uz
Feedback
ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

Kanalga Telegram’da o‘tish

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  analitikasi

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  (@computer_android_tricks) kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 11 983 obunachidan iborat bo'lib, Taʼlim toifasida 17 269-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 838-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 11 983 obunachiga ega bo‘ldi.

04 Mart, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -107 ga, so‘nggi 24 soatda esa 0 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 0% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining N/A% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 0 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 0 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 0 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 05 Mart, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Taʼlim toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

11 983
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-337 kunlar
-10730 kunlar
Postlar arxiv
#𝐓𝐞𝐜𝐡🌍𝐙𝐨𝐧𝐞ᴱᵗʰ_News 📌የኮምፒውተር ተህዋስ [ማልዌር] የተገጠመላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቻይና ስሪት የሆኑ ስልኮች📲 አፍሪካ ውስጥ መቸብቸባቸው ተሰምቷል። 📲አፕስትሪም የተሰኘ አንድ ተቋም ነው ይህን ይፋ ያደረገው። ቢያንስ በ53 ሺህ ይህ ተህዋስ የተገጠመላቸው የቴክኖ ስልኮች ኢትዮጵያ፣ ካሜሩን፣ ግብፅ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መሸጣቸው ተነግሯል። 📲የስልኮቹ አምራች የሆነው ትራንዚሽን የተሰኘ ኩባንያ ተህዋሱ የተገጠመው ከእኔ እውቅና ውጪ በአከፋፋዮች ነው ይላል። አፕስትሪም የተሰኘው የመሰል ተህዋሶች አጋላጭ ድርጅት በዚህ አይስማማም። 📲"ይህ ማልዌር [የኮምፒውተር ተህዋስ] ሚሊዮኖችና ገቢያቸው አናሳ የሆኑ ሰዎች በሚገዙት ስልክ ላይ መሰል ተህዋስ ያለ ተጠቃሚዎች መገጠሙ ኢንዱስትሪው ምን ያክል የሰዎችን ግላዊነት እየተጋፋ እንዳለ የሚያሳይ ነው" ይላሉ የአፕስትሪም ባለሙያ የሆኑት ጄፍሪ ክሊቭስ። 📲'ትሪያዳ' የተሰኘው ተህዋስ አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የሚገጠም ሲሆን 'ኤክስሄልፐር' የተባለ ኮድ ተጠቅሞ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ ያሻውን የሚያደርግ ነው። የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው ሞና ሊሳ "ነፍስ ዘራች" 📲ይህ ማልዌር ብዙ ጊዜ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የሚቀላቀል ነው። ይህ ተህዋስ ሞባይል ስልክዎ ላይ ያለዎትን ገንዘብ [የአየር ሰዓት] ያለ ፈቃድዎ የሚወስድ ነው። 📲በርካታ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የበይነ መረብ ክፍያ የሚፈፀመው በአየር ሰዓት ነው። 📲አፕስትሪም የተሰኘው ተቋም ቢያንስ 200 ሺህ ስልኮች ያለፈቃዳቸው 'ሰብስክራይብ' ካደረጓቸው አገልግሎቶች እንዲወጡ አድርጓል። 📲ትራንዚሽን ሆልዲንግስ የተሰኘው ተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ኩባንያ ቻይና ውስጥ ካሉ ግዙፍ ኩባንያዎች አንዱ ሲሆን አፍሪካ የምርቶቹ ቁጥር አንድ ገዢ ናት። 📲ቴክኖ፤ ችግሩ ያረጀና ያፈጀ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ቀርፌዋለሁ ይላል። ለቢቢሲ ጉዳዩን የተመለከተ የጽሑፍ መግለጫ የላከው ድርጅቱ፤ "ቴክኖ ደብለዩ2 ስልኮች ያላቸው ሰዎች መሰል ችግር እንዳያጋጥማቸው መጫን የሚችሉት መተግበሪያ [አፕሊኬሽን] አለ። ወደ ቴክኖ ሱቆች መጥተው እርዳታ መጠየቅም ይችላሉ" ይላል። 📲ከወራት በፊት አንድ ሌላ ድርጅት ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ዩኤምኤክስ የተሰኙ የቻይና ምርት የሆኑ ስልኮች ላይ ማግኘቱ አይዘነጋም። ይህ ስልክ አሜሪካ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች በመንግሥት መከፋፈሉ ይታወሳሉ። 📲በፈረንጆቹ 2016 ራያን ጆንሰን የተሰኙ ተመራማሪ 700 ሚሊዮን አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ማልዌር እንደተገጠመባቸው ይፋ አድርጎ ነበር። 📲ማልዌር ማለት ስልኮችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ የሚገጠመው ተህዋስ ሲሆን መረጃ ከመመዝበር አልፎ ስልኮችንና ኮምፒውተሮች ከጥቅም ውጪ❌ ሊያደርግ ይችላል። ©ethio tech ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ ‼️እስካሁን የተማማርናቸውን ትምህርቶች እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን በ video ለማግኘት የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ። ✅ Subscribe Our youtube Channel 👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

ሰላም ውድ የ Tech🌍Zoneᴱᵗʰ ቤተሰቦች ዛሬ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ድረገፆችን (Websites) እንጠቁማቹ። 🔺 የትምህርታዊ ድረገፆች ◽️ www.khanacademy.org ◽️ www.academicearths.org ◽️ www.coursera.com ◽️ www.edx.org ◽️ www.open2study.com ◽️ www.academicjournals.org ◽️ codeacademy.org 🔺የመፀሀፍት ድረገፆች ◽️ www.bookboon.com ◽️ http://ebookee.org ◽️ http://sharebookfree.com ◽️ http://m.freebooks.com ◽️ www.obooko.com ◽️ www.manybooks.net ◽️ www.epubbud.com ◽️ www.bookyards.com ◽️ www.getfreeebooks.com ◽️ freecomputerbooks.com ◽️ www.essays.se ◽️ www.sparknotes.com ◽️ www.pink.monkey.com 🔺Online ትምህርታዊ ድጋፎች ◽️ www.ocwconsortium.org ◽️ www.ocwconsortium.org ◽️ http://ocw.tufts.edu ◽️ http://ocw.upm.es ◽️ http://www.open.edu ◽️ http://ocw.usu.edu/ ◽️ http://open.umich.edu/ ◽️ http://ocw.nd.edu/ 🔺የጥያቄዎች ምላሽ ◽ www.ehow.com ◽ www.whatis.com ◽ www.howstuffwork.com ◽ www.webopedia.com ◽ www.plagtracker.com ◽ www.answers.com 🔺መፈለጊያ (Search) ድረገፆች ◽ www.about.com ◽ www.alltheweb.com ◽ www.altavista.com ◽ www.askjeeves.com ◽ www.excite.com ◽ www.hotbot.com ◽ www.looksmart.com ◽ www.lycos.com ◽ www.dmoz.org ◽ www.google.com ◽ www.mamma.com ◽ www.webcrawler.com ◽ www.aol.com ◽ www.dogpile.com ◽ www.10pht.com 🔺የአፋልጉኝ ድረገፆች ◽ www.anywho.com ◽ www.infospace.com ◽ www.switchboard.com ◽ www.whitepages.com ◽ www.whowhere.lycos.com 🔺የዜና ድረገፆች ◽ www.abcnews.com ◽ www.cbsnews.com ◽ www.cnn.com ◽ www.foxnews.com ◽ www.msnbc.com ◽ www.nytimes.com ◽ www.usatoday.com 🔺ስፖርታዊ መረጃዎች ◽ www.sportsmangist.com ◽ www.sportsline.com ◽ sportsillustrated.com ◽ espn.go.com ◽ foxsports.lycos.com ◽ www.nbcsports.com ◽ www.sportingnews.com 🔺የህክምና ትምህርቶች ◽ www.healthatoz.com ◽ www.kidsdoctor.com ◽ www.medexplorer.com ◽ www.medicinenet.com ◽ www.nlm.nih.gov ◽ www.planetwellness.com ◽ my.webmd.com 🔺ጋዜጦች ◽ www.indexcopernicus.com ◽ www.ajol.info ◽ www.doaj.org ◽️ www.sabinet.co.za ◽️ www.oajse.com ◽️ www.lub.lu.se/en.html ◽️ www.copernicus.org 💠Best websites for games and softwares 📌 PC GAMES 🔰http://oceanofgames.com/ 🔰http://www.ovagames.com/ 🔰http://fitgirl-repacks.site/ 🔰http://skidrowgamez.net/ 🔰http://full-pcgames.com/ 🔰http://www.xfullgames.com/ 🔰http://www.newgamesbox.com/ 🔰http://www.y8.com/ 📌 SOFTWARES 🔰http://getintopc.com/ 🔰https://fullstuff.co/ 🔰http://www.piratecity.net/ 🔰http://gigahax.com/en/ 🔰http://karanpc.com/ 🔰http://www.mixhax.com/ 🔰http://www.novahax.com/ 🔰http://full-pcsoftware.com/ 🔰http://dl.par30dl.com/Software/ 🔰http://s0ft4pc.com/ 🔰http://filehippo.com/ 🔰http://www.fileeagle.com/ 🔰http://softfunda.com/ 🔰https://www.freewaresys.com/ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ ✅ Subscribe Our youtube Channel 👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

የኢትዮ ቴሌኮም ቅናሽ! ' ኢትዮ ቴሌኮም ' የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 35 በመቶ ቅናሽ አደረገ፤ እንዲሁም በቤትዎ ይቆዮ የጥቅል አገልግሎት 59 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አዲስ ማለዳ ጋዜ
የኢትዮ ቴሌኮም ቅናሽ! ' ኢትዮ ቴሌኮም ' የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 35 በመቶ ቅናሽ አደረገ፤ እንዲሁም በቤትዎ ይቆዮ የጥቅል አገልግሎት 59 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል። የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይም የ29 በመቶ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን አገልግሎቱም ከነገ ነሐሴ 21/2012 ጀምሮ በስራ ላይ ይውላል። በተጨማሪ እስከ 11 የሚደርሱ ሀገራት ላይ የውጭ ጥሪ አገልግሎት 50 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ታውቋል። ከውጭ አለም አቀፍ ጥሪ ለሚቀበሉ ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ስጦታ ይበረከትላቸዋል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም በ11 የውጭ ሀገራት የድምፅ ጥቅል ላይ የታሪፍ ቅናሽ አድርጓል! ወደ አሜሪካ ፣ ብሪታንያ ፣ ካናዳ ፣ ጀርመን ፣ ሳኡዲ አረቢያ ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ ኬንያ ፣ ህንድ ፣ ቻይና ፣ ደቡብ አፍሪካ እና አውስትራሊያ በሚደረጉ ጥሪዎች ላይ ቅናሽ ተደርጓል። በዚህም መሰረት በ59 ብር 10 ደቂቃ ፣ በ100 ብር 20 ደቂቃ እንዲሁም በ195 ብር 50 ደቂቃ እንዲሆን ተደርጓል። ከላይ የተጠቀሰውን መጠን ከነገ ነሐሴ 21 ጀምሮ #ፓኬጅ በመሙላት መጠቀም እንደሚችል ከአል አይን (Al Ain) ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። የኢትዮ ቴሌኮም የምስጋና ስጦታ! ኢትዮ ቴሌኮም ከነገ ሐሙስ ነሐሴ 21/2012 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ የምስጋና ስጦታ ማዘጋጀቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋል። የድርጅቱ ደንበኞች 1 GB የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ፣ 40 ደቂቃ ድምጽ አገልግሎት ፣ 100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት በነጻ እንደሚያገኙ መገለፁን ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ ተወስኖ የቆየውን የ4G / LTE አገልግሎት በክልል ከተሞች ለመጀመር ማቀዱን ይፋ አድርጓል

ስለ ስልክ ቫይረስ ምን ያህል ያቃሉ ▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁ What is Virus ?? #Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ ➲Spyware Virus ➲Malware Virus ➲Ransonware Virus ➲Adware Virus ➲Trojan Horse Virus ናቸው እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው ⓵ ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው ⓶ በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File) ለምሳሌ Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ ⓷ ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው ⓸ ስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል ይህ ማለት እኛ ስልኩን ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል ⓹ Software File ማጥፋት የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ => Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል. ስለ #ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናያለን እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን ⓵ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ ለምሳሌ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time #ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል ለምን ቢባል Fake የሆኑ #ድረገጾች ላይ #ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል ⓶ Bluetooth Email እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን በኋላ መዘጋቱን #Check Up ማድረግ ⓷ የስልካችንን #Software Update ማድረግ በሰአቱ እና በግዜ ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን #ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ #Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ #About Phone የሚል አለ እሱን እንዴ #Click እንላለን ከዛ Software Update የሚለውን #Click ማለት ⓸ ትክክለኛ እና #Original Antivirus መጠቀም ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File #Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት #Remove ማድረግ እነዚህን Original Antivirus ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ ➷➷➷➷➷➷ ➊ #Norton Antivirus ➋ #KasperskyAntiVirus ➌ #BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection ⓹ ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ #Email ለምሳሌ በ #G -mail ነው Email ለምሳሌ በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች #Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ #Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም ⓺ ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application # Update ማድረግ ለምን ቢባል አንዳንድ Applicationኖች ከ ቆይታ ብዛት የተነሳ ወደ ቫይረስ ይቀየራሉ ስለዚህ ሁሉኑም Application በየጊዜው Update ማድረግ አለብን ስልካችን ላይ ያሉ Applicationኖችን Update ለማድረግ መጀመሪያ ወደ PlayStore ላይ እንገባለን ከዛ (My APP) ዉስጥ እንገባለን ከዛ Update መሆን ያለበት Application ካለ እራሱ ይህን Application Update አድርግ ብሎ ይጠቁመናል ከዛ Update የሚለውን #Click ማድረግ ⓻ Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል (Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ? Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው #ቫይረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ስለዚህ ማንኛውንም Notification ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን ⓼ ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል © GSM X Team ▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁ ❖‼️እስካሁን የተማማርናቸውን ትምህርቶች እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ። ✅ Subscribe Our youtube Channel 👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

የቲክቶክ እገዳ ************ ትራምፕ ቻይና የአሜሪካንን የመንግስት ተቋማቶች እና የሰራተኞችን አጠቃላይ ሁኔታ ለመሰለል እየተጠቀመችበት በመሆኑ ቲክቶክ የተሰኘው አፕ ይታገድልኝ ማለታቸው የዓለ
የቲክቶክ እገዳ ************ ትራምፕ ቻይና የአሜሪካንን የመንግስት ተቋማቶች እና የሰራተኞችን አጠቃላይ ሁኔታ ለመሰለል እየተጠቀመችበት በመሆኑ ቲክቶክ የተሰኘው አፕ ይታገድልኝ ማለታቸው የዓለም አነጋጋሪ ዜኖ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ ትናንት ቢቢሲ ባወጣው ዜና ደግሞ የቻይናው የቴክቶክ ካማፓኒ ከእውነታ በራቀ ውንጀላ ስማችን እየጠፋ በመሆኑ ይህንን ጉዳይ በህግ እንዲታይልን ከማድረግ ውጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለንም ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ByteDance የተሰኘው የቻይና የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ስህተት ነው ብሎ ቢቃወምም የዋሺንግተን አመራሮች ይህ መተግበሪያ የአሜሪካውያንን መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ እየሰጠ ነው ሲሉ አምርረው መናገራቸውን አላቆሙም፡፡ 80ሚሊዮን የሚሆኑ አሜካዊያንን ቲክቶክ የተሰኘውን መተግበሪያ የሚጠቀሙ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን በዚህ ወር ውስጥ ብቻ ከቢሊዮን በላይ ቪዲዮዎች ወርደዋል፡፡ መተግበሪያው ከዳንስ እስከ አጫጭር የፖለቲካ ንግግሮች ተቀርፀው የሚተላለፉበት ሲሆን ለብዙሀን አስገራሚ የሆነው ደግሞ ተጠቃሚዎቹ አብዛኞቹ ታዳጊያን መሆናቸው ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ከአሜሪካን ውጭ ህንድ መተግበሪያውን ያገደች ሲሆን አውስትራሊያም በቀጣይ ቀናት ውስጥ እርምጃ እንደምትወስድ እየተነገረ ነው፡፡ በተለይም በዚህ ወረርሽኝ አማካኝነነት ሊገን የቻለው ይህ ቲክቶክ የተሰኘው መተግበሪያ አሁንም ሰዎች በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሁነው ባሉበት ወቅት ላይ ቢዘጋ ብዙ ሰዎች ላይ መደናገጥን ያስከትላል ሲሉ የቲክቶክ ካምፓኒ የህግ ባለሞያ መከራከሪያ ነጥባቸውን ለቢቢሲ ማቅረባቸው ተዘግቧል፡፡ ምንጭ፡ ቢቢሲ ✅ Subscribe Our youtube Channel 👇👇 https://youtu.be/rjsfMBVERmk

📌ብዙ ጊዜ ትላልቅ ሶፍቴሮችን ዳውንሎድ ለማድረግ እና አክትቬት ለማድረግ ብዙ ሰዎች ያሸግራቸዋል። 📌ለምሳሌ:- የትኛውንም Engineering Sofware እንዴት አድርገን Download በማድረግ
📌ብዙ ጊዜ ትላልቅ ሶፍቴሮችን ዳውንሎድ ለማድረግ እና አክትቬት ለማድረግ ብዙ ሰዎች ያሸግራቸዋል። 📌ለምሳሌ:- የትኛውንም Engineering Sofware እንዴት አድርገን Download በማድረግ Activate ማድረግ እንችላለን? 📌በዛሬው የ"Youtube" ቪዶችን AutoCAD Architecture 2020 እንዴት Download አድርገን Activate ማድረግ እንደምንችል ለቅቄላችኋለው። ‼️እስካሁን የተማማርናቸውን ትምህርቶች እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ። ✅ Subscribe Our youtube Channel 👇👇 https://youtu.be/rjsfMBVERmk

❖Android መተግበሪያ ለማበልጸግ መሰረታዊ መያዝ ያለባቸው ነገሮች(ለጀማሪዎች) ▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁ 💠 ቋንቋ መማር Java እና XML ሁለቱም ለ #Android መተግበሪያ ወሳኝ ቋንቋዎች ናቸው። ስለዝህም የነዚህ ቋንቋ እውቀት የ #Android መተግበሪያ ለማበልጸግ የሚያስፈልጉህ ቅደመ ሁኔታዎች ናቸው። በ Java ላይ መሰረታዊ ማወቅ ከሚገባህ ነገሮች ውስጥ: 💎Packages 💎Objects & classes 💎Inheritance & interfaces 💎Strings & numbers,generics, 💎Collections 💎Concurrency ❖በ Java እና በ XML ላይ ጥሩ ግንዛቤ ከያስክ አሪፍ መተግበሪያ በመጨረሻም ታበለጽጋለህ። 💠 መተግበሪያውን እንድታበለጽግ ከሚረዱህ ቱሎች ጋር መግባባት ከነዚህ ቱሎች(IDE) ጋር ነገረ ስራቸውን ማወቅ ባጣም ጠቃሚ ነገር ነው ፣ ይህም በፍጥነት መተግበሪያውን እንድታበለጽግ ይረድሃል። ከነዚህም ቱሎች መሃል Android Studio IDE አንዱ ነው። 💠 የመተግበሪያውን ምስረታ ክፍፍል ላይ እውቀት መያዝ (Application Components) የመተግበሪያው ኮምፖነንት መተግበሪያው መተግበሪያ ሆኖ እንዲወጣ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ፣ በሌላ አማርኛ እነዚህ ኮምፖነንቶች የመተግበሪያው ገንቢ አካል ናቸው። እያንዳንዳቸው ኮሜፐነንቶች የየራሳቸው ሚና አላቸው፣ አንዳንዶቹ በሌላ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። እነዝህም ኮምፖነንቶች: 💎 Activities ባጭሩ, የመተግበሪ የስክሪን ገጽ እንደማለት ነው፣ የተወሰነ ስራ/ተግባር የሚፈጽም። ለምሳሌ የቴሌግራም መተግበሪያ ሲጫን የሚመጣው "እንኳን ደህና መጣህ" አንድ Activity ሲሆን ቁጥር አስገብተህ የምትመዘገብበት ደሞ ሌላ Activity ነው። 💎 Services ይህ ደሞ ከዃላ ሆኖ የሚሰራ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ረጅም ሰዓት የሚወሰድ ተግባር ላይ ተመራጭ ናቸው። ምሳሌ: ሙዚቃ እያዳመጥክ ቴሌግራም ስትጠቀም ወይም ሌላ ነገር ስትጠቀም ፣ መዚቃው ግን ከዃላ መጫወቱን ቀጥሏል፣ ይህ የ Service አንዱ ምሳሌ ነው። 💎 Content providers ይህ ደሞ አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ ቋት ላይ ትክረቱን ያደርጋል, ዳታውን በተለያዩ ፎርማት ይቀመጣል: በፋይል ሲስተም, ድህረገጽ ላይ, በ SQLite የመረጃ ቋጥ ላይ። 💎 Broadcast receivers ይህ ኮምፖነንት ደሞ በመተግበሪያህ ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሁን በስልክህ ሲስተም ጭምር ነው የሚከታተለው። ምንም የሚታይ ገጽታ የለውም። መተግበሪያውን ዘግተ ወተህ ግን ከመተግበሪያው notification ሲደርስህ ይህ አንዱ የዚህ ተጽዕኖ ነው። ይህ ኮምፖነንት ለሌላ ኮምፖነንት እንደ መግቢያ በር ሆኖ ያገለግላል። 💎 Activating components 💠 በ Threads, Loaders እና Tasks ላይ ጥሩ ግንዛቤ መያዝ ያስፈልጋል። ▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁ ❖‼️እስካሁን የተማማርናቸውን ትምህርቶች እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ። ✅ Subscribe Our youtube Channel 👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

በሞባይል ስልካችን ከ2 እስከ 5 ከሚደርሱ ሰዎች ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ጥሪ ማድረግ እንደሚቻል ታቃላችሁ⁉️ ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ ❖ አንድ እንድ ግዜ ከ2 ሰዎች በላይ በአንድ ግዜ በተመሳሳይ ሰዓት መደወል ልንፈልግ እንችላለን። ለምሳሌ ለስራ ወይም ለጫወታ ከጓደኞቻችን ወይም ከስራ ባልደረቦች ጋር በተመሳሳይ ሰዓት በስልክ ማውራት ካለብን ለየእያንዳንዱ ሰው ከመደወል ይልቅ በአንድ ጥሪ ሁሉንም ማግኘት የምንችልበት አገልግሎት ስልካችን ላይ አለ። ⇨ ይህ አገልግሎት ኮንፈረንስ ኮል ይባላል። ኮንፈረንስ ጥሪ ለማድረግ፦ ❶ኛ- መጀመሪያ ወደ ሚፈልጉት ሰው ይደውሉና ስልኩ እስከሚነሳ መጠበቅ ❷ኛ-በመጀመ የደወሉላቸው ሰው ስልኩ ሲያነሱ መስመር ላይ እንዲጠብቁ ይናገሩ ❸ኛ- ወደ ሁለተኛው ሰው ስልክ ይደውሉና እስከሚነሳ ይጠብቁ ❹ኛ- የሁለተኛው ስልክ ሲነሳ እንደ ስልካችሁ አይነት በቀጥታ መርጅ (Merge) የሚለውን ምርጫ ይጫኑ። ወይም ኦፕሽን(Option) ውስጥ በመግባት ኮንፈረንስ(Conference) ወይም ጆይን(Join) የሚለውን በመጫን የኮንፈረንስ ጥሪ ማደረግ ትችላላችሁ። ❖ ተጨማሪ ሰዎችን ወደ ኮንፈረንስ ጥሪ ለማስገባት ከፈለጋችሁ ከተራ ቁጥር 2 እስከ 4 ያለውን መድገም ነው። 🗣 Subscribe Our youtube channel https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

✳️ የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ◽️ ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡ ◽️ የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን (Apps) ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል። ◽️ ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ (Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ◽️ ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡ ◽️ የተለዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ◽️ መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡ ◽️ የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡ ◽️ የተሳሳቱ የኢሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው) ◽️ የአይፒ አደራሻዎ በበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡ ◽️ ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡ 📌📌 የተለያዩ ትምህርቶችን በቪዶ ለመከታተል የ youtube ቻናላችንን subscribe ማድረግ አለባችሁ። 🗣 Subscribe Our youtube channel https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

🔰HOW TO GET FREE UNLIMITED GMAIL ACCOUNTS🔰 1) At first You Must have Just 1 Gmail Account 2) Then go to the site https://thebot.net/api/gmail/ and put that account name here (without @gmail.com) 3) Just press "Generate" and you will get Thousands of FREE ACCOUNTS. 4) They are all Connected to your first account so YOU JUST USE THE NORMAL MAIL INBOX FOR ALL THE ACCOUNTS!!! 🗣 Subscribe Our youtube channel https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

📌 ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ሁለተኛ ሳተላይት ወደ ሕዋ ልታመጥቅ ነው!! ◽️ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ ከኢቲቪ ጋር በ
📌 ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ሁለተኛ ሳተላይት ወደ ሕዋ ልታመጥቅ ነው!! ◽️ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ዝርዝር መረጃው በቀጣይ ይፋ እንደሚሆን ጠቅሰው፣ በ2013 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ናኖ ሳተላይት ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሕዋ ለማምጠቅ እየተሠራ ነው ብለዋል። ◽️ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሕዋ የሚመጥቀው ሳተላይት ባለፈው ታኅሣሥ ወር ወደ ሕዋ የመጠቀችው ETRSS-1 ሳተላይትን በመጠቀም ማግኘት የማይቻሉ መረጃዎችን ለማግኘት እንደሚረዳም ዋና ዳሬክተሩ ተናግረዋል። ◽️ ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው ሳተላይት የማምጠቅ ሥራ ባለፈው ታኅሣሥ ወር ላይ ወደ ሕዋ ከተላከችው የመጀመሪያዋ ሳተላይት ልምድ በመውሰድ የሚሠራ በመሆኑ ፈተናዎች ቀላል እንደሚሆኑ ዶ/ር ሰሎሞን ገልጸዋል። ◽️ ታኅሣሥ 2012 ዓ.ም ውስጥ የተላከችው ሳተላይት ከምትልከው ትልቅ የመረጃ ሀብት ማግኘት ተችሏል ያሉት ዶ/ር ሰሎሞን፣ በአምስት ወራት ውስጥ ለምርምር ተቋማት እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መረጃ ከሳተላይቷ መገኘቱን ተናግረዋል። ◽️ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ዐሥር ሳተላይቶች ለማምጠቅ እቅድ ይዛ እየሠራች ነው ተብሏል። 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ 🗣 Subscribe Our youtube channel https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

📌 ቶሺባ ከ35 አመታት በኻላ ላፕቶፕ ማምረት አቆመ! በሀገራችን ከቅርብ አመታት በፊት እጃችን ላይ በስፋት ይገኝ የነበረዉ የቶሺባ ላፕቶፕ ምርት ማቆሙን አስታዉቀል! ያለውን የኮምፒዩተር ድርሻ ለ
📌 ቶሺባ ከ35 አመታት በኻላ ላፕቶፕ ማምረት አቆመ! በሀገራችን ከቅርብ አመታት በፊት እጃችን ላይ በስፋት ይገኝ የነበረዉ የቶሺባ ላፕቶፕ ምርት ማቆሙን አስታዉቀል! ያለውን የኮምፒዩተር ድርሻ ለ Dynabook brand ባለቤት ለሆነው Sharp ሸጦታል! በ 1985 የመጀመሪያዉን T1100 በማምረት ነበር የኮምፒዩተር አለሙን የተቀላቀለዉ፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ እየከሰረ መጥቶ እስከ 2013 ድረስ በአመት 17.7 million ላፕቶፖችን ይሸጥ ከነበረበት ወርዶ 1.4 million ነበር በባለፈዉ አመት የሸጠዉ! በዚህ አመትም 576.3bn yen (£4.2bn) ኪሳራ አስተናግዷል፡፡ ለዉድቀቱ እንደ ምክንያት ሚጠቀሰዉ Apple, Dell, እና Lenovo ultraportable ላፕቶፖችን እንደ MacBook Air and XPS series ማምረት መጀመራቸዉ የቶሺባን ተፈላጊነት ቀንሶታል፡፡ ሌላኛዉ ምክንያት ደግሞ አዳዲስ ምርቶችን በማምረት የገዢዎችን ቀልብ መሳብ አለመቻላቸዉ ነው ! 🗣 Subscribe Our youtube channel https://www.youtube.com/channel/UC41VxoyfSBqLHZn2rYaaucg

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  - Telegram kanali @computer_android_tricks statistikasi va tahlili