cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Talk about love ስለፍቅር እናውራ

"💞ፍቅር💞 ❤ገደብ የሚባል ነገር❤ አያውቅም አይቀበልም መሰናክል እና አጥር ዘሎ ግንብ ደርምሶ መድረስ ያለበት ቦታ ይደርሳል ምክንያቱም💕ፍቅር💕እውነት ነው እውነትም አሸናፊ ነውና::” 📺በቻናላችን ላይ 📩እወድሀለው/እወድሻለው 📩Happy Birth Day ለማለት contact @wakanda0 እየተዝናናን ስለ ፍቅር♥ አስተያየት @wakanda0

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
12 443
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በዝግታ First ቀስብዬ ገላዋን አሸዋት ለስላሳ አካሉዋን በጆቼ ዳበስኳት ከዛም ቀስ እያልኩኝ ገላዋን አራስኳት በሰሜት ውስጥ ሆኜ በዝግታ ናጥኳት በጣቶቼ ውስጧን በደንብ ጎረጎርኳት . . . . . . በስተመጨረሻም ውዷ ብርጭቆዬን በደንብ አለቅልቄ ውሀ ጠጣውባት:: ግን ምን አስባቹ ነበር😳 ሆ                 ✍ተገጠመ በኪያ
Hammasini ko'rsatish...
┈┈••◉❖◉●••┈ ዝም ብለሽ ስሚኝ🌺 ❣️ :¨·......................:¨·.❣️ ......... ✍️ፃፍኩልሽ💌 ........ አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት ዛሬ ግን ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ
Hammasini ko'rsatish...
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ! ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል 9 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። በዚህም በበሽታው የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 105 ደርሷል።  የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው መካከል 8 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ነው። በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 105 መድረሱን ገልጸዋል። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ስድስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው። አራቱ (4) ከአዲስ አበባ ሲሆኑ ሶስቱ (3) ከጅቡቲ መጥተው በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን አንድ (1) የጅማ ከተማ ነዋሪ ነው። አንድ ታማሚ ያገገመ ሲሆን አንድ ደግሞ በጽኑ ህሙማን ውስጥ ይገኛል። እንደ አገር 84 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል። __ ዛሬ 1 ሰው ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ አገግሟል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ደረሱ። ምንጭ፦ ኢዜአ
Hammasini ko'rsatish...
#coronaUpdate በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው! የታማሚዎች ሁኔታ ፦ ታማሚ 1: የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች። ታማሚ 2: የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች። ታማሚ 3: የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። ታማሚ 4: የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት እየተጣራ ነው። Via: Dr. Lia Tadesse
Hammasini ko'rsatish...
በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ (9) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው! በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ አላቸው። ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት። አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል። የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው። በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል። እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል። ምንጭ፦ ኢዜአ
Hammasini ko'rsatish...
ሰበር ዜና! የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
#coronaUpdate በኢትዮጵያ አንድ የ9 ወር ህጻንን ጨምሮ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ! በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 264 ሰዎች ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ የዘጠኝ ወር ህጻን የተያዘ ሲሆን እናቱም ቫይረሱ ተገኝቶባታል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል አንዱ (1) ኤርትራዊ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 52 አድርሶታል ነው ያሉት። ምንጭ፦ ኢዜአ
Hammasini ko'rsatish...
ከጤና ሚ/ር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ ................................ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፤ ዛሬ መጋቢት 27 በቫይረሱ ተይዘው በህክምና ላይ የነበሩ የ60 ዓመት ሴት ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል። ግለሰቧ የፈረንሳይ አገር ጉዞ እንደነበራቸው እና በየካ ኮተቤ ገብተው ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል።
Hammasini ko'rsatish...
​​♥️እውነተኛ ፍቅርን የሚያጠነክሩ 5 ጠቃሚ ምክሮች♥️ ​​❶. በፍቅር አይን መተያየት:- በተለይ የባለትዳሮችን የህይወት ጓዳ ድረስ የመዝለቅ፣ የትዳርን ሳንካዎች በመካፈል የመቆልመምን ዕድል ለበርካታ ዓመታት ለታደሉት አማካሪዎች የትዳር ህይወት የተለየ ትንታኔ አለው፡፡ የትዳር ህይወት በገሀዱ ዓለም የጓዳ መድረክ የሚከወን የመንትዮች ተውኔት ሌላ ምዕራፍ ሲሆን ከእነዚህ መንትዮች የታዳሚነት ድርሻን ብቻ ጠቅልሎ መያዝ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቀው የተዋናይም የታዳሚንም ድርሻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ በባለሙያዎቹ አይን ሲታይ የራስንም የተጓዳኝንም የክወና ብቃት በትዳር ህይወት ውስጥ ለመፈተሽና ስለ አንደኛው አጋር ያለ አመለካከት ሁለቱንም ወገን ያስተያየና ያገናዘበ እንዲሆን ይረዳል፡፡ የተጓዳኝ የእርስ በርስ አመለካከት ሳንካን ሲያስከትል የሚያስተውለው በአብዛኛው ወደ ትዳር ከተገባ በኋላ ነው፡፡ በተለይ ‹‹ከመጋባታችን በፊት የነበረው ያ ሁሉ እንክብካቤ ያ ሁሉ ጉርሻ፤ ያ ሁሉ በሞቴ… ያ ሁሉ ቁልምጫ… ኧረ እጅና ጓንት ነበር የሚሉን… የዛሬን አያደርገውና ክንዶቹ ከቦታቸው ቢታጡ ቢታጡ ቀሪ አድራሻቸው ከወገቤ ነበር…›› የሚል የባለትዳር ሴቶች ስሞታ ከትዳር አማካሪዎቹ ጆሮ በተደጋጋሚ ለመድረስ አለመቦዘኑ እውነታውንና ችግሩን አጉልቶ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ልክ ከሁለቱም ወገን እንዳልታየ የዳኝነት ውጤት ‹‹ያብዬን ወደ እምዬ›› ላለመለጠፍ መጠንቀቅና የተጓዳኝ ድክመቶች አነጣጥሮ በማየት አቃቂር ከመፈለግ ‹‹በአንተ ትብስ…›› በጥላቻ አይን መተያየቱ ትዳርን ከማናጋት አይመለስም፡፡ በፍቅር አይን መተያየት በራስና በተጓዳኝ ውስጥ ያሉትን የፍቅር ችሮታዎች ትክክለኛ ገፅታ በቅጡና በትኩረት በመመልከት ለግድፈቶች የሚሰጥን ትኩረት በማቅለል እውነተኛ ፍቅርን በእውነተኛ ገፅታው ማቆም ይቻላል፡፡ ስለዚህ በፍቅር አይን በመተያየትና የሚያፈቃቅሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥንዶች እውነተኛን ፍቅር በአይናቸው ለማየት እንደሚችሉ ሊያውቁ ይገባል፡፡ ❷. የአመለካከት ልዩነቶችን ከአንድነት ውስጥ ማውጣት:- በተጓዳኞች ግንኙነት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ በርካታ የአንድነት ልዩነቶች በአመለካከት መለያየት አስታከው ከተፍ ማለታቸው አይቀርም፡፡ ከባለትዳሮች የትዳር ጎጆ እግር የጣለውንና ይህን መሰል ፅዋ እየተጎነጨ የደረሰ ወይም የደረሰበት ሁሉ የልዩነቶቹን ጣዕም በቅጡ ያውቃቸዋል፡፡ አንደኛው ወገን የሌላኛውን አመለካከት ለመቀየርና ለማሳመን የራሱን አመለካከት አክርሮ በመያዝ ‹‹እኔ ያልኩት ብቻ›› የሚልን አቋም ሲያራምድ ይስተዋላል፡፡ በተለይ ወረት ያላየውና እውነተኛን ፍቅር ጋልበው ከትዳሩ ዓለም መግባት ለሚሹት ጎጆን ከመቀለሳቸው አስቀድመው በመካከላቸው አንድነታቸውን የሚወስኑና ሁለትነታቸውን ብቻ የሚያመለክቱ በርካታ የህይወት ፍልስፍናዎች (እውነታዎች) በየግላቸው እንዲያዙ የሚያደርጉ አሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የአመለካከት ልዩነቶች ከቀለሱት ጎጆ በር ሲያንኳኩ እንዳመጣጣቸው ለማስተናገድና ለመሸኘት የማይዳግታቸው፡፡ በተጨማሪም ፍቅርና ትዳር የመማማርና በመተራረም ሂደት የሚያሳድጉት እንደሆነ ቀስ በቀስ የሚረዱትና በሙሉ እርግጠኝነትና ተስፋ የዘላቂ የፍቅር ደጀን የሚሆናቸው፡፡ ❸. ለእውነተኛ ፍቅር አሸናፊነት መጣር:- በመፈቃቀር የጥንድነትን ጉልበት መግለጥና የፍቅርን ፍቱን ኃይል መጋበዝ የሚቻለው ከሁለቱም ወገን በተውጣጣ የፍቅር ኃይል ነው፡፡ ጥንዶች ከየግላቸው የሚያዋጡት የፍቅር መስዋዕት ከአንድ መዋሉ ደግሞ ታላቅ የፍቅር ኃይልን በመፍጠር ለእውነተኛ ፍቅር ዘላለማዊ ጉልበትን ይቸራል፡፡ ‹‹ከመቀበል ይልቅ መስጠትን ማስቀደም›› የፍቅር ቀዳሚ መርሆ እንደመሆኑ መጠን ፍቅርን ለመቀበል ፍቅር መስጠትን በማስቀደም ‹‹ከእኔነት›› በቀደመ ይልቁንም በ‹‹እኛነት›› የሚፀናውን እውነተኛ ፍቅር ከእጅ ማስገባቱ አይዳግትም፡፡ በትዳር ዓለም እያሉ ለዚህ ትዳር ዘለቄታ ይነስም ይብዛ ደፋ ቀና ማለት አይቀርም፤ በዚህን ወቅት ፍቅርን መስጠት ማስቀደሙ በፍቅር ህይወት የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በፍቅር ኃይል በመግዛት ለመፍታት ፍቱን ጉልበትን ይሰጣል፡፡ የትዳር ህይወትን በአሸናፊነት ለመወጣት አንደኛ ወገን ሌላውን ለማሸነፍ (ለመግዛት) ከመሽቀዳደም ይልቅ በእውነተኛ ፍቅር (የመፈቃቀር) ጉልበት ለትዳሩ ለመገዛትና ለፍቅር አሸናፊነት ቅድሚያን መስጠቱ ይመረጣል፡፡ በእነዚህና መሰል የፍቅር ሀሳቦች ውስጥ መስዋዕት የሆኑለት ራሱ ፍቅር ነገ እነሱን መልሶ በፍቅር ይጠግናቸውና ፍቅር በፍቅር ያደርጋቸዋል፡፡ የፍቅር ሰዎችም ሆነን እንደ ምሳሌ የምንነሳ ያደርገናል፡፡ ለተጋቢዎችም ለአዲስ ተፈቃቃሪዎችም መልካም ፍቅር ይሁንላችሁ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.