cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Abu Muss'ab - አቡ ሙስዓብ

I am Student Of Comparative Religion.

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
317
Obunachilar
-124 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ፋላሲ? ባለፈው ምሽት በቲክ ቶክ መንደር አጋጣሚ Mohammed Abebaw live እየሰበከ አይቼ ከስንት ልመና በኋላ ወደ ሊቭ ሩሙ አስገብቶኝ ነበር። እኔም ስገባ ቀላሉ የጠየኩት ጥያቄ👇 በክርስትናው ባይብል "Red letters" ተብሎ ከሚታወቁ ኢየሱስ በምድር ላይ ሲሰብክ ከተናገራቸው እና የኢየሱስ ብቻ ከሆኑ ንግግራት ልክ ሰውነቱን፣ ነብይነቱን እና መልዕክተኛነቱን እንደተናገረው ሁሉ 'አምላክነቱን' ወይም 'ተመላኪነቱን' በራሱ አንደበት(Red Letters) ለምን አልገለጸም? የሚል ነበር። የፓስተሩ መልስ ግን በመጀመርያ "ጥያቄህ ድምዳሜ" አለበት ስለዚህ ስህተት ነው የሚል ነበር። እኔም "ለምን ባንደበቱ አልገለጸም?" ለሚለው ጥያቄዬ ፓስተሩ "አዎ በአንደበቱ ገልጿል" የሚል አቋም የያዘ ስለመሰለኝ ወዲያው ጥያቄዬን በማስተካከል "ኢየሱስ በራሱ አንደበት(Red Letters) አንደኛውን የሚታየውንና በሰዎች ሁሉ የሚታወቀውን ምንነቱ(ሰውነቱን) እንደገለጸው ሌላኛው ክርስትያኖች አለው የምትሉት ምንነቱን(አምላክነቱን) የገለጸበትን ክፍል አሳየኝ?" የሚል ጥያቄ አቀረብኩለት። ፓስተሩ ግን አሁንም ጥያቄህ "ፋላሲ ነው!" የሚል መልስ ደጋግሞ ከመስጠት ውጭ ፍንክች አልልም ብሎ ገገመብኝ።😀 ለመሆኑ ፋላሲ ምንድነው? ምን አይነትስ ፋላሲ ነው ጥያቄዬ የያዘው? በጥያቄዬ ምንም አይነት ድምዳሜ ወይም Yes/No የሚል አቋም ሳላስተጋባ ጥያቄ መጠየቄ በራሱ እንዴት ፋላሲ ሊባል ይችላል? ይሄን ጥያቄዬን ፋላሲ ያለው ፓስተር የኔን ጥያቄ ስህተት ለማሳየት ተመሳሳይ አይነት ጥያቄ ከቁርአን ብጠይቅህ አትመልስም በማለት "ቁርአን ውስጥ ነብዩ ሙሐመድ በራሳቸው አንደበት በራሳቸው ቃል እኔ ነብይ ነኝ ተከተሉኝ ያሉበትን የሳቸውን ቃል ብቻ አሳየኝ?" በሚል ጥያቄ በሳቅ ያፈረሰኝን አረሳውም። የኔ ጥያቄ ነው ፋላሲ ወይስ የርሱ? ለማንኛውም የሙስሊሞችን በነገረ ክርስቶስ ዙርያ በጣም አስፈላጊ ጥያቄ ለማጣጣል የቀረበውን የፓስተሩን counter ጥያቄ ካሁን በፊትም በሌላ Aman Shalom የተባለ ሰባኪ ሲቀርብ ስላየሁ የሁለታችንን ጥያቄ ልዩነት እንድትገነዘቡ በቀላል ምሳሌ ላስቀምጥላችሁ። 1) የኔና የሙስሊሞች ጥያቄ ምሳሌ፥ የተለያዩ ለስላሳዎችን ምስል በመለጠፍ "ለስላሳ አለ(እንሸጣለን)" ብሎ የለጠፈ ትንሽዬ ምግብ ቤት ውስጥ ገብቶ "ኮካ ኮላ አምጣልኝ" ብሎ እንደማዘዝ ነው። 2) የፓስተሩና የክርስትያኖች ካውነተር ጥያቄ ምሳሌው ደግሞ፥ ኮከብ ምልክትና "የሙስሊም ስጋ ቤት" ብሎ የለጠፈ ሱቅ ሄዶ "የክርስትያን ስጋ አምጣልኝ" ብሎ እንደማዘዝ ነው። ባይብል ውስጥ ኢየሱስ በምድር ቆይታውና በስብከቱ በራሱ አንደበት የተናገራቸው ቃላት ለክርስትና Core ተደርጎ በግልጽ የሚቀመጥና የሚታመንበት ሲሆን ከራሱ ከባይብል ይህን አሳዩኝ ማለት ፋንታ፣ ሚሪንዳ፣ ኮካና ስፕራይት የሚሸጥ ሰው ዘንድ ሄዶ ኮካ አቅርብልኝ ብሎ እንደማዘዝ ነው። በሌላ በኩል የሙስሊሞችን አስፈላጊ ጥያቄ ለማጣጣል ተብሎ የሚቀርበው የክርስትያን ወገኖች ጥያቄ ደግሞ የቁርአን ሙሉ ቃሉ(ከሀ-ፖ) ባለቤትነት የአላህ ብቻና ብቻ እንደሆነ ባላገናዘበ መልኩ በቁርአን ውስጥ ነብዩ፣ አቡጀህል፣ ክርስትያኖች ወይም አይሆዶችም ሆኑ ማንኛውም ፍጡር በቀጥታ በቃላቸው የተናገሩትን ከቁርአን ውስጥ ስጠኝ ብሎ መጠየቅ፥ የሙስሊም ስጋ ቤት የተለጠፈበት ታፔላ ዘንድ ሄዶ የክርስትያን ስጋ ስጠኝ ብሎ እንደማዘዝ ነው። ስለዚህ፥ የተኛው ጥያቄ ነው ስህተትና ፋላሲው ለስላሳ ከሚሸጥበት ቤት ሄዶ ኮካ ኮላ ማዘዝ ነው ወይስ የሙስሊም ስጋ ቤት ሄዶ የክርስትያን ስጋ ማዘዝ??? @Abu_Mussaab
Hammasini ko'rsatish...
"Claiming Jesus as God is like claiming Cristiano Ronaldo who has 5 children and a GF as a Gay even if he kept telling you he is heterosexual like Jesus kept telling he was human." ከማ ረዋሁ ወሶሐሐሁ Triple-ኤ😐 T.me/Abu_Mussaab
Hammasini ko'rsatish...
Abu Muss'ab - አቡ ሙስዓብ

I am Student Of Comparative Religion.

"ሊቀ ጳጳሱ ፍራንሲስ እብደታቸውን ሊያቆሙ ያገባል!" ባለፈው ከ3 ሳምንታት በፊት የሊቀ ጳጳሱን አወዛጋቢ Liberalist ትምህርቶች ግብረሰዶማዊነት ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ዜናውን በትኩሱ እንደዘገብኩላችሁ ይታወሳል። እነሆ ዛሬ ደግሞ የዛ ውጤት በገሃድ ወጥቶ ካቶሊክን እየረበሻትና እየከፈላት እንደሆነ የሚያስነብበው ታዋቂው የThe Catholic Thing ድረገጽ "ሊቀ ጳጳሱ ፍራንሲስ እብደታቸውን ሊያቆሙ ያገባል!" በሚል ጠንከር ያለ ማስጠንቀቅያ በሚመስል ርዕስ ባለፈው ቅዳሜ የለጠፈውን ልጥፍ ይዤላችሁ ተከስቻለሁ። ድረገጹ እንዳስነበበው፥ የሰሞኑ የሊቀ ጳጳሱ እንግዳ ሀሳቦች የካቶሊክን የተለመደና ቋሚ ዶክትሪን በሚንድ መልኩ የግበረሰዶማውያን ጋብቻ እንደ ወንጀል ሳይቆጥር በቸርች ሳይቀር ተባርኮ መጋባት እንዲችሉ የማመቻቸት፤ ዝሙትን የመሰሉ የተለያዩ ኃጢአቶችን የፈጸሙ ሰዎች በወጉ ንስሐ ሳይገቡ ራሱ ኃጢአታቸውን ለመናዘዝ እስከ መጡ ድረስ ቀሳውስት ማንኛውንም ኃጢአተኛ ሰው ፍትሐት ሊያደርጉለት እንደሚገባ እና የመሳሰሉ አዳዲስ ተቃራኒ አስተምህሮቶችን ማምጣታቸውን ጠቅሶ በዚህም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታሪክ የትኛውም ሊቀ ጳጳስ ተናግሮት፣ ፈጽሞት እና አግራርቶት የማያውቀውን ነገራት አድርገዋል በማለት ይከሳቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ድረገጹ እንግዳ አስተምህሮቶቹን የተቃወሙ አንዳንድ አባቶች ካለ ምንም ጥፋታቸው ከስልጣናቸው ተነስተው እንደተባረሩና በምትኩ መሰል አዲስ አስተምህሮቶችን በሚቀበሉ አዳዲስ አባቶች እንደተተኩ ይገልጣል። ድረገጹም አክሎ፥ እነዚህ ዘመኑንና ያለንበትን ሁኔታ አይመጥኑም ተብለው እንዲቀየሩ የተደረጉ ዶክትሪኖችን አስተመልክቶ ከእግዚአብሔር ውጭ ሊቀ ጳጳሱም ይሁን ቀደምት ሐዋርያትም ቢሆኑ ማንም የመቀየርና የመሻር ስልጣን እንደሌለው በመጠቆም ሊቀየር የሚችለው ምናልባት መንፈስ ቅዱስ በትክክል እንዲቀየሩ የገለጠለት ቅዱስ ሰው ቢገኝ እንደሆነና ይህ ደግሞ በዚህ ጊዜ እንደማይሆን ያትታል። ለበለጠ መረጃ ማስፈንጠርያውን ተከትለው ያንብቡ፦ https://www.thecatholicthing.org/2023/02/18/pope-francis-must-stop-the-madness/ ማስታወሻ በአለም ክርስትና ካቶሊክም ይሁን ኦርቶዶክስ ወይም ፕሮቴስታንት የቤተክርስቲያን መሪ በተባሉ ጉምቱ አባቶች ሳይቀር በተደጋጋሚ መሠረታዊ በሚሏቸው ዶክትሪኖች ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ እንደማይስማሙ ይታወቃል። በመሆኑም ክርስትያን ወጎኖቼ የነዚህን ዶክትሪኖች መሠረት፤ መቸት፤ በማን እንደተጻፉና ለምን እንደተጻፉ፤ ግልጸኝነታቸውና እውነተኝነታቸውን፤ መለኮታዊ ይሁኑ ሰብአዊ ዶክትሪኖች ባጠቃላይ ከስር መሠረቱ መመረመርና ማጥናት እንደሚገባ ለመጠቆም እወዳለሁ። በተያያዘ ዜና በቅርቡ ኢንሻአላህ በዚሁ ቻናሌና ገጼ በቀደምት የቤተክርስትያን 2ኛውና 3ኛው ክፍለ ዘመን ጉምቱ አበው መካከል በመሠረታዊ የአዲስ ኪዳን ቀኖና መጽሐፍና አፖክሪፋ መጽሐፍት ሳይቀር የተለያዩና የማይስማሙ እንደነበሩ አስመለክታችኋለሁ። http://T.me/Abu_Mussaab
Hammasini ko'rsatish...
Pope Francis Must Stop the Madness - The Catholic Thing

Fr. Gerald E. Murray: Pope Francis’ manifest neglect of his duty to defend the Church’s teaching in the face of grave errors urgently calls for a “tough love” intervention.

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.