cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ብራና ብዕሮቹ👈

Like me they can and i can like them this is our thinking can u follow with. For any coment & you want to post send by this @zedomina Just do it

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
169
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Join 👇👇👇 @wiz_mardi
Hammasini ko'rsatish...
ወጣ ወጣ ስትል ክፉ ምች መቷት፣ ተቸግሬያለሁኝ ያችን ልጅ አሟት፡፡ Ethiopian የአማርኛ ቅኔዎች Poetry- Application https://play.google.com/store/apps/developer?id=Oromnet+Software+and+Application+Development+PLC
Hammasini ko'rsatish...
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence) 👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው። ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ። 1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)። የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ። 2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)። አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ። 3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)። በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል። 4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial) ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ። 5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude) ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል። 6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)። ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ። 7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row) ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ። 8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up) በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል። 9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out) ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ። 10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution) ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ። የፍቅር_ሳይኮሎጂ #በቅንነት ሼር @bierochu
Hammasini ko'rsatish...
⏳ለአዕምሮአችን⌛️ መቀላጠፍ ና ጤንነት የሚረዱ 10ነጥቦች !!!! 1. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው ። በቫይረስ መጠቃት የለበትም ። ሁልጊዜ ሊጸዳ ይገባዋል፡፡ አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ - በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡ 2. አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል ። ያስወግዷቸው፡፡ 3. አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡ 4. አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡ 5. ጥሩ ምግቦች አእምሮ ስል እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ የአሳ ዘይትና ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በቀን በቀን ካገኘ ሥራ ማቀላጠፍ ያውቅበታል፡፡ በቂ ውኃ መጠጣት ለአእምሮ እንደ ግሪስ ያገለግላል፡፡ 6. አእምሮ በቫይረስ ይጠቃል፡፡ የአእምሮ ቫይረስ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? አሉታዊ አስተሳሰቦች፡፡ ምቀኝነት፣ ክፋት ማሰብ፣ በማይረቡ ነገሮች መጨነቅ አእምሮን ያውካሉ፡፡ ይህን ቫይረስ ለማጽዳት መልካም መልካሙን ማሰብ ብቻ ይበቃል፡፡ 7. ቁርስ አይዝለሉ፡፡ መኪናዎ ማለዳ ተነስተው እንደሚያሞቋት ሁሉ አእምሮዎንም በአሪፍ ቁርስ ያነቃቁት፡፡ ቀኑን ሙሉ በንቃት እንዲሰራ ጥሩ ቁርስ ያስፈልገዋል፡፡ 8. ተሸፋፍነው አይተኙ፡፡ አእምሮ እጅግ ብዙ መጠን ያለው ኦክሲጂን የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ሲታፈን ግራ ይገባዋል፡፡ መኪና የሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ ኢንደስተሪዎች፣ ብዙ ሲጋራ የሚጨስባቸው አካባቢዎችን ያስወግዱ፡፡ በተቃራኒው መናፈሻ፣ አረንጓዴ ተክሎች የሚበዙባቸው ሜዳማ ስፍራዎች የእግር ጉዞ ቢያደርጉ አእምሮ በጣም ያመሰግንዎታል፡፡ 9. የከሰል ጭስ ለአእምሮ መርዝ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ቤታቸውን በእጣንና በከሰል ጭስ ያፍናሉ፡፡ በነጋታው ኃይለኛ ራስ ምታት ያማቸዋል፡፡የከሰል ጭስ አእምሮን ሊገድለው ይችላልና ይጠንቀቁ፡፡ 10. ለእርስዎ የማያስደስትዎትን ነገር ለሰው ሲሉ ብቻ አያድርጉ፡፡ የማያምኑበትን ነገር በፍጹም አይተግብሩ፡፡ ወደፊት ለጸጸት የሚዳርግዎትን መልካም ያልሆነ ተግባር በድብቅም ቢሆን አይስሩ፡፡ ፀፀትና የሕሊና ወቀሳ ለአእምሮ መርዛማ ነገሮች ናቸው፡፡ ሙሰና፣ ከትዳርዎ ውጭ መማገጥ፣ በሰው ላይ ተንኮልና ሴራ መፈፀም አእምሮን እስር ቤት ውስጥ ማጎር ማለት ነው፡፡ አእምሮ ሰላሙን አጥቶ ሰላምዎን እንዳይነሳዎ መልካም መልካሙን ብቻ ያድርጉ፡፡ 11. መልካም ምክር ለክፉ ጊዜ ስንቅ ነው፡፡ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉት የበለጠ ሰዎች እንዲወድዎት ያደርጋል፡፡ እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን! ምስጋናችን ከልብ ነው! 👇👇👇👇👇👇👇👇 @bierochu
Hammasini ko'rsatish...
ሊለዩን ላሰቡት ለጣሩ በብርቱ ሲሆን አየሁና ልፋታቸው ከንቱ ልፉ ቢላችሁ ነው አልኳቸው በልቤ የፍቅራችን ጽናት መቶብኝ ካሳቤ @aratmetofkr
Hammasini ko'rsatish...
💨ቅብጥብጡ ውሻ ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ 🔆የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡ 🔆በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡ 💨የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡ 🔆የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡ 💨ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡ ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . . 🔆ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ 💨ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! 🔆ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው! 💨🔆💨🔆💨🔆🌊🔆📒💨📔💨🔆bierochu birana
Hammasini ko'rsatish...
Wow 😍😍😍😍😘😘❤️
Hammasini ko'rsatish...
አንድን አባት ሰዎች መጡና " ዘውትር ጸሎት በማድረግህ በሕይወትህ የጨመረልህን ነገር ንገረን?" አሉት፡፡ እርሱ ግን "ጸሎት በማድረጌ ከጨመርኩት ይልቅ የቀነስሁት ይበዛልና እርሱን ልንገራችሁ፡፡ ጸሎት በማድረጌ ከሕይወቴ ውስጥ ጭንቀት ፍርሃት ተስፋ መቁረጥና ቁጥነት ቀንሻለሁ አላቸው፡፡ ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ @bierochu
Hammasini ko'rsatish...