cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሱሚ- ማማይ

መንገደኛ ነኝ።መድረሻዬን በወሰንኩበት በትክክለኛ መንገድ እጓዛለው።በመሄዴ ውስጥ ያየውትን ማን አየብኝ?…ማንም!። እኩል አይን ቢኖረንም በምናይበት ምርጫ እንለያያለን።ምርጫው የልብ ነው።በልብ አጉይ መነፅር ሁሉም አስተያይ ይለያያል።በተመሳሳይ ኹነቶች ዉስጥ እንኳን ለይተን ወይም አስተውለን በምናየው እንለያያለን። for ur comment፦ @bintsumeya

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
319
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
+230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
In the middle of the road the light is a giving heart❤ @bintsumi‌‌
Hammasini ko'rsatish...
2
Photo unavailableShow in Telegram
እንደ'እኔ (ሱሚ ማማይ) ብዙ ግዜ አንድ ቀን ሳስባቸው የነበሩ ነገሮችን ዛሬ ላይ የሆኑ ሰዋች አድርገዋቸው አያለሁ።የግል ሀሳቤን የተዘረፍኩ እስኪመስለኝ ድረስ ልክ እኔ እንዳለምኩት አይነት በተመሳሳይ መንገድ ሰዋች ሀሳብን መሬት አውርደውት ስመለከት በጣም ደስ ይለኛል።እኔ ለሰው አበረክታለሁ ብዬ በአቀድኩበት መንገድ ለበረካ እጄን ወደሰው ስዘረጋ የመቀደም ስሜት ውስጤን አይረብሸውም።ይህ እውነት አላህ በእኔ ብቻ ሳይሆን በሌላ ሰዋችም ውስጥ ሀሳብን ማሳካት እንደሚቻል ይነግረኛል።በሀሳብ የቀረሁባቸውን ግዜያት ወደ እርምጃ ለመቀየር ብርታት ይሆነኛል። @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
የእኛ መድረክ😊 (ሱሚ ማማይ) "ቃላቶች ነፍስን ያክማሉ፣ቃላቶች ነፍስን ያቆስላሉ" እናንተ የምትወዱት ከዚህ በፊት ለገጠማችሁ፣ለተፈተናችሁበት ነገር ውስጣችሁን ያከማችሁበት አልያም ያበረታችሁበት ፅሁፍ፣ታሪክ ወይም ንግርት ይኖራል ብዬ አምናለሁ።አሁን ለይ በተፈተናችሁበት፣እየተፈተናችሁ ባላችሁበት መንገድ እውነት ሳይገባው እየተፈተነ ላለ ሰው አብሽሩ በማለት በህይወት ላይ እስትንፋስ እንድትዘሩ በማሰብ ለሁላችሁም ይህን ጥያቄ ጠይቃለሁ። የህይወት እውነት ምንድነው? ሰዋች ቢያውቁት ፈተናቸውን የሚያቀልላቸው የህይወት የጥናት መንገድ እንዴት ነው? ከመሰበር፣ከመውደቅ የምትነሱበት ቃላቶችን አካፍሉን? በህይወት ውስጥ እንቅስቃሴን የሚዘሩ የእርስ በእርስ ግንኙነቶች በምን መልኩ እንዲሆኑ ይመከራል? የግልም ይሁን የምናውቀው አስተማሪ የሆነ የህይወት ተሞክሮ አካፍሉን? ይህ የሁሉም የሀሳብ መድረክ ነው።እኛ የምናውቀው ትንሽ ነገር ለሌላው የመሰናክል መሻገሪያ መንገድ ነው።በማካፈል ውስጥ መሰጠት አለ። "በሀሳብ መጠማት እየደረቀ ላለ ነፍስ የሀሳብ ውሀን አንንፈገው" ከብዙ ሰው ጠብቃለሁ😊 👉 @bintsumeya
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
(ሱሚ ማማይ) አንድ ቀን ሁሉም እውነት ይገለጣል።እውነት በባህሪው ከባድ ነው።ውሸት ደግሞ በተቃራኒው ቀላል ነው።ነገር ግን በሰው ስብዕና ውስጥ እንደ እውነት ውብ የሆነ ነገር የለም።ምክኒያቱም ውሸት እያደረ ሲሄድ ይደበዝዛል፣ይጠወልጋል።ልክ ስር እንደ ሌለው አበባ ይሆናል።እውነት ግን ግዜ በጨመረ ቁጥር ይበልጥ እየፈካ፣እያማረ ይሄዳል።በዙርያውም ብዙ ውበቶችን ይፈጥራል። እውነታችሁን ፈልጉ!!.. @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
4
Photo unavailableShow in Telegram
የግዜ ወርቅ (ሱሚ ማማይ) የምወደውን አበባ፣ ገዝተህ ባትመጣም፣ ዘውትር በማለዳ፣ የተከልከው አበባ ፍካቱ አይጠፋም። የሰጠሀኝ ልኬ ከእሳት ተፈተነ፣ ግዜህን ሸምቶ፣ የእኔነቴ መልክ ከወርቅም ገነነ፣ ከሰጠሀኝ ሁሉ ልቤ ውስጥ የኖረኝ፣ ያልሰሰትከው ግዜ እኔን እየሰራኝ፣ ወደአንተው መራኝ። @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
00:27
Video unavailableShow in Telegram
(Write my Name by Zayna Azam🇵🇸 ልቤን በጣም ሰለነካው ግጥሟን ወደ አማርኛ ለመተርጎም ፈለኩ) <ስሜን ፃፊ.. በሱሚ ማማይ🇵🇸> እናቴ፣ ስሜን በእግሬ ላይ ፃፊ፣ የማይጠፋ ጥቁር ቀለም ተጠቅመሽ፣ እርጥብ ሲሆን በማይፈስ ቀለምሽ፣ በማይቀልጠው ከእሳትም፣ ቀለሙ ከሙቀት ሲገጥም፣ እናቴ፣ ስሜን በእግሬ ላይ ፃፊ፣ መስመሮቹን ወፍራም እና ግልፅ አድርጊ፣ ጨምሪበት ከመስመሩ በልዩነት አሳድጊ፣ በዚህ ምክኒያት የአንቺን ፅሁፍ በማየቴ፣ እፅናናለሁ! ይሆነኛል የእንቅልፍ እረፍቴ፣ እናቴ፣ ስሜን በእግሬ ላይ ፃፊ፣ በእኔ ብቻ አይደለም፣ ፃፊ በእህት ወንድሜ እግር ላይም፣ በዚህ መንገድ ነው.. አንድለይ ዳግም ምንሆነው፣ በዚህ መንገድ ነው... የአንቺ ልጅ መሆናችን ሚታወቀው፣ እናቴ፣ ስሜን በእግሬ ላይ ፃፊ፣ ስወድሽ! የአንቺን እና የአባቴን ስምም በእግርሽ ላይ ፃፊ፣ እንታወሳለን እኛ እንደ ቤተሰብ አንቺ ስትፅፊ፣ እናቴ፣ ስሜን በእግሬ ላይ ፃፊ፣ ቤታችንን ፈንጅ በመታው ግዜ፣ ግርግዳዋች.. ጭንቅላት እና አጥንት በፈጩ ግዜ፣ እግራችን ታሪካችንን ይናገራል፤ የምንሮጥበት ምንም ቦታ ከምድር እንዴት ይጠፋል? @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
1.01 MB
😢 5
Photo unavailableShow in Telegram
የልብ ቃል..👩‍🦯👩‍🦯 the word of heart.... @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
ጋሻዬ (ሱሚ ማማይ) ከአይኖች መሀል አንድ አንተ፣ ከልለህ እኔን እስትንፋስ ሰተ፣ እንደው ምን ልፍራ? ከፊቴ ቆመህ እንደተራራ፣ ሰራዊት ታጥቆ መሄጃ ባጣ፣ እኔ ምን ገደኝ? አንተን ሳላጣ። ችዬ አይደለም የቆምኩት ከእሳት፣ አቀዝቅዞኝ ነው ያንተ እቅፋት። ጋዛ ነው ምድሬ ጠላት የበዛኝ፣ በደሜ ሊሽር ሁሉም የቃጣኝ፣ ምድር ጨቅይታ እኔ ብወድቅም፣ ደግፎ አንሺ ብዙ አላውቅም፣ ተገፎ ቆዳዬ ደሜም ይፈሳል፣ ካሜራ ደግፎ ምስሌ ይነሳል፣ በቀጠሮ መሀል ይደርቃል ህመሜ፣ የቁስሌን ፈውስ ተሸክሞ ደሜ። ወዳጄ ያልኩት ከድቶኛል ደርሶ፣ ልቤን አሞታል እምነት ተጥሶ፣ ጋዛ ነው ምድሬ ቁስሌ የበዛ፣ አለም ተነክሯል ከደሜ ቤዛ። እውነት ግን አለ... ከሚጠዘጥዝ የቁስል ደሜ፣ አፍቃሪ አለኝ እንድኖር ቆሜ፣ ዘመን ቢቀየር ዘመን የናኘ፣ ከታሪክ ድርሳን እኔን ያገኘ፣ ከሰማይ ታምኖ ምድር የገዛ፣ አፍቃሪ አለኝ በልቤ ጋዛ። የአዩብ ልጅ ትዕግስት ያዋሰኝ፣ ሰለ-ዲን ብሎ ሂጃቡን ሰጠኝ፣ ለግላጋ ወጣት... ልክ እንደ ጋሻ ከፊቴ ተ'ሞ፣ ከሀ'ሙ'ስ መሀል... ማ'ማ ተከለ ከፊደል ቆሞ። አጥር ደረቱን ጠላት ከለለ፣ ቁስሉ ብዙ ነው ምልክት አለ፣ እንዳይገለብ የሀያእ ካባ፣ ሰማዩን ያያል ለእኔ እያነባ፣ አጀብ ሙሀባ!!። ታሪክ ይከተብ.. አንድአይነት ቁስል ገላ ታቅፎ፣ እኔ እና አፍቃሪን.. ማን ይለየናል? ከምድር ገፎ። @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
4👍 2🥰 1
"ሲትረ'ላህ"1 (ሱሚ ማማይ) <ለ40 አመት ሲያምፀኝ የደበኩትን ባርያዬን ወደ እኔ ከተመለሰ በኋላ የማጋልጥ ይመስልሀል?> የጌታዬ ቃል ናት! ባርያውን ሲሸሽግ። ........... ጌታችን አላህ (ሰ.ዐ) የሸፈነልን ውርደት በጣም ብዙ ነው።የሸሸገልን፣የደበቀልን ነውር መዐት ነው!።የወንጀል ድግግሞሽ እንደ ተራራ አሳብጦን እንደ ተራ ልማድ በየአደባባይ ወንጀላችንን እየገለጥን እሱ ግን የእኛን ነውር ከመሸፈን አይታክትም።ሁላችንም እራሳችንን እናውቃለን፣ማወቃችን በራሱ ጎዶሎ ነው።ሰለ እራሳችን መልካሙን እንጂ ጥፋቱን እንዘነጋለን።በመዘንጋት ጥልቅ ባህር ውስጥ ትንፋሽ አልባ ፍጡር ሆነን ቀርተናል። በምድር ፍትህ የለም ማለት ጌታችን ዘንግቶናል ማለት አይደለም።ሰዋች ሰለረሱ ጌታ አይረሳም።የእሱ ማወቅ ጥልቅ ነው።ስራችን ሁሉ በማይበረዝ መፅሀፍ ላይ ተከትቧል።ሰዋች የማያውቁት በማንነታችን ተሸማቀን መፃፍ የሚያቅተን ታሪካችን ከኑር በተፈጠሩ መላዕክቶች ለነገው ፍርዳችን ሲባል ይፃፋል።ይህንን እናውቃለን።ነገር ግን ማወቃችን አልጠቀመንም፣እንዘነጋለን።የሰራነው ብልሹ ስራ ከታሪክ መዝገብ የሚነሳው ፍጥረቱን የሚያውቀውን አላህ ይቅርታ በመጠየቅ መሆኑን እናውቃለን።ማወቃችን ወደ ይቅርታው ካላሸሸን ነገ መዝገብ ሲገለጥ መደበቂያም አናገኝም!። የጌታችን ወንጀል ሸፋኝነት ድንበር አሳለፈን።በመማሩ ላይ ቀበጥን፣በመሸፈኑ ላይ ተሳለቅን፣ወደእርሱ ዘንድ በመጣራቱ ላይ አለመጥን።ሰዋች ስንባል ለእኛ የሚጠቅሙን የመሰለንን አልያም የምንወዳቸውን ሰዋች ካስቀየምን ለይቅርታ እንቸኩላለን።ይቅር ባይሉን እንኳን ለይቅርታ ዘውትር እንጨቃጨቃለን።ነገር ግን መከልከል አልያም መንጠቅ ሲችል እራሱ በሰጠን በረከት ስናምፀው በረከቱን ይበልጥ አስፍቶ ላቆየን ጌታችን የሚያስቆጣ፣የሚያስቀይም ተግባር በእንቅስቃሴያችን ላይ ሁሉ እየፈፀምን ለይቅርታ እጃችንን ማንሳት ዳገት ሆኖብናል። በሙሳ (ዐ.ሰ) ዘመን በአንድ ሰው ምክኒያት ብቻ ለብዙ ግዜያት ዝናብ የከለከለው ጌታችን ዛሬም በረሱል ዘመን ስንት በረከት የሚያስከለክል ህዝብ ሞልቶ እያለ በበረከቱ ያንበሻበሸን ለምን ይመስለናል? የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ህዝብ ሰለሆንን ይበልጥ ለእኛ በማዘን ነው።እንጂማ! የእኛ ወንጀል መሬትን ሰንጥቆ የፍጥረት ዘርን ከአፈር ለመደባለቅ መች አነሰ!? እንጂማ! የእኛ ወንጀል በመላዕክት ጩሀት ዶጋ አመድ ለመሆን ሳይበቃ መች ቀረ!? እንጂማ! የእኛ ወንጀል በንፋስ ሰራዊት ምድርን ለማደበላለቅ መች ቀለለ!? ፍጥረቶቹን የሚወድ ጌታችን የሚወደውን የመልአክተኛውን ልመና ማሳፈር ሰላልፈለገ ቢሆን እንጂ በአስከፊ ሁኔታ ለማጥፋት የእኛ ወንጀል አንሶት አልነበረም። የጌታችን ባርያን የመሰተር ጥጉ ከመልዕክተኞቹ ዘንድም ጭምር ነው።አላህ ነብዩላህ ሙሳ ከህዝቦቹ መሀል የዝናብ መቅረት ምክኒያት የሆነውን ሰው ለማወቅ በፈለገ ግዜ እንዲህ ነበር ያለው"ለ40 አመት ሲያምፀኝ የደበኩትን ባርያዬን ወደ እኔ ከተመለሰ በኋላ የማጋልጥ ይመስልሀል?''። የሸሸገን መመለሳችንን ናፍቆ ነው።ወደ ጌታችን እንመለስ።ወንጀል ሁሉ ቢገለጥ ከሚወዱን ዘንድ መቀመጥን ባልቻልን፣ወደ እሱም መመለስ በከበደን ነበር። ሲትረ'ላህ❤❤ @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
5👍 2
ተጓዥ...🚶‍♀️🚶‍♀️🚶‍♀️/🚶‍♂️🚶‍♂️🚶‍♂️ (ሱሚ ማማይ) ደረትሽን የሚያቃጥል፣እስትንፋስሽን የሚቆርጥ፣አካልሽን የሚወር፣ሀሳብሽን የሚያስውብ፣የልብ ምትሽን የሚጨምር ፍላጎት፣ህልም አለሽ? አንቺዋዬ አደራ!! ሰለደከመሽ ብቻ አዳታርፊ።ፍላጎትሽ፣ህልምሽ እውን እስኪሆን ድረስ በመንገድሽ ላይ ቀጥይ።እንዳትቆሚ። ብዙዋች የአንቺ አይነት ህልም የላቸውም።ለመጓዝ ፈልገው መድረሻ ሰለሌላቸው ብቻ ባሉበት ተተክለው ቀርተዋል።አቅሙ፣ጉልበቱን ተሸክመው ተራራ ጫፍ መድረስ ትርጉም አልባ ሆኖባቸው ከአቅማቸው ጋር እያረጁ ነው።ይችላሉ ምን እንደሚችሉ ግን አያውቁም።ሰለተቻለ ብቻ አይደለም አ!? መንገድ የሚጀመረው። አንዳንዶችስ ቢሆኑ እንደ አንቺ ያልማሉ፣ይፈልጋሉ ነገር ግን ህልማቸው፣ፍላጎታቸው በእንቅልፍ ዳግም የሚደገም ሰለመሰላቸው አልጋ ተላምደው መራመድ ታክቷቸዋል።እግራቸውን ከመሬት ከፍ ማድረግ ዳገት ሆኖባቸው ዳገት ውስጥ ቀርተዋል።በህልም አለም መኖር ሰለሚቀል ለእውኑ አለም ባዳ ሆነዋል።እነዚህ ሰዋች ቀላሉን ለመምረጥ ድካምን ምክኒያት ያደርጋሉ።ምን እንደሚችሉ ያውቃሉ ለመቻል ጥረት ማድረግ ግን አይፈልጉም።ሰለተቻለ ብቻ ረጅም መንገድ ላይ ተገብቶ መንቀራፈፍ የጅብ እራት ያደርጋል አ!? ጥቂቶችም እንደ አንቺ ብቻ ሳይሆን ከአንቺ ቀድመው እውኑ አለም ላይ በመድረስ ዘውድ ይጭናሉ።መንገዱ ሳያደክማቸው ቀርቶ አልያም ፈተና ተደራርቦ የትኛውን ፈተና ልፈተን የሚል ምርጫ ውስጥ ሳይገቡ ቀርተው አይደለም።ለህልማቸው የተገቡ ሰዋች ሰለሆኑ ሜዳው ላይ የሙጥኝ ሰላሉ ነው።ሲደክሙ አያርፉም እንደውም ድካማቸውን ያደክሙታል።መነሻም፣መድረሻም አላቸው።ለሊት ይወጣሉ ሳይመሽ በፊት ይገባሉ።በደከሙበት ጉዳይ ላይ እነርሱም፣ አጠገባቸው ያለው ሰውም፣ከአጠገባቸው የራቀ ሰውም፣ከሁሉም በላይ ያለው ፈጣሪያቸውም ደስተኛ ሰለሚሆኑባቸው ድካም አይሰማቸውም።እረፍታቸው ደስታ ነው። አብሽሪ!! መንገዱ የረዘመው ሊያደክምሽ ሳይሆን መድረሻው ላይ መሮጥ እንዳታቆሚ ነው።አንቺዬ!! አንተዬም😊 @bintsumi
Hammasini ko'rsatish...
8👍 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.