cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዘ ኦርቶዶስ ተዋህዶ

ንዑ ደቂቅ ወስምዑኒ ፈሪሀ እግዚአብሔር እመሀርክሙ መዝ 35

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
217
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🕯"በእንተ ጸሎት"🕯 ሀ, በጉዞ እያለህ የሕሊና ጸሎትን በመጸለይ ከአምላክህ ጋር ተነጋገር። "በማንኛውም ጉዞ ወቅት ከዳዊት መዝሙር ወይም ለአንተ የሚስማማና ሌላ ጸሎት ከመጸለይ አትቦዝን።ይህን በማድረግህ ልቡናህ ወደ እግዚአብሔር ይቀናል። "አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ ፣ የፈጸምኳቸውን ብዙ ኃጢያቶቼን አትቁጠርብኝ፤ ይቅር ባይ አምላክ ነህና ራራልኝ። ከድካሜ አበርታኝ፣ አድነኝም፣ እንደ ወደቀሁ እቀር ዘንድ አትተወኝ። ጌታዬ ሆይ በእነዚህ በተቀደሱ የጾም ዕለታት ከአንተ ጋር እንድሆን ፍቀድልኝ፣ ልቡናዬ ከአኝተ ጋር የተጣበቀ እንዲሆን ፈቃድህ ይሁንልኝ፣ ፍቅርን ስጠኝ። በረከትህንና ረድኤትህን አታጓድልብኝ፤ ዕርዳኝ፣ ለአንተ የሚስማማ ንጹህ ልቡናን ስጠኝ። ከኃጢያቴ አንጻኝ፣ እጠበኝ ፣ ከበረዶ ይልቅ እነድነጻ አድርገኝ፣ ከክፉ ሁሉ ጠብቀኝ። በምሰራው ስራ ሁሉ ከእኔ አትራቅ፤ እንደ ኃጢያቴ ብዛት እንደ ሰውነቴ ክፋት ሳይሆን እንደ አንተ አምላካዊ ምህረት ቸርነት ይደረግልኝ።" በማለት መጸለይ ያስፈልጋል። እንግዲህ በጉዞ እያለን በእነዚህና እነዚህን በመሳሰሉ ጸሎታት ልቡናችን ከመባከን ተጠብቆ ወጥቶ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት እንዳለበት ተረድቶ ከጸሎት አለመራቅ ዘወትር መጸለይ ይገባል። በቀጣይ፦ በሌሎች መካከል እያለህም መጸለይን ስለመለማመድ.....
Hammasini ko'rsatish...
🕯^ስለ ጸሎት^🕯 ^ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው^ "ጸሎት ኃጢያትን ሁሉ ጸጥ በማድረግ ክሂል ያላት፣ ከፈተናዎች የምንሻገርባት ድልድይ፣ በመከራዎች ላይ የተገነባች ቅጥር(የታጠረች አጥር)፤ ጠብን የምታርቅ ጸብአ አጋንንትን የምታበርድ፣ የቅዱሳን መላዕክት ምስጋና፣ ረቂቃን መናፍስትም የሚመገቧት ምግብ፣ የምትመጣው ኀሤት፣ የትሩፋት ሁሉ መገኛ ምንጭ፣ የጸጋ ሁሉ መፍለቂያ፤ የተሰወረች ልዕልና፣ የነፍስ ምግብ፣ የአእምሮ መብራት፣ ተስፋን የምታስተምር፣ በቀቢጸ ተስፋ ላይ የተሰነዘረች ምሳር፣ ከኀዘን መዳኛ፤ የመነኮሳት ብዕል፤ የባህታውያን ድልብ፤ የቁጣ ማብረጃ፤ ዕድገትን የምታሳይ መስተዋት፣ከፍታን የምታሳውቅ(የምትገልጥ)፣ የራስን አኳኋን የምታመለክት፤ ወደፊት የሚመጡ ነገሮች ተከስቶ፣ የክብር ምልክት።" መሆኗን ነገረን። በማስከተልም ጸሎት በእውነት ለሚጸልያት እውነትን ለያዘ ሰው፤ "ከሚመጣው ፍርድ በፊት ያለች ልዩ የፍርድ ዐደባባይ፣ የፍርድ አዳራሽ" መሆኗን ገልጿል። ተወዳጆች አንባብያን ሆይ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በወርኃ አጽዋም እንዲሁም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እና እንቅስቃሴያችን የጸሎት ሕይወትን ለማሳደግ ዓላማችንን እናሳድግ፣ካስለመድነው አንቀንስ(ኢታልምድ ወኢትክላእ)በማለት ይመክሩናል። ለአብነትም የሚከተሉትን ልምምዶች እንመልከት..... ይቀጥላል በቀጣይ፦ ሀ, በጉዞ እያለን አጭር የሕሊና ጸሎትን በመጸለይ ከአምላክህ ጋር መነጋገር...
Hammasini ko'rsatish...
#ነሐሴ ሰባት ጽንሰታ #ለማርያም_ድንግል #ጴጥርቃ እና #ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ:: ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ፡፡ ✣ ✣ ✣ #share አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን ፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ #ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ #ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ #7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ #ጨረቃዋም #ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: ✣ ✣ ✣ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ #ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ #የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡ ✣ ✣ ✣ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ #ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና #ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት #ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፤ #ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ# ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደችውን #ሃናን ወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች፡፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ #ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ #እያቄም ጋር አጋቧት:: ✣ ✣ ✣ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡- ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ✣ ✣ ✣ ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው፡፡ ✣ ✣ ✣ ሃናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: ✣ ✣ ✣ እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ ሰባት በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህ ብሎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ ዕለት #ነሐሴ_7 ቀን ተፀነሰች፡: ✣ ✣ ✣ እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች:: ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ።
Hammasini ko'rsatish...
መዋዕለ ማይ፣ መዋዕለ መብረቅ ወነጐድጓድ+ በቤተ ክርስቲያናችን አስተምሕሮ መሠረት ከሐምሌ 19 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 10 ድረስ ያለው የክረምቱ ንዑስ ክፍል "የውኃ/የባሕር የመብረቅና የነጐድጓድ ወቅት" በመባል ይታወቃል። ♥አስቀድመን ክረምቱን ስንቀበለው ❖ደምፀ እገሪሁ ለዝናም❖ "የዝናም ኮቴው(ዳናው) ተሰማ" እያልን ነበር፣የዝናም ኮቴ(ዳና) ማለትም ደመና ሲሆን ከውቅያኖስ ውኃ ተሸክሞ ወደከፍታ ወጥቶ ለምድር ዝናምን፣ጠልና ልምላሜን የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመግለፅ ነው፣ ለዚህም ነበር እስካሁን የክረምቱ የመጀመረያው ንዑስ ክፍል "መዋዕለ ደመና" ይባል የነበረው " ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና" "ሰማይን በደመና የሚሸፍነው" እንዳለ ዳዊት። ✔ ይኸውም ደግሞ ለዓለም ዓመታዊ የውኃ ክምችት ለማስቀመጥ እግዚአብሔር አስቀድሞ በወሰነው መሠረት ያለማቋረጥ የሚከናወን ተፈጥሯዊ ሂደት ነው " ጉም ከምድር ትወጣ ነበር የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር" እንዳለ ሙሴ በኦሪት ዘፍ 2:6 ። ♥ሊቃውንቱም ይህንን ሁኔታ ሲገልጡት ደመና የተፈጠረው ከይቡስ(ከደረቅ) ምድር "ይቡስ ጢስ" ፣ ከርጡብ(እርጥብ) ባህር "ርጡብ ጢስ" በማውጣት በዋዕየ ፀሐይ በማስማማት ነው ካሉ በኋላ " መገብተ ደመናት( በደመና ላይ የተሾሙ መላእክት) ደመናውን በውቅያኖስ ላይ ይዘረጋሉ፣ መገብተ ማያት( በውኃ ላይ የተሾሙ መላእክት) ውኃውን እየቀዱ በደመናው ይሞላሉ፣ መገብተ ነፋሳት( በነፋስ ላይ የተሾሙ መላእክት) ደመናውን በነፋስ ወጥረው፣አስረው ጠርቀው ወደላይ ያወጡታል በተፈለገው ሀገርና ምድርም ያዘንሙታል በማለት ያስተምራሉ። ♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲመሰክር "በተነ ጊሜ ረቂቅ ዘየዐቊሮ ለማይ ወያዐርጎ እምቀላይ ወያወርዶ እምኑኀ ሰማይ" "ስስ በሆነ ጉም ትነት(ጢስ) ውኃን የሚቋጥረው፣ከወንዝ ወደላይ የሚያወጣው፣ከሰማዩም ከፍታ ወደታች የሚያወርደው" በማለት ገልጦታል (ሰዓታት)። ♥አትናቴዎስም በቅዳሴው "ተዐቊር ማየ በከርሠ ደመና ለሲሳዩ" "ለሰው ምግብ ውኃን በደመና ማህፀን የመትቋጥር" በማለት አስተምሯል። ✔ይህ የዝናም ሂደት ሲደጋገም ወንዞች ይሞላሉ፣ባህር በውኃ ሙላት ትጨነቃለች፣ ውቅያኖስም እንዲሁ....ይህ ወቅት ነው "መዋዕለ ማይ" ተብሎ የተጠራው።።። ❖መዋዕለ መብረቅ ወነጐድጓድ:- የመብረቅና የነጐድጓድ ወቅት "መብረቅ" በረቀ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን: ብልጭ አለ፣ፈለቀ፣አንጸባረቀ፣ተወረወረ፣ተመዘዘ የሚለውን ትርጉም መደብ አድርጎ "የእሳት ሰይፍ የእሳት ፍላጻ በዝናም ጊዜ ከደመና አፎት የሚመዘዝ የሚወረወር" ማለት ነው፣ኪ. ወ . ክ። ♥የመብረቅን ተፈጥሮ በተመለከተ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንዲህ ይገልጡታል"የመብረቅ ተፈጥሮ እንደምነው ቢሉ ውኃው በደመና አይበት ተቋጥሮ፣በነፋስ ወደል ጋዝ ተጭኖ ሲወጣ ደመናና ደመና በተጋጩ ጊዜ እንደ አረቄ ከውኃ ይወጣል፣ወተት ሲገፋ ቅቤ እንዲወጣው" መዝ 134:7 አንድምታ ትርጓሜውን ተመልከት፣ ይህንን እሳቤ ሳይንሱ ኮርጆ እንዲህ ይላል"The action of warm air rising and cold air sinking plays a key role in the formation of thunderstorm" "የሞቃት አየር ወደላይ መውጣትና የቀዝቃዛ አየር ወደታች መውረድ ለመብረቅ መፈጠር ቁልፍ ሚና ይጫወታል" ይህም የኛ ሊቃውንት ቃል በቃል" ደመናና ደመና ሲጋጩ...." በማለት የገለጡት ነው!!!!!! አቤት የኛ ሊቃውንት!!!!!!!!! በረከታቸው ይደርብን አሜን!!! ♥ይህም ክሥተት እንዲፈጠር የሚያደርጉ መላእክት አሉ፣ ከነዚህም ውስጥ አንዱና ዋናው ቅዱስ ዑራኤል ነው፣ በመብረቅ በነጐድጓድና በብርሃናት ላይ የተሾመ መልአክ ነው ሔኖክ 6:1፡፡ የስሙ ትርጉምም ይህን ያመለክታል፣"ብርሃነ እግዚአብሔር" ማለት ነው፣ፍኖተ ብርሃናትን ለሔኖክ ሲያስጎበኘው የነበረውም ይህ መልአክ ነው፣ደመናት ሲጋጩ የሚወጣው መብረቅና ነጎድጓድ ሰውን እንዳይጎዳ፤ ሀገር እንዳያጠፋ የሚቆጣጠር ይህ መልአክ ነው በዚህም ምክንያት "ሰአል ለነ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ኀበ እግዚአብሔር ከመ ያዝንም ለነ ዝናመ ምህረት ...." "የምህረት ዝናም እንዲያዘንምልን ለምንልን ..." እያልን ስሙን እየጠራን በቅዱስ ዑራኤል ስም እግዚአብሔርን እንማፀናለን!!!!። ♦መብረቅ ቅዱስ ጳውሎስ ከኦሪት ወደ ወንጌል ተመልሶበታል ሐዋ 9:3 በምጽአት ጊዜ ክርስቶስ የሚገለጥበትን ሁኔታ የሚያሳይ ሆኖ ተጠቅሷል ማቴ 24:26 ♥ "ነጐድጓድ" በደመናቱ ግጭት ምክንያት የሚፈጠር ድምፅ ነው፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን መኖር፣ ጌትነቱንና ፈጣሪነቱን የሚያረጋግጡ ናቸው ሮሜ 1:21 አምላካችን ክረምቱን የተባረከ፣ዝናሙን ዝናመ ምሕረት ያድርግልን፣ በመብረቅ ጠላታችን ዲያብሎስን ያርቅልን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
🕯"ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል።" "አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ኃይል አለውና። ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።" ^መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ^ ^የበረሃ ፈርጦች^
Hammasini ko'rsatish...
🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 መምህረ ዜማ ማኅሌታይ ያሬድ 👇👇👇👇👇👇👇 ☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️ ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ገብርኤል "ሐምሌ ፲፱" የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ: በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ለዓለም ወለዓለመ ዓለም: ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል: ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል: ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ: በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት #ለቂርቆስ ሕጻን፡፡ ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ #ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ። ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡ ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት #ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። ነግሥ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ ዚቅ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። መልክአ ቂርቆስ ሰላም ለዝክረ ስምከ #ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡ ዚቅ #ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: #ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር። ወረብ "#ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን #ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ። ዚቅ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት። ወረብ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/ ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን #ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ። ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ #ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ። ዚቅ በጸሎቱ ለቅዱስ #ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡ ወረብ በጸሎቱ ለቅዱስ #ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/ ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር #ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡ ዚቅ በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: #ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡ ወረብ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/ ባርካ #ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/ መልክዐ ኢየሉጣ ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: #ኢየሉጣ ቅድስት #ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: #ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ #ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡ መልክዐ ገብርኤል ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: #ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ። ዚቅ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት። ወረብ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት #ሊቀ_መላእክት/፪/ እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/ ምልጣን ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ። አመላለስ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/ ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/ ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ እስመ ለዓለም ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ #ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡ ወረብ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/ እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/ አመላለስ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/
Hammasini ko'rsatish...
🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 🍁 መምህረ ዜማ ማኅሌታይ ያሬድ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺💐💐💐 #ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ_ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3_ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡ #በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን ("ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ እናቴ ሆይ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ "እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ..." ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤ * በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡ * ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡ * አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡ * በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው * የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡ * በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡ (ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡) ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailable
#ሐምሌ_7_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤ #ወልዱ_ለአቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ልደቱና_እረፍቱ_ነው፡፡ ዕረፍቱ የኾነው በሐምሌ 7 (6,705 ዓመተ ዓለም፥ በ2ት እንድቅትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፥ በ7ት ጥንተ ዮን፥ በወንጌላዊው ማቴዎስ ዘመን በዕለተ ረቡዕ) ነው፡፡ ያረፈውም በአፄ ይስሐቅ ጥያቄ የጋራ መናገሻ መድኀኔ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ባርኮ ሲመለስ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ሲኾን ፤ አርድዕቱ ሥጋውን ይዘው ሂደው በአባቱ መካን በደብረ ጎል (አሁን በደብረ ባሕርይ) አሳርፈውታል፡፡ ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል ከ40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤ 1. ✼ ኆኀተ ብርሃን 2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም) 3. ✼ መዝሙረ ድንግል 4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ 5. ✼ ውዳሴ መላእክት 6. ✼ ውዳሴ ነቢያት 7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት 8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት 9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን 10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን 11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር 12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት 13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን 14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ 15. ✼ መሰንቆ መዝሙር 16. ✼ እንዚራ ስብሐት 17. ✼ ውዳሴ መስቀል 18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት 19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት 20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት 21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ 22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ 23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም) 24. ✼ ውዳሴ ስብሐት 25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ 26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ 27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት 28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት) 29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ) 30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት 31. ✼ መልክአ ቊርባን 32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን 33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም 34. ✼ ክብረ ቅዱሳን
Hammasini ko'rsatish...
እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን! ==> ወበዛቲ ዕለት ሐምሌ ፭ . . . . “ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ”<== “ክበር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር፤ (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ. ፻፲፭/ ፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15) “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።”ማቴ.፲፫፡፲፩ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታቱ ለቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት ቀን በዓላቸው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ አሜን። ==> ፨ ☆♥☆♥☆♥ቅዱስ ጴጥሮስ ☆♥☆♥☆♥ ፨ ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኮኩኽ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ ስምዖን ነው። ዮሐ.፩፡፵፭ (1፥45)፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል፡፡ እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መነኸርያ በነበረችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡ ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ይተዳደር የነበረው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ነበር። ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗለ። ማቴ. ፬፡፲፱ (4፡19) ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን ዕዳ በዕዳ ከተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋያ ነውና ሮምን ደርቦ ሰርቶታል። በሮምም ፳፭ (25) አስተምሯል። ከዚያ በፊ ግን በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣በቀጳዶያና በቢታኒያ አስተምራል። በትምህርቱም ጣቢታ ከሞት አስነስቷል። ሐዋ. ፱፡፴፪-፴፬ (9፡32¬-34) ያስተማራቸው ምዕመናም ከሃማኖታቸው እንዳይወጡ ፪ (2) መዕክታትን ጽፎላቸዋል። ንጉሱ ኔሮን ቆሳር መምለኬ ጣኦት ነበርና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር። ለጣዖትም እንዲሰግድ ባስገደደው ጊዜ ለጣኦ አልሰግድም በማለቱ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት። አይሁድ ሲጣሉት ወደ ጌታ ቢያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር። ይዞ ዳግም ቢሰቅሉትም ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው። በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅሎታል። ሥጋውን ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንቦ እንዳይፈርስ በማረ በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል። ==> ፨ ☆♥☆♥☆♥ ቅዱስ ጳውሎስ ☆♥☆♥☆♥ ፨ ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖ ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል። የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ህገ ኦሪትን ተምሯል።በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19) ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ። ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ። ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ። ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። እነርሱም። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት። ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል። ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቆሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያፍም የ72 አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው። ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡
Hammasini ko'rsatish...