cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ገድለ ቅዱሳን

@Gedelat ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡ በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
6 672
Obunachilar
+324 soatlar
-27 kunlar
-730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

01:28
Video unavailableShow in Telegram
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [    አናቅጸ ሲዖል ! [ የሲዖልደጆች ]     ] 🔔 ከቅዱሳን ፍኖት ካንዲቱ ሃይማኖት ከጸጥታ ወደብ ከተዋሕዶ በረት ብዙ የዋሃንን ነጥቆ ያጠፋቸው ከአሚነ ሥላሴ ከጠባቧ መንገድ ድንገት ያሳታቸው የበግ ለምድ ለብሶ ይመጣል ተብሎ የተነገረለት መናፍቅ አውሬ ነው የነብሳችን ጠላት ! ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው ፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ ፤ የዓመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል ፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ ፤ ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዓይኖች አሉአቸው ፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው ፤ የተረገሙ ናቸው። ❞ [ ፪ጴጥ.፪፥፲፪ ] ❝ ከውሾች ተጠበቁ ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ ፥ ❞  [ፊል.፫፥፪]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
Hammasini ko'rsatish...
2.23 MB
Photo unavailableShow in Telegram
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊         [     ያ ለ    እ ም ነ ት !     ]           ክፍል - ፲፩ - እና የመጨረሻ ክፍል በምሽቱ መርሐ-ግብር ይቀርባል።          ይከታተሉ !   🕊 በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊 ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬
Hammasini ko'rsatish...
🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
[ + ደሙን ክሶልናል + ] .mp32.87 MB
[ + ማን እንደርሱ + ] .mp34.07 MB
Photo unavailableShow in Telegram
                          †                           🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 ❝ አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ንጉሠ ነገሥት ወእግዚኣ ኣጋእዝት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ኦ ትዕግሥት ወአርምሞ በፍቅረ ዚአነ በጽሐ እስከ ለሞት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ወንሕነኒ ንግበር በዓለነ ቅድስተ ፋሲካ በሐሴት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ገባሬ ሕይወት ክርስቶስ ❞ [ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ ፣ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ ፣ ... ወዮ ትዕግሥትና ዝምታ ፣ እኛን ከመውደዱ የተነሣ እስከ መሞት ደረሰ ፣ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ፣ እኛም የተቀደሰች በዐላችንን ፋሲካን [ ትንሣኤን ] በደስታ እናክብር ፣ ሕይወትን የሠራ [ የፈጠረ ] ክርስቶስ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ። ] ------------------------------------------------- [ ድጓ ዘፋሲካ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Hammasini ko'rsatish...
[ ስንክሳር ሰኔ - ፬ - ] .mp33.84 MB
🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ ❖   ሰኔ -  ፬  -  ❖ [ ✞ እንኩዋን ለታላቁዋ ሰማዕት "ቅድስት ሶፍያ" እና ለቅዱስ "ዮሐንስ ዘሐራቅሊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ] † 🕊   ሶፍያ [ SOPHIA ]   🕊 † ሶፍያ [ "ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ ] በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህ ስም የሚጠሩ አያሌ ቅዱሳት አንስት ሲኖሩ አንዷ ዛሬ ትከበራለች:: † 🕊 ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት  🕊 † ቅድስቷ የተወለደችው በምሥራቅ ሮም ግዛት ውስጥ በ ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ዘመኑ የጭንቅ : የመከራ በመሆኑ ሕዝቡ በስደት ይኖር ነበር:: የቅድስት ሶፍያ ወላጆች ክርስቲያኖች ናቸውና በመልካሙ መንገድ በንጽሕና አሳድገዋታል:: ባለጠጐች በመሆናቸው አገልጋይ ቀጥረውላት : ያማረ ቤት ሰርተውላት በዚያ ትኖር ነበር:: ሁሉ ያላት ብትሆንም ሁሉን ንቃ በጾምና በጸሎት ትኖር ነበር:: ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለከተማው መኮንን [ገዢ] ሊድሯት መሆኑን አወቀች:: ወደ ቤቷ ገብታ ፻ [100] ጊዜ ሰገደች:: ወደ ፈጣሪዋም ጸለየች:- "ጌታየ ሆይ! የዚህን ዓለም ቀንበር አታሸክመኝ:: አልችለውምና:: ያንተው ቀንበር ግን የፍቅር ነውና እችለዋለሁ" አለች:: አገልጋዩዋን ጠርታ ብዙ ወይን አጠጥታት ልብስ ተቀያየሩ:: በሌሊትም ወጥታ ወደ በርሃ ሔደች:: ዓላማዋ ምናኔ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ግን ሌላ ነበር:: በመንገድ ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ ብዛት ሲሰደዱ አገኘቻቸው:: እርሷ ስደትን አልመረጠችም:: እያጠያየቀች "ሰው በላ" ከተባለው አረመኔ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ደረሰች:: በንጉሡ ፊት ቀርባ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አለችው:: ንጉሡ ከመልኩዋ ማማርና ከድፍረቷ የተነሳ አደነቀ:: ሊያባብላት: ሊያስፈራራትም ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው ጦር ባለው የብረት ዘንግ ደብድበዋታልና ደም አካባቢውን አለበሰው:: መሬት ለመሬት እየጐተቱ እሥር ቤት ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ፈውሷት ሔደ:: አንዴ በእሳት: አንዴም በስለት: ሌላ ጊዜም በግርፋት አሰቃዩዋት:: ከሃይማኖቷ ግን ሊያነቃንቁዋት አልቻሉም:: በመጨረሻ አንገቷን እንድትሰየፍ ንጉሡ አዘዘ:: ወታደሮቹም ፈጸሙት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቅድስት ሶፍያን በክብር አሳረጋት:: "ስምሽን የጠራ: መታሰቢያሽን ያደረገ ምሕረትን ያገኛል" አላት:: † 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ  🕊 † ቅዱሱ የነበረው በተመሳሳይ በዘመነ ሰማዕታት ነው:: አባቱ ዘካርያስ: እናቱ ኤልሳቤጥ: እርሱ ደግሞ ዮሐንስ ይባላል:: የሚገርም መንፈሳዊ ግጥጥሞሽ ነው:: የቅዱሱ ወላጆች የሃገረ ሐራቅሊ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ የተመሰከረላቸው ደጐች ነበሩ:: ዘካርያስ አርፎ ዮሐንስ በመንበሩ የተቀመጠው ገና በ ፳ [20] ዓመቱ ነበር:: በወቅቱ ከ፪ [2] አንዱን መምረጥ ነበረበት:: ፩. ለጣኦት ሰግዶ በምድራዊ ክብሩ መቀጠል ፪. ወይ ደግሞ በክርስትናው መሞት ቅዱስ ዮሐንስ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ነውና ፪ [2] ከባባድ ነገሮችን ፈጸመ:: በመጀመሪያ በአካባቢው ያሉ ጣዖት ቤቶችን አወደመ:: ቀጥሎ ወደ ንጉሡ ሔዶ በመኩዋንንቱ ፊት "ክርስቶስን የተውክ ሰነፍ" ብሎ ገሠጸው:: ከዚህ በኋላ በቅዱሱ ላይ የተፈጸመው መከራ የሚነገር አይደለም:: ያላደረጉት ነገር አልነበረም:: እሳቱ: ስለቱ: ሰይፉ: መንኮራኩሩ . . . ከሁሉ የከፋው ግን ቆዳውን ገፈው በእሳት ጠብሰውታል:: እርሱ ግን ስለ ሃይማኖቱ ይሕንን ሁሉ ታግሶ በዚህች ቅን አንገቱን ተሰይፏል:: አምላካችን እግዚአብሔር ግፍዐ ሰማዕታትን አስቦ እኛን ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ሰኔ ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት ፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት] ፫. ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት ፬. ቅድስት ማርያ ሰማዕት ፭. ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ [ሰማዕታት ፮. ቅዱስ አሞን ሰማዕት [ †  ወርኃዊ በዓላት ] ፩፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፪፡ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ " እንግዲሕ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጀሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: " [ማቴ.፲፥፳፮] (10:26) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ ለታላቁ አባት በደብረ ዳሞ ገዳም ለ37 ዓመታት ላገለገሉ 3 ታላላቅ ገዳማት በስማቸው ለተሰየመ #ለአቡነ_ሠምረ_አብ_ዘሳይንት_ወዘትግራይ ዓመታዊ ለልደት በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                                                                   ✝️ ✝️ ✝️                         ❤#አቡነ_ሠምረ_አብ_ዘሳይንት_ወዘትግራይ፦ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ሲሆኑ የትውልድ ሀገራቸው በወሎ አምሐራ ሳይንት ነው። አቡነ ሠምረ አብ የትውልድ ዕለታቸው ሰኔ 4 ቀን ነው።በብሕትውና ከተረጋገጠላቸውና ከ47ቱ ከታወቁት ሊቃውንት አንዱ ናቸው። ❤ አባ ሠምረ አብ ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ሄደው በዚያ 37 ዓመት ተቀምው፤በኋላም ወደ ገርዓልታ ሄደው በስማቸው የተሰራውን ታላቁን  ገዳም ቆረቆሩ። (ገርዓልታ አቡነ ሠምረ አብ ገዳም)፤በዚህም ምክንያት አቡነ ሠምረ አብ ዘትግራይ ይሏቸዋል። በተጨማሪም አስደናቂ የሆነ ገዳማቸው በጎንደር ደንቀዝ ውስጥ ይገኛል። ❤ በኢትዮጵያ ውስጥ በጻድቁ ስም 3 አብያተ-ክርስቲያናት ተሰርተዋል።የዕረፍት ቀናቸውም ጥር 4 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ሠምረ አብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!።  ምንጭ፦ ዜና ቅዱሳን። @sigewe https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886 https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Hammasini ko'rsatish...
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886