cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM

በደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው https://www.facebook.com/Fikureegzi4 √ ዌብሳይታችን www.fikureegzi.com √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg ለሀሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!! @FikureEgzi04

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
7 326
Obunachilar
-524 soatlar
+497 kunlar
+39530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

01:51
Video unavailableShow in Telegram
እንኳን ለፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤታችን 56ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ። በዓለ ንግሥ እና ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🗓 ከግንቦት 19-21/2016 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 10:30 ሰዓት ጀምሮ ⛪️ በደብራችን አውደ ምህረት 👉 ለዚህ መርሃ ግብር ከወዲሁ ቀጠሮዎን በደጀ ሰላሙ ለማድረግ ይዘጋጁ‼️ "የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት" መቃብያን ካልዕ 10 ÷1
Hammasini ko'rsatish...
👍 12 2👏 1
7👍 2👏 1
" የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት " መቃብያን ካልዕ 10 ÷1         56 ዓመት በአገልግሎት                  ክፍል ፯ ሰንበት ትምህርት ቤት የቤተ ክርስቲያን ልጆች በአንድ ጥላ ሥር ተሰብሰበው ቃለ እግዚአብሔር የሚማሩበት መንፈሳዊ ተቋም ብቻ ሳይሆን የተማሩትን በልዩ ልዩ መንገድ እርስ በእርሳቸው የሚማማሩበት ለሌሎችም የሚያስተምሩ ልዩ ልዩ ጸጋ ያላቸው አባላት ያሉበት ቦታ ነው በዚህ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ውስጥ ትምህርት ከሚሰጥባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ሥነ ጥበብ ነው በሃምሳ ስድስት ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ ውስጥ  በዚህ ዘርፍ እነዚህ ዐበይት ሥራዎች ተሰርተዋል በመሠራትም ላይ ይገኛሉ ፨ በልዩ ልዩ የአወደ ምሕረት እና የአዳራሽ ጉባኤያት ላይ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁ ግጥሞችን ፣ ትረካዎችን እና ጭውውቶችን በማዘጋጀት ጥበባዊ በሆነ መንገድ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን የሀገራችንን እና የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክ ለምእመናን እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል ፨ በሁለት ወር አንድ ጊዜ የሥነ ጥበብ ምሽቶችን በማዘጋጀት በልዩ ልዩ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅቶች  ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ተደራሽ ያደርጋል ፨ የሥነ ጽሑፍ ውድድሮችን እያዘጋጀ ፀሐፊያንን ያበረታታል። ፨ አባላት በተለያዩ የሥነ ጥበብ ዘርፎች እንደ ፍላጎታቸው ሥልጠና የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል ስልጠናዎችን ይሰጣል ፡፡ ፨ የሥዕል ክህሎት ያለቸውን አባላት እና ምዕመናን  በመመልመል የአጭር ጊዜ ተከታታይ ትምህርት ሥልጠና ይሰጣል። ፨ ቅዱሳት ሥዕላትንም በተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፎች በማዘጋጀት ለምእመናን እና ለአባላት  የግንዛቤ ማስጨበጪያ መርሐ ግብር ያዘጋጃል። ፨  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትን የጠበቁ ሥዕላትን ለማዘጋጀት የዝግጅት ሥራዎች በመሠራት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ። ፨ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሚያዘጋጀቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ እንዲሁም በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት በሚዘጋጁ መርሐ ግብራት ላይ  ተጋባዥ በመሆን ልዩ ልዩ የሥነ ጥበብ ዝግጅቶችን ያቀርባል። ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከዚህ የበለጠ አገልግሎት እንዲኖራት ሁሉም ምዕመናን እንደሙያው እን እንደተሰጠው ፀጋ ሰንበት ት/ቤቱን አገልግሎት እንዲደግፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
Hammasini ko'rsatish...
🙏 2
02:09
Video unavailableShow in Telegram
በዓለ ንግሥ እና ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤታችን 56ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመልከት የተዘጋጀ ልዩ መርሐ ግብር። 🗓 ከግንቦት 19-21/2016 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 10:30 ሰዓት ጀምሮ ⛪️ በደብራችን አውደ ምህረት 👉 ለዚህ መርሃ ግብር ከወዲሁ ቀጠሮዎን በደጀ ሰላሙ ለማድረግ ይዘጋጁ‼️ "የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት" መቃብያን ካልዕ 10 ÷1
Hammasini ko'rsatish...
15👍 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤታችን 56ኛ ዓመት የምስረታ በዓል  በማስመልከት የተዘጋጀ ልዩ መርሐ ግብር። 🗓 ከግንቦት 19-21/2016 ዓ.ም                       🕰  ከቀኑ 10:30 ሰዓት ጀምሮ              ⛪️ በደብራችን አውደ ምህረት  👉 ለዚህ  መርሃ ግብር ከወዲሁ ቀጠሮዎን በደጀ ሰላሙ ለማድረግ ይዘጋጁ‼ "የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት"  መቃብያን ካልዕ 10 ÷1
Hammasini ko'rsatish...
🙏 4👏 3 2👍 1🥰 1
🙏 9👏 2🕊 1
" የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት " መቃብያን ካልዕ 10 ÷1         56 ዓመት በአገልግሎት                ክፍል ፮ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከምሥረታው ጀምሮ አገልግሎቱን በስፋት ከፈጸመባቸው እና እየፈጸመባቸው ከሚገኙ  ዘርፎች መካከል አንዱ የጸሎት እና በጎ አድራጎት አገልግሎት  ነው ለዛሬ በዚህ ዘርፍ ካሉ የሰ/ት/ቤቱ የአገልግሎት ሱታፌዎች መካከል ጥቂቱን እናስቃኛችሁ ፨ የሁሉ ነገር መሠረት ጸሎት ነው እና ዓመቱን ሙሉ በሰ/ት/ቤታችን ረብዕ እና አርብ ከ11 ሰዓት ጀምሮ የጸሎት መርሐ ግብር ይካሄዳል፣ በየወሩ 4 እና በ21የጽዋ ጸሎት ፣ በአዋጅ አጽዋማት ጊዜ የሱባኤ ጸሎት ከትውልድ ወደ ትውልድ እያተለላፈ ዛሬም ድረስ በካህናት እና በወንድሞች የሚመራ የጸሎት መርሐ ግብር ሳይታጎል እንደቀጠለ ነው። በሀገራችን እና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ መከራ በበዛ ጊዜ እግዚአብሔር የምሕረት ዓይኑን ወደ እኛ እንዲመልስ የምሕላ ጸሎት መርሐ ግብር በተለያየ ጊዜ እንዲዘጋጅ ይደረጋል:: ፨ በዓመት ሁለት ጊዜ ለትንሣኤ በዓልና እና ለጾመ ፍልሰታ ፍቺ በቋሚነት ነዳያንን በማስፈሰክ ፣በየሳምንቱ በሰንበት እሑድ የቁርስ ምገባ መርሐ ግብር በማዘጋጀት፣ የተለያዩ አልባሳትን በማሰባሰብ ድጋፍ በመስጠት በደብሩ ዙሪያ ያሉ ነዳያንን የመደገፍ ሥራዎች ይሰራሉ በቋሚነትም ድጋፍ መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ ለመንደፍ ከደብሩ ምግባረ ሰናይ ክፍል ጋር እየተሰራ ነው። ፨ ዐበይት በዓላትን ምክንያት በማድረግ በደዌ ተይዘው በተለያዩ ጠበል ቦታዎች እና የሕክምና ተቋማት ያሉ ሕሙማንን ፣በእስር ቤት ያሉ ታራሚዎችን የእንኳን አደረሳችሁ መርሐ ግብር በማዘጋጀት የመጎብኘት፣ በጸሎት የማሰብ ፣ በቃለ እግዚአብሔር የማጽናናት እና ድጋፍ የመስጠት ሥራዎች ከመርሐ ግብርና አባላት ጉዳይ ክፍል ጋር በጋራ ይሠራሉ። ፨ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ነጻ የትምህርት አድል የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል። ፨ ሥራ ያጡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ሥራ የሚያገኙበትን ዕድል እያመቻቸ ይገኛል ፡፡ ፨ የአጥቢያውን ምዕመናን በመቀስቀስ እና ማስተባበር ከብሔራዊ የደም ባንክ ጋር በመተባበር በዓመት 3 ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ይዘጋጃል። ፨ አባላት ያላቸውን አቅም እና ሙያ አስተባብረው በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለሚያስገልጋቸው የተለያዩ አካላት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ቀድም ካሉ ዓመታት ጀምሮ የተለያዩ የወረርሽኝ በሽታዎች ሲከሰቱ የግንዛቤ ማስጨበጪያ መርሐ ግብር (በተለያም ለነዳያን) የማዘጋጀት እና ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት ሥራዎች በስፋት ይሠራሉ ሰንበት ትምህርት ቤታችን  ከዚህ በበለጠ አገልግሎት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ተልዕኮ ይወጣ ዘንድ ሁለንተናዊ ድጋፋችሁ ከእናንተ ከምዕመናን እንዳይለየን በቅዱስ ዮሐንስ ስም አደራ እንላለን።
Hammasini ko'rsatish...
4👍 1
9👏 5👍 4🥰 2🙏 1
👏 3👍 1 1
Po'stilar arxiv