cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

TEKVAH ETHIOPIA

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 602
Obunachilar
+324 soatlar
+107 kunlar
+3230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ - ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር - ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር - የአውሮፕላን ነዳጅ ➡ ብር 70.83 በሊትር - ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 62.36 በሊትር - ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 61.16 በሊትር ሆኖ ባለበት ይቀጥላል። የቤንዚን ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ በሊትር 78 ብር 67 ሳንቲም ገብቷል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
ፋብሪካው ለተገደሉ ሰራተኞች ቤተሰቦች ድጋፍ! የወንጂ ስኳር ፋብሪካ አስተዳደር የዛሬ 2 ወር ከስራ ገበታ ታግተው በግፍ ለተገደሉ 5 ሰራተኞቹ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው አንድ መቶ ሺህ (100,000) ብር ድጋፍ አደረገ። እነኚህ ሰራተኞች ለሸንኮራ አገዳ ተከላ መሬት ዝግጅት ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም በታጣቂዎች ታግተው ቆይተው መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም 5ቱ መገደላቸው ይታወሳል። ከገንዘቡ ተጨማሪም ከየተጎጂ ቤተሰቦች መካከል ለአንድ ሰው ቋሚ የስራ እድል ፋብሪካው በማመቻቸት እንደ ማፅናኛ በዘላቂ ለመደገፍ መወሰኑም ታውቋል። በተመሳሳይ ፋብሪካው በገቢ ዝቅተኛ ለሆኑ አንድ መቶ አቅመ ደካማ የአካባቢው ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት ድጋፍም ማድረጉን የፋብሪካው ሕዝብ ግንኙነት መረጃ ያመለክታል።ለተጎጂ ቤተሰቦቹ ድጋፉ በይፋ የተበረከተው ፋብሪካው የዘንድሮ (2016 ዓም) በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸምን የስራ አመራር ቦርድ አባላት በተገኙበት ከተካሄደው ግምገማና የመጪ አመት እቅድም ላይ በመከረው ሁነት አጋጣሚ ላይ ነው። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ምክትል ር/መስተዳድር እና የፋብሪካው ስ/አ/ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አወሉ አብዲ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የዘንድሮው አፈጻጻም ካለፉት 3 አመታት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ጥሩ ውጤት እንደተመዘገበ ገልጸዋል። ፋብሪካው ለረዥም ዓመታት በኪሳራ ውስጥ የቆየ ሲሆን መጋቢት 20 / 2014 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ 496/2014 ፋብሪካው ራሱን ችሎ በስራ አመራር ቦርድ እንዲተዳደር መወሰኑ ይታወሳል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Ethiopia በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል። ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል። ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል። " የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል። የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል። በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2😁 1
#AddisAbaba ሀሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ተነግሯል። ፈተናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን ነው የሚሰጡት ተብሏል።   ፈተናው በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺህ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ተገልጿል። በፈተና ወቅት ተመዛኞች ስልክ ሆነ ማንኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዞ ፈተና ክፍል መግባት እንደማቻል ተገልጿል። ተመዛኞች ፦ ➡️ የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ➡️ ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና ፈተና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል። ምንም እንኳን ፈተናው በፍቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,491 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ቢገለጽም የምዘና ፈተና ለመውሰድ #ስላልተመዘገቡ ወይም ፍቃደኛ ስላልሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ምንም የተባለ ነገር የለም።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከሀዋሳ አዲስ አበባ በሚበር አውሮፕላን ጭስ ቢታይም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ የበረራ ቁጥር ኢቲ 154 ዛሬ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ አውሮፕላኑ ውስጥ ጭስ ታይቷል። ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ መጠየቁን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቻይናዊቷ ሚስት ለትዳር አጋሯ ያሳየችው ፍቅርና እንክብካቤ በበርካቶች ተወድሷል በምስራቃዊ ቻይና አንሁይ በተባለችው ግዛት ነዋሪ የሆነችው ሰን ሆንግሻይ ባሏ በ2014 በገጠመው ድንገተኛ የልብ ድካም ኮማ ውስጥ ይገባል። በአጭር ጊዜ ከኮማ ይወጣል፤ የቤተሰቡም ስጋት ይወገዳል ተብሎ ቢጠበቅም ምን እየተካሄደ እንደሆነ በውል መረዳትና መግለጽ የማይችለው ባል 10 አመታት ኮማ ውስጥ ይቆያል። ከሰሞኑ ግን ሰን ለድፍን አስር አመታት በተስፋ የጠበቀችው፤ በብዙ የደከመችለት ጉዳይ ፍሬ አፍርቶ የምትወደውና የሁለት ልጆቿ አባት ነቅቷል።ያለፉትን አመታት እንዴት እንዳሳለፈች በእምባ ታጅባ ስትነግረው የሚያሳይ ምስልም ተለቋል። “ምንም እንኳን በጣም ቢደክመኝም ቤተሰባችን ወደቀድሞው ደስታው እንዲመለስ የተከፈለ መስዋዕትነት አድርጌ እወስደዋለሁ” ስትልም ዳዋን ለተሰኘው የቻይና መገናኛ ብዙሃን ተናግራለች። የሰን ባል ረጅም አመት ኮማ ውስጥ መቆየቱን ተከትሎ የሚስቱ ድጋፍ እጅግ ወሳኝ ነበር።የሰውነት አካሉን ማዘዝ ስለማይችል አይንቀሳቀስም፤ ይህም ካለሚስቱ ድጋፍ መጸዳዳት እንኳን እንዳይችል አድርጎታል። አይኑ በሂደት በከፊል መገለጥ መጀመሩ ተስፋየን እያለመለመው ሄደ የምትለው ሰን ከጊዜ ወደ ጊዜ ህመሙ እየበረታ ፈተናዋን ቢያበዛባትም እስከህይወቱ ፍጻሜ አብራው ለመቆየት ቃል ለገባችለት ባሏ ሙሉ ጊዜዋን ሰጥታ ያለመሰልቸት ተንከባክባዋለች። ለ10 አመት የባሏን ህመም የተጋራችውና ፍቅሯን በተግባር ያሳየችው ቻይናዊት ሚስት ለልጆቿ አርአያ ሆናለች። በርካቶች “እውነተኛ ፍቅር ማለት ይህ ነው” እያሉ አድናቆታቸውን እየገለጹላት ይገኛሉ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 3👏 1
የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናልን ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ ተጠናቀቀ ********** የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናልን ከዋናው የአስፋልት መንገድ ጋር የሚያገናኘው የ1.2 ኪ.ሜ. ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ግንባታ ተጠናቅቋል። ግንባታው የተጠናቀቀው ይህ መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ወደቡ በአሁኑ ሰዓት በቀን ከ150-200 የከባድ ጭነት ገቢ ተሸከርካሪዎችን እያስተናገደ መሆኑን የተቋሙ መረጃ ጠቅሷል። የመንገዱ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት መግባት የወደቡን የአገልግሎት አሰጣጥ እጅግ ቀልጣፋ እንደሚያደርገው ይታመናል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ትላንት በአዲስ አበባ ፣ በቦሌ ክ/ከተማ " ስካይ ላይት ሆቴል " አካባቢ #እግረኞች ላይ በደረሰ የትራራፊክ ግጭት 1 ሰው ሞቷል። አንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶው " ቸራአሊያ " በሚባል አካባቢ #እግረኛ ላይ በደረሰ ግጭት ደግሞ አንድ ሰዉ ሞቷል። ልደታ ክ/ከተማም በተመሳሳይ የአንድ ሰው በትራፊክ አደጋ ሞቷል። በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ደግሞ ቡና በመሸጥ ላይ የነበረችው ወጣት ወደ ኋላ እየሄደ በነበረ ኤፍኤሳር መኪና ተገጭታ ሞታለች። የመረጃዎቹ ምንጮች የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት / የአዲስ አበባ ፖሊስ (ኢትዮ ኤፍ ኤም) ናቸው።
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
Available In Hand 🛒🔥😍 # minoxidll #Quality 👌 Original minoxidll 📐መጠን 6 pc   📩በቴሌግራም (Telegram contact) :@Yonatan_Be 📲ስልክ ቁጥራችን(Phone):+251939367801 +251978082486 📍- አድራሻ adama around of franko @ethio_online_hd
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
Tapswap ከ notcoin ቀድሞ list ሊደረግ ነው ወገን 😁 ድፍን 24 ቀን አላችሁ ያልጀመራችሁ ዛሬውኑ ጀምሩ 👇👇 https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_6467448245
Hammasini ko'rsatish...
👍 3