cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ምን የለሽ ተራ

ምንም የማታጡበት ነገር ስለፈለጋችሁት እናወራለን ግጥም አስደናቂ እውነታዎችን አዳዲስ ሙዚቃዎች ቀልዶች ወዘተ ... ይቀርብላችሆል ላሎት አስተያየትና @WhoCares2m መናገር ለምፈልጉት

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
179
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ። የማይሻረው ቃሉ በእርግጥም እውን ሆነ የማይሞተው ጌታ በሞቱ ሞትን ሻረ ልጆቹን ወዶ እራሱን ሰጠ በቀራንዮ አደባባይ ፍቅሩን ገለጠ። የበረከት፣ የእንድነትና የፍቅር በዓል ይሁንልዎ 🦋 🦋 🦋 🦋 🦋 🦋 🦋
Hammasini ko'rsatish...
እጅግ ደጋግሜ አንብቤው ሁሌም የምወደው ፅሁፍ ነው! አንብቡትማ...... 🎯🎯🎯 በአንድ ወቅት ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ በመሀላቸው ልዩ የሆነ ፍቅር ነበራቸው ሁለት ልጆችም ወልደው ነበር ። ነገር ግን ችግር ላይ በመውደቃቸው ባል ሊሰራ ተሰማምተው ራቅ ወዳለ ከተማ ሄዶ መስራት ጀመረ። በተከታታይ ለ16 ዓመታት ሰራ ከዚያ ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ሲነሳ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ ሰማ፤ደሞዙ በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው 3000 ብር ተሰጠው። የተሰጠውን ተቀብሎ እግረ መንገዱ ስራ ካገኘ እየሰራ ጠርቀም ያለ ብር ይዞ ቤተሰቦቹ ጋ ለመሄድ ተነሳ። በመንገዱ አንድ ሸምገል ያሉ አባት አገኘ... "ወዴት ትሄዳለህ ልጄ፧ ከየት ነውስ ምትመጣው?" አሉት። እሱም ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው ።እሳቸውም እንዲህ አሉት:--- "እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ቀላል ነው ፤ እሱም እንዴት አባቴ?" ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም "በል አንድ ሺህ ብሩን አምጣና እነግርሀለሁ" አሉት የቸገረው ነውና አንስቶ አንድ ሺህ ብሩን ይሰጣቸዋል። እኒህ አባትም "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" ይህ ምክር አንድ ነው ይሉታል። ሁለተኛውን ሺህ አምጣና ሁለተኛውን መንገድ ልንገርህ ይሉታል። እሱም በየዋህነት ሁለተኛውን ሺህ ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ፤ ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ምክሬ ነው" ይሉታል ። "በቃ ይሄ ነው?" ቢላቸው "አዎን ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም አሰፈላጊውና የመጨረሻውን ስጦታዬን ልስጥህ" አሉት ሰጠ። እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" ብለውት በባዶ ኪሱ ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት። እሱም ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ። በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ መሸ ነጋዴዎቹም ለምን ባቋራጭ አንሄድም በማለት ጉዞ ጀመሩ እሱም አብሮዋቸው ጉዞ እንደጀመረ የሽማግሌው አባት ምክር አንድ ትዝ አለው። "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው። ሰለዚህ ተመልሶ በሚያወቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ ከተማ ገባ ። "የመሸበት እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ" በማለት ሰው ጠየቀ። አንድ የዛ ከተማ ሰውም "የውልህ ወንድሜ እዛ ቤት ሂድ ያሳድርሀል፤ ነግር ግን እዛ ሰው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም እድልህን ሞክር።" እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት የእንግዳ ነው ተብሎ ገባ ። ታድያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረው ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴት ሆነክ ተረፍክ ፧ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴች ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው ከተማው ለቅሶ ብቻ እኮ ነው የሆነው" አለው። ያቺ በአንድ ሺህ ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛ ህይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው። ሰለ መሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብ ከጓዳ ብቅ አለች " እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም የተወሰነ አካሉዋ ብቻ ነው ሰው የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ እስክትገባ ናፈቀ። "ከዚህች ጋር እንዴት ትኖራለህ?" ብሎ ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው "በማያገባህ አትግባ" የሚለው ። ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን ተቋቁሞ አደረ። ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም የሞላበት ሜዳ አሳየው እንግዳውም "ይሄ ምንድ ነው?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን እየነቀነቀ ዝም አለ ። የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ "በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ፤ ይህ የምታየው ሰው ሁሉ ሰለ ሚስቴ የማያገባቸውን አሰተያየት ሰለሰጡ የተገደሉ ናቸው፤ እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድነት የመጡ ነበሩ። አንተ ግን ታላቅ ሰው ስለሆንክ የሀብቴን 1/4 ኛ ሰጥቼሀለሁና ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ። እዛች ደሳሳ ጎጆ የደረሰው ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር። ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን አላጣውም በትልቅ እንጨት የምትዘጋ በሩን ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች። አይኑ ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች በንዴት ጦፎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል 3ተኛው ምክር ትዝ አለው። "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው። ከቤቱ ውጭ በተጋደመው ዛፍ ላይ ቁጭ ብሎ አደረ። ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን ስታየው እልልታዋን አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት። ከእንቅልፉ የነቃው ባል በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀችው "ይህ የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ ሁለተኛው" ብላ እንግዲህ የመጨረሻው ምክር የልጆቹን ነፍስ ከማጥፋት እረዳው ማለት ነው። ሰውዬው ሶስቱ የሽማግሌው አባት ምክሮች በደስታ ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል አደረጉት። ✅ አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ ✅ በማያገባህ አትግባ ✅ ክፉ ለማድረግ አትቸኩል
Hammasini ko'rsatish...
ስዕል ና ግጥም ቦርጨቅ ህልሙን የሚተ'ልም በተወጠረ ጨርቅ ተስፋውን ሲለቁጥ በቀለም ሽንቁጥጥቁጥ የቀለም ጠብታ ከብሩሽ ተስማምታ ወደ እግዜሩ መሩት እግዜሩንም ሳሉት በርግጥም ሰዐሊው እግዜርን ያላየ በምስሉ ሸራ ላይ እንዴት ተነበየ? ቢጠየቅ ሰዓሊው ሰይጣኑንም ሲስል ቀለሙን ቀልሞ ጨለማ ሊያስመስል በብሩሹ ነክሮ ከል አከናነበው ፅልመትን አልብሶ ብርሀን ነፈገው እኮ እንዴት? ያልታየ እንደ እውነት ቢጠየቅ ሰዓሊው ሰዓሊው ዝም! ነው ዝምታው ሰሙ ነው ወርቁ ስዕሉ ነው በተድፋፋ ቀለም እውነት ለመቃረም ቃላት በአፍ ሊያልፉ እንዳሰፈሰፉ በምስል ሸራ ላይ ዝምብለው ረገፉ ዝምታ ሲበዛ ጥያቄን ይጭራል ምስሉም ይናገራል በስዕሉ በኩል በግልፅ የምናየው እግዜዜሩና ሰይጣን ሲፎካከሩ ነው ከዚ እይታ ውጪ በአትኩሮት ብናየው ለኛ የማይታየን ቀርቦ የተሸሸገን ሰዓሊውስ ማነው? ስለማንነቱ ቢጠየቅ ሰዓሊው ሰዓሊው ዝም! ነው ዝምታው ሰሙ ነው ወርቁ ስዕሉ ነው ሱራፌል ጌትነት 🦋ሱራ ቢራቢሮ🦋 🅢ስውር ገፅ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
Hammasini ko'rsatish...
እዚ ግሩፕ ላይ ያላቸው Leave the ቻናል
Hammasini ko'rsatish...
Hiiiiiiii
Hammasini ko'rsatish...
~~~~ ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፣ ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት። አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ፣ እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ። ገንዘብ መፈጠሩ ለሰው አገልጋይ፣ ሆኖ ሊሰራበት አልነበረም ወይ። አሁን ግን መስገብገብ በጣም ስለበዛ፣ ሰው ባሪያ እየሆነ ለገንዘብ ተገዛ። የሐሰት ወገኖች ተመቸን እያሉ፣ ብዙ ጊዜ አድመው እየተማማሉ። እውነትን ከአለም ላይ ሊያጠፏት ተነሱ፣ እውነት ግን ሁልጊዜ መክታ ለነሱ፤ ታግላ እያሸነፈች ስትኖር ረግታ፣ ጠላቶችዋ ሁሉ በሷ ጥፋት ፈንታ፤ አንድ ባንድ ወድቀው እየተሰበሩ፣ ከስማቸው ጋራ ሁሉም ጠፍተው ቀሩ። ባለም ላይ ተሰርቶ በብዙ ጥበብ፣ ማዕርግ የሚባለው የደረጃ ግንብ። በዚህ በሚያዳግት ባቀበት መንገድ፣ ግማሹ ሲወጣ ግማሹ ሲወርድ። ከወደዳር ቆሞ ማስተዋሉን ሳይተው፣ ምንኛ ደስ ይላል ለተመለከተው። ብልኅ አስተዋይ ሰው 'ያለምን ነገር፣ ዘልቆና ጠንቅቆ የሚመራመር፣ ትልቅ ቁም ነገር ነው ረቂቅ ምስጢር። ✨Join & Share✨ ❣❣❣❣ ❣❣
Hammasini ko'rsatish...
አለም የተፈጠረቹ ዩንቨረስቲ በገቡ ሰዎች ሳይሆን ደደብ ተብለው ከትምህርት ቤት በተባረሩ ሰዎች ነው። ዛሬ ዩንቨረስቲ አለመግባትክ ከአላማክ ሊያደናቅፍክ አይችልም!!! የአንፖል ፈጣሪው ወይም የአለም ብርሃን በሚል የሚታወቀው ቶማስ ኤደሰን ደደብ ነክ ተብሎ ከትምህርት ቤት ተባሯል ነገረ ግን እራስኑ አስተምሮ ከራሱ ተርፎ ለአለም ብረሃን መሆነ ችሏል። አልበረት አንስታይን በአሁኑ ዘመን ብዙ ተማሪዎች ከስራ ማጣት ጋር በተያያዘ የሚጠሉትን የኢንጅነሪንግ ትምህርት እንኳን ዩንቨርስቲ ገብቶ እንዳይማር ተደርጓል ነገረ ግን እራሱን አስተምሮ ዩንቨርስቲ ውስጥ ለማስተማር በቅቷል ብዙ ምርምሮችንም አድርጎ ከራሱ አልፎ ለአለም ሕዝብ በቅቷል። በአጠቃላይ አለማችን ዲዛይን የተደረገቹ እራሳቸውን በራሳቸው ባስተማሩ ሳይንቲስቶች ነው ሰለዚህ ሁሌም ቢሆን እራሳችንን ከማስተማር ወደዋላ ማለት የለብንም። ገንዘብ ለመያዝ ዩንቨርስቲ መግባት እና በማረግ መመረቅ አይጠበቅብክም ወይም ድግሪ መያዝ አይጠበቅብክም ቢሌነር ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዱ ቢልጌት ሲሆን የዩንቨረስቲ ተምህርቱን እንኳን በቅጡ ያልጨረሰ ግለሰብ ነው ይሁን እንጂ ገንዘብ ለማግኘት አላገደውም በወቅቱ እሱ ጋር ሲማር የነበረው ሰቃይ ተማሪ ግን የሱ ድርጅት በሆነው ማይክሮሶፍት ውስጥ ተቀጥሮ እየሰራ ነው። ትምህርት አልተሳካልኝም እና ነገሮች ተበላሽተዋል ብላቹ ተስፍ አትቁረጡ!!! ትምህርት ተምረክ እንደጨረሰክ የመንግስት ቅጥረኛ ለመሆን ብቻ አትጣደፈ ወይም የመንግስት ሰራተኛ የመሆን ህልም ብቻ አይኑርክ ባይሳካ እንኳን ትልቅ ህልም ይኑርክ!!!
Hammasini ko'rsatish...
ስፈራው የኖርኩት ቢመጣብኝ ድንገት (2) ያልከኝን በማመን ከህመሜ ስድን... (ከህመሜ ስድን) የተዘጋው ልቤ ሲጀምር መከፈት...(ሲጀምር መከፈት) እኔ ነኝ ያልከኝ ሰው ለካስ ነበር ውሸት..(ለካስ ነበር) ውሸት...........🥺💔💔💔 ያ ሁሉ ነገር ውሸት ነበር ግን ለምን አስፈላጊ ነበር💔💔❤️‍🔥🖤🖤🖤 @Infinitkidu
Hammasini ko'rsatish...