cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዳሩል አርቀም ገነቴ "الذب عن السنة"

ሱናን በመከተል የተለያዩ ጠቃሚና አስተማሪ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ቻናል ፣ ከዲን ያፈነገጡ ተግባሮች የሚጋለጡበት ርምት የሚሰጥበት ።ቢዲዓ እና በልማዳዊ ለሚፈፀሙ ጥፋቶች የሚጋለጥበት,,,

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
191
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ኡማም ኢብኑልቀይም እንዲህ ይላሉ ፣ ❞ﻓﺎﻟﺨَﺒﻴﺚ ﻳﺘﻔَﺠَّﺮ ﻣِﻦ ﻗَﻠْﺒﻪ اﻟﺨُﺒﺚ ﻋﻠﻰ ﻟِﺴﺎﻧﻪ ﻭﺟﻮاﺭِﺣﻪ، ﻭاﻟﻄّﻴِّﺐ ﻳﺘﻔﺠﺮ ﻣﻦ ﻗﻠﺒﻪ اﻟﻄﻴﺐ ﻋﻠﻰ ﻟِﺴﺎﻧﻪ ﻭﺟﻮاﺭِحه " "ቆሻሻ ሰው ቆሻሻው ከልቡ ወደ ምላሱና አካሉ ይንቧቧል ። መልካም ሰው መልካም ነገር ከልቡ ወደ ምላሱና አካሉ ይፈሳል " እናማ ፣ የአንዳንድ ሰዎች ክፉ ተናጋሪነትና አደብ ማጣት አያሰደንቀን ! ! ልብ ውስጥ ያለውን ምላስ እየተፋው ነው ። የአንዳንዶች አስቀያሚ ስራም አይግረመን — ቀልብ ውስጥ ያለውን አካሉ ተርጉሞት እያስረዳን ነው ። አላህ ቀልባችንን ፣ ምላሳችንን ፣ ስራችንን ያሳምርልን !! @Muhammedsirage
Hammasini ko'rsatish...
ለዐረብ ሀገር ወንድምና እህቶች ~~~~~~~~~~~~~ ① ከሁሉም በፊት ለዲናችሁ ቅድሚያ ስጡ። ከተውሒድ ጀምራችሁ ግንዛቤያችሁን በተለያዩ መንገዶች አስፉ። ለአላህ ምስጋና ይግባውና በዚህ በኩል ብዙ ወንድሞችና እህቶች ዘንድ ተነሳሽነት ይታያል። ② ለአሰሪዎቻችሁ ታማኞች ሁኑ። የሰው ሀላፊነት እስከተቀበላችሁ ድረስ አላህን ፈርታችሁ ሀላፊነታችሁን ባግባቡ ተወጡ። በሰዐትም፣ በስራም፣ በገንዘብም፣ በክብርም፣ በልጆችም የምትታመኑ ሁኑ። አማናን መወጣት ትልቅ ሃላፊነት ነው። ③ በተቻላችሁ ከአላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል ተጠንቀቁ። በጋራ የኪራይ ቤቶች ሊፈፀሙ ከሚችሉ አደጋዎች እራሳችሁን ጠብቁ። ④ እርስ በርስ ተዛዘኑ። ስራ ለሌለው ስራ በመፈለግ፣ ለተቸገረው በብድር ወይም እራስን በማይጎዳ መዋጮ ተጋገዙ። ⑤ ከወንጀለኞች ራቁ። አረብ ሀገር በርካታ ኢትዮጵያውያን በወንጀል ስራ ላይ መሰማራታቸው የሚታወቅ ነው። በነሱ ሳቢያ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተደጋጋሚ ስማቸው ይጠፋል። የሚገርመው ብዙ ለነዚህ ወንጀለኞች ሽፋን የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ነው። በነሱ ጥፋት አብራችሁ እንዳትጎዱ ተጠንቀቁ። እንዲያውም ለሌላ የሚተርፍ የተረጋገጠ ወንጀል ካያችሁ ለሚመለከተው አካል ጠቁሙ። ይሄ ለዲናችሁም ለገፅታችሁም ዋጋ አለው። ⑥ ቤተሰቦቻችሁን አትርሱ። ወላጅ ወላጅ ስለሆነ ብቻ ከባድ ሐቅ እንዳለው እሙን ነው። ከዚያም ባለፈ ስንት ፍዳቸውን አይተው አሳድገዋል። አረብ ሀገር ትሄዱ ዘንድ የተቸገሩላችሁም ብዙ ናቸው። እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ወላጆቻችሁን አትርሱ። በዚያ ላይ አንዳንዶቻችሁ ወደ ወላጆቻችሁ ልጅ የላካችሁ ትኖራላችሁ። በዚህን ጊዜ ሐቁ ድርብርብ ነውና ኣኺራችሁን እንዳታጨልሙ ተጠንቀቁ። ⑦ እራሳችሁን አትርሱ። የወጣችሁት እንጀራ ፍለጋ ነው። ከፋም ደላ የሰው ሀገር የሰው ነው። ህልማችሁ ቋጥሮ ወደ ሀገር ለመመለስ እንጂ በልቶ ለመጥገብ፣ ደምቆ ለመልበስ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ብልጥ መሆን ያስፈልጋል። መስራቱን ቻሉበት። መያዙንም ቻሉበት። ለቤተሰብ ስትልኩም አቅማችሁንም፣ ኖሯቸውንም፣ ሁኔታቸውንም እያገናዘባችሁ ይሁን። ለጎረምሳ ጫት መቃሚያና መንሸራሸሪያ አትላኩ። በዚህ ወንድሞቻችሁን ታበላሻላችሁ እንጂ አትጠቅሟቸውም። ገንዘባችሁንም አጥታችሁ ወንጀለኛም ትሆናላችሁ። ባጭሩ የምትሰሩትን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ለማዋል ተጣጣሩ። ባዶ እጃችሁን ላለመግባት በተቻላችሁ ተጠንቀቁ። ችግር መጥፎ ነው። ቤተሰብ እንኳን እንዲገፋችሁ ያደርጋል። አገራችን ለባዶ እጅ ቀርቶ ለያዘም እየከበደ ነው። ⑧ እቅድ ይኑራችሁ። ለቆይታችሁ ገደብ አስቀምጡለት። በግምት አትኑሩ። ሁለት አመት ሰራርቼ አገሬ እገባለሁ ብለው ሃያ አመት የኖሩ አሉ። ከአላማ ካልተወጣ ክፋት አልነበረውም። እየባከኑ ሲሆን ግን ያሳዝናል። "ምን ይዤ ልግባ?" እያሉ እየተብከነከኑ መኖር ይጎዳል። ስለዚህ ገደብ ያለው እቅድ ይኑራችሁ። ለእቅዳችሁም በትጋት አስቡ፣ በትጋት ስሩ። መገናኘታችሁ እቅዳችሁን የሚያሰናክል፣ ለትርጉም የለሽ ወጭ የሚዳርግ ከሆነ ተራራቁ። ⑨ ሴቶች ሆይ! መንገደኛ አታግቡ። እስኪ አሁን ሂንዲ፣ ፓኪስታኒ ማግባት ምን ይባላል? እንዲህ አይነቱ ትዳር ዘላቂ የመሆን እድሉ እጅግ የጠበበ ነው። ልጅ ከመጣም ከነ ጭራሹ አባቱ ጋር አይኖርም። ስለዚህ ለራስም ለልጅም ፈተና ነው። (10) ለኸይር ስራ እጃችሁን ስትዘረጉ ጥንቁቅ ሁኑ። ኸይር አትስሩ አይባልም። ግን በትክክል ለታለመለት ግብ የሚደርስ መሆኑን ቢያንስ ሚዛን የሚደፋ ግምት ያዙ። (11) ለትዳር ክብር ይኑራችሁ። ትዳርን መስፈርት በማያሟላ በተጨመላለቀ መልኩ ሳይሆን በሥርዓት ፈፅሙ። አትበዳደሉ። ኣኺራችሁን በማይጎዳ መልኩ በስርኣት ኑሩ። ለጋብቻ የተጋነነ ወጭ አታውጡ። ከሰሞንኛ ሆይሆይታ ይልቅ ለዘላቂው ትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ። መለያየት ግድ ካለም ባግባቡ ይሁን። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ቻናሉን ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። መልእክቱን ለሌሎች በማሰራጨት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።

🔊《رفع العلم وظهور الجهل آخر الزمان》🔊 🔶 #الشيخ_محمد_آدم_الإتيوبي 🔶 رحمه الله 🔊 #فوائد_صوتية 📚 المصدر : #شرح_البخاري ⁦🗂️⁩التصنيف: #الفتن | #العلم __________________________ 🔘 aleti
Hammasini ko'rsatish...
4_5827664128340133539.mp34.40 MB
📌📌📌ታላቁ አሊም ሙሀመድ አሊይ ኣደም አሏህ ይዘንላቸዉና ዶ/ር ጀይላን ኸድርን በተመለከተ እንዲህ አሉ፦ «እኔ በምችለዉ ያክል መክሬዋለሁ ከዚህ ቡሃላ ከተቀየረ በርሱ ላይ ተዉራትና ኢንጁልን እንኳ ባነብበት መድሃኒት የለዉም» ሌሎችም ገለፃዎች አሉ እናድምጠው 🎙🎙🎙الشيخ محمد الشيخ على أدم رحمة الله عليه አድምፁት አደራ ሼር እናድርገው ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba ወንድማዊ ምክራችሁን በዚህ አድርሱኝ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ @AbuAyub_bot
Hammasini ko'rsatish...
AUD_47541898.mp310.81 MB
በታላቁ ሸይኽ አብደልሀሚድ ያሲን አል–ለተምይ የተሰጠ ፈትዋ በገነቴ ከተማ ቁጥር 2
Hammasini ko'rsatish...
ፈታዋ ገነቴ 2 co.mp37.54 MB
በታላቁ ሸይኽ አብደልሀሚድ ያሲን አል–ለተምይ የተሰጠ ፈትዋ በገነቴ ከተማ
Hammasini ko'rsatish...
ፈታዋ ገነቴ 1 co.mp310.88 MB