cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people." Rinu Ruzvelt

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
18 239Obunachilar
+924 soatlar
+447 kunlar
+26830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሕይወት የምትጀምረው መቼ ነው? ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ይከራከሩ ነበር፡፡ አንዱ፣ “ሕይወት የምትጀምረው ልክ አንድ ጽንስ በተጸነሰበት ቅጽፈት ነው” በማለት ያንን እምነቱን በግለት ያስተጋባል፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ “አይደለም! ሕይወት የምትጀምረው የተጸነሰው ልጅ የመጀመሪያውን ትንፋሽ ወደመተንፈስ ደረጃ ሲደርስ ነው” በማለት የተጋጋለ ምላሹን ይናገራል፡፡ ይህንን ሃሳብ ሳይለቁ ለሰዓታት ሲከራከሩ የተመለከተ አንድ ሰው እያዋዛ አንድን ትምህርት ትቶላቸው አለፈ፣ “ሁለታችሁም ተሳስታችኋል፤ ሕይወት የምትጀምረው ሰው የተፈጠረለትን ዓላማውን ሲያውቅና ያንን መከተል ሲጀምር ነው”!!! ዓላማችንን እንወቅ! በግለት እንከታተለው! እንኑረው! @zephilosophy
Hammasini ko'rsatish...
ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች! ወዳጆች ዛሬ የአለም የንባብ ቀን እንደመሆኑ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለመፃሕፍት የተነገሩ የተለያዩ ሠዎችን አባባል ዛሬ ልንዘክር ብዕራችንን ከወረቀቱ አገናኝተናል፡፡ መፅሐፍ የሚሠጡት ጥቅም የታወቀ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ግን አዋቂ መሆን አይቻልም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡ ለማንኛውም አባባሎቹን እነሆ እላለሁ..! ሃሳብና አስተያየታችሁ የተጠበቀ ነው፡፡ መልካም ንባብ! ‹‹መፅሐፍ አንድ ቁምነገር አለው፡፡ ይሄም እግርህን ከቤትህ ሳታነሳ ዓለምን እንድትዞር ያደርግሃል›› (ጁምባ ራሂሪ) ‹‹አንባቢ ከመሞቱ በፊት አንድ ሺ ኑሮ ይኖራል፡፡›› (ጆርጅ ማርቲን) ‹‹መፅሐፍት ተንቀሳቃሽ አስማቶች ናቸው›› (ስቴፈን ኪንግ) ‹‹እንደ መፅሐፍ ያለ ታማኝ ጓደኛ የለም፡፡›› (ኸርነስት ኸርሚንግወይ) ‹‹ አንድ ነገር አንርሳ! አንድ መፅሐፍ፣ አንድ እስኪብርቶ፣ አንድ ሕፃን፣ አንድ መምህር ዓለምን መለወጥ ይችላሉ፡፡›› (ማላላ ዮሶፍዜ) ‹‹ዓለም መፅሐፍ ናት፡፡ ዓለምን ተጉዘው ያላዩ መፅሐፍ ይግለጡ፡፡›› (ቅዱስ አውግስጦስ) ‹‹መፅሐፍ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን የህይወት ጉድፍ የሚያስወግድልን የነፍሳችን ማጠቢያ ነው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው) ‹‹ማንበብ ለአዕምሮ ሲሆን አዕምሮም አካላችን ምን ማድረግ እንዳለበት ያቀናጃል›› (ያልታወቀ ሠው) ‹‹መፅሐፍ ከባድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ታጭቋልና፡፡›› (ኮሜሊያ ፈንክ) ‹‹ዛሬ አንባቢ የሆነ ነገ መሪ ይሆናል፡፡›› (ማርጋሬት ፉለር) ‹‹ዛሬ ልታነበው የምትችለውን መፅሐፍ ለነገ አታቆየው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው) ‹‹ካነበብኩ መላው ዓለም ለእኔ ክፍት ነው፡፡›› (ሜሪ ማክሎድ ቤቱን) ‹‹አንዳንድ መፅሐፍት ነፃ ይተዉናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ነፃ አድርገው ይሠሩናል፡፡›› (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን) ‹‹መፅሐፍ ወደፊት ልንሆን የምንፈልገውን የያዘ ህልማችን ነው፡፡›› (ኔል ጌማን) ‹‹ቤተ-መፃሕፍቶች ልክ እንደጥሩ ትዝታ መዓዛቸው ያውደኛል፡፡›› (ጃኩሊን ውድሰን) ‹‹መፅሀፍ አስተሳሰባችንን የሚያቀጣጥል መሣሪያ ነው፡፡›› (አላን ቤኔት) ‹‹ሌላ ሠው ያነበበውን ብቻ እያነበብክ ከሆነ ሌላ ሠው የሚያስበውን ብቻ ነው እያሠብክ ያለኸው፡፡›› (ሐሩኪ ሙራካሚ) ‹‹ቤት ያለመፅሐፍት ማለት አካል ያለነፍስ ማለት ነው፡፡›› (ሲስሮ) ‹‹ተራ ሠዎች ትላልቅ ቲቪ አላቸው፡፡ ብልህ ሠዎች ግን ቤተመፃሕፍት አላቸው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው) "መፅሀፍ ማለት በኪሳችን ይዘነው የምንዞረው በመልካም ፍሬዎች የተሞላ እርሻ ነው።” #ቻይናውያን “መፅሀፍ ስናነብ ወደ ውስጣችን በጣም ጠልቀን በመግባት ስለራሳችን የበለጠ ብዙ ነገሮችን ማወቅ እንጀምራለን።” #ዊልያም ሀዝሊት
Hammasini ko'rsatish...
"ፍቅር ግንኙነት ሳይሆን የመሆን ሁኔታ ነው" ምንጭ ፦ ህያውነት (ኦሾ) ተርጓሚ ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ ፍቅር ግንኙነት ሳይሆን የመሆን ሁኔታ ነው፤ ከማነም ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ አንድ ሰው ፍቅር ውስጥ ነው ወይም አፍቅሯል ሳይሆን የሚባለው <እገሌ ፍቅር ነው> ነው የሚባለው፡፡ በእርግጥ አንድ ሰው ፍቅር ሲሆን በፍቅር ውሰጥ ነው ያለው ነገር ግን ይህ ምርጫ ሳይሆን ውጤት ነው፡፡ ምንጩ ፍቅር መሆኑ ነው፡፡ ማን ፍቅር ሊሆን ይችላልን? ማን እንደሆናችሁ የማታውቁ ከሆነማ ፍቅር ልትሆኑ አትችሉም፡፡ ይልቁኑ ፍርሃት ትሆናላችሁ፡፡ ፍርሃት የፍቅር ተቃራኒ ነው፡፡ ሰዎች እንደሚያስቡት የፍቅር ተቃራኒ ጥላቻ አይደለም፡፡ ጥላቻ የፍቅር ተቃራኒ ሳይሆን ፍቅር ተገልብጦ ሲቆም ነው፡፡ እውነተኛ የፍቅር ተቃራኒ ፍርሃት ነው፡፡ ፍቅር ያሰፋል፣ ፍርሃት ያጠብባል፡፡ ፍርሃት ይዘጋል፣ ፍቅር ይከፍታል፡፡ ፍርሃት ያጠራጥራል፣ ፍቅር ያሳምናል፡፡ ፍርሃት ብቸኛ ያደርጋል፡፡ ብቸኛ ከማድረግም አልፎ ያጠፋል፡፡ የሌለ ሰው እንዴት ብቸኛ ይሆናል? እነዚህ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ደመናዎች፣ ፀሃይ፣ ከዋክብት በሙሉ እናንተ ውሰጥ ናቸው፡፡ ፍቅር ማለት ውስጣዊ ቁልፋችሁን ስታውቁ ነው:: ማንም ህፃን ከፍርሃት ነፃ ነው፤ ህፃናት የሚወለዱት ያለምንም ፍርሃት ነው፡፡ ማህበረሰቡ ፍርሃት አልባ እንዲሆኑ ቢረዳቸውና ቢደግፋቸው ዛፎችና ተራሮች ላይ እንዲንጠለጠሉ፣ ውቅያኖሶችንና ወንዞችን እንዲያቋርጡ በረዳቸው ነበር፡፡ ማህበረሰቡ ጀብደኛ እንዲሆኑ፣ ካረጀ እምነት ይልቅ የማይታወቀውን እንዲመረምሩ ቢያደርጋቸው ኖሮ፤ ታላላቅ የህይወት አፍቃሪዎች ባደረጋቸው ነበር፡፡ ይህ ነው እውነተኛ ሃይማኖት፡፡ ከፍቅር በላይ ሃይማኖት የለም፡፡ ተመሰጡ፣ ደንሱ፣ ዝፈኑ፣ ወደ ውስጣችሁ ጠልቀችሁ ግቡ፡፡ የአዕዋፋቱን ዝማሬ በአንክሮ አድምጡ፡፡ አበቦቹን በአድናቆት ተመልከቱ፡፡ አዋቂ አትሁኑ፤ ነገሮችን አትፈርጁ አዋቂ መሆን ማለት ይህ ነው ለእያንዳንዱ ነገር መደብ፣ ፈርጅ ማውጣት፡፡ ከሰዎች ጋር ተገናኙ፣ ከሰዎች ጋር ተቀላቀሉ፣ በተቻላችሁ መጠን ከብዙ ሰዎች ጋር ተገናኙ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተለያየ ሁኔታ የእግዚአብሄርን መልክ ያሳያል፡፡ ከሰዎች ተማሩ፡፡ አትፍሩ፡፡ ፍቅር እምብዛም የማይገኝ አበባ ነው፡፡ ብቅ የሚለው አንዳንድ ጊዜ ነው፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አፈቀርን ብለው የውሸት ኑሮ ይኖራሉ፡፡ እንደሚያፈቅሩ ያምናሉ፡፡ ከእምነት የዘለለ ግን አይደለም፡፡ ፍቅር ብርቅዬ አበባ ነው:: ብቅ የሚለው አልፎ አልፎ ነው፡፡ የሚከሰተው ፍርሃት ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ፍቅር የሚከሰተው በጣም መንፈሳዊ ሃይማኖተኛ ለሆነ ሰው ነው፡፡ ሁሉም ወሲብን፣ መላመድን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ፍቅርን ግን ሁሉም አያገኙትም፡፡ ፍቅር ድፍረት ይሰጣል፤ ፍቅር ፍርሃትን ያጠፋል ጨቋኞች የእናንተ ፍርሃት ጥገኛ ናቸው፡፡ አንድ ሺ አንድ ፍርሃት ይፈጥሩባችኋል፡፡ ስለዚህ በፍርሃት ትከበባላችሁ፤ ሥነ - ልቡናችሁ በፍርሃት ይሞላል፤ በውስጣችሁ ትሸበራላችሁ:: ፊታችሁ አንድ አይነት ገፅታ ብቻ ነው ያለው፣ ውስጣችሁ ግን በፍርሃት ድርብርብ የተሞላ ነው:: በፍርሃት የተሞላ ሰው ምርጫው ጥላቻ ብቻ ነው - ጥላቻ ተፈጥሯዊ የፍርሃት ውጤት ነው፡፡ በፍርሃት የተሞላ ሰው በብስጭት የተሞላ፣ ከህይወት የወጣ ነው፡፡ በፍርሃት የተሞላ ሰው ማረፊያው ሞት ይመስላል፡፡ ፈሪ ሰው ከህይወት በተፃራሪ ራሱን የሚያጠፋ ነው፡፡ ህይወት አደገኛ ትሆንበታለች፡፡ ለመኖር ማፍቀር ያስፈልጋል፡፡ ስጋ ለመኖር መተንፈስ እንደሚያስፈልገው፣ ለነፍስም ፍቅር ያስፈልጋታል፡፡ ፍቅር ደግሞ ክፉኛ ተበክሏል፡፡ የፍቅር ሃይላችሁን በክላችሁ በውስጣችሁ መከፋፈል ፈጥራችኋል፤ ውስጣችሁን ለሁለት ከፍላችሁታል፡፡ የርስ በርስ ግጭት ፈጥራችሁበታል፡፡ ሁልጊዜም በግጭት ላይ ናችሁ:: በዚህ ግጭት ሃይላችሁ ተሟጥጧል፡፡ ስለዚህም ህይወታችሁ ደስታ የራቀው ሆኗል፡፡ በሃይል የተሞላ ሳይሆን የደነዘዘ ጣዕም የሌለው፣ ብልህነት የሌለው ህይወት ሆኗል፡፡ ፍቅር ብልህነትን ይስለዋል፤ ፍርሃት ደገሞ ያዶለዱመዋል፡፡ ብልህ መሆን ማን ይፈልጋል? ስልጣን ላይ ያሉ ይህን አይፈልጉም፡፡ እናንተ ብልህ እንድትሆኑስ እንዴት ሊፈልጉ ይችላሉ? ብልህ ከሆናችሁ እቅዳቸውን ጨዋታቸውን ትነቁባቸዋላችሁ፡፡ ስለዚህ መሃይም እና የማይረባ እንድትሆኑ ይፈልጋል፡፡ ስራን በተመለከተ ውጤታማ እንድትሆኑ ይፈልጋሉ፤ ብልህ እንድትሆኑ ግን አይፈልጉም፡፡ በዝቅተኛ አቅማችሁ እንድትኖሩ ነው የሚፈልጉት፡፡ የሳይንስ ተማራማሪዎች እንደሚናገሩት የሰው ልጅ በመላ የህይወት ዘመኑ የአቅሙን አምስት በመቶ ብቻ ነው የሚጠቀመው፡፡ ተራው ሰው አምስት በመቶውን ከተጠቀመ ልዩ የሆነ ሰውስ? አልበርት አንስታይን፣ ሞዛርት፣ ቤትሆቨን? ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት በጣም ከፍተኛ ተሰጥኦ ያላቸው እንኳን ከአስር በመቶ በላይ አይጠቀሙም፡፡ እና የላቀ ችሎታ አላቸው የምንላቸው እንኳን አስራ አምስት በመቶውን ብቻ ነው የሚጠቀሙት፡፡ ሁሉም ሰው የአቅሙን መቶ በመቶ የሚጠቀም ቢሆን ይህች ዓለም ምን እንደምትመስል አስቡ.... ጣዖታት በምድር ቀንተው ምነው ምድር ላይ በተወለድን ይሉ ነበር፡፡ ምድር ገነት ትሆን ነበር፡፡ አሁን ግን ሱዖል ናት፡፡ የሰው ልጅ ብቻውን ቢተው፣ ሳይበከል ቢቀር .... ፍቅር ቀላል ይሆን ነበር፤ ምንም ችግር አይኖርም፡፡ ቁልቁል እንደሚወርድ ውሃ ወይም ሽቅብ እንደሚወጣ ትነት፣ እንደሚያብቡ ዛፎች፣ እንደ ዘማሪ አዕዋፋት ይሆን ነበር፡፡ ተፈጥሯዊና ህያው ይሆናል! ነገር ግን የሰው ልጅ ብቻውን አልተተወም፡፡ አንድ ህፃን ሲወለድ ጨቋኞች ዘልለው ሃይሉን ያደቁታል፤ ሃይሉን ያዛቡታል፤ መኖር ያለበትን ያህል ሳይሆን የውሸት ህይወት እየኖረ እንደሆነ እንዳያውቅ፣ እየኖረ ያለው በእውነተኛ ነፍሱ እንደሆነ እንዳይገነዘብ ያደርጉታል፡፡ ለዛም ነው በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ስቃይ ውስጥ የገቡት - እነዚህ ሰዎች እንደተሰናከሉ ራሳቸውን እንዳልሆኑ፣ አንድ የተሳሳተ ነገር እንዳለ.... ይሰማቸዋል ። @Zephilosophy @Zephilosophy
Hammasini ko'rsatish...
አብዘርዲዝም - ካምዩ ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ምንጭ ፦ ፍሉይ አለም መጠለያ ባጣህበት ሁኔታ በዝናብ እየተደበደብክ እየተጓዝክ ሳለ፣ መሳቅ ጀምረህ አታውቅም? የሆነ ጉዳይ በእጅጉ ተበላሽቶብህ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ አይነት ስሜት ፈገግ ብለህ አታውቅም? በችግሮችህ ውስጥ ሳለህ እያንዳንዷን ደቂቃ ወደህ አታውቅም? ይህን አልበርት ካምዩ አብሰርዲቲ ይለዋል፡፡ ካምዩ ፈረንሳያዊ የኤግዚስታንሻሊዝም (ህላዌነት) ፈላስፋ ነው፡፡ በቀላል ታሪክም ፍልስፍናውን ይጀምራል፡፡ ሲሲፈስ የተባለ የጥንታዊቷ ግሪክ ንጉስ አማልክቱን የሚያስቆጣ ተግባር ፈጸመ። ሲሲፈስ ሞትን በሰንሰለት አሰረው፡፡ ይህንንም በማድረጉ የሰው ልጅ ዘላለም ኗሪ ሆነ። በመጨረሻም አማልክቱ ሲሲፈስ ያደረገውን አወቁ፤ በርሱ ላይም ዘላለማዊ ቅጣት ፈረዱበት፤ የሞትንም ሰንሰለት በጠሱ፡፡ እናም ሲሲፈስ ለመቀጣጫ እንዲሆነው ዘላለም ድንጋይ ሲያንከባልል እንዲኖር ተፈረደበት። ግዙፍ ቋጥኝ እየገፋ ወደ ተራራ አናት ያደርስዋል፤ ወዲያውም ቋጥኙ ወደ ተራራው ስር ተንከባሎ ይወርዳል፤ ሲሲፈስም እንደገና ከታች ጀምሮ ወደ ላይ ቋጥኙን ይገፋዋል፡፡ ቋጥኙም ተመልሶ ወደ ተራራው ግርጌ ይወርዳል... ይህ የሲሲፈስ ዘላለማዊ ቅጣቱ ነው። ያንተስ ሕይወት ከርሱ ይለያልን? የሲሲፈስ እልፍ ጊዜ እየተመላለሰ ቋጥኝ ማንከባለሉ ትርጉም አልባ እንደሆነ ይሰማሃል? ሆኖም ያንተ ሕይወት ትርጓሜው ምንድን ነው? ሕይወትህን ልክ እንደ ሲሲፈስ ትርጉም አልባ ቋጥኞችን ስትገፋ ነው የምታሳልፈው፡፡ የማይሞላ ሆድ አለህ... ሚልዮን ጊዜ መግበኸው ሚልዮን ጊዜ ጎድሎብሃል፤ የማይሞላ ፍላጎት አለ... ሚልዮን ጊዜ ተደስተህ ሚልዮን ጊዜም ተከፍተሃል። በጠዋት ከእንቅልፍህ ትነሳለህ፤ ገንዘብን ፍለጋም ወደ ስራ ትሄዳለህ... ቀኑ ይመሻል ዳግም ይነጋል... በጥዋት ወደ ስራ ትሄዳለህ. ከእለታት በአንዱ ቀንም ራስህን በሞት አልጋ ላይ ታገኘዋለህ፡፡ እናም በሕይወት ዘመንህ የምታደርገው ነገር ሁሉ ልክ እንደ ሲሲፈስ ቋጥኝ መግፋት- ዘበት ነው! የሰው ልጅ ህልቆ መሳፍርት በሌለው ሁለንተና ላይ ራሱን ሲያገኘው፤ “ለምን?” የሚል ጥያቄን ይጠይቃል። ለምን ተፈጠርኩ? ለምን እኖራለሁ? የሕይወቴ ትርጉምስ ምንድን ነው? ሆኖም እውነታው ይህ ነው... ያንተም የኔም የመኖር ሁኔታ በአጋጣሚዎች የተፈጠረ እንጂ ትርጓሜ ያለው ነገር አይደለም በጸጥታ ውስጥ ባለው በግዙፉ ሁለንተና ውስጥ አንተ ማን ነህና ሕይወትህ ትርጉም ይኖረዋል? ሁለንተናም ስላንተ ግድ የለውም... ለጥያቄህም መልስ የለውም፡፡ ሆኖም ይህ መሆኑን ብናውቅም፤ ሰው ነንና የሕይወታችንን ትርጉም መፈለጋችንን አናቆምም የሞትን ቀን ያበቃለታል። ሞት በሕይወታችን የኖርንላቸውን ተግባራቶች በሙሉ ዋጋ ያሳጣቸዋል፡፡ ይህንን ነው አብሰርዲዝም ወይም የሕይወት ዘበትነት ሲል የሚጠራው፡፡ እና ዘበት በሆነ ዓለም ላይ እንዴት እንኑር? ታይታኒክ በተባለው ፊልም መጨረሻ ላይ መርከቧ እየሰመጠች ሳለ ሙዚቀኞች ቫዮሊን ሲጫወቱ ይታያል፡፡ እንደሚሞቱ ቢያውቁም፣ ቅጽበታቸውን ብቻ መኖር ጀመሩ፤ የሚወዱትንም ሙዚቃ ከልባቸው ተጫወቱ፡፡ ካምዩ በአንደኛው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይለናል - "የምር የሆነ አንድ የፍልስፍና ጥያቄ ብቻ ነው ያለው፤ ጥያቄውም - ራሴን ላጥፋ ወይስ ቡና ልጠጣ?” እንደ ካምዩ እሳቤ የሰው ልጅ የሚኖርበት ምክንያት ከሌለው ሶስት ነገሮች ያደርጋል፡ የመጀመሪያው ራሱን ያጠፋል፡፡ ማለቂያ አልባ በሆነው ሁለንተና ውስጥ የምትበራ አንድ ሻማ የርሷ ጭል... ጭል ማለት ትርጉም የለውምና ራሷን እፍ ብላ ታጠፋለች፡፡ ይህን ካምዩ የዓለምን ዘበትነት ማምለጫ ይለዋል። ሁለተኛው philosophical suicide ይፈጽማል፡፡ ይህም ማለት ሕይወት ትርጉም ባይኖራትም ትርጉም እንዳላት አድርጎ ማሰብ ይጀምራል። ለዚህ ዋነኛ ተጠቃሽ የሚሆኑት ጭፍን አማኞች ናቸው፡፡ በእምነት ውስጥ መመርመር የለም... የምትኖርበት አላማ እንዳለህ እና የምታምንበት ሀይል ለዚህ አላማ እንደፈጠረህ ያለምንም መጠራጠር በጭፍን ትቀበላለህ፡፡ ስለሆነም መኖርህ ዋጋ አልባ ወይም ዘበት እንደሆነ አይሰማህም፡፡ በሶስተኛነት የምናገኘው ካምዩ absurd hero ይለዋል። ይህ ሰው ሕይወቱ ትርጉም እንደሌላት ያውቃል፤ ለሌሎች ሰዎች ትርጉም የማይሰጥ ነገር ግን ለእርሱ ብቻ ዋጋ ያለው ... ለእርሱ ብቻ የሚሰራ የሕይወት ትርጉምንም ይፈጥራል። ይህ የትርጉም ፈጠራ ሂደትም በራሱ ደስተኛ ያደርገዋል። ለሲሲፈስም ድንጋዩን ወደ ተራራ ማንከባለሉ ለእርሱ ትርጓሜ አለው፡፡ ይህ ለስው ልጆች የከፈለው መስዋእትነት ምልክት ነው. ይህ አማልክቱ ለእርሱ የሰጡት ቅጣት ምንም እንዳልሆነ ማሳያ መንገዱ ነው... ፈገግ ብሎም ድንጋዩን ይገፋል... የእርሱ ፈገግታም አማልክቱን እንደሚያስቆጣቸው ያስባል። እናም ድንጋይ ማንከባለሉ ብቻ ልቡን በደስታ ይሞላዋል። ካምዩም ሕይወት ትርጉም አልባ እንደሆነች ቢያውቅም እንኳ እንደ ሲሲፈስ ሁን ይልሃል። በዝናብ ውስጥ ደንስ... ትርጉም አልባ በሆነች ዓለም ላይ ለራስህ ብቻ እውነት የሆነ የመኖር ትርጉም ፍጠር፡፡ @Zephilosophy @Zephilosophy
Hammasini ko'rsatish...
ክቡር ሰው - ካንት ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም ከጓደኞችህ ጋር እራት እየበላህ፣ አንዱ ተስተናጋጅ ከመጠን በላይ እያጨበጨበ አስተናባሪውን ይጣራል “እዚህ ጋር አንድ ምግብ፡፡” አንዳንድ ሰውም በሰላም ላደረሰው ሾፌር “እንዴት ነህ፣ ቻው ወይም አመሰግናለሁ” ሳይል ከታክሲ ወርዶ ወደ ጉዳዩ ያቀናል፡፡ ወንጀለኞች ህጻናትን ሰርቀው እንደ እቃ ይሸጣሉ፡፡ መንግስትም አገሩን ከዳ ብሎ ያስበውን ግለሰብ ያስገድላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች በጋራ የያዙት ነገር ምን አለ? ኢማኑኤል ካንት አስተናጋጁን የሚያመናጭቀው ጓደኛህም፣ ለሾፌሩ ግድ የሌለው ተሳፋሪም፣ ልጆች የሚጠልፉ ወንጀለኞችም፣ አስገዳዩ መንግስትም... ሁሉም የሰውን ልጅ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ አስተናግደዋል ይለናል። ካንት በምክንያታዊነት ላይ ባለው የጸና አቋም በእጅጉ ይታወቃል። ለእርሱ ምክንያታዊነት ከሁሉ የላቀ ንብረታችን እንደሆነ ነው የሚነግረን። ከዚህም በላይ ምክንያታዊነት ምን ልክ ምን ስህተት ምን ኃጢአት ምን ጽድቅ እንደሆነ ይለይልናል፡፡ ካንት የሞራል ህግጋት አይለወጤ እና የጸኑ ናቸው ብሎ ያስባል። የሚደረስባቸውም በምክንያት እና ምክንያታዊነት ብቻ ነው። ይህንንም ምክንያታዊ ግብረገብነትንም ለማስረዳት ካንት ባለ ብዙ ገፅ መጽሐፎችን አሳትሟል። ካንት ሁሉም ሰው ሊነካ የማይገባው ክብር አለው ይለናል። እናም የሁላችንም ድርጊቶች ይህን ክብር የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም የሰውን ክብር መንካት የለብንም፡፡ ሰዎች የምንገለገልባቸው ቁሳዊ መሳሪያዎች አይደሉም፡፡ ሁሉም የራሳቸው ዋጋ አላቸው። ለሁሉም ሰው ግድ ሊኖረን ይገባል። ሁላችንም እንደ ግለሰብ ዋጋ እንዳለን እናስባለን፡፡ ዓለም የግለሰቦች ጥርቅም ናትና ለራሳችን የምንሰጠውን ዋጋ ለሁሉም ሰው መስጠት የተገባ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ጥያቄ እና ምክንያት ሳንደረድር፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለራሳችን ከፍ ያለ ዋጋን ከሰጠን፣ እንደ ማህበርም ለሌሎች ሰዎች ዋጋ ሊኖረን ይገባል። አዎ በማህበረሰብ ውስጥ አንደኛው ተገልጋይ፣ ሌላኛው አገልጋይ ሊሆን የተገባ ነው፤ ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ሰዎችን እንደ ሰውነታቸው ልናከብራቸው የተገባ ነው፡፡ አስተናጋጁም፣ የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ሀገር ከዳተኛው ሰው ናቸው። ሁሉም ለራሳቸው ዋጋን ይሰጣሉ፡፡ ካንት ከእርሱ በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን አገልጋዮቹን በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር፡፡ በቀጣይም ሰውን እንዴት ማዋራት እንዳለብህ ስታስብ ይህን “እንደ ሰው እያከበርኳቸው ነው ወይንስ እንደ መሳሪያ እየተጠቀምኩባቸው?” ይህም ቀላል እና ሊተገበር የሚገባው ግብረገባዊ ህግ ነው፡፡ @Zephilosophy @Zephilosophy
Hammasini ko'rsatish...