cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኣጭር መንፈሳዊ ታሪኮች

ኣዳዲስ መዝሙሮች ,, ,, ኣስተማሪ ታሪኮች ወ.ዘ.ተ ይቀላቀሉንን ይግቡ ይቀላቀሉ በወንጌል ይስበኩ ድንግል ነች የኛ ዋስ ||| |||| ኣይናችን ነሽ ♥ማርያም♥ ኣንችን ኣይንኩብን የ ♥ተዋህዶ♥ ልጆችሽ ☜እንወድሻለን ግቢ ከ ቤታችን በረከታችን ነሽ በ ሃሴት ቁመናን ♥ደስታን♥ ስለወለድሽ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
198
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሆነ ሃገር መሪ መሰሉኝ ። ብቻ የሆነ ቦታ ስማቸውን የሰማሁትም ይመስለኛል። እናም እኚህ ሰው ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ላይ “በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት” ጠቅሰው በዚህ መልኩ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ለእኚህ መሪ እየታረደ ያለው “ ዐማራ ” የተባለ ነገድ እንጂ ኢትዮጵያውያን ምንም እንዳልሆኑ የሚነግራቸው ቢኖር መልካም ነበር። እንዴት ያለውን ቀልደኛ የበሻሻ አራዳ ነው የጣለብን? የመድኃኔዓለም ያለህ።
Hammasini ko'rsatish...
✞ የክብር ስግደት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ✞ እንኳን ለጻድቁ አባት አቡነ ገብረ ሕይወት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ከቅዱሱ አባታችን ጸጋና ሰማያዊ ኃይል ለመካፈል መልክአቸውን ከጸለያችሁ በኋላ የክብር ስግደት እየደጋገማችሁ በስማቸው ስገዱ፡፡ የክርስትና ንግሠ በዓል ዝክር ሻማ አብርቶ፣ የበረከት ዳቦ ቆርሶና ማሳመሪያ ቄጤማ ጎዝጉዞ ብቻ አይገለጽም፡፡ ይሄ የክብረ ቀኑ የበዓል እንድምታው ነው፡፡ የእምነት እንድምታው የሚገለጸው በስግደትና በጸሎት ነው፡፡ በመሆኑም ሙሉ የሆነ ክብረ-እምነትን፥ ክብረ-በዓልን እናክብር፡፡ ከዘልማድ አካሄድ ወጥተን የምግባር ሰዎች እንሁን @bemaleda_neku
Hammasini ko'rsatish...
Zemnay yemaryam Lje - (2) (2) a8fEhuTQgfA.m4a4.87 MB
✥ ብዙኃን ማርያም 👆👆👆 በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤ በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን ‹‹ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ›› ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ መካከል ፫፻፲፰ (ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው ‹‹ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው›› ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም ‹‹ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን›› ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡ ይቀጥላል ..... ♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥ ♥♥♥♥♥♥♥♥♥ ✞✞✞✞✞✞✞✞ የ ♥ድንግል♥ ♥ማርያም♥ ልጆች
Hammasini ko'rsatish...
#ብዙኃን_ማርያም መስከረም 21 እንኳን አደረሳችሁ
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.