cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (Amde Haymanot Sunday School)

ይህ ገጽ የመንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ትምህርቶችንና መልእክቶችን በፎቶ ፣ በቪድዮ እንዲሁም በጽሑፍ ለምዕመናን የሚያደርስበት መንፈሳዊ ገጽ ነው፡፡ ለጥያቄና አስተያየት ካለዎት በhttps://t.me/Behailu_Dessalegn ወይም https://t.me/mogesb87 ይጻፉልን፡፡

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 098
Obunachilar
+124 soatlar
+137 kunlar
+4530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#Update የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል። በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል። " ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል። ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል። በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
ለገዳማችን አገልጋዮች ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ። የመንበረ መንግሥት ግቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም ስር ለሚገኙ መደበኛ አገልጋዮች በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አመራር ሰጭነት በተዋቀረው ኮሚቴ አማካኝነተ ከቤተ ክህነት እና መንፈሳዊ ኮሌጅ በመጡ መምህራን በሁለት ዙር ለ14 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን አሁን እየተሰጠ ባለዉ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ላይ ከ60 በላይ የገዳማችን አገልጋዮች እየተሳተፉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ስልጠው በትምህርተ ሃይማኖት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ፣ የስብከት ዘዴ ፣ ትምህርተ ኖሎት ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች ላይ ያተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/AmdehaymanotSundayschool/ ዩትዩብ ፦ https://youtube.com/channel/UC_USHmHSlXg_-g0wwsPcQCg ቲክ ቶክ፦ https://vm.tiktok.com/ZML9jVNJW/ ቴሌግራም፡ https://t.me/Amde_Haymanot_Sunday_School
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
በልዩ የመጽሐፍ ምረቃ በዓል ላይ ይታደሙ ! የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳን ኪ/ማርያም ያዘጋጁት "መዝገበ መጽሐፈ ቅዳሴ" እሑድ ሰኔ 2 / 2016 ዓ.ም በልዩ መንፈሳዊ ዝግጅት ይመረቃል። በዕለቱ ከቀኑ 6:00 - 9:00 በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ ልዩ የመጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብር ላይ መገኘት የምትፈልጉ ቀጣዩን ሊንክ በመንካት👉🏼 (https://forms.gle/M1dkbx5jozcwtQ9d7) ፣ ስምና ስልካችሁን በመላክ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
የ2016 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጀመረ። ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ከምታካሒደው ጉባኤ ሁለተኛውን የግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ጀምራለች። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባስተላለፉት መልእክት " እግዚአብሔር አምላክ በቤተክርስቲያናችን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል እንኳን ለዛሬው ለስብሰባ ዕለት አደረሳችሁ ፤"ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፤ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ  እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ" 1ቆሮ 1÷10 ላይ ያለውን ቃል መነሻ በማድረግ ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበት ሁኔታ እጅግ ከባድና አስቸጋሪ መሆኑን ያመለከቱት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያን ከፈተና ተለይታ እንደማታውቅና በየጊዜው ከውስጥም ከውጪም የሚመጡ እንዳሉ ገልጸዋል ፤ የውጪው ፈተና ባይቀርላትም በውስጥ የሚነሱት ፈተናዎች ግን አገልግሎቷን በተቃና ሁኔታ እንዳታደርግ አድርገዋታል ፤ መንፈሳዊ አገልግሎት ተዘንግቶ ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ነዋይ በዝቷል ፤ ባህልና ትውፊታችን ተሸርሽሯል ፤ ይሕም በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ታማኝነትና ተደማጭነት ሊቀንሱበን እየተንደረደሩ ነው ፤ ሰዎች ከክርስቲያናዊ ከቀኖና እና ስርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው ፤ መለያየት ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን እንደሆን ይታወቃል ፤ የውስጣችን ሰዎች ለዚህ ምቹ ሁኔታን ሲፈጥሩ ይስተዋላል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቋል ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት:- በሀብተ መንፈስቅዱስ ወልደን ፣ በሀብተ ክህነት ሾመን ፣ በመዓረገ ምንኩስና አልቀን  በአገልግሎት የሾምናቸው ሁሉ መንፈሳዊውን አገልግሎት እንዴት ዘነጉት? ወይንስ መጀመሪያም ሳይችሉ ሾምናቸው? ወይንስ ሆን ብለው ቃሉን ቸል አሉት? ሁሉም ውሉደ ካህናት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል ፤ ነገር ግን ይሕን የሚያደርጉ እና ያደረጉ ሁሉ ሥራቸው ሚዛን አይደፋም ፤ አንድነትና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማ መገምገም ፤ ሕግና ሰላምን ተመራጭ ያደረገ ነገር ማድረግ ይገባናል ፤ ባለፉት ዓመታት ብዙ በደል ተፈፅሟል ፤አሁንም አልቆመም ፤ ለዚህ አስተማማኝ መዋቅር ማበጀት ያስፈልጋል፤ በደልን በካሳና በእርቅ በይቅርታ መዝጋት ፤ ለቀጣዩም ተቋማዊ ስርዓት ማበጀት አስተማማኝ ነገር ሲሆን በደልንና ጥፋትን ትተን ግን በመለያየት መቀጠል የማይሆን ስለሆነ ወደ ሰላምና እርቅ የሚያመራ ስብሰባ ማድረግ አለብን፤ ይህ ዐቢይ ጉባኤ ወሳኝና ቀኖናዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተክርስቲያን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን እንዲወስን እናሳስባለን፣ የዚህ ዓመት ጉባኤ መጀመሩንም አበሥራለሁ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ " በማለት ምልዓተ ጉባኤውን አስጀምረዋል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 11 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ 12፡00 በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ
Hammasini ko'rsatish...
👍 3