cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Chuye❤️

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
144
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

😘ምኞት😘 🔥ክፍል 35 ✍ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ደሞኮ ሄዳም አልተፋታትም አሁንም በየሄደበት ቦታ በየመጠጥ ቤቱ ሳይቀር ስሟን ያጠፋል ። አንድ ቀን እኔ በነበርኩበት መጠጥ ቤት እንደለመደው ስሟን ሲበክል ስሜትን መቆጣጠር አቃተኝ አቦ ብቻ ድንገት ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩና ማሰቢያህን ሽጠህ በደመነብስ ብቻ የምትኖር ሰውዬ ለዛሬ ምሬሀለሁ ከዛሬ ቡሀላ ግን እኔ ባለሁበት የምኛትንም ሆነ የቤተሰቦቻን ስም ስታጠፋ ቢያጋጥመኝ እጨርስሀለሁ ።አውሬ ምን ስታረጋት እንደነበር የማናውቅ መሰለህ እንዴ አልኩት እሄው ከዛን ቀን ቡሀላ እኔ ባለሁበት ድርሽ ብሎ አያውቅም ።አለ ሰውየው። የሰው ነገር ይገርማል ቆይ ግን ምን እያለ ነው ስሟን የሚያጠፋው አለ ሚኪ። አቦ እሄ ክፍት አፍ ምን እማይለው አለ ደሞ እሚያናድደው አንዳንድ የሰፈሩ ሰዎዎች ድሮም በሳ የሚቀኑ እና ፈልገው ያልተሳካላቸው ወሬኛች እሱ እሚቀባጥረውን እየጨመሩበት ማባዛታቸው ነው ። እሱን ተወው አንዴ በፌስ ቡክ የተዋወቀችውን ዲያስቦራ አፍቅራ እህቷን ጥላ ወደ አዲስ አበባ ጠፋች ይላል። አንዴ አዲስ አበባ ከሄደች ቡሀላ አልፈልግሽም ሲላት መመለስ አፍራ ሆቴል ውስጥ ተቀጥራ ሴተኛ አዳሪ ሆኖ ሰዎች አይተዎት ነገሩኝ ይላል። ሚኪ ም...ን...ምን....አ..ል..ክ..አለ አፉ እየተሳሰረ ። ሰውየው ሚኪ ምን ያህል እንደተቀያየረ እና ፊቱ ደም እንደለበሰ ቢያስተውል ኖሩ ደንግጦ ወሬውን ለመግታት ሰከንድም ባልፈጀበት ነበር ግን አላስተዋለውምና ወሬውን ቀጠለበት። እኔ ምንም ይሁን ምን ጥላ መጥፋታ ልክ ነች ባይ ነኝ ከዚህ ህይወት የማይሻል ነገር የለም እውነቱን ልንገርህ ትንሽ ብትቆይ መሞቷ ወይ ማበዷ እማይቀር ነበር እንዴ በጭንቀት በሽታ ተይዛ እኮ በሀኪም እርዳታና ወላጆቿን በሚያውቁ ሙስሊም እና ክርስትያን ወዳጆቻቸው ፀሎት ነው የተሻላት ። አሁንም ትኑር ትሙት የሚያውቅ የለም ብቻ ሰላም እንድትሆን እመኛለሁ። አቦ እሄን ሰውዬማ መጨረሻውም ያሳያኝ ደሞኮ....ብሎ ሌላ ታሪክ ሊጨምር ሲዳዳው ሚኪ እራሱን መቆጣጠር አልቻለም ነበርና በቃ በቃ ብሎ ጮኸበት ወድያው ይቅርታ ጮኩብህ እባክህ ይብቃህ ከዚህ በላይ ስለምኛት ምንም አትንገረኝ አለ። በዚህ ሰአት ነበር ሰውየው ሚኪን ያስተዋለው ሚኪ ሁለመናው ልውጥውጥ ብላል ። ሀይ ስለማታውቃት ልጅ ነግሬህ እንዲህ መረበሽህ ይገርማል አቦ ለሰው አዛኝ እና ሩህሩህ ልብ ነው ያለህ ከማለት ውጪ አንድ ነገር አለ ብሎ ፍፁም አልጠረጠረም። እኔማ አዛኝም ሩህሩህም አይደለሁም ደደብ ብቻ ነኝ። ጨካኝ እና ከሀዲ ሳልሆን በችኩልነት የጨካኝ እና የከሀዲ ሰው ተግባር ፈፅሜ በፀፀት አለንጋ እየተገረፍኩ የምኖር ጭንቅላቱም ህይወቱም ምስቅልቅል ያለበት ሰው ነኝ አለው ሚኪ እንባው አይኑ ላይ እንደተንጠለጠለ። በዚህ ሰአት ሰውየው ግራ ተጋባ "ምን እያልክ ነው ወንድሜ? ሊገባኝ አልቻለምኮ!አለው። ሚኪ ወደ እራሱ መለስ አለና እባክህ ይቅርታ ወሬ ቀይር በቃ የልጅታ ታሪክ የራሴን መጥፎ የሂወት አጋጣሚ ስላስታወሰኝ ተረብሼ ነው አለው። ሰውየው እውነት ነው ሁላችንም የየራሳችኝን ቁስል አናጣም እኮ አብሽር በቃ እርሳው እና ፈታ በል አለና ቢራውን አንስቶ ባንድ ትንፋሽ አንቆረቆረው አጠጣጡ እሱም የራሱን መጥፎ ጠባሳ ውል ያለበትና በቢራው ጎርፍ ለማስወገድ የሚሞክር ይመስላል።በዚህ መሀል ሚኪ አንድ ረዘም ያለ ቀጭን ጥቁር ሰውዬ ከምኛት እህት ግቢ ሲወጣ ተመለከተና እሄ ማነው ? አለው እሄ ነዋ ያ ደርጉ ያልኩህ ጭራቅ ሰውዬ ከኔ ጋር ስለተጣላ ከሰፈር ወጣ ብሎ ነው እሚጠጣው አለው።ሚኪ የምኛት እህት ባል ደርጉ ወዴት አቅጣጫ እንደሚሄድ ባይኑ ተከተለው ራቅ እንዳለ ስልኩን አውጥቶ ሰው እንደሚያናግር በመምሰል አብሮት ያለውን እመለሳለሁ አለውና የሁለቱንም የቢራ ሂሳቡ ከፍሎ ደርጉን ከጀርባው ይከተለው ጀመር... ይቀጥላል..... ሼር...ሼር 😘ምኞት😘 🔥ክፍል 36 ✍ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ሚኪ የምኛት እህት ባል ደርጉን ራቅ ብሎ ከውሃላ እየተከተለው ነው። ደርጉ ጫንቃውን ከበደው መሰል በተደጋጋሚ ወደ ጀርባው እየዞረ ሚኪን እየገላመጠ ይጓዛል። ምን ትገላመጣለህ ድሮም ክፉ ሰዎች ጥላቸውንም አያምኑም የሚሰሩት ክፋት እና ተንኮል ፈሪ ስለሚያደርጋቸው ከውኻላቸው የሚከተላቸው ሰው ሁሉ የሚያጠቃቸው ይመስላቸዋል። በራስ መተማመናቸው በራስቸው እኩይ ምግባር ተሸርሽሮ በማለቁ ባጋጣሚ እንኳን ከማያውቁትና ከማያውቃቸው ሰው ጋር አይን ለአይን ቢገጣጠሙና የሚያያቸው ሰው እይታ ትንሽ ግዜ ከወሰደ ...."እሄ ሰውዬ ለምን ያፈጥብኛል? የት ያውቀኛል? ምን ፈልጎ ነው? የሚሉ ጥያቄዋች በአእምሮአቸው ቶሎ ቶሎ እየተመላለሱ ሰላም ይነሷቸዋል ። "የሰው ትልቁ ጠላቱ የራሱ ባህሪ ነው " የሚባለው ለዚህ አይደል ።እንደዚህ አይነት ሰዎች በተለይ በዛ ካለ ሰው ጋር በታደሙባቸው አጋጣሚዋች ከሆነ አቅጣጫ ወደ እነሱ እያዩ የሚያወሩ እና የሚስቁ ሰዎች ካጋጠሙአቸው መላቅጣቸው ይጠፋና መግቢያ ቀዳዳ ይጠፋቸዋል። ሰው ሁሉ ስለነሱ የሚያወራና በጥቅሉ ስንት እሚወራ ነገር ያላት አለም በነሱ ዙርያ ብቻ የምትሽከረከር ስለሚመስላቸው በራሳቸው ክፋት የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ህይወት መምራት ይቸገራሉ። አታውቀኝ አላውቅህ ከጀርባህ መጋዜ ብቻ የሚረብሽህ የስራህ ውጤት ነው ዘመዴ ዝም ብለህ መንገድህን ቀጥል አለ ሚኪ በሆዱ አስሬ እየዞረ የሚመለከተውን ደርጉን እየተመለከተ። ደርጉ አንድ መንደር ውስጥ ያለች ጨለምለም ያለች ግሮሰሪ ውስጥ ሲገባ....ሚኪ ጥርጣሬውን ለመቀነስ አስቦ ግሮሰሪዋን አለፋትና ራቅ ብሎ ካለ አንድ ስልክ እንጨት ላይ ተደግፎ ለደቀቃዋች ስልኩን እየነካካ ከቆየ ቡሀላ ደርጉ ወደ ገባባት ግሮሰሪ ዘው ብሎ ገባ ። ከደርጉ በስተጀርባ ጨለም ያለ ቦታ መርጦ ተቀመጠና ቢራ አዘዘ። ደርጉ ካንድ ሴት እና ካንድ ስካር አፉን ያዝ ካረገው ጎልማሳ ወንድ ጋር ሞቅ ያለ ጫወታ ይዞ ስለነበር የሚኪን መግባት ልብ አላለም። ደርጉ ሞቅ እስኪለው ሌላ ጫወታ ሲጫወት ከቆየ ቡሀላ ሞቅ እንዳለው የየእለት ርእሱ የሆነውንና የለመደውን የምኛትን ስም የማጥፋት ዘመቻ ለመጀመር መንደርደሪያ ሀሳብ እንኳን አላስፈለገውም ነበር። "ዛሬ ደሞ ያቺ ጋጠ ወጥ እህታ ኬት ትዝ እንዳለቻት እንጃ ሚስቴ እህቷን አንስታ ስትነፋረቅብኝ እኮ ነው ዛሬ መጠጣት ሳልፈልግ ተበሳጭቼ የመጣሁት " ብሎ ርእሱን አስተዋወቀና ወደ ዝርዝር ቡጨቃው ገባ። ደርጉ ወሬውን ከሚያወራላቸው መሀል ወንዱ እሄ ወሬ የሰለቸው ይመስላል ሴታ ግን ስለምኛት መጥፎ መወራቱ አስደስቷት ይሁን ገበያዋን ለማሞቅ ደርጉ በተነፈሰ ቁጥር ታስካካለች። ደርጉ የወሬውን ዙር እያከረረ : የሴቷ ሳቅ እየናረ : ሚኪ የሚያዘው የቢራ ቁጥር እየጨመረ በደርጉ ወሬ የጀመረው ብስጭት እየመረረ መጣ። ደርጉ ቀጠለ " የማንም ዲያስቦራ ነኝ ተብዬ አጭበርባሪ በፌስ ቡክ ላግባሽ ሲላት አምና ከምትሄድ እዚሁ የኔ ገረድ ሆና ብትኖር ይሻላት ነበር እቺ ገልቱ ዘረ ገልቱ ። ደሞ ሰሞኖን አንድ አዲስ አበባ የሄደ ዘመዴ "ቺቺንያ"የሚሉት ሰፈር ውስጥ በአንድ ጭፈራ ቤት ሴተኛ አዳሪ ሆና አይቻታለሁ አለኝ " ሲል ሚኪ ብስጭቱ ከአቅሙ በላይ ሆነ እራሱን መቆጣጠር ተስኖት ብድግ አለና ... ስማ ውሽተም ቀዳዳ ነህ ይችን ልጅ አውቃታለሁ ከሚወዳት ሰው ጋር ተጋብታ በደስታ እየኖረች ነው። "ግን አንተ የሚስትህ እህት አይደለች የሷን ክፉ ስታወራ አታፍርም ? ነው ወይስ ያሰብከው ስላልተከልህ ነው?!" ሲለው ደርጉ ድንገት በወረደበት ዱብዳ በመደናገጥ መጠጥ በሰጠው
Hammasini ko'rsatish...
ድፍረት ለፀብ ብድግ ከማለቱ ሚኪ ያልተከፈተውን ቢራ አናቱ ላይ አፈነዳው ደርጉ ወደቀ ጥግ ላይ የነበሩ ሁለት የደርጉ ወዳጆች ወደ ሚኪ ተንደረደሩ.. ይቀጥላል.... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Hammasini ko'rsatish...
😘ምኞት😘 🔥ክፍል 33 ✍ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ሚኪ ሁለተኛው ሀይስኩል እንደደረሰ ጠጋ ብሎ የትምህርት ቤቱን ዘበኛ የምኛት እህት እዛ እንደምታስተምር ቢያረጋግጥም የከሰአት ፈረቃ አስተማሪ ስለሆነች አሁን እንደማያገኛት ስለተነገረው በመልክ ለይቶ ስለማያውቃት ልታስተምር ወደ ትምህርት ቤቱ ስትገባ እንዲያሳየው እትምህርት ቤቱ በር ላይ ከተኮለኮሉት አንዱን ተማሪ በመጥራት ነግሮት ነበርና የምኛት እህት የስድስት ሰአቱን ፀሀይ ለመከላከል ጥላዋን እንደዘረጋች ካንድ ጓደኛዋ ጋር ስትመጣ በተማሪው ጥቆማ መሰረት ተመለከታት ። የሆነ ነገራቸው ከምኛት ጋር ስለሚመሳሰል ምኛትን ያያት ያክል ነበር የደነገጠው ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ እስክትገባ ባይኑ ከሸኛት ቡሀላ ባለባጃጁን ስልክ ተቀብሎ በመሸኘት መውጫ ሰአቷን ጠብቆ ባከባቢው በመገኘት እንደወጣች ከውኻላ ከውኳላ በቀስታ ተከትላት ወደ ሰፈራ የሚወስዳት ባጃጅ ውስጥ ስትገባ ተከትላት ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ። እህቷን ምኛትን አፈቅርሻለሁና አብረሽኝ ኑሪ በማለት ከሳ ተለይቷ ወደ አዲስ አበባ እንድትሄድ ካሳመናት ቡሀላ አውላላ ሜዳ ላይ የጣላት ሚኪ አጠገቧ መቀመጡን ለማወቅ ሰዋዊ ተፈጥሮዋ አይፈቅድላትምና አንዴም ዞሯ ሳታየው እቤቷ ደረሰች። "እዚህጋ ወራጅ" አለች።አቆመላት።ወረደችና የመጣችበትን ሂሳብ ከቦርሳዋ አውጥታ ስትከፍል ሚኪ ስርቆ ሲያያት ያዘችው አይን ለአይን ተገጣጠሙ።እሱ ክው ብሎ ቢደነግጥም እሷ ከቁብም ሳትቆጥረው ሂሳቧን ከፍላ ከፊሉ ዘርዘር ብሎ በእንጨት ከፊሉ ደግሞ በተፈጥሮ ቅጠላ ቅጠል ዙርያውን በታጠረው ባለ ቆርቆሮ ከተም በሪው ግቢ ውስጥ ገባች። ሚኪ እዛው ባጃጅ ውስጥ ሆኖ ምኛትን ግቢ ውስጥ ባአይኑ ፈለጋት ግቢው ጭር ያለ ነው ። ቀኑን ሙሉ ከሚኪ ጋር ሲዞር የዎለው ባለ ባጃጅ እሺ አሁን ደሞ ወዴት ልሂድ የሚል ጥያቄ ባዘለ አስተያየት ሚኪን ሲመለከተው "ሂድ ትንሽ አለፍ በልና ታወርደኛለህ አለው። እንደተባለው አደረገ ከተስማሙት ሂሳብ በላይ ጨምሮ ሰጠውና ከፈለኩህ እደውልልሀለሁ ብሎ ሸኘው። ሰፈሩን ቃኘት ሲያደርገው አንድ ጥግ ላይ ካለች መደብር በር ላይ ቁጭ ብለው ቢራ ከሚጠጡት ሰዋች ውጪ ጭር ያለ ነው። ድሬ ዳዋ ውስጥ በየሰፈሩ ያሉ መደብሮች አብዛኛዎቹ ከሸቀጣ ሸቀጡ ጎን ለጎን ቢራ ይሸጣሉ ቀን በሙቀት ሲጨናነቅ የዋለን ጭንቅላት ማታ ሆቴል ሄዶ በጫጫታ ከማጨናነቅ ንፋስ እየተቀበለ መደብሮች በር ላይ ከራሱ አልያም አብሮት ካለው ጋር እያወጋ ቢራውን የሚኮመኩመው ሰው ቁጥሩ ቀላል አይደለም። ሚኪ በምኛት እህት ቢት በር ላይ አንዴ ወዲ አንዴ ወድያ እየተመላለሰ ቢንጎራደድም እሚገባም እሚወጣም ሰው ማየት አልቻለም። ወደ መደብሩ ጠጋ አለና ደንበርካ ላይ ተቀምጦ ቢራ አዘዘ።የተቀመጠበት ቦታ ከምኛት እህት ቤት ጋር ትይዩ ስለነበር አይኑ ግቢው ላይ እንደተተከለ ሶስተኛውን ቢራ ጀምራል እንዳጋመሰው የምኛት እህት የስራ ልብሷን ቀይራ የድሬ ሴቶች መገለጫ እና ተወዳጅ የሆነውን ሺቲ ለብሳ ወደ መደብሩ እየመጣች ነው ሚኪ ገና ግቢ ውስጥ ሆና እንደተመለከታት የግቢው መውጫ ላይ አፈጠጠ ስትወጣ አያት የሚያምር ዥንጉርጉር ሺቲ ለብሷ በቀኝ ጎኗ በኩል ሰብስባ የውስጥ ሙታንታዋ ላይ ሽጣዋለች "ኦ ማይ ጋድ ሺ ኢዝ ሴክሲ" አለ ሚኪ ከስራ ልብሷ በተሻለ መልኩ ድብቅ ውበቷን በሸቲው ጎልቶ በማየቱ። አናገርከኝ ወንድሜ አለ ከሚኪ በቅርብ ርቀት ብቻውን ቢራ ይዞ የተቀመጠው ጎልማሳ። አይ ወዲህ ነው አለ ሚኪ ጮክ ብሎ መናገሩን ስላልታወቀው ደንግጦ። ምናለ ምኛቴ ከዚህ ግቢ አንችም እንደ እህትሽ እየተውረገረግሽ ብትወጪልኝ አለ ሚኪ እህቷን እያየ። የምኛት እህት ከሚኪ አጠገብ ያለውን ሰውዬ ኬፍ አለችውና ገብቷ እንቁላል ገዝታ ተመለሰች። እየውልህ ከሀገር ከወጣሁ ብዙ አመት ሆኖኛል እቺን ልጅ ግን የማን ልጅ እንደሆነች ማስታወስ ባልችልም የዛሬ 10 አመት አከባቢ እማውቃት መሰለኝ ተማሪ ሆና የአቶ በአካል ልጅ ነች እንዴ? አለው አጠገቡ ያለውን ሰውዬ። "ኧረ ምን ትረሳለህ በደንብ አውቃሀታል በጣም አሳዛኝ ቤተሰብ ነው የናት እና አባቷ አሟሟት ድፍን ድሬ ዳዋን ነበር ያስለቀሰው "አለ ሰውየው። ኧረ ባክህ በጣም ያሳዝናል ቆይ እቺ ብቻ ነበረች እንዴ ልጃቸው ? ሌላ አልወለድም ? አለ ሚኪ ወሬውን እሱ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለማዞር። "ኧረ አንድ ምኛት የምትባል የዚች ታናሽ ሴት ልጅ ነበረቻቸው እቺ በሷ አይን ምን ታምራለች ወይ ውበቷ እሷን ለማግኘት ስንቱ እንዳልተጋደለ አቦ ተወኝ ባክህ ስለነሱ ቤተሰብ ሳስብ እኔ ራሴ ውስጤ ይረበሻል"አለ ሰውየው ማለት?እንዴት? አለ ሚኪ ወደ ሰውየው በደንብ እየተጠጋ.... ይቀጥላል.... ሼር....ሼር 😘ምኞት😘 ክፍል 34 ✍ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ማለት?እንዴት? አለ ሚኪ ወደ ሰውየው በደንብ እየተጠጋ። ምኛትኮ እልል የተባለላት የድሬ ቆንጆ ነበረች ትምህርት ቤት መማር እስኪያቅታት ነበር የሚያስቸግሯት አባታ ግራ ቢገባው እስከ አስረኛ ክፍል ትምህርት ቤት እየመጣ ነበር እሚወስዳት። አንዴ 9ክፍል ሆና ምን እንደ ተፈጠረ ታቃለህ ? ሚኪ ጭንቅላቱን አወዛወዘ ወሬውን እንዲቀጥልለት በመጓጓት። በዚህ በኩል የአዲስ ከተማ ሰፈር አለ የተባለ ጉልበተኝ በዛ በኩል ከግሪክ ካምፕ ሰፈር ብዙ የሚወራለት የሀብታም ልጅ ሁለቱም በተመሳሳይ ግዜ ላይ በፍቅሯ ይወድቃሉ ። በፍክክር ሁለቱም ቡድን ይመሰርቱ እና ከትምህርት ቤት ስንወጣ የቡድን ፀብ ይነሳና ቀውጢ ይሆንልሀል። በንጋታው መውጫ ሰአት ላይ የቡድን ፀቡ በምን ምክንያት እንደመጣ የትምህርት ቤቱን ተማሪዎ ችንና ወላጅ በትምህርት ቤቱ ይሰበሰባሉ የፀቡ መንስኤና ፀቡ ውስጥ የተሳተፉትን አሳልፈው እንዲሰጡ ከመድረክ ሲጠየቅ ማን ደፍሮ ይናገር ዝም ጭች ሆነ አቦ አንድ እኛ ሰፈር የሚኖሩ ሲያወሩ ሁላ በግጥም መልክ መናገር የሚቀናቸው ሴትዬ ነበሩ ሰው ዝም ሲል ብድግ አሉና በግጥም አፈነዱት። ያያት ወንድ በሙሉ : ምኛትን ሲመኛት አንዱ አንዱን ገደለው : መስሎት የሚያገኛት እሷ እንደሁ ምኛት : ነች የማንም አትሆን የናንተ መባላት :ኧረ ለምን ይሆን አንተም ለቀቅ አርጋት :አንተም ለቀቅ አርጋት ፈልግ አምሳያህን: እሷም ትማርበት አትሀኑ እንቅፋት። ብለው ቁጭ አሉ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር እና በስብሰባው የታደሙ ተማሪዎች ወትሮም ነገሩን የሚያውቁም በወሬ የሰሙም ነበሩና ሴትዮዋ ሲያፈነድት በሳቅ ፈረሱ። ሚኪ እየተጠጋ እየተጠጋ ሰውየው አፍ ውስጥ ሊገባ ምንም አልቀረውም ። ሰውየው ደስ እያለው ሲያወራ ከነበረው ወሬ ባንዴ ቅይር አለና ምን ዋጋ አለው "አያቴ ድሮ "መጨረሻህን ያሳምርልህ ብላ የምትመርቀኝ " ምርቃት ጥቅሙ የገባኝ የምኛትን መጨረሻ ሳይ ነው። እንዴት? አለ ሚኪ "ሁለቱንም ወላጆቿን ድንገት ሲሞቱ እጣ ፋንታዎ እዚ ደርጉ የሚባል አረመኔ እና በሰፈሩ የተጠላ ሰውዬ እጅ ላይ ጣላት"። ደርጉ ማነው? ማለት አግብታ ነበር እንዴ? "ኧረ የምን ማግባት የህቷ ባል ነዋ ደርጉ ሰው መሰለህ ፍዳዋን ሲያሳያት ያ ሁሉ ውበታ ፀሀይ እንደወጣበት ጉም በኖ ጠፋ እህቷ እራሱ እንዴት ችላው እንደምትኖር ለሁሉም እንቆቅልሽ ነው ። " አውሬ ታውቃለህ በስተት ነው ሰው የሆነው እንጂ ስራው ሁሉ የሰው አይደለምኮ እኔ እንኳን ቤቴ ወደላይ ነው እህቴ የነሱ ጎረቤት ነች ያውልህ ያኛው ግቢ ውስጥ ነው እምትኖረው ከነሱ ጋርም ትቀራረባለች ስለ ምኛት ባወራች ቁጥር ታለቅሳለች ።እንደዛ ቤተሰቦቻ አፈር አይንካሽ ብለው እንዳላሳደጓት እሱ አፈር አስመሰላት አፈር ይብላና እሄ አረመኔ" አለ ልጅ ወደ እ
Hammasini ko'rsatish...
የሽንት ቤቱ በር ክፍት ነበር በውስጧ "ውይ ፈጣሪዬ ገላገልከኝ ከፍተውለት ነው ማለት ነው የሄድት" ብላ እያስበች ዘው ብላ ወደ ውስጥ ገባች መሳይ ትንሽ ዝም ካለ ቡሀላ አጠገቡ ሆኖ ለሚያዋራው ለሱ ብቻ ከሚታየው ጓደኛው ጋር ማውራት ጀመረ•• መብራት ስለጠፋ ደስ አለህ አደል ድሮም አንተ ጭለማ እንደምትወድኮ አውቃለሁ ካልጠፋ ነገር ጭለማ መውደድህ እስቲ ምን ይሉታል ? ጥርስህን ላራግፍልህ ትንሽ ነው የቀረኝ ዝም ብለህ አታግጥጥ ! እሄ መብራት በትዛዝ ነው የጠፋው " አዋ በትዛዝ በትዛዝ ነው የጠፋው ብልሽት አይደለም ትከራከራለህ እንዴ ብሎ ሲጮህ ምኛት እዛው ሽንት ቤት እንዳለች በድንጋጤ ለመጮህ ዳዳት። መሳይ ልፍለፋውን ቀጠለ በትዛዝ ቆይ እኛ ኢትዬጲያ የምንኖረው ሀገራችን ስለሆነች እንጂ ተከራይተናት ነው እንዴ? ሙዚቃ ጮክ አድርገህ ከፍተካል ብሎ መብራቱን ከቆጣሪው እንደሚያጠፋ ክፉ የቤት አከራይ የሀገርን መብራት ሲፈልጉ የሚያጠፉብን ሲፈልጉ የሚያበሩልን ።ኢትዬጲያ የኛ ብቻ ነች እናንተ በክራይ ነው የምትኖሩት ካሉ እሄን ሁሉ ህዝብ ያከራየውን የኢትዮጲያን ባለቤት አከራዩንም በግልፅ ይንገሩን ።" ምኛት ወሬው ምን ለማለት እንደፈለገ ተምታታባትና "እሄ ትክክለኛው የእብዶች ወሬ መሆን አለበት ደሞ ኢትዮጲያ ብቸኛ ባለቤትና አከራይ አላት ይላል ሆሆሆ ፈጣሪ እባክህ ማረው! በገዛ ሀገራችን እንደተከራይ ለቀቁ ውጡ የሚሉን በዙኮ እሺ የኛ ኢትዬጲያ ወዴት ነሽ ኧረ ባክሽ ፍርድ ስጭን እስቲ ዛሬ ድምፅሽን አሰሚ የኔም ፍቅር ተወልዳ ባደገችበት ሀገር እንደ ተከራይ ተሳቆ መኖሩ መሯት እኮ ነው ጥላኝ የተሰደደችው ሀገሬ ሰው ፍርድ አልሰጥ ብሎኛል እስቲ አንቺ ፍረጅኝ ። እሺ የኔን ኢትዬጲያ እና የኔን ፍቅረኛ የት ሄጄ ነው ምፈልጋቸው ነገ የምትተነፍሱትም አየር የኛ ነው ቢሉን ምን ሊውጠን ነው ኧረ ዝም አትበይ እናት ሀገሬ"። እሚያወራው ለማልቀስ በቀረበ የሲቃ ድምፅ ነበርና ምኛት ፍርሀቷ ሳታስበው ወደ ብሶት ተቀይሮ የራሷን ሚኪን እንድታስታውስ ስላደረጋት እምባዋ ግጥም አለ... ይቀጥላል.... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Hammasini ko'rsatish...
😘ምኞት😘 🔥ክፍል 31 ✍ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . አላትና እሷን ትቶ ደሞ ወደ ጎኑ በፍጥነት በመዞር ለሱ ብቻ ለሚታየው ጓደኛው... " ምን ያስቅሀል የተለያየ ጭንቅላት ተመሳሳይና አሰልቺ ነገር አያወራም ብዬ ነውኮ። ትንቢተ እየፈራች ጠጋ ስትለው ቀና ብሎ ለደቂቃዋች አፍጥጦ ከተመለከታት ቡሀላ "ልክ አደለሁ እህት አለም "ኣላት ታናሹ ብትሆንም እንድ እህቱን ትንቢተን እህት አለም እያለ ሲጠራት ደስ ይለዋል ። "ልክ ነህ ውንድሜ : ትናደዳለህ ግን ደግሞ ማድመጥህን እታቆምም " ብዙ ግዜ አጠገቡ ቁጭ ብላ የተለያየ ጥያቄ እያነሳች ከወንድማ ጋር ማውራት ያስደስታታል በእብደት ውስጥም ሆነ ጤነኛ ከተወሰኑት በቀር የሚያወራው ቁም ነገር ነው። "ለምንድን ነው አንድ ጭንቅላት ብቻ ነው ያላቸው ያልከው ወንድሜ ? ስትለው ብዙ ሰው ህዝቡ ምን ይፈልጋል እንጂ ምን ያስፈልገዋል ብለው ማሰብ የማይችሉ የህዝቡ መሪ ሳይሆኑ ሲጮህ አብረው የሚጮሁ ሲስቅ አብረው የሚስቁ ሲሳሳትም እብረው የሚስቱ ተከታዮች ናቸው። የህይወትን ጣእም ሳይሆን አሰልቺነታን የሚያባብሱ እብዶች ።" አለና ተነስቶ ወደ ሽንት ቤት ሄደ ትንቢተ ትናንት ያወሩትን እያስታወሰች ዛሬ እዚህ ብቻውን ጥላው መሄዷ ይበልጥ አስከፍቷት እንባ ተናነቃት። ወደ አባቷ ዞረችና..... "እሺ አባ ምናልባት አንድ ነገር እንኳን ቢፈጠር ለማንኛውም ስልክ ከጎረቤት ይዘን ብንሄድስ?" "ኧረ ባክሽ አንቺ ልጅ ተይኝ ከሱ ባሽብኝኮ እሄ እኮ ኮንደሚንየም ነው የምን ጎረቤት ነው እምታወሪው ደሞስ አንድ እብድ እዚህ አስቀምጠናል አደራ ጠብቁልን ልትያቸው ነው ይልቁንስ ምግቡን አጠገቡ አስቀምጭለትና እንሂድ" አላት ፍቱን አጨማዶ መሰይን ቁልቁል እያየው። መሳይ አባቱንም እህቱንም በየተራ አያቸውና "እህትአለም" አለና ጠራት "ወዬ ወንድሜ" "እሄ እብድ አባትሽ ምንድን ነው እሚያወራው? ሲላት ዝም አለችው አሁንም እንደገና "እህት አለም" "ወይ ወንድሜ" "እሄ የኔና ያንቺ እባት ስራው ምን መሆን እንደነበረበት ታውቂያለሽ ?" "እእእእእ" " እሄ ጎማ በሚመስል ነገር የተቀጣጠለው ረጅሙ አንበሳ አውቶብስ የሱ ሹፌር ነበር መሆን ያለበት" አባትዬው ምን ሊያወራ ነው ደሞ ብሎ አፍ አፉን ያየዋል" "ለምን ወንድሜ" "ለምን.... የሚመሳሰሉበት ነገር ስላለ ነዋ እሄውልሽ የዛ አውቶቢስ ሹፌር ባንድ ደሞዝ ሁለት መኪና ሲነዳ የኛ አባት ደግሞ ባንድ ደሞዝ ሁለት ሚስት ነዳ! አለና የብድ ሳቁን ለቀቀው። ምኛት በመሳይ ንግግር ድንገት ሊያመልጣት የነበረውን ሳቋን እጃ ላይ አስቀረችው። አባትዬው ነይ እንሂድ ነይ እንሂድ ብሎ ሲወጣ ወንድማን ጎንበስ ብላ ሳመችውና ተከትላው ወጣች አባታ ከውጪ ሲቆልፍበት ግን ለውንድሟ በማዘኗ ሰውነታ ተንቀጠቀጠ ቢሆንም እንደምንም ችላው ካባቷ ጋር ተያይዘው ሄዱ። እንደሄዱ እብዱ መሳይ ሳሎን ውስጥ ከሬድዬው ጋር መከራከሩን ሲጀምር እቃ ቤት ደሞ የምኛት ጭንቀት ጀመረ ከራሷ ጋር ማውራት ጀመረች "አስረውት ይሆን እንዴ የሄድት ?ካልታሰረ እንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል? እሄን ለማረጋገጥ እስኪተኛ መጠበቅ አለብኝ ማለት ነው?ቢተኛስ ሬድዮው እንደዚህ እየለፈለፈ ቤት በኩል ይሰማኛል" ግራ ግብት ብሏት እዛው እቃ ቤት ትቁነጠነጣለች እሱ ከራሱ ጋር እያወራ ይስቃል. ሰአቱ ሄዷል መሸ... ሳሎን እና እቃ ቤት ሳይፈልጉ የተጣሉት ሁለቱ ተበዳዬች በየረሳቸው አለም ላይ ሆነው ሰአታት ተቆጠሩ።ከሬድዮኑ በላይ እየጮ ሲለፈልፍ የነበረው እብድ መሳይ በመሀል ለብዙ ደቂቃ ድምፁ ጠፋ ሬድዮው ማውራቱን ቀጥሏል። ምኛት ሞባይሏን በማብራት ድምጿን አጥፍታ እራቷን በልታ ጨረሰች አሁንም ከራድዮኑ ውጪ ሌላ ድምፅ የለም ። "ተኝቶ ይሆን እንዴ?" ብላ አሰበች ሆኖም ከተደበቀችበት እቃ ቤት ወጥታ የመሳይን ሁኔታ ለማጣራት ፈራች በሩ ላይ ቆማ የነበረ ቢሆንም ለመውጣት ድፍረት በማጣቷ ወደ ፍራሿ በመመለስ ጋደም አለች ። እንቅልፍ ሳይወስዳት ትንሽ እንደቆየች እንድ ያላሰበችው ነገር ድንገት በመከሰት መውጣሽ ግድ ነው እላት ችላው ለመተኛት ብትሞክርም ድሮም ሽንት ቋጥራ መቆየት የማይሆንላት ምኛት ሽንት ቤት መጠቀም ግድ ሆነባትና እንደ አዲስ ጭንቀትና ፍርሀት ሁለመናዋን ወረራት። ሀሳብ የሆነባት ምናልባት ተኝቶ እንኳን ቢሆን ያለችበትን እቃ ቤት በር ድምፅ ሳታሰማ መክፈት ብትችልም ምናልባት ባያያት እንኳን የሽንት ቤቱን በር አፉን ሳይከፍት መከፈት እንደማትችል ታውቀለችና እየተቁነጠነጠች ትንሽ ብትቆይም ከዛ በላይ መታገስ እንደማትችል ስትረዳ ••• ያበጠው ይፈንዳ እንጂ ሽንቴን ወጥሮኝ አልፈነዳ እንግዲህ አለች... ይቀጥላል..... 😘ምኞት😘 🔥ክፍል 32 ✍ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . እየተቁነጠነጠች ትንሽ ብትቆይም ከዛ በላይ መታገስ እንደማትችል ስትረዳ ••• ያበጠው ይፈንዳ እንጂ ሽንቴን ወጥሮኝ አልፈነዳ እንግዲህ አለች••• " በሩ ሲጮ ህ ሰምቶ ዘሎ ቢያንቀኝ የማን ያለህ ልል ነው" እያለች በቀስታ ወደ በሩ ተጠጋችና ቀሞች ምንም ድምፅ የለም በሩን በመክፈትና ባለመክፈት ፍርሀት ስታመነታ ትንሽ እንደቆየች .... እስኳሁን ድምፁን አጥፍቶ የነበረው መሳይ ድንገት ሳቁን ለቀቀው። ምኛት በጣም ከመደንገጧ የተነሳ ልባ ያመለጠቻት ነበር የመሰላት። እብዱ መሳይ ሳቁን እንደጨረሰ "አይ እናንተ የኛ አገር ጋዜጠኛች አገር በተላየየ ችግር እየታመሰ እናንተ ስለ ሮላንዶ የጫማ ቁጥር ታወራላችሁ አይ እምዬ ኢትዬጲያ" አለና ፊቱን ወደ ግራው አዙሮ "አየኽልኝ አይደል? ሰማኽልኝ አይደለ?ምን ዝም ትላለኽ አትናገርም ? እኔም እኮ እንዳንተ ኳስ እወዳለሁ ግን ስለ ሮላንዶ የጫማ ቁጥር መስማት ምን ይጥቅመኛል? እነዚህ ጋዜጠኛ መሳዬች የምናወራው ለማን ምን ይጠቅማል? ብለው አያወሩ የተመደበውን ሰአት ምን አውርተን እንጨርሰው ከማለት ውጪ እስቲ የሮላንዶን የጫማ ቁጥር ከማውራት እኔ ለፍቅረኛዬ የፃፍኩትን ደብዳቤ ቢያነቡልኝ አይሻልም እ....እ" አለና መልሶ ውደ ነበረበት ፀጥታ ተመለሰ። ምኛት ቀስ ብላ የእቃ ቤቱን በር በመክፈት እና አንገቷን ወጣ በማድረግ ስትመለከት ከምኝታ ቤት አልጋ ላይ አውርደው መሬት ባነጠፉለት ፍራሽ ላይ እግሮቹን ዘርግቶ ራድዮኑን አጠገቡ አስቀምጦ የእጆቹን ጥፍሮች እየበላ ቁልቁል ፍራሹ ላይ ያፈጠጠ ጅንስ ሱሪና ጥቁር ቲሸርት የለበሰ ረዘም ያለና የሚያምር ቀጭን ወጣት ተመለከተች። " ውይ ሲያሳዝን ምኑም እብድ እይመስልምኮ በፈጣሪ" እያለች ለሰከንዶች ካየችው ቡሀላ አሁን ትልቁ ሶፋ ስለሚከልለው በደንብ ባትታየውም ወደ ሽንት ቤት ለመግባት ብትሞክር ግን ፊት ለፊት እንደሚያያት ስለተረዳች ፈርታ ጭንቅላቷን ወደ ውስጥ መለሰችው። ሽንቷ ሊያመልጣት ደርሳል "ወይኔ ጉዴ እሄ ሰውዬ እንቅልፉን እሚተኛም አይመስለኝም ምን ይሻለኛል እኔ መፈንዳቴ ነው" አለችና ከሆዷ በታች በሁለት እጆቿ በመያዝ እዛው በሩ ስር ቁጢጥ አለች። እዛው ቁጢጥ እንዳለች ስትቁነጥነጥ ደቂቃዎች አለፉ መሳይ ከሬድዬው እኩል እየለፈለፈ በመሀል ባንድ ግዜ ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ አለ ። ምኛት ግራ ተጋብታ በፍጥነት ወደ በሩ በመዞር በአንድ አይና ወደ ኮሊደሩ ስታጮልቅ ጨለማ ነው ምንም ነገር አልታይ አላት መብራት ጠፍቷል መብራቱን ፈጣሪ ለሷ ብሎ ያጠፋላት ያክል ነበር ደስ ያላት በዚህ መብራቱ በጠፋበት አጋጣሚ ተጠቅማ መሳይ እብዲ ሳያያት ሽንት ቤት ገብታ መገላገል እንዳለባት ለመወስን ግዜ አላጠፋችም። ወድያው የእቃ ቤቱን በር በጥንቃቄ ከፋታ በመውጣት በቀስታ ወደንሽት ቤቱ ተጠግታ ለመክፋት እጃን ወደ እጀታው ላከች
Hammasini ko'rsatish...
ነ ደርጉ ቤት እያፈጠጠ። ሚኪ ስሜቱ ድብልቅልቅ አለበት ታዲያ አሁን የት ነች ?ማለቴ አሁንም እነሱ ጋር ነው ያለችው? አለው። "አረ ምአረ ምን እነሱ ጋር ነች ብን ብሏ ጠፋችላቸው ከወጣች ቡሀላ እምጥ ትግባ ስምጥ የሚያውቅም የለም"ሲለው ሚኪ ከደረቱ በታች የሆነ ነገር ብ...ጥ...ስ ሲል ተሰማው ወይኔ ምኛቴ እዚህም አልመጣሽም ማለት ነው አለ በለሆሳስ። አንገቱን ወደ መሬት አዘቅዝቆ መሬት መሬቱን እያየ ጩህ ጩህ ያለውን ስሜት እንደምንም ለመቆጣጠር ሞከረ። ሰውየው የሚኪን ሁኔታ ስላላስተዋለ ወሬውን ቀጥሏል... "ደሞኮ ሄዳም አልተፋታትም አሁንም በየሄደበት ቦታ በየመጠጥ ቤቱ ሳይቀር ስማን ያጠፋል አንድ ቀን እኔ በነበርኩበት መጠጥ ቤት... ይቀጥላል... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Hammasini ko'rsatish...