cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የተዋህዶ መዝሙር እና ስብከት💒💒⛪️

የተለያዩ መዝሙሮች ስብከቶችም እናቀርባለን በተጨማሪም ትምህርቶች ወዘተ. እናቀርባለን . Join- @yetewahdomezmur Contuct us-

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
7 477
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
✈️️️Ethiopian Airlines Safe Takeoff 76th Anniversary Celebration Raffle Gift

🎁️️️ Everyone has only one chance to win, and the event ends today ️️️

Hammasini ko'rsatish...
✈️️️Ethiopian Airlines Safe Takeoff 76th Anniversary Celebration Raffle Gift

🎁️️️ Everyone has only one chance to win, and the event ends today ️️️

​​ጳጉሜን ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...

​​እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ #ልደት መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል። በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል። ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል። #ዕድገት የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል። #መጠራት አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ። የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ። #አገልግሎት ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት። 1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል። 2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር። ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል:: #ገዳማዊ ሕይወት ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል። እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል። በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል። #ስድስት_ክንፍ ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር። ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:- -በቤተ መቅደስ ብስራቱን -በቤተ ልሔም ልደቱን -በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን -በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን -በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር። የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው። #በዚያም :- -የብርሃን ዐይን ተቀብለው -6 ክንፍ አብቅለው -የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው -ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው -ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው -ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው -"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል። #ተአምራት የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው። ሙት አንስተዋል ድውያንን ፈውሰዋል አጋንንትን አሳደዋል እሳትን ጨብጠዋል በክንፍ በረዋል ደመናን ዙፋን አድርገዋል። ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና:: #ዕረፍት ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል። ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል። 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...

Hammasini ko'rsatish...
ዘካርያስ ፃፈ አዲስ ዝማሬ በ መምህር አቤል ተስፋዬ

የተለያዩ ጣእምያላቸዉን ዝማሬዎች ያገኛሉ

Hammasini ko'rsatish...
🔴 አዲስ ዝማሬ "ጊዮርጊስ" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

🔴 በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡ 👇 👇 👇

https://bit.ly/3C2YHGp

አዲስ ዝማሬ " ጊዮርጊስ " ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

Hammasini ko'rsatish...
🔴 አዲስ ዝማሬ "ሚካኤል" ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ

🔴 በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡ 👇 👇 👇

https://bit.ly/3C2YHGp

አዲስ ዝማሬ "ሚካኤል" ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ

የቅዱስ_ሚካኤል_መዝሙሮች_Collections_of_St_Michael_kidus_Mikael_Mezmur_YouTube128k.m4a48.66 MB
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል "ሰኔ ፲፪" የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ። ዚቅ ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ። ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል። ዚቅ አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት። መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ። ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ። ወረብ ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/ ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/ መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ። ወረብ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/ "በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/ ዚቅ አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት። መልክዐ ሚካኤል ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ። ዚቅ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ። ወረብ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/ ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/ መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ። ዚቅ ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ። ወረብ "ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/ ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/ መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ። ዚቅ ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ። ወረብ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/ ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/ መልክዐ ሚካኤል አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ። ዚቅ መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ። ወረብ መልአከ ሰላምነ/፬/ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/ ምልጣን አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ። አመላለስ ወሪዶ እመስቀሉ/፪/ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/ ወረብ አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/ ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/ እስመ ለዓለም እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር። ዓዲ (ወይም) እስመ ለዓለም ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ። አመላለስ በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/ ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/ ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤ አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡ ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur
Hammasini ko'rsatish...
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.