cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
68 678
Obunachilar
-1224 soatlar
-267 kunlar
+28930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ፒያሳ
Hammasini ko'rsatish...
ዛሬ በመንግስት እና በግል አጋርነት መርሃ ግብር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ አስጀምረናል። በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ያስጀመርናቸው 4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ከ 14 እስከ 22 ወለል ያላቸው ዘመናዊ ህንጻዎች ሲሆኑ፣ የግንባታ ተገቢ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ የገባውን ጊፍት ሪል እስቴት በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግን እወዳለሁ። የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮችን ከህግና አሰራር ጋር በማጣጣም ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ምቹ የስራና የመኖሪያ ከተማ ለማድረግ መስራታችንን ቀጥለናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Hammasini ko'rsatish...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ለ2016 ዓመት የሚውል 21 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አስትድቋል። ከጸደቀው ተጨማሪ በጀት ውስጥ 909 ሚሊዮን ብር ለመደበኛ እንዲሁም 20 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለካፒታል በጀት የሚውል መሆኑ ተገልጿል። ምክር ቤቱ በዛሬ መደበኛ ጉባኤው በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረበውን የኮሪደር ልማትና በአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ እየተካሔደ ያለው የመልሶ ማልማት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ አጽድቆታል። የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ማጽደቁ የሚታወስ ነው። ——— አዲስ ማለዳ
Hammasini ko'rsatish...
👍 47 8👎 6
አስር ስዓት እና አዲስ አበባ
Hammasini ko'rsatish...
👍 84 16😢 16🤯 9🔥 6😁 6
ጎሮን ከቦሌ አራብሳ የሚያስተሳስረው የመንገድ ፕሮጀክት የየረር ነፋሻማና ሰንሰለታማ ተራራዎችን በቅርብ ርቀት የሚያስቃኘው እና የጎሮ አካባቢዎችን - ከቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ መንደሮች ጋር በልማት ለማስተሳሰር እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው አዲስ የመንገድ ፕሮጀክት በግንባታ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የአራብሳ -አይሲቲ ፓርክ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 6 ኪ.ሜ ርዝመትና 60 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን የግንባታ ስራውን አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያከናወነው የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ቤዛ አማካሪ ድርጅት እየተከታተለው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የሙሌት እና ተያያዥ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ሲሆን፣ አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀሙም 20 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ አሁን በግንባታ ላይ ከሚገኘው ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ - ጎሮ የመንገድ ፕሮጀክት ጋር የሚተሳሰር በመሆኑ፤ ከመሐል ከተማ ወደ ጎሮ እና አራብሳ ለመጓዝ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ለከተማዋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መፋጠን ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ሌላ የዲዛይን ስራው ላይ የአረንጓዴ ልማትን ያካተተ በመሆኑ ውብና ማራኪ ገፅታን በመፍጠር ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ ለመገንባት ያግዛል። የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
Hammasini ko'rsatish...
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አፏል። አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 " ጠሮ መስጂድ " አካባቢ ነው። ለሊት 11 ሰዓት ገደማ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ከላይ ወደ ታች (ወደ ቤቱ) ተንዶ 3 ክፍል ያለው ቤት ላይ አደጋ ደርሷል። በዚህም ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሟቾቹ ፦ ➡ የ4 ዓመት ህጻን ፣ ➡ ሶስት የ11 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች  ➡ ከ25 እስከ 30 ዓመት ያሉ 3 ወጣቶች ናቸው። ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ አደጋው የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ላይ ነው። መረጃው የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ነው። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
ፒያሳ
Hammasini ko'rsatish...
😁 147👍 88 15😢 15🥰 1
የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95% የሚሆነውን ማስመለስ ቻለ፡፡ ********** ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7፣ 2016 ዓ.ም በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801,417,747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር የተገለጸ ሲሆን ከዚህም ገንዘብ ላይ ብር 762,941,341 ማስመለስ ችሏል፡፡ ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 5 በመቶ ብር 38,474,938 ገንዘቡን ተመላሽ ካላደረጉ ግለሰቦች የማስመለስ ሥራው እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 29😁 19 4🤯 3