cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Good samaritan club"

"Therefore to him that knoweth to do good, and doeth(it) not, to him it is sin" james 4:17 "እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሰራዉ ኃጢአት ነው" የያዕቆብ መልክት ፬:፲፯ for any comment @abuttysdaa an @edbornagain Leave ከማለቶ በፍት ያናግሩን. We are here to create compassion..join us

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya11 176Amxar9 479Toif belgilanmagan
Reklama postlari
231
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ያለፈው ጉዳት ጉዳይ! አዲስ ጅማሬ በአዲስ ዓመት! ባለፈው ዓመት ደጋግሞ የጎዳችሁና ደጋግማችሁ በይቅርታ አልፋችሁት አሁንም እየተጎችሁበት ያለ ሰው ካለ፣ የይቅርታው ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ በያዝነው ዓመት ምናልባት መማሰተካከል ያለባችሁ አካሄድ ሊኖር እንደሚችል ላስታውሳችሁ፡፡ ከሰዎች ጋር ያለንን አስቸጋሪ ግንኙነት የመያዣው መንገድ ሁለት ነው፡- 1) ሰዎቹን ለመለወጥ መሞከር፤ ወይም 2) ራሳችንንና አደራረጋችን መቀየር፡፡ በዚህች አለም ላይ የሰዎችን አስቸጋሪ ባህሪይ እንደመሸከምም ሆነ ለመለወጥ እንደመሞከር አስቸጋሪ ነገር የለም፡፡ ከዚያ የተሻለው መንገድ ራሳችንንና አያያዛችንን መለወጥ ነው፡፡ ራሳችንንና አደራረጋችንን ለመለወጥ፡- 1.  የሰዎቹ ሁኔታ ስሜታችንን እንዳይጎዳው መጠንከርና መታገስ፡- ይህ ሂደት እጅግ አድጋሚና ታላቅ ጥንካሬን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሆኖም፣ ከሰዎቹ ጋር ያለን ግንኙነት የጠለቀና በቀላሉ የማንፋታው አይነት ከሆነ የሚመረጥ መንገድ ነው፡፡  2.  ከሰዎቹ ጋር ያለንን ግንኙነት ሚዛናዊና በልኩ ማድረግ፡- አንዳንድ ሰዎች ራሳችንን በነጻነት ስናቀርብላቸውና ጠጋ ስንላቸው አያያዙን አይችሉበትም፡፡ ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት መጠነኛ፣ እንዲሁም በአስፈላጊው ሁኔታና ጊዜ ላይ ብቻ የተወሰነ እንዲሆን ማድረግ የግድ ነው፡፡ 3.  ከሰዎቹ መለየት፡- ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት እንደ ትዳር ያለ በቃል-ኪዳን የተሳሰረ ካልሆነና ከእነሱ መለየት የሚያስከትለው ሁኔታ በሚገባ ከታሰበበት (ይቅር የማለትና ልብን ከቂመኝነት የመጠበቁ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ) ከአንዳንድ ሰዎች የመላቀቂያው ቀላሉ መንገድ የሚከፈለው ዋጋ ተከፍሎ ከእነሱ መለየት ነው፡፡ Dr Eyob Mami @samaritanclub @samaritanclub
Hammasini ko'rsatish...
==> ✓ ፍቅር ማለት ውበት አይደለም ==> ✓ ፍቅር ማለት ጥቅም ፍለጋ አይደለም ==> ✓ ፍቅር ማለት ዝሙት ፍለጋ አይደለም ==> ✓ ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም ==> ✓ ፍቅር ማለት ስለወደዱን መውደድ አይደለም ==> ✓ ፍቅር ማለት ስላከበረን ማክበር አይደለም ==> ✓ ፍቅር ማለት ስላገዘህ አንተም ቀን ጠብቀህ ብድር መመለስ አይደለም ==> ፍቅር ማለት ከማንነት የፀዳ ==> ==> ፍቅር ማለት ከማዳላት የራቀ ፍቅር ማለት ከመፍረድ እጁን ያወጣ፣በመከራም፣በሀዘንም ፣በጭንቀትም፣በደስታም፣ መተሳሰብ ፣መተጋገዝ፣መረዳዳት...አንተ ያላገኘሀውን ነገር መውደድ፣ስለወንድምህ እራስህን አሳልፈ መስጠት፣የወንድምህን በደል መሸከም ባንተ እንዲፈፀም ሌሎች እንዲያገኙት መመኘት፤ጠላትህን መፈፀሙ አይቀርምና።።።። የማትፈልገውን በሌላ አለመፈፀም..ተመልሶ በራስህ አይቀርምና። Source : kutube 😍 @abutty777 have a blessed day😍😍😍😍 @samaritanclub @samaritanclub
Hammasini ko'rsatish...
🌻ጌዜ በነፃ የምናገኘው ነገር ቢሆንም ጥቅሙ ግን በዋጋ አይተመንም ። ልንጠቀምበት እንጂ የግላችን ልናደርገው አንችልም ። 🌼ስራ ላይ ልናውለው እንጂ ይዘን ልናቆየው አንችልም አንዴ ካጠፋነው መልሰን አናገኘውም ። አዲሱ አመት ጊዜያችንን በአግባቡ በመጠቀም ያሰብነውን የምናሳካበት ይሁንልን፣ 📍ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ነው። የእኛ ሰብዓዊነት የሚወሠነው የሌሎችን ሰብዓዊነት ስንገነዘብ ነው፡፡ ሌሎችም እንደእኛ ሰው መሆናቸውን ከተረዳን እንረዳዳለን እንጂ አንገፋፋም፤ እንተቃቀፋለን እንጂ አንገፈታተርም፤ የሚያፈናቅሉ እጆች ተሠብሥበው የሚያቅፉ ይሆናሉ፡፡ 🌻ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን !                     አሜን😇      "መልካም አዲስ አመት"💛     ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ . !!🙏 📍የተሰማቹን አጋሩን!! ሃሳባችሁን እዚሁ ላይ ፃፍፍ አድርጉልን    👇👇 @Samaritanclub @Samaritanclub
Hammasini ko'rsatish...
እውነትና ገንዘብ አንድ ቢሊየነር ነበር ፣ መክናው ውስጥ ሆኖ የአንድ ሰባኪ አስተምሮ ይሰማል። ሰባኪው ስለ አብታም ሰዎች ፣ ከሁሉም ገንዘብም እንደሚያስቀድሙ ፣ ሁሉም ነገር ከገንዘብ በኋላ እንደሚመጣ እንደሚያስቡ፣ ነገር ግን ገንዘባቸውን ይዘው እንደ ማይሞቱ ይሰብካል። ቢሊየነሩም በሰማው ነገር በጣም ሳቀ። በልቡም ደሃ ስለሆነኮ ነው ፣ ገንዘብ ቢኖረው እንዲ አይናገርም ነበር። ይላል። እናም አንድ ቀን ሰራተኞቹን ሰብስቦአቸው ፣ አንድም ሳንቲም ያለአግባብ እንዳት ባክን ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው። ከዛን በዚህ ቢሊየነር ስግብግብነት የተማረረ አንድ ጥበበኛ ሰው እንዲህ ብሎ ይጠይቃል። ጥበበኛው :- አለቃ ወደ አሜሪካ ከመምጣትህ በፊት የት ነበርህ!? ቢሊየነሩ :- ህንድ ነበርኩ። ጥበበኛው ;- US ለመምጣት ምን አደረክ ታዲያ!? ቢሊየነሩ :- የህንድን ሩፕ (Rupees) ወደ US$ ቀየርኩ። ጥበበኛው :-ብዙ አገር ሄደሃልን!? ቢሊየነሩ:- አዎ ብዙ አገራትን ጎብኝቻለሁ። ብሪታኒያ ፣ ፍራንስ፣ ኢታሊያ ብዙ አገራት። ጥበበኛው :- ብሪታኒያ ስትሄድስ ምን አደረክ!? ቢሊየነሩ:- ሩፕ(Rupees) ወደ pound sterling ለወጥኩት። ጥበበኛው :- ለምን? ቢሊየነሩ :- የህንዱ Rupees ብሪታኒያ ዋጋ ስለ ሌለው ነው። ጥበበኛው ;- ሰማይ መግባት ትፈልጋለህ? ቢሊየነሩ :-እንዴታ ። "ጥበበኛው:- እንግዲህስ ገንዘብህን ወደ ምፅዋት ቀይር። ሰማይ ቤትም ገንዘብ ዋጋ የለውምና። በገንዘብህ በጎ ነገርን ካደረክ ሰማይ ትገባለህ። አለው። ቢሊየነሩም በሰማው ነገር በጣም ተደነቀና ፣ አንድ ትልቅ የመርጃ መካከል አቋቋመ። #መልካምነትን_እንኑር #መልካም_ግዜ @samaritanclub @samaritanclub @abuttysda
Hammasini ko'rsatish...
ሰላም ቤተሰቦቼ !! ተመልሻለሁ! እንደ ጌታ ፍቃድ በቅርቡ በአዳዲስ አስተማሪ ጽሁፎች እመለሳለሁ፡፡ ጔደኞቻችሁን invite አርጉ!? አብረን እንስራ! ጌታ ይባርካችሁ @samaritanclub @samaritanclub
Hammasini ko'rsatish...
━━━━━✧❂✧━━━━━ How to attract Good Vibes !!! • Thank the Universe • Laugh/ Smile • Do something you love to do • Feed yourself with positive energy • Expect Miracles • Forgive yourself and Trust yourself • Tell someone else how amazing they are • Eat foods with good energy • Go outside and enjoy nature • Respect your vibe :) ━━━━━✧❂✧━━━━━ Channel ✨ @Samaritanclub ✨ ✨ @Samaritanclub ✨ ━━━━━✧❂✧━━━━━
Hammasini ko'rsatish...
ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም ፡፡ ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡ በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡ ይህን ማድረግ አደጋ አለው! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል! በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡ በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡ በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡ እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ። ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡ ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ ይህ ጀግና ፈጣሪን የሚመስል ገራሚ ሐይል ነው፡፡ ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡ የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ሰው ምን ይለኛል? ይላል፡፡ ስህተት ይፈራል፡፡ ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ ጀግናው ማንንትት ግን እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል? ይላል፡፡ ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡ እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል። የላቀ አስተሳሰብና ክህሎት በማስቀደም ስኬትን መጎናጸፍ። @samaritanclub
Hammasini ko'rsatish...
0.87 KB
ትክክለኛ የተቃራኒ ጾታ ፍቅር በምን ይመዘናል? 👉አንዳንድ ስሜት ተኮር መካሪዎች "ፍቅር ሲይዝህ በቃ ልክ መጀመርያ ስታያት ይታወቅሃል/ስታይው ይታወቅሻል" በማለት ስሜትን እንድንከተል ሊመሩን ይሞክራሉ። 👉አንዳንድ ሂደት ተኮር ሃሳብ ሰጪዎች ደግሞ "ፍቅር መላመድ ነው በቃግቢበትና/ግባበትና ቀስ በቀስ ትለምጂዋለሽ/ትለምደዋለህ" በማለት የተስፋ ቁማር እንድንጫወት ያነሳሱናል። 👉አንዳንድ ዘመን አመጣሽ መካሪዎች ደግሞ "ፍቅር እንደ ሙቅ ውሀ ነው ወደ አንዱ ውስጥ ትገባና ሲቀዘቅዝህ ወጥተህ ወደሌላ ትኩስ ውሀ(ፍቅር ) ውስጥ ትገባለህ እንጂ እንደ ጋለ የሚቆይ ፍቅር የለም" በማለት የእንደልብ ህይወትን ዘር ይዘሩብናል ታድያ ትክክለኛ ፍቅር ይህ ነውን?? ይቀጥላል ከተጠቀሙበት share በማድረግ አብረውን ይሁኑ 👩‍❤️‍👨 @relationship4christ 👩‍❤️‍👨 👩‍❤️‍👨 @relationship4christ 👩‍❤️‍👨
Hammasini ko'rsatish...