የዓለም ሃይማኖት ለመሆን የበቃበት ሐዋርዊ ጉዞ በመንፈስ ቅዱስ ተባርኮ የተጀመረበት በጉዞው ውጤታማነት የሐዋርያት የዓለም ብርሃንነት(ማቴ.፭፥ ፲፬) ፣የዓለም ጨውነት (ማቴ.፭÷፲፫) የተረጋገጠበት ዓለም በጥበቡ ሊደርስባት ያልቻለው የድኅነት ዓለም ምሥጢር በስብከተ ወንጌል ሥርጭት ገሃድ የሆነባቸው ናቸው። #የቅዱሳን ሐዋርያት የዕረፍት ዕለት የቤተ ክርስቲያን የድል አድራጊነት ዕለት እንደሆነ አድርጋ በዐዋጅ ታከብረዋለች። #በነቢያት የተነገረው ቃለ ትንቢት መድረሱንና በዘመናቸው መፈጸሙን ለዓለም እንዲያስተምሩ ጌታችን ራሱ "ኑተከተሉኝ "ብሎ የጠራቸውና የመረጣቸው ናቸው። ይኸውም ይታወቅ ዘንድ " ..ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል" ብሏቸዋል (ማቴ ፲፫÷፲) #ሐምሌ ፭ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕረፍታቸውን ታከብራለች። "በዓል" አብዐለ ፣አከበረ ፣አስከበረ ፣አበለጠገ ፣ዕለትን በዓል አደረገ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው።በቁሙ ሲፈታ የደስታ ፣የዕረፍት ቀን ፣የዓመት፣የወር፣ በሣምንት የሚከበር ፣።ያለፈ ነገር የሚታሰብበት ተዝካር፣ሕዝቡ የበዓሉን ምሥጢር እያሰበ ደስ ብሎትና ለብሶ አጊጦ የሚዘምርበት ፣ዕልል የሚልበት የሚል ትርጉም ይሰጡታል ። እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ ከሰጣቸው መታሰቢያዎች መካከል በዓላት ተጠቃሽ ናቸው። የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚገለጥባቸው ፣የቅዱሳኑ ተጋድሎ የሚታሰቡባቸው ዕለታት ናቸው(#በዓላት ገጽ_፲፮፤ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ) #ጴጥሮስ ማለት መርግማለት ነው።መርግ ወይም ናዳ ከወደላይ ሲመጣ ያስፈራል ። እሱም ሞተ ሥጋ ወሐይወ በመንፈስ እያለ ሲያስተምር ያስፈራልና። አንድም ሻፎ ደንጊያ ማለት ነው። ይህ ሥጋን ከአጥንት ይለያል ።እሱም ምእመናንን ከመናፍቃን ይለያልና። አንድም ደንጊያ ማለት ነው። ይህን የቀን ሐሩር የሌሊት ቁር አይለወጠውም። እሱም በመከራ አይለወጥምና ። አንድም ከዋው ደንጊያ ማለት ነው።ያ እየፈጋ ይሄዳል ።እሱም ከ፲፩ዱ ስብከት ሁሉ እየገባ ያስተምራል (#የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ምዕ፲÷፪) ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጴጥሮስ ፊቱ ሰፋ ያለ ሲሆን ሪዛምና መካከለኛ ቁመት የነበረው ራሰ በራ ነው።በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ ነበር። .በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተ ሳይዳ ተወለደ። የአባቱ ስም ዮና ይባላል። ከ ፭ ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጎልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማስገር ጀመረ። ለደቀመዛሙርነት መምረጥ ዕድሜው ፶፭ ዓመት እንደነበረ ይነገራል ።ቅዱስ ጴጥሮስ ያገባው የበርናባስን እና የአርስጦቡሎስን እኀት ስለነበር በጋብቻ ይዛመዳሉ ።ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ (ምሥጢረ ሐዋርያት ) የሚቆጠር ነው። #የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ሰም እንዳወጣችለት ይነገራል ።ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሓው ነው። _ቅዱስ ጴጥሮስ በ፬ቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል ፩ .በሽምግልና አባትነቱ ፪ .ጌታ በቂሣርያ በሰጠው ቃል ኪዳን ፫ .የሐዋርያት አፈ ጉባኤ ሁኖ ይናገር ስለነበር ፬ .በጥብርያዶስ ባሕር በተሰጠው ቃል መሠረት ነው። በበዓለ ኀምሳ ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ለተሰበሰቡት አይሁድ አፈ ጉባኤ ሁኖ ወንጌልን የሰበከ ፫ሺህ ምእመናንን አሳምኖ የመጀመሪያዋን አጥቢያ ቤተሰቡ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የመሠረተ እርሱንም ነው (የሐዋ .ሥራ ፪÷፲፬ _፴፯) _በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ እንዲመረጥ ሐሳብ ያቀረበ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው (የሐዋ ፩÷፲፮ ) _በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጤም ፣ በሶርያ ፣በጳንጦን፣በገላትያ ፣በቀጰዶቅያ፣በቢታንኒ እና በሮሜ ሰብኳል።በሮሜ ከተማ ለ25 ዓመታት አስተምሯል ። # ቅዱስ ጴጥሮስ መዋዕለ ስብከቱ ሲፈጸም ሐምሌ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም ቁልቁሊት ተሰቅሎ በሰማዕትነት ዐለፈ ቤተ (#ክርስቲያንህን ዕወቅ_61) ዛሬም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሆኝፍኑ ሐዋርያት ሁሉ ጌታውን በግብር የተከተለ ጴጥሮስን መምሰል አለባችቸው ። ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስነታቸው ጳውሎስ ዘሩ ከዕብራውያን ፤ከብንያም ነገድ ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው። በንግድ የታወቀች የኪልቂያ ዋና ከተማ ናት። አባቱ በዜግነት ሮማዊ ነበር። በ፲፭ ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሀገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት የአይሁድን ሥርዐትና ሕግን እየተማረእስከ 30 ዓመት ቆየ ።ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሲመታ ልብስ ይጠብቅየነበረው ቅዱስ ጳውሎስ ነው። ቅዱስ አውግስጢኖስ " በእስጢፋኖስ ጸሎት በተ ክርስቲያን ያጠፋውን ጳውሎስን አገኘች"በማለት ተናግሯል ።በ ፴፪ ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ .ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ አገኘ። ከዚያ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ ። (የሐዋ.ሥራ፱÷፩) #ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረው በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሀገር መሄዱን ራሱ ተናግሯል (ገላ.፩÷፲፯)ለ፫ ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ተመለሰ ።ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጤርሴስ ከተማ ለ፱ ዓመታት ቆይቷል። #የመጀመሪያው የተከናወነው በ46 ዓ.ም አካባቢ ነው። ማርቆስ አብሮ ተጉዟል ። የተሸፈኑትም ሀገሮች ሲሊንውቂያ፣ቆጵሮስ ፣ስልማና ፣ጳፋ፣ጰርጌን፣ገላትያ ፣ጵስድያ፣ኢቆንዮን ፣ሊቃኦንያ፣ልስጥራ፣ደርቤን ፣ጵንፍልያ ፣አታልያ እና አንጾኪያ ናቸው #ሁለተኛው የተከናወነው በ50 ዓ.ም አካባቢ ነው። የተሸፈኑትም ሀገሮች ፦ደርብያ፣ልስጥራ ፤ፍርጊያ፣ገላትያ ፣ሚስያ፣ጢርአዳ፣ሳሞትራቄ፣ናፑሊ፣ፊልጵስዩስ፣ተሰሎንቄ ፣በርያ፣በርያ፣አቴና ፣ቆሮንቶስ ፣አንክራኦስ፣ኤፌሶን ፤ቂሳርያ ፣ኢየሩሳሌም ፣እና አንጾኪያ ናቸው። ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚህ ጉዞ በልስጥራ ከተማ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
#ሦሰተኛው የተከናወነው በ54 ዓ.ም አካባቢ ነው። የተሸፈኑትም ሀገሮች ፦ደርብያ፣ልስጥራ፣መቄዶንያ ፣ፊልጵስዩስ ፣ ጳጥራ ፣ጢርአዳ፣ ትሮጊሊዩም ፣ ቆሮንቶስ ፣ሩድ ፣አሶን ፣ጵቶልማይስ ፣ጢሮስ፣ ሚሊጢኒን ፣አንጠቀከስዩ ፣አንክራኦስ፣ኤፌሶን ፤ቂሳርያ እና ኢየሩሳሌም ናቸው።ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ65 ዓ.ም ተይዞ ወደ ወኀኒ ገባ። ለሁለት ዓመት ከ6 ወር በጨለማ እስር ቤት ታስሮ ከቆየ በኋላ 74 ዓመት ዕድሜው በሮማ ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሠይፎ በ67 ዓ .ም ሐምሌ ፭ ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ።(_ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ_ገጽ_ 111) በእርግጥ በሰማዕትነት ለመሞት ጊዜና ምክንያት አለው ። #ሥልጣነ ክህነቱና ሐዋርያነቱ በቅዱሳን ሐዋርያት ብቻ ያልተወሰነ እንደሆነ ሁሉ መከራ መስቀል መቀበሉም በሐዋርያት ብቻ ተወስኖ ያልቀረ መሆኑን መረዳት ይገባል። "...ወመሀርዎሙ ይዕቀቡ ኩሎ ዘአዘዝኩክሙ .....ወናሁ አነ እሄሉ ምስሌክሙ በኩሉ መዋዕል እስከ ኅልቀተ ዓለም ያለውን ቃል መመልከቱ ይጠቅማል (ማቴ ፳፰÷ ፳) ቅዱስ ጳውሎስ "..በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው "ይላል (ኤፌ፪÷፳) እነ ቅዱስ ጴጥሮስ ለቤተ ክርስቲያን ተሰቀሉ ፤ የዘመኑ ፣ አገልጋይች ቤተ ክርስቲያንን ልንሰቅላት ነው ። እነ ቅዱስ ጳውሎስ አንገት ሰጡ እኛ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የሚገባውን ዐሥራቱን በኵራቱ እንሰርቃለን (ት.ሚል. ፫÷፲) ቅዱስ ጴጥሮስን የድሮው ጩኸት አንቅቶታል ክርስቲያኑንስ የሚነቃው መቼና ይሆን ? (ኤፌ፭÷፲፬) ━━━━━༺✞༻━━━━ ዘቦ ዕዝን ሰሚዐ ለይስማዕ (ማር.፬፥፱፣ማቴ፲፩፥፲፭፣) ★ ★ ★ መ/ር ተመስገን ዘገዬ ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም # ተጨማሪ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ E-mail [email protected] telegeram https://t.me/+U-n_2um5SI7skWIk Instagram temesgen.zegeye4 YouTube - www.youtube.com/@hamernoah208 Website -hamernoah.wordpress.com Facebook https://www.facebook.com/temesgen.zegeye.7
Hammasini ko'rsatish...
Hamere Noah: ሐመረ ኖኅ

እንኳን ደህና መጡ፣ 📞Contact me Call by +251934446444 BY telegram group Hamere Noah: - nhamere@gmail•com My_Instagram 👉temesgen.zegeye4 መካነ ድር፡ https:hamernoah.wordpress.com ዩቲዩብ 📷subscribe and share

https://www.youtube.com/channel

Photo unavailableShow in Telegram
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፯ (የሐምሌን ወር ዕትም በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ ! magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል ━━━━━༺✞༻━━
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.