cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወዳጆች

"በኃይልህ ሰላም በጌጠኛ ቤት ልማት ይሁን" መዝ. ዳዊት 122:-7

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
189
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
-530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሰኔ 12 ምክንያተ በዓሉ ምንድነው ? በአጭሩ! ............ የምህረት የይቅርታ መልአክ ! ............ 1ኛ ሰኔ 12-በዚህ ቀን ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡ 2ኛ በዚህች ዕለት የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ያበቃባት ዕለት ናት፡፡ 3ኛ ዳግመኛም ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ካያሳየውና በጌታችን ፊት አቅርቦት ካስባረከው በኋላ ጌታችንም በቅዱስ ቃሉ ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የሥቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሀ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር በዝርዝር የነገረው ቅዱስ ሚካኤል ዘወትር የሚራዳው ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ዕረፍቱ ነው፡፡ ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡ ቅድስት አፎምያን ቅዱስ ላሊበላ እና ባህራንን የረዳቸውና ያዳናቸው ቅዱስ ሚካኤል ክክፉ ሁሉ ይጠብቀን ከሚሰማውና ከሚታየው መከራ ይሰውረን ። #የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን😍 የሀብከ ብርኀኔ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailable
<<በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋልና>> መዝ ፺፩፥፲፩
Hammasini ko'rsatish...
የፃድቁ በረከት ይደርብን።
Hammasini ko'rsatish...
02:30
Video unavailable
9.37 MB
Photo unavailable
ዕርገተ ክርስቶስ፤ እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ፤ ዕርገት ከታች ወደ ላይ፥ከምድር ወደ ሰማይ መውጣት ማለት ነው።ቅዱስ ዳዊት፡-የጌታ ርደቱን (ከሰማይ ወደ ምድር መውረዱን) በመዝሙረ ትንቢት እንደ ተናገረ ሁሉ ነገረ ዕርገቱንም ተናግሯል።ይኸንንም:-“እግዚአብሔር በእልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤” በማለት የራቀውን አቅርቦ፥ የረቀቀውን አጉልቶ በመንፈስ ዘምሯል።መዝ፡፵፮፥፭ ትንቢቱ የሚፈጸምበት ሰዓት በደረሰ ጊዜም ጌታ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በ፵ኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን አስከትሎ ወደ ቢታንያ ሄዷል። በአንብሮተ እድም ባርኳቸዋል። እየባረካቸውም ራቃቸው፥ወደ ሰማይም ዐረገ ሉቃ፡፳፬፥፶ ከዚያ በፊት ትንሣኤውን እርግጠኞች እንዲሆኑ በተለያየ ቦታ እየተገለጠ ተዳስሶላቸዋል፥አብሯቸው በልቷል፥ጠጥቷል፥ምሥጢረ መጻሕፍትን ገልጦላቸዋል።መጽሐፈ ኪዳንንም አስተምሯቸዋል “ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ፥ ዐርባ ቀን እየታያቸው፥ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው፥በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው” የሐዋ ፩፥፫ የጌታ ዕርገቱ በትንቢት የተነገረ፥በቅዱሳን መላእክትና በቅዱሳን ሐዋርያት የተመሰከረ ነው።እነርሱ በእውነት የዓይን ምስክሮች ናቸውና።የሐዋ፡፩፥፱-፲፩።ስለሆነም ዕርገቱ የታመነ ነው ።ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዕርገቱ ፍጹም የታመነ መሆኑን ሲያስረዳ “ሕማም የሚስማማውን ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሄደ፥ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፤ሥጋው አልተለወጠምና።”ያለው ለዚህ ነው።ሃይ፡አበው፡ክፍል ፲፫፥፲፭። የጌታ ጥንተ ዕርገቱ ሐሙስ ግንቦት ፰ ቀን ፴፬ ዓ.ም. በዘመነ ማርቆስ ነበር።
Hammasini ko'rsatish...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
በጻድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን አዲሱ ህንፃ ላይ የቤተክርስቲያንን አስተምሮ በጽሑፍ እንዲህ አኑረዋል። ለሚያነብ ጥሩ አማራጭ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
ሐረር ቅዱስ ዑራኤል።
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.