cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኦቶዶክስ ተዋህዶ የድንግል ማርያም ልጆች የማንቅያ ቻናል

የእመቤታችን የአስራት ልጆች እንኳን ወደ ዚህ ግሩፕ በሰላም መጣችሁ እያልን ትምህርት አዘል የሆኑ ነገሮችን በዚህ ቻናል ማግኘት ይችላሉ። https://t.me/joinchat/AAAAAEhvqPwK_TtRW-g2iA

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
340
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

+ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር + እመቤታችን ጌታን ጸንሳ ከወለደችው በኋላ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ እንደ ልጅነቱ እያገለገላት ፣ እንደ አምላክነቱ እያገለገለችው አብራው በአንድ ቤት ውስጥ ኖራለች፡፡ ሌላውን እንተወውና ይኼ ነገር ብቻ ለማሰብ ያስጨንቃል! ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ አንድ ቤት ውስጥ መኖር እንዴት ያለ ነገር ነው? ልብ በሉ ድንግል ማርያም ጠዋት ከእንቅልፍዋ ስትነቃ "እንዴት አደርህ?" የምትለው ፈጣሪዋን ነበር:: ማታ ስትተኛ "ደህና እደሪ" የሚላትም አምላክዋ ነበር:: የማይተኛው ትጉሕ እረኛ በተኛች ጊዜ ሕፃን ሆኖ ከአጠገብዋ ያደረ ከእመቤታችን በቀር ማን አለ? ኪሩቤልና ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ የሚሉትን አምላክ እንደ እናት "እሹሩሩ" ብላ ያስተኛች እርስዋ ነበረች:: ምድርን በአበባ ልብስ የሚያስጌጠውን ጌታ በተኛበት ያለበሰችውም እርስዋ ነበረች:: ዓለምን በእጆቹ የያዘውን ጌታ ክንዶችዋን ያንተራሰችው እርስዋ ነበረች:: እነዚያን ሌሊቶች ድንግል ማርያም እንዴት አሳልፋ ይሆን? በሕልምም በእውንም ከፈጣሪ ጋር ማሳለፍ እንዴት ያለ ጸጋ ነው? ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፡፡ እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ለሠላሳ ዓመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነበር፡፡ የጠዋትና ማታ ጸሎትሽ ከልጅሽ ጋር ማውራት የሆነልሽ : ልጅሽ የሚሠጥሽ መልስ የፈጣሪ መልስ የሆነልሽ እመቤቴ ሆይ ስላንቺ ክብር ማሰብ ምንኛ ያስጨንቃል? እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት! እመቤታችን እና ጌታችን በእነዚያ ሁሉ ዓመታት ምን ሊነጋገሩ ይችሉ ነበር? ከእርስዋ በቀር ማን ይነግረናል? ድንግል ሆይ አንቺ ካልነገርሽን ማን ይነግረናል? ለማዕድ ስትቀመጡ ምን ብሎ ጸልዮ ይሆን? እንደ ሐዋርያቱ ቆርሶ ሠጥቶሽ ይሆን? ውኃን እንዲጠጣ ሞልተሽ ስትሠጪው ውቅያኖስን እንዴት በውኃ እንደሞላ ነግሮሽ ይሆን? በእርግጥ በእነዚያ ዓመታት ክርስቶስ ለእናቱ ምን ምን ሲነግራትስ ኖሮ ይሆን? ስለየትኛውስ ምሥጢር ሲገልጥላት ነበር? ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያነጋገሩት የአይሁድ መምህራን ‹በማስተዋሉና በመልሱ ሲገረሙ ነበር› እመቤታችን ከሕጻንነቱ ጀምሮ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ አብራው ስትኖር በስንቱ ነገር ስትደነቅ ኖራ ይሆን? /ሉቃ. ፪፥፵፯/ እንደ መንፈሳዊት እናት ድንግል ማርያም ለልጅዋ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እየነገረች አሳድጋው ይሆን? ሙሴ ስላያት ዕፀ ጳጦስ ታሪክ አልነገረችው ይሆን? ታሪኩን ሰምቶ "ያቺ ዕፅ አንቺ ነሽ እሳቱ ደግሞ እኔ ነኝ"ብሏት ይሆን? ውኃ ስለፈለቀበትና እስራኤል ስለጠጡበት ዓለት ነግራው ይሆን? እርሱስ "ያ ዓለት እኮ እኔ ነበርሁ" ብሎአት ይሆን? ብሉይን ስታነብ ሐዲስን እየተረጎመ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ልብዋን አቃጥሎት ይሆን? ሉቃ. ፳፬፥፴፪/ ጠቢበ ጠቢባን ሊቀ ሊቃውንት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤትሽ ጉባኤ የዘረጋብሽና ያስተማረሽ ድንግል ሆይ አንቺ እንደሆንሽ በልብሽ ከመጠበቅ ውጪ ብዙ አትናገሪም:: ሆኖም ልጅሽ ምን ምሥጢር ነግሮሽ ይሆን? ኤልሳቤጥ እንኳን ዮሐንስን ጸንሳ ስለጽንሱ የምትለው ብዙ ነገር ነበራት:: ፈጣሪ በአንቺ ዘንድ ያደረ ድንግል ሆይ አንቺስ ምን ትነግሪን ይሆን? "የመለኮት እሳት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው:: እንደምን አላቃጠለሽም? የኪሩቤል ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘረጋ? በግራ ነው ወይንስ በቀኝ? ታናሽ አካል ስትሆኚ ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ይችላል?" እያልን ከአባ ሕርያቆስ ጋር እንጠይቅሻለን:: እንዳንቺ ፈጣሪውን የሚያውቅ ፍጡር የለምና የዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት : የነገረ መለኮት ምሁራን : የወንጌሉ ተንታኞች ሁሉ ከአንቺ እግር ወድቀው እንደ አዲስ ስለ ክርስቶስ ሊማሩ ይገባቸዋል:: ልህቅተ ሊቃውንት እመቤታችን ሆይ ሊቃውንት ሁሉ ያንቺ ተማሪዎች ናቸው:: ባለ ቅኔዎች ሁሉ ባንቺ ፊት ገና ፊደል አልቆጠሩም:: ሰውና መላእክት አንድ ላይ ተሰልፈው "ብርቱ የሚሆን በአንቺ ያደረገውን ታላቅ ነገር" ሊሰሙ ይጠባበቃሉ:: ወዳጄ ጥቅስ ፍለጋህን ትተህ እግዚአብሔርን በእቅፍዋ ከያዘችው ቃሉን በሹክሹክታ በጆሮዋ ከሰማችው ድንግል እግር ሥር እንደ እኔ ብትደፋ ይሻልሃል:: የእግዚአብሔርን እጆች ይዛ የመጀመሪያዎቹን የሕፃንነት እርምጃዎቹን እንዲራመድ የመራችውን ድንግል መቆም ያቃተንን ደካሞች እንድትመራን አብረን ደጅ ብንጠናት ይሻላል:: እነ ጴጥሮስ በቅዱሱ የታቦር ተራራ ከጌታ ጋር ነበሩ ፊቱ ሲያበራ አይተው በዚህ ካልኖርን ብለው ተመኝተው : ኤልያስና ሙሴን አግኝተው ነበር:: ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር የኖርሽው እመቤታችን ሆይ የልጅሽ ልብሱ ስንት ቀን አብርቶ ይሆን? ከነቢያትስ እነማንን አምጥቶ አሳይቶሽ ይሆን? እንደ ጴጥሮስ "ሦስት ዳስ እንሥራ" የማትይዋ የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ሆይ ቤትሽ ደብረ ታቦር ሆኖልሻልና ልጅሽ ምን አሳይቶሽ ይሆን? ከእግዚአብሔር አብ "ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሚው" የሚል ድምፅ መስማት የማያስፈልግሽ "ለእኔም ልጄ ነው" ማለት የምትችይዋ እናት ሆይ እንደ እግዚአብሔር አብ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" ለማለት ሥልጣን የተሠጠሽ ሆይ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር መኖርሽን ባሰብሁ ጊዜ ጠባብዋ ሕሊናዬ ኃጢአት ያደቀቃት ሰውነቴ እጅግ ተጨነቀች:: ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ብዙ ራእይ አይቶ "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኩ" ብሎ ጻፈ:: ሠላሳ ዓመታት የጌታ ቀን የሆነላት በመንፈስ የነበረች ድንግልስ ስንት ራእይ አይታ ይሆን? መላ የሰውነታችን አካል ሁሉ አፍ ቢሆን የእርስዋን ክብርና ምስጋና ተናግረን መፈጸም አንችልም:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሰኔ 21 2012 ዓ ም አዲስ አበባ (ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም)
Hammasini ko'rsatish...
#ፈጸመ_ስምዖ ፈጸመ ስምዖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉሥ ወኮነ መድኃኒተ ለኲሉ ዘነፍስ ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ #ትርጉም፡-በንጉስ ዳኪዎስ ዘመን ተጋድሎዉን ጨረሰ እምነት ላለዉ ሁሉ መድኃኒት ሆነ በዚህም ባስሊዎስ እና ጎርጎርዮስ ተደሰቱ፡፡ ♡#በፍጥነት_ይቀላቀሉ_አብረን_እንዘምር♡ ╭═•|❀:✧๑✝♡๑✧❀|: ═╮ @ort_mezmur @meazhaimanot ╰═•ೋ•✧✝๑♡๑✧•  ═╯
Hammasini ko'rsatish...