uz
Feedback
ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

Kanalga Telegram’da o‘tish

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  analitikasi

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  (@computer_android_tricks) kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 11 983 obunachidan iborat bo'lib, Taʼlim toifasida 17 269-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 838-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 11 983 obunachiga ega bo‘ldi.

04 Mart, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -107 ga, so‘nggi 24 soatda esa 0 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 0% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining N/A% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 0 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 0 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 0 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 05 Mart, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Taʼlim toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

11 983
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-337 kunlar
-10730 kunlar
Postlar arxiv
❖ All Windows and Microsoft Office Activator Collections 1.0 👺Activate your Windows and Ms. Office ❖Includes : KMS Tools, KMSpico, Microsoft Toolkit, ReLoader, RemoveWAT, Windows Loader and more. 💥@Computer_Android_tricks

+1
⚛️ Adobe Photoshop 2022 v23.1.0.143 (x64) Pre-activated - Part1 #Adobe #Photoshop #Photoshop2022

✅ Adobe Premiere Pro 2022 v22.1.2.1 (x64) Pre-activated #Adobe #Premiere #PremierePro #PremierePro2022 #Premiere2022

+2
IE11-Windows6.1-x64-en-us.exe53.32 MB

Internet Explorer 11 (Offline installer)

#mobile_problems ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች #1.ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጹን መጨመር ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር ቀዳዳን ማፅዳት ከላይ በተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡ #2.የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች በኋላ ይቋረጣል፡፡ የስልካችን የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /ኮል ታይም ሊሚት/Call time limit/ የሚለውን ማጥፍት በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto quick end የሚል መቼትን ማጥፍት፡፡ 👉call record 👉General call setting 👉More 👉Auto quick -end 👉Off #3.የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ መበየድ፡፡ #4.Insert SIM የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert Sim የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት #5.ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/ DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር #6.ኔት ወርክ የሌለው ስልክ አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር #7.እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም ስፒከሩን መቀየር #8.ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ ማይኩን መቀየር #9.ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን አይቀበልም ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት #10.ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት #11.ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ ኬብል መቀየር #12.የምን ሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/ ስፒከር መቀየር #13.ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ማሞቅ ወይም መቀየር #14.ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር #15.ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ ቁጥር ይደረድራል/ ኪፓድ አይሲን መቀየር #16. ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀር JOIN👇👇 https://t.me/Computer_Android_tricks

All Versions of .Net Framework V1.0-3.5 V4.7.1

✅ Windows 11 Original ISO (Direct download link) Your download should begin immediately once you click on the link given. The
✅ Windows 11 Original ISO (Direct download link) Your download should begin immediately once you click on the link given. These ISO files include the following editions of Windows 11: 👉 Windows 11 Home 👉 Windows 11 Home N 👉 Windows 11 Home Single Language 👉 Windows 11 Education 👉 Windows 11 Education N 👉 Windows 11 Pro 👉 Windows 11 Pro Education You will have the option to select the edition during the Windows 11 installation. 📌 Download Link 👉 Here 🔥 🔥 For more Information https://www.microsoft.com/en-us/software-download/windows11 #Windows11 #Windows #Microsoft

Windows 10 Version 21H1 Original ISO Download 📌 Consumer - (S/SL/Home/Pro/Edu) 👉 Google Drive links - 32Bit (x86) - 64bit (
Windows 10 Version 21H1 Original ISO Download 📌 Consumer - (S/SL/Home/Pro/Edu) 👉 Google Drive links - 32Bit (x86) - 64bit (x64) 👉 One Drive Links - 32BIt (x86) - 64bit (x64) 📌 Business - (Pro/Enter/Edu) 👉 Google Drive links - 32Bit (x86) - 64bit (x64) 👉 One Drive Links - 32BIt (x86) - 64bit (x64) 📌 IoT Enterprise 👉 Google Drive links - 64bit (x64) - Arm64 👉 One Drive Links - 64bit (x64) - Arm64 #Windows10 #Windows

✅ በቲውተር ፖስት የምናደረገው በፌስቡክ አካውንታችን ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡ - ይህን ለማድረግ የሚከተለውን Step ይከተሉ፡- - በቲውተር አካውንታችን Setting የሚለው ውስጥ ይግቡ.... - በመቀጠልም በ Setting ውስጥ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ወደታች በመሄድ Apps የሚለውን ይጫኑ.... - በመቀጠልም Apps የሚለውን ስንከፍት Facebook Connect የሚል ምርጫ እናገኛለን፡፡ እሱን ምርጫ በመጫን የፌስቡክ አካውንታችንን በማስገባት የቲውተር አካውንታችንን ከፌስብከ አካውንታችን ጋር በቀላሉ ማገናኘት እንችላለን ማለት ነው፡... - አስፈላጊ ከሆነም ሁለቱንም በማገናኘት በፌስቡክ ፖስት ያደረግነውም በቲውተር ፖስት እንዲሆን እንዲሁም በቲውተር ፖስት ያደረግነውም ደግሞ በፌስቡክ ፖስት እንዲሆን ማድረግ ይቻላል... - የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር ጋር ማገናኘታችን በዋነኝነት በቲውተር ከ140 ፊደላት በላይ የያዘ መልዕክት ማስተላለፍ ስለማይቻል በፌስቡክ የፈለግነውን መልዕክት ስንፅፍ በቲውተር ላይም ለሚገኙ ሰዎች የፅሁፉን ሙሉ መልዕክት በሊንክ ስለሚያስቀምጥልን በቀላሉ እንዲደርሳቸው ማድረግ ያስችለዋል፡፡ 📢: ✅https://t.me/Computer_Android_tricks

👉 ሲም ካርድ ምንድን ነው? - ሲም ማለት የተመዝጋቢ ማንነት ሞዱል SIM Stands for Subscriber Identity Module ከማንኛውም የሞባይል ስልክ በጣም አስፈላጊ አካል ነው፡፡ - በአንዳንድ አገሮች ICC (Integrated Circuit Card ) and UICC ( Universal Integrated Circuit Card ) በመባልም ይታወቃል፡፡ በቀላል አነጋገር ሲም ካርድ በመሠረቱ SIM Card is a or ማይክሮ መቆጣጠሪያን መሠረት ያደረገ የመዳረሻ ሞዱል (microcontroller-Based Access Module) ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መረጃን የሚያከማች (A Small Portable Memory Chip) የ 16 አኃዝ ወይም የ 17 አኃዝ ኮድ ያለው ሲሆን ግን እንደየሀገሩ ይለያያል... የኔትወርክ አጓጓዥ መረጃን እና የሚያከማች አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቺፕ ነው፡፡ ልዩ የተጠቃሚ መታወቂያ/የሞባይል ስልክ ቁጥር ነው። - የሲም ካርድ ሲም ካርዶች በ 3 መሠረታዊ መጠኖች ይገኛሉ መደበኛ ማይክሮ እና ናኖ ከነዚህ ሶስት መጠኖች ውስጥ መደበኛ መጠኑ የመጀመሪያው ነው፡፡ - ማይክሮ እና ናኖ ሲም ካርዶች ከመደበኛው ሲም ካርድ ዙሪያ ያለውን ተጨማሪ ፕላስቲክን በመቁረጥ አነስተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ ለተሻለ ግንዛቤ የሚከተለውን ምስል ይመልከቱ ፡፡ 📍የሲም ካርድ ዓይነቶች ሲም ካርዶች በዋናነት 2 አይነቶች ናቸው - GSM (ጂ.ኤስ.ኤም) እና CDMA (ሲዲኤምኤም) ናቸው። 👉 GSM ማለት (Global System for Mobiles) SIM ለሞባይል ዓለም አቀፍ ስርዓት ማለት ነው፡፡ በማንኛውም የሞባይል ስልክ ውስጥ ሊገባና ሊወጣ ይችላል፡፡ 👉 CDMA ማለት ሲተነተን Code Division Multiple Access ማለት ነው፡፡ አንዴ ከመጀመሪያው ስልክ ውስጥ ሊወገድ ወይም ሊወጣ አይችልም። 👉 eSIM ካርድ በአሁኑ ጊዜ eSIM Card ተብሎ የሚጠራ አዲስ የሞባይል ስልክ ግንኙነት ቴክኖሎጂ አለ፡፡ eSIM ማለት Embedded ሲም ማለት ነው፡፡ እንደ GSMና CDMA SIM አይነት አይደለም ገና ስልኩ ሲሰራ አብሮ ከስልኩ ጋ ተጣብቆ የሚመረት ነው እንዲሁም በ eSIM ላይ ያለው መረጃ እንደገና ሊፃፍ ስለሚችል የኔትወርክ ኦፕሬተርዎን መለወጥ ይችላሉ ፡፡ 📍 ሲም ካርድ ክፍሎች እና ተግባር በሲም ካርድ ላይ የተለያዩ የወረዳ ክፍሎች የተለያዩ ተግባራት አሏቸው ፡፡ የሚከተለው የአንድ ሲም ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው ፡፡ 1. VCC ( Power Supply ) - የሲም የኃይል አቅርቦት ፒን ነው ፡፡ 5V DC ኃይልን ይደግፋል፡፡ ሲም ካርዱ እንዲሰራ ይህ የቪ.ሲ ፒን ከ 5V DC ጋር መቅረብ አለበት ከዚያም በሲም ካርዱ ውስጥ የተካተተው IC (Integrated Circuit) ብቻ ነው የሚሰራው ፡፡ 2. RST ( Reset ) - የሲም ካርዱን Signal እና ግንኙነቶችን (Communication) እንደገና ለማስጀመር የሚያገለግል ፒን ነው ፡፡ ይህንን ፒን ሲጠቀሙ ሲም ሁሉንም የወቅቱን Signal ዳግም በሚያድስ ነባሪው ሞድ ያደርገዋል ፡፡ የ RESET ፒን በሞባይል መሳሪያዎች ወይም በሲም ካርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይሠራል። በአጠቃላይ ሲም ተጠቃሚዎች ይህንን ተግባር እንዲጠቀሙ አነስተኛ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ 3. CLK ( Clock ) - ሰዓት-ሲምውን ለ processor የሰዓት Signal ይሰጣል፡፡ 4. GND (Ground) -ሲም የ Integrated Circuit ያለው አነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ሃርድዌር እንደመሆኑ Ground ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ GND አሁን ለሲም ካርዱ ትክክለኛ ሥራ ወረዳውን ያጠናቅቃል፡፡ 5. VPP ( Voltage Programming Power ) - ቀደም ሲል ይህ ፒን በሲም ካርዱ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ያለውን ውሂብ ለመፃፍ ወይም ለመሰረዝ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ቮልት ለመሸከም ያገለግላል ነገር ግን አሁን ይህ ስራ በVCC የሚሰራ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ አይደለም፡፡ 6. SIM Data I/O Pin - ግብዓት / ውጤት-በሞባይል ስልኮች በሲም ካርድ ውስጥ ያለውን data ለማንበብ እና ለመፃፍ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ እንደ የ data ማስተላለፊያ ፒን የሚሰራ ግማሽ ባለ ሁለትዮሽ የግንኙነት ፒን ነው። ሲም ካርዱ እያነሰ እና እየቀነሰ ሲመጣ አፈፃፀሙ እና አቅሙ በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ምርምርም ምስጋና ይግባው ፡፡ 📤 ➩ ሀሳብ/አስተያየት :↩️ 📣: @Tech_Zone_admin_Bot ⚡️Share And Support Us. https://t.me/Computer_Android_tricks

#Telegram ቴሌግራም በተጠናቀቀው 2021 / እ.አ.አ. / ድንቅ የሚባል አመትን እንዳሳለፈ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል። ጥር ወር ላይ በመላው ዓ
+2
#Telegram ቴሌግራም በተጠናቀቀው 2021 / እ.አ.አ. / ድንቅ የሚባል አመትን እንዳሳለፈ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል። ጥር ወር ላይ በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ የተደረገ መተግበሪያ ፣ በጥቅምት ወር በአንድ ቀን ብቻ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል የቻለ እንዲሁም በታህሳስ ወር በፍጥነት እያደገ ያለ መተግበሪያ ተብሎ መታወጁ ተገልጿል። የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፥ " የእድገቱ ሁሉ ባለቤቶች ተጠቃሚዎቹ እንደሆኑ እናውቃለን " ያሉ ሲሆን በተጠቃሚዎች የሚሰጡትን አስተያየቶች በጥሞና በማድመጥ አመቱን ሙሉ ቴሌግራም ለተጠቃሚዎቹ የተሻለ እንዲሆን አድርገናል ብለዋል። ቴሌግራም በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት በቻናሎች፣ ግሩፖች እንዲሁም የአንድ ለአንድ መልዕክ ልውውጥ ወቅት ሪአክሽን መስጫ (👍👎❤️😢...) እንዲሁም የመልዕክት መተርጎሚያ የተካተተበት በዓመቱ 12ኛ ዋና ማሻሻያ ተደርጎበት ተለቋል። አዲሱ የሪአክሽን ማሻሻያ የሚሰራው የቻናሉ ወይም የግሩፑ ባለቤቶች ክፍት ሲያደርጉ ነው። እንዴት ? (ወደ ቻናሉ /ግሩፕ በመግባት Edit ✍ የሚለውን መጫን ፣ በመቀጠል Enable Reactions የሚለውን ON ማድረግ እና የሚሰጡትን Reaction መምረጥ) ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያችሁን (ባለ ሰማያዊ ምልክቱን) Update በማድረግ ማሻሻያዎቹን እንድትመለከቷቸው መልዕክት እናስተላልፋለን። የቴሌግራም መተግበሪያችሁን Update ለማድረግ👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

' 07 ' 👉 የስልክ ቁጥር መለያ - #SafaricomETH ቢዝነስ ዴይሊ ጋዜጣ ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚጀምረው የሞባይል ስልክ አገልግሎት የስልክ ቁጥሮች መለያ ቁጥ
' 07 ' 👉 የስልክ ቁጥር መለያ - #SafaricomETH ቢዝነስ ዴይሊ ጋዜጣ ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚጀምረው የሞባይል ስልክ አገልግሎት የስልክ ቁጥሮች መለያ ቁጥር 07 እንደሚሆን ማስታወቁን ዘግቧል። እንደጋዜጣው ዘገባ ሳፋሪኮም በኬንያ ለሚሰጠው የሞባይል አገልግሎት የሚጠቀመው መለያ ቁጥር 07 ሲሆን አሁን ኢትዮ ቴሌኮም ከሚጠቀምበት መለያ ቁጥር 09. ቀጥሎ በሀገሪቱ ሁለተኛው ይሆናል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን እየቀጠረ ሲሆን ጥር ወር ላይ ብቻ 100 ሠራተኞችን እንደሚቀጥር አሳውቋል። ምንጭ፦ https://www.businessdailyafrica.com/bd/corporate/companies/safaricom-set-use-07-prefix-ethiopia-phones-3655590

💖 IBM SPSS Statistics 26.0 untuk 32 + 64 bits IBM® SPSS® Statistics is the world’s leading statistical software used to solve business and research problems by means of ad-hoc analysis, hypothesis testing, and predictive analytics. Organizations use IBM SPSS Statistics to understand data, analyze trends, forecast and plan to validate assumptions and drive accurate conclusions.

✳️ ኢትዮጵያ ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚያስከፍሉ ሀገራት በቀዳሚነት ተቀመጠች😢 ◽️መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገ 'ፕራይስ ኮምፓሪዝን' የተሰኘ የምርምር ተቋም አደረግኩት ባለው አዲስ ጥናት በዓለማችን ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚጠይቁ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ◽️ጥናቱ በኢትዮጵያ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር በ307.84 ዩሮ ገደማ እንደሆነ በመግለጽ ይህ ዋጋ ኢትዮጵያን á‰ á‹“ለም ላይ ከሚገኙት ሀገራት ከፍተኛ ዋጋ የሚጠየቅባት ሀገር ያደርጋታል ብሏል። ◽️ይህም ለወርሃዊ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ሽያጭ በአማካኝ 30.99 ዩሮ ከምትጠይቀዉ ዩናይትድ ኪንግደም ጋር በንፅፅር ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ዋጋ ወደ አስር እጥፍ እንደሚጠጋ ተጠቁሟል። ◽️ውድ የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ካለባቸዉ ሀገራት መካከል ለብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር 236.09 ዩሮ የምታስከፍለዉ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች። ◽️በተቃራኒው በጥናቱ በአለም ላይ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በርካሽ ዋጋ ከሚገኝባቸው ሀገራት ተርታ መካከል ዩክሬን የአንደኝነት ደረጃን የያዘች ሲሆን ለአገልግሎቱ የሚከፈለዉ ወርሃዊ ክፍያ በአማካኝ 4.42 ፓውንድ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ➖➖➖➖➖➖➖ ✅https://t.me/Computer_Android_tricks

#Meta #FacebookDead 📄ፌስቡክን ጨምሮ የተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን የሚያስተዳድረው ኩባንያ ስያሜውን ወደ 'ሜታ' ከቀየረ በኋላ አዲሱ ስሙ እስራኤል ውስጥ መቀለጃ ሆኗል። አዲሱ የ
#Meta #FacebookDead 📄ፌስቡክን ጨምሮ የተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን የሚያስተዳድረው ኩባንያ ስያሜውን ወደ 'ሜታ' ከቀየረ በኋላ አዲሱ ስሙ እስራኤል ውስጥ መቀለጃ ሆኗል። አዲሱ የፌስቡክ ስም 'ሜታ' የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ቋንቋ 'ሟች' የሚል ተቀራራቢ ትርጉሙ የያዘ በመሆኑ በእስራኤላውያን ዘንድ መሳለቂያ ሆኗል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች #FacebookDead በሚል ሃሽታግ ትርጉሙን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እያጋሩ ነው። 'ዘካ' የተባለው ታዋቂ የአደጋ ጊዜ ነፍስ አድን በጎ ፈቃደኞች ቡድን በፌስቡክ አዲስ ስያሜ ላይ አሹፏል። ቡድኑ በትዊተር ገጹ ላይ "አትጨነቁ፣ [ልናድነው] እየሠራን ነው" በማለት አስፍረዋል። ሌላው የትዊተር ተጠቃሚ ደግሞ "ሁሉም የዕብራይስጥ ተናጋሪ የሚስቅበት ጥሩ ምክንያት ስለቀረበልን እናመሰግናለን" ብሏል። ፌስቡክን ጨምሮ በርካታ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮችን የያዘው ግዙፉ ተቋም ከባድ ትችት እየቀረበበት ባለበት በዚህ ወቅት የሁሉም መድረኮች አቃፊ የሆነውን ድርጅት ስያሜ 'ሜታ' የሚል አዲስ ስም መስጠቱ በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል። Credit: BBC Amharic Website

🚨BREAKING News : Facebook, WhatsApp and Instagram, which share the same IT infrastructure, are all down

ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ? ✅ ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው። ✅ ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን። ✅ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ። በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው። ✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች። ✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው። ✅ ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ። ✅ Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው። ምስሉን ይመልከቱ!⁉️ ✅ Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል። ✅ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን። ✅ ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ! ✅ ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች #Like #shear ይደረግ።

✴️ ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን 🔆 ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ wifi በመጠቀ
✴️ ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን 🔆 ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ  wifi በመጠቀምም በዋየርለስ ወይም ያለ ኬብል ፕሪንተራችንን ከኮምፒውተራችን ጋርም ማስተዋወቅ እንችላለን። 🔆 እኔ ግን ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ያለምንም wifi እና software ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር እንዴት ማስተዋወቅ እንደምንችል ነው። 🔆 ኮምፒውተራችንን እንዴት ከፕሪንተራችን ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን። 1⃣ control panel ውስጥ በመግባት device printer እንመርጣለን ወይም start ን በመንካት search box ላይ device and printer ብለን እንፅፋለን። ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማያያዙን እንዳንረሳ። 2⃣ በመቀጠል add printerን  እንመርጣለን ።search እስኪጨርስ እንጠብቃለን። 3⃣ add alocal printer የሚለውን መርጠን next እንለዋለን። 4⃣ በመቀጠል ፕሪንተራችንን ያያዝነው በኬብ ስለሆነ ከሚመጣልን ምርጫ የመጀመሪያውን USB portን እንመርጣለን።next እንለዋለን 5⃣ አሁን ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የፕሪንተራችንን ስም በመፈለግ መርጠን next ቀጥሎም next እንለዋለን። 6⃣ በመጨረሻም print a test page የሚል ይመጣልናል click አርገን test እናደርግና finish ብለን እንጨርሳለን። ለወዳጆ ያጋሩ