cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

"የስነፁሁፍ "መድረክ yesnetsuhuf medrek

https://t.me/joinchat/ME_tioE_0Z0xNjVk kedir adisi

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
203
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሁሌ በሰው ፊት የሚያዋርድህን ጀለስ ዛሬ ከቸከሱ ጋ ስታገኘው በአል ነው ብለህ ገላህን @kediradisi አሉ እውነት ነው?፠ ፠
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አንድ ሰው ግን ምንም ቀልድ አይገባውም ለቀልድ ብዬ አናቱን በኮብል ስለው እሱ አምርሮ ተጣላኝ@kediradisi
Hammasini ko'rsatish...
በሬድዮ የሙዚቃ ምርጫ ላይ ነው እና አንዷ ሙዚቃ ለመጋበዝ መስመር ላይ ገብታለች 👨‍🦳ሄሎ ጤና ይስጥልን ይህ የሙዚቃ ግብዣ ሰአታችን ነው ማን እንበል 👱‍♀Z ነኝ 👨‍🦳ይቅርታ ሙሉ ስምሽን 👱‍♀አይ ማንም እንዲያውቀኝ ስላልፈለኩ ነው 👨‍🦳እሽ ለማን ነው የመረጥሽው 👱‍♀ለ A 👨‍🦳ሙሉ ስሙስ 👱‍♀አይ! እሱንም ሰው እንዳያውቀው 👨‍🦳እሽ ከየት ነው 👱‍♀አይ! የአካባቢው ሰው እንዳያውቀን 👨‍🦳እሽ ምንድን ነው ታዲያ 👱‍♀ያው እሱም ይወደኛል እኔም እወደዋለው 👨‍🦳እንዴ እሽ አንች ዉደጅው እስ እንደሚወድሽ በምን አወቅሽ 👱‍♀ማ አሰግድ !?😳 እኔ ዘነቡን እንደሚወድ ድፍን የዲላ ህዝብ ነው የሚያውቀው። chanala ችንን ለማግኘት ፠፠፠ ፠፠ ፠፠፠ ፠፠፠@kediradisi
Hammasini ko'rsatish...
አውራ ሥህተት. ከሥህተቶች ሁሉ ሥህተት, የሌላ ሠውን ጭንቅላት, እንደራሥ ጭንቅላት መገመት.
Hammasini ko'rsatish...
ውዳሤ.
Hammasini ko'rsatish...
. እናቱን አይወዳትም፡፡ ምላሷ እንደ ኤሌክትሪክ ሲለበልበው ነው የኖረው፡፡ አንድም ቀን እንደ ልጅ የእናት ፍቅር ሰጥታኛለች ብሎ አያምንም፡፡ ገና ህፃን እያለ ባጠፋ ቁጥር ሰንበር በሰንበር እስኪሆን ድረስ ታቀምሰው የነበረው ዱላ ህመም ዛሬም ድረስ አይረሳውም፡፡ ዕድሜው ገንዘብ ለማግኘት ሲበቃ መጀመሪያ የወሰደው እርምጃ ቤት ተከራይቶ ለብቻው መኖር ነው፡፡ የእናቱን ምላስ ሽሽት! ከቤት ከወጣ በኋላ እናቱን አንድም ቀን ሊጎበኛት ሄዶ አያውቅም፡፡ እናቱ የመጀመሪያ ሰሞን ወደ ቤት እንዲመለስ አዲስ የተከራየው ቤት ድረስ እየተመላለሰች ትለምነው ነበር፡፡ እሱ ግን ‹‹ቤቱ ይስፋሽ! ከዚህ በኋላ ያንቺን ጭቅጭቅ የምችልበት አቅም የለኝም!›› አቋሙን በግልፅ ነገራት፡፡ ይኸው ዛሬ ከአራት ዓመት በኋላ ሚስቱ እናትህን አስተዋውቀኝ እያለች ብትወተውተውም በጄ አላለም፡፡ ካለፈው ወር ጀምሮ እናቱ መታመሟን መንገድ ላይ ያገኙት የሰፈሩ ልጆች ሁሉ ቢነግሩትም ልቡ ርህራሄ ተላብሶ በድላኛለች ብሎ የሚያስበውን በደል ሊረሳለት አልቻለም፡፡ ‹‹ልጅነቴን የሃዘን ማቅ አልብሳዋለች!›› ይላል፡፡ እናቱ ስትነሳ ትዝ የሚለው ዱላዋ እና የሚያንገበግብ ምላሷ ብቻ ነው፡፡ አዕምሮው የሚያስታውሰው …. ሜዳ ላይ እየተጫወተ ድንገት ከልጆች መሃል ነጥላ በር ሳትዘጋ ወጣህ በሚል ሰበብ አንገቱን አንቃ ጭኑን የምትመዠልገውን ሴት ነው፡፡ በዚህ ሳቢያ የጓደኞቹ መቀለጃ እንዲሆንና የበታችነት ስሜት እንዲፈጠርበት እንዳደረገች ይሰማዋል፡፡ ሚስቱ የደረሰች እርጉዝ ነች፡፡ አልጋ ላይ ከጎኑ በጀርባዋ ተኝታ ‹‹አብዱዬ ዛሬ ምጤ ሳይመጣ አይቀርም በጣም እየቆረጠኝ ነው›› አለች፡፡ ‹‹ሃኪም ቤት እንሂድ?›› ተቁነጠነጠ፡፡ ብዙ ቀን እንደዚህ ሆዴን እየቆረጠኝ ነው ብላው ሃኪም ቤት ሲደርሱ ገና ነሽ ተብላ ተመልሳለች፡፡ ምጥም ሆነ ሆድ ቁርጠት መሄዱ አይከፋም ብሎ ስላሰበ የወሊድ ክትትል ወደምታደርግበት ሆስፒታል አመሩ፡፡ ሆስፒታሉ ውስጥ በርካታ ነብሰጡሮች ይታያሉ፡፡ የአብዱ ሚስት ዘጠኝ ወር ስላለፋት ቅድሚያ አግኝተው ዶክተሩ ጋር ገቡ፡፡ ዶክተሩ ጥቂት ምርመራዎችን ካደረገ በኋላ ምጥ እንደጀመራትና በአስራ-ሶስት ሰዓታት ውስጥ ትወልዳለች ተብሎ እንደሚገመት አስረዳቸው፡፡ አብዱ ሰዓቱን ሲመለከት 12:30 ይላል፡፡ እዛው ማደራቸው እንደሆነ ሲገባው የሚስቱ እህት ጋር ደውሎ ሁኔታውን አስረዳት፡፡ ከአንድ ሰዓት በኋላ የሚስቱ እህት እና እናት አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ይዘው ሆስፒታል ደረሱ፡፡ የአብዱ ሚስት በስሱ ‹‹እህህህ›› ‹‹እህህህ›› እያለች ታቃስታለች፡፡ እየደጋገመች ሰዓት ትጠይቃለች፡፡ ድምጿን ከፍ አድርጋ መጮህ ስትጀምር ነርሶቹ እየመጡ እየጮኸች ኃይል ማባከን እንደሌለባት ይመክሯታል፡፡ አብዱ በእህቷ እና በእናቷ መሃል ተቀምጣ የምታቃስተውን ሚስቱን ከፊት ለፊቷ ያለው ወንበር ላይ ተቀምጦ በስስት ይመለከታል። ፊቷ ፍም መስሏል። የህመም ምስል ግንባሯ ላይ ተከትቧል። ጭምድድ. . .ፈታ. . . ጭምድድ. . .ፈታ ይላል። ፊቱን ከሚስቱ ላይ አንስቶ የሆስፒታሉ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ የተቀመጡ ሌሎች ነብሰጡሮችን በአይኑ ቃኘ። ከአይናቸው እንባ የሚፈስ ጠና ያሉ አንዲት ሴት ተመለከተ። የመጀመሪያ ልጃቸው እንዳልሆነ ገምቷል። ሆስፒታሉን በጩኸት እያናጉት ነርሶቹ እየተመላለሱ እንዲረጋጉ ሲለምኗቸው ተመለከተ። ‹‹አብዱዬ ስንት ሰአት ሆነ?›› ሚስቱ እያቃሰተች ጠየቀችው። ‹‹ሶስት ሰአት ሊሆን ነው።›› ‹‹ገና አስር ሰአት ሁሉ እንዲህ ልሆን ነው?›› ማልቀስ ጀመረች፡፡ በአጠገቧ እያለፈ የነበረው ነርስ ፈገግ ብሎ ‹‹ገና መቼ ተጀመረና …. ምጡ ሲጀምርሽማ አንደበትሽ መች እንዲህ ይፈታል?›› ብሎ እየሳቀ ሄደ። ከለሊቱ አምስት ሰአት! የአብዱ ሚስት ማቃሰት አንጀት የሚበላ ለቅሶ የቀላቀለ ሆኗል። አሁን እናቷ ወደ መታጠቢያ ቤት ስለሄዱ አብዱ ከጎኗ ተቀምጦ ደረቱን አስደግፏታል። ትንሽ ቆይታ ጀርባዋ ለሁለት የተከፈለ ፤ አንገቷ ቦታውን የለቀቀ መሰላት። ሰውነቷ እሳት ውስጥ እንደተጣለ እጣን ተንቦገቦገ። ‹‹ኣ ኣ ኣ እምም እምም አብዱዬ ኣ ጀርባዬን እከክልኝ እስኪ ኣ›› አብዱ ጀርባዋን ለመዳሰስ እጆቹን ሰደደ። መዳፉ ጀርባዋ ላይ ሲያርፍ የበለጠ አንገበገባት። ‹‹ተወኝ አብዱዬ ተወኝ›› ትከሻዉን ጨምድዳ ይዛ ታቃስታለች። ከደቂቃዎች በኋላ የአብዱ የሸሚዝ ቁልፎች በሚስቱ የስቃይ ጭምደዳ አኩርፈው መርገፍ ጀመሩ። አብዱ የሚስቱን ስቃይ ሲመለከት ‹‹ልጅ ባይወለድስ ፣ ቢቀርስ›› ሲል አሰበ። በህይወቱ የሰው ልጅ በዚህ ደረጃ ሲሰቃይ ተመልክቶ አያውቅም። የአብዱ ሚስት የስቃይ መጠኗ በየደቂቃዎቹ እየናረ ሰአቱ ከጠዋቱ አንድ ሰአት ሆነ። አሁን ሚስቱ የምትናገረውን በቅጡ የምታውቅ አትመስልም። ህመሙ ሲጠናባት የአብዱን ትከሻ ትነክሳለች። በእጆቿ ደረቱን ትደበድበዋለች። ድምጿን ያለ ቅጥ ከፍ አድርጋ መጮህ ጀምራለች። ነርሶቹ መውለጃ ሰአቷ ስለተቃረበ ወደ ማዋለጃ ክፍል አስገብተው አስተኟት። አብዱ እና እናቷ አብረዋት ገቡ። እህቷ በጣም ስለደከማት እንግዳ መቀበያ ክፍሉ ውስጥ አሸለበች። ሰአቱ ሶስት ሰኣት ተኩል ሲሆን ቤተሰቦቿ እንዲወጡ ተደረገ። አዋላጅ ዶክተሩ እና ነርሶች ወደ ክፍሉ ገብተው በሩን ዘጉት። አብዱ ከውጪ ቆሞ ጣራን በሚነቀንቀው የሚስቱ የሲቃ ጩኸት ውስጥ ካረገዘች ቀን ጀምሮ ያሳለፈችውን ስቃይ ማሰብ ጀመረ። የበላችው ሆዷ ውስጥ አልቀመጥ እያለ ሲያስመልሳት ፤ ማታ እንቅልፍ አጥታ ስትንቆራጠጥ . . . ስሜቷ ሲዘበራረቅ …. ብዙ ትዕይንቶች ታዩት። በመሃል ግን ሳያስበው ጭንቅላቱ አንድ ጥያቄ ጫረ። ‹‹አንተ ስትወለድ እናትህ ይህን ሁሉ መከራ አልቀመሰችም እንዴ?›› ‹‹ኧረ እኔ ስወለድ እንዲህ አላስቸገርኩም!” ለማስተባበል ሞከረ …. ግን አልቻለም። እናቱ ያሳረፈችበትን የዱላ እና የምላስ ውርጅብኝ በሚስቱ ካየው የምጥ ስቃይ ጋር ሲመዝነው የትቢያ ያህል ቀለለበት። ምንም የሚገባውን ባትሰጠውም እናቱ በመውለዷ ብቻ ታላቅ ክብር እንደሚገባት ተሰማው። ሚስቱ ወልዳ ወላጆቿ ቤት ከገባች በኋላ አብዱ የታመመችውን እናቱን መጠየቅ እንዳለበት አምኖ ለእስከዛሬዉም ይቅርታ ሊጠይቅ ወደ ድሮ ሰፈሩ አቀና። በዉስጡ እዛ ሲደርስ ሊላት የሚችለውን እየተለማመደ ነበር። ‹‹ይቅርታ እማይዬ ልጅነት አሳስቶኝ በድዬሻለሁ።›› ሊል አሰበና የልቡን አልገልፅ አለው። በቃ ሳያት የመጣልኝን ብዬ እግሯን እስማለሁ ብሎ አሰበ። ወደ ቤታቸው የሚወስደው ቅያስ ጋር ሲደርስ ትንፋሹን አሰባስቦ ታጠፈ። በራቸው ላይ በርካታ ሰዎች ተሰብስበዋል። እጃቸውን ወደ ኋላ አጣምረው የሃዘን ድባብ ያጠላበት ፊት የሚያሳዩ አባቶች ፤ ከሚኒባስ መኪና ውስጥ ቃሬዛ የሚያወርዱ ወጣቶች ፤ ልብ የሚያሸብር የለቅሶ ድምፅ የሚያሰሙ ሴቶች አካባቢውን ወረውታል። አብዱ በግልምጫ ታጅቦ በደመነፍስ የተሰበሰበውን የሰው ጎርፍ ሰንጥቆ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገባ። ቤት ውስጥ ሲገባ ጎረቤቶቹ እናቱን ከአልጋ ወደ ቃሬዛ ለአራት ተሸክመው ሲጭኗት ተመለከተ። ማመን አልቻለም። ልጁ ወደ ምድር በመጣችበት ሰሞን እናቱ ምድርን ለቀቀች። በድን ሆነ። ይቅርታ ለመጠየቅ በእጅጉ ማርፈዱ ገባው። ‹‹እማማማማኣኣኣ›› ጩኸቱ መንደሩን አናጋው። ተፈፀመ ፠ ፠፠፠ ፠፠፠ ፠#sher ፠፠፠ ፠፠፠ ፠፠ ፠፠፠@kedi
Hammasini ko'rsatish...
ውዳሤ. ምን ብዬ ላወድሥህ ምን ልበልህ እኔ, ላገልግልህ እሥቲ ፍቀድልኝ በህይወት ዘመኔ. ኧረ ለመሆኑ ከሠማይ ነው ከምድር የተገኘኸው, የትኛውሥ መሀጸን ነው አንተን የወለደው. በጥላቻ ምትክ ፍቅርን ያሥተማርከኝ, ከእራሥህ ይልቅ ለእኔ የምታሥብልኝ. ፍቅር አሠጣጥህ የባል ተግሣፅህ ደገሞ የአባት, መልካም መሆንማ አቤት! ሥትችልበት. መጥፎነቴን ቀይረህ መልካም ያረከኝን, ምርጥ ምምህሬ ነህ አንተን የሠጠኝ አምላክ ይመሥገን. ትልቁ ሀብቴ የምድር ሥጦታዬ, የመኖሬ ምክንያት አምላክን ማመሥገኛዬ. ፠፠፠ ፠ ከወደዱት ሼር እና joyn ያርጉ ፠፠ ፠ ፠፠፠ ፠፠ @kediradisi
Hammasini ko'rsatish...
ውሸት አልነበረም == = በከድር አዲሴ ውሼትህ አልሽና ሰበርሽው ቅስሜን አታውቂም እና ነው ያ ያለፈውን?፤ እህምም በቅቶኛል ላስታግስ ህመሜን ባንቺ ስለት ቃላት የተወጋጋውን፤ ግን እንዴት እንዴት ውሸታም ነህ አልሽኝ አንችን ስንከባከብ ስጠብቅ እያየሽኝ፤ በቃ ይሁን በቃ እኔ እችለዋለሁ ፍቅሬን ለብቻዬ አሳድገዋለሁ። ፠ ፠፠፠ ፠፠፠ ፠፠፠@kediradisi ፠፠፠
Hammasini ko'rsatish...
እርግማን. የዘራኸው ሁሉ አረም ሆኖ ይብቀል, ለጥ ያለው ሜዳ ይሁንብህ ገደል, ዙሪያህ በሙሉ ይታጠር በተንኮል ያፈራኸው ፍሬ ይቀየር በአመድ, በላይህ ላይ የመከራ ዶፍ ይውረድ, የቀና አይሁንልህ የምትሄድበት መንገድ. የረገጥከው መሬት ይሁን እሾህ አሜኬላ, ፈጽሞ እንዳታገኝ ጥጋት ከለላ, ህይወት አትጣፍጥህ ትሁንብህ አተላ. ይሽተት ገላህ ማንም አይጠጋህ, ፈጣሪንም እለምነዋለሁ አንተን እንዲዘነጋህ. የወደድከው ሁሉ ፈፅሞ ይጥላህ, የእኔ ያልከው ሠው ሁሉ ይራቅህ, ግራ ይግባህ እሺ መፈጠርህ. ዘውትር እዘን እንዳሣዘንከኝ, ምንም ሣላደርግህ ለሄድከው ጥለኸኝ.፠፠፠ ፠ ፠፠ ፠፠፠ @kediradisi
Hammasini ko'rsatish...
ሆኖ ይብቀል
Hammasini ko'rsatish...