cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

🌷ከሱኒዋ እህት ለሱኒይቷዋ🌷🌷ﻣﺎ ﺃﺟﻤــﻞ ﺃﻥ ﺗﻜــﻮﻥ ﺍﻟﻤــﺮﺃﺓ🌷 👑ﻃﺎﻟﺒﺔ ﻋﻠﻢ ﻧﺎﺷﺮﺓ ﻟﻠﺨﻴﺮ ﻋﺎﺭﻓﺔ ﻟﻠﺴﻨﺔ

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالأِنْسَ إِلاَّ لِيَعْبُدُونِ  *ሱራህ 51, አያህ 56* ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ ================================

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
872
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
-1330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Repost from AI-IKHILAS
✨✨✨✨✨✨ ኢብራሂም ቢን አብዱል ዋሂድ አልመቅዲሲይ --- ዲያእ አልመቅዲሲይን ወደ ዒልም ጉዞ ሊሄድ ሲል እንዲህ ሲል መከረው፦ "ቁርዐንን መቅራትን አብዛ መቼም አትተወው ነገሩ እንዲህ ነው የምትፈልገው ነገር ሁሉ ቁርዐንን በቀራህ ቁጥር ይገራልሀል" = ዲያእ እንዲህ ይላል ፦ "ይህንን ምክር ተቀብዬ ተገበርኩት ብዙ ጊዜም ሞከርኩት እራሴን ስመለከተው ቁርዐንን የቀራሁኝ ጊዜ ሀዲስን ማዳመጥና መሀፈዝ የሚቀለኝና ቁርአንን ያላነበብኩ ጊዜ የሚከብደኝ ሆኜ አገኘሁት" ❓የከበደህ ነገር አለን?! ❓እንዲሳካ  ምትፈልገው  ነገርስ?! ❗️ቁርዐንን ላይ ሙጭጭ በል ያኔ ምትፈልገው ነገር ገር እና ቅርብ ይሆንልሀል ልብህንም በብርሀኑ ያስደስትልሀል። ይ🀄ላ🀄ሉን https://t.me/AlIkhilasmedresa
Hammasini ko'rsatish...
AI-IKHILAS

አላህ የፃፈልን ርዝቅ እየበላን ሞታችንን የምንጠብቅ የአላህ ባሮች አላህ ያድርገን

Repost from AI-IKHILAS
“ሽርክ” የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮ وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال : سمعت رسول الله ﷺ يقول : قال الله تعالى : "أنا أغنى الشركاء عن الشرك ، من عمل عملا أشرك فيه معي غيري تركته وشركه" رواه مسلم: ٢٩٨٥ አቡሁረይራ (ረዲየሏሁዓንሁ) ከረሱል ﷺ ሰምተው ባስተላለፉት “ሐዲስ አል'ቁድስ” አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡- “ከተጋሪዎች ሁሉ መጋራት የተብቃቃሁ ነኝ ፤ ከእኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እርሱን ከነማጋራቱ እተወዋለሁ፡፡” ሙስሊም: 2985 ይህ ሐዲስ ከዑለሞች ዘንድ “ሐዲሰ አል'ቁድስ” በመባል ይጠራል፡፡ ረሱል ﷺ አንድን ሐዲስ ወደ አላህ ካዛመዱት “ሐዲስ አል'ቁድስ” በመባል ይጠራል፡፡ ወደአላህ ካልተዛመደ ግን “ሐዲስ አን'ነበውይ” በመባል ይጠራል፡፡ (¹) አላህ ሸሪካ የሌለው ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነው፡፡ አንድ ሰው በሚሰራው ስራ የአላህን እና የሰዎችን ውዴታ የሚሻ ከሆነ ስራው ተቀባይነት ያጣል፡፡ ግማሹን ተቀብሎ ግማሹን ይተወዋል አይባልም፡፡ ከሰዎች ውዳሴን ፈልጎ ሶደቃ ቢሶድቅ አላህ ከእርሱ አይቀበለውም፡፡ ከሰዎች ሙገሳን ፈልጎ ሶላት ቢሰግድ አላህ ከእርሱ አይቀበለውም፡፡ አላህ ከተጋሪዎች ማጋራት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡ አንድ ሰው ሶላቱን ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ “እከሌ ማሻ አላህ ይሰግዳል! ሶላትን ያበዛል!” የሚል የሰዎችን አድናቆት የሚፈልግ ከሆነ ሩኩኡን ሱጁዱን ቂያሙን መቀመጡን ሁሉ ቢያስረዝም አይኑ ከሱጁድ ቦታ ተተክሎ ቢቆይ ሶላቱን አላህ አይቀበለውም፡፡ አላህ ከዚህ ሰው ሶላት የተብቃቃ ነው፡፡ “እከሌ ለጋስና ቸር ነው፡፡ ሶደቃ ለምስኪኖች ይሶድቃል፡፡” መባልን ሽቶ ለምስኪኖች ገንዘብ የሚሰጥ እና ዘወትር የሚያበላ ቢሆን እንኳ ከአላህ ዘንድ ስራው ተቀባይነት አያገኝም፡፡ አንድ ሙኽሊስ (አምልኮቱን ለአላህ ብሎ የሚፈጽም ሰው) በዒባዳው አፈጻጸም ላይ ሪያዕ (ለይዩልኝ) ገባብኝ ብሎ ቀልቡን ቢሰማውና ከሰይጣን መሆኑን አውቆ ወዲያውኑ ቢከላከለው በአምልኮቱ ላይ የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ሰይጣን ሁልጊዜ ሙኽሊስ የሆኑ ሰዎችን ይፈታተናቸዋል፡፡ ስለዚህ ለሰይጣን ተገዥ መሆን ሳይሆን የሚያመጣውን ፈተና በጽናት መወጣት ነው የሚገባው፡፡ እርሱን በመስጋት ወይም ሪያእ (ለይዩልኝ) ይገባብኛል ብሎ በመስጋት ኢባዳውን ማቋረጥ የለበትም፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው በአቋማችን ላይ መጽናት ብቻ ነው፡፡ እኛ ከጠነከርን ሰይጣን በፍርሃት ወደኋላ ይሸሻል፡፡ ﴿مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ﴾ الناس: ٤ “ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች (ሰይጣን) ክፋት (እጠበቃለሁ) በል፡፡” (ናስ: 4) ሶላቱን ሙኽሊስ ሆኖ ጀምሮ ሪያዕ (ይዩልኝ) ገባበት ከዚያም ምንም ሳይከላከለው አምልኮቱን እስኪጨርስ በዚያው ቀጠለ ሶላቱ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ይበላሽበታል፡፡ ምክንያቱም ሶላት መጨረሻው ከተበላሸ የመጀመሪያውም ይበላሻል፡፡ በዒባዳችን ውስጥ ሪያዕን (ለይዩልኝ) ልንፈራ ይገባል፡፡ ሪያእን ፈርተን ደግሞ ዐዒባዳን ፍጹም መተው የለብንም፡፡ ሰይጣን ወደ ሰዎች ይመጣና “አትስገድ” “አትቅራ” ምክንያቱም ሪያዕ ይሆንብሃል፡፡” ይለዋል፡፡ “ሶላትህን በኹሹዕ (አላህን በመፍራት) አትስገድ ሪያዕ ይሆንብሃል፡፡” ይለዋል፡፡ ሰይጣን ይህን በማለቱ ከዒባዳ የሚዘናጉ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ የሰይጣን ተንኮል መሆኑን አውቀን በዒባዳችን ላይ መጽናት ነው የሚገባን፡፡ ለሰይጣን ቅንጣት ያክል በር መክፈት አይገባንም፡፡ ይልቁንም አላህን መፍራት መረጋጋት ለሶላታችን አንኳርና በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰይጣንን እየተከላከልን አላህ በሚፈልገው መንገድ ኢባዳችንን ከፈጸምን ምንም አይጎዳንም፡፡ ይህን ካደረግን ሰይጣን ወደኋላ ሸሽቶ የሚደበቅ አካል ነው፡፡ (²) የሰው ልጅ በሐቂቃ ካየነው በሁለት ክስተቶች የተከበበ ነው፡- 1ኛ፡- ወደዒባዳ ከመግባቱ በፊት፤ ለምሳሌ፡- ሰይጣን ይመጣና “ሰዎች ስለሚያወድሱህ አትስራ” በማለት ከዒባዳ እንዲዳከም ያደርገዋል፡፡ 2ኛ፡- ወደዒባዳው ከገባ በኋላ፤ ዒባዳ ውስጥ ከገባ በኋላ ሰይጣን እየወሰወሰ ዒባዳውን ሊያበላሽበት ይሞክራል፡፡ በዚህ ሰዓት በአላህ እየተጠበቀ ሰይጣንን መከላከልና ወደኋላ እንዲሸሽ ማድረግ ነው ያለበት፡፡ በዚህ ቦታ የሚከተለው ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ዒባዳን ጨርሰን ካበቃን በኋላ ሰዎች ቢያወድሱንና ብንደሰት ዒባዳችን ሊበላሽ ይችላል? መልሱ፡- ዒባዳችን ሊበላሽ አይችልም የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ዒባዳዋ በሰላማዊና በኢኽላስ ተፈጽማለች፡፡ እኛ ውዳሴን ሳንፈልግ ብንወደስ ይህ አላህ በዚህ በዱንያ ላይ ያደረገው የሙእሚኖች ፈጣን ብስራት ነው፡፡ አላህ እኛን ሳንፈልገው የውዳሴ ቦታ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ይህ ምንም ችግር የለውም፡፡ ሰዎች አወደሱት እርሱም ውዳሴያቸውን ሰማ “የመልካም ውዳሴ ቦታ ያደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው” ቢል ችግር የለውም፡፡ ዋናው ነገር ዒባዳችን ካበቃ በኋላ በፈጸምናት ዒባዳ ላይ ተነስተው ሰዎች ቢያወድሱን እና እኛ ብንደሰት በዒባዳችን ላይ የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ብቻ ግን ከውዳሴው ተነስተን በነፍሳችን በመደነቅ ሌሎች የአላህ ባሮችን ለመናቅ እና ዝቅ ለማድረግ ምክንያት ከሆነ ግን ይህ ስራችንን የሚያበላሽ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በልቦናው ምንም ትዝ ሳይለው ዒባዳውን በመልካም በመጨረሱ አላህ መልካም ስራ ገጠመኝ ብሎ አላህን አመሰገነ ተደሰተ ይህ ዒባዳውን ፍጹም አይጎዳውም፡፡ ይህን አስመልክቶ የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡- "من سرته حسنته وساءته سيئته فذلك مؤمن" الترمذي: ٢١٦٥، احمد: ١١٤ “መልካም ስራው ያስደሰተው መጥፎ ስራው ያስከፋው ይህ ሰው ሙእሚን ነው፡፡” ቲርሚዚይ: 2165, አህመድ: 114 አላህ ከትልቁም ከትንሹም ሽርክ ሁላችንን ይጠብቀን! شرح رياض الصالحين لفضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله ٦/ ٣٤٠ ========================== (¹) ይህን አገላለፅ ዑለሞች የሚጠቁሙት በሁለቱ ሐዲሶች መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት እንጅ "ሐዲስ አንነበዊይ" ወህይ (ራዕይ) አይደለም ለማለት ታስቦበት አይደለም። ምክንያቱም ነብያችን ﷺ አላህ እንዳለው:– ﴿ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَى۞إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَى﴾ النجم: ٣-٤ "ከልብ ወለድም አይናገርም። እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራዕይ እንጅ ሌላ አይደለም።" አንነጅም: 3‐4 (²) ፉዶይል ብን ዒያድ (ዓለይሂረህመቱላህ) "ለሰዎች ሲባል ሥራን መተው ይህ ከሪያዕ (ከይዩልኝ) ነው።" ብለዋል። አል`አዝካር ሊነወዊይ ገፅ/19 https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AI-IKHILAS
የዳዕዋ መንሐጅ /አካሄድ/ በቤት ውስጥ ቤት ውስጥ ያለው ዳዕዋ እና የልጆች የአስተዳደግ ስርዓት ፤ የኢስላማዊ ትምህርት አቀራረብ እና ተግባራዊነት ፤ ከመስጅድ እና ከትምህርት ቤት ለየት ማለት አለበት፡፡ በዚህ ላይ በተለይ ሙስሊሞች አናሳ በሆኑበትና የልጆች አስተዳደግ በስርዓት በማይመራበት አካባቢ ፤ በቤት ውስጥ የሚደረገው ዳዕዋ አንገብጋቢነትና የሴቶች ተሳትፎ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ሙስሊም እህቶቻችን በዳዕዋው ስራ እንዲሰማሩና ውጤት እንዲያመጡ ከተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡- ✓ ሸሪዓዊ እውቀት ፤ ✓ በእውቀት መስራት ፤ ✓ ባወቁት ነገር ዳዕዋ ማድረግ እና ✓ ችግሮች ሲያጋጥሙ ትዕግስት ማድረግ ናቸው፡፡ የዳዕዋውን መንሐጅ በሚከተለው መልኩ አላህ ግልጽ አድርጎታል፡- ِ “ይህች መንገዴ ናት ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም በል፡፡” ዩሱፍ በዚህ መሰረት ዒልም (እውቀት) ለዳዕዋ ዝግጅት ዋና መሰረቱ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የቤት ውስጥ ዳዕዋ መሰረቶች በቤት ውስጥ ለሚደረገው ዳዕዋ መሰረቶቹ በርካታ ሲሆኑ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርጉንን ዋና ዋና የሚባሉትን እንደሚከተለው ለመጠቆም እንሞክራለን፡- 1. ኢማን እና እውቀትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ ትምህርቶች/ 2. ስነ-ምግባርን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ትምህርቶች/ 3. ሞራልን በማነጽ ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ ትምህርቶች/ 4. ማህበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/ 5. አካላዊ ጥንካሬን የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/ 6. ጾታዊ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/ 7. ዳዕዋን አስመልክቶ የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/ https://t.me/AlIkhilasmedresa
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AI-IKHILAS
ህጻንን ከሶፍ ማራቅ በሸሪዓ እንዴት ይታያል” ጥያቄ፡ - አንድ ህጻን በሶፍ ውስጥ ተቀምጦ እያለ ከተቀመጠበት ቦታ ማራቅ ይቻላል? መልስ፡- ህጻንን ከተቀመጠበት ሶፍ ማራቅ አይገባም፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚሆነው የሚከተለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ሐዲስ ነው፡- "ال يقيم الرجل الرجل من مقامه ثم يجلس فيه" “አንድ ሰው በዚያ ቦታ እርሱ ሊቀመጥ ዘንድ ሌላውን ከቦታው አያስነሳው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡ የተከለከለበት ምክንያት በህጻኑ ላይ ድንበር መተላለፍ ፣ ቀልብን መስበር ፣ ከሶላት እንዲሸሽ ማድረግ እና ጥላቻን መዝራት በመሆኑ ነው፡፡ ሕጻናቶችን በአንድ ሶፍ አድርገን ከኋላ ብናደርጋቸው እንኳ ጨዋታ ቀልድ በሶላት ውስጥ ይከሰት ነበር፡፡ ይህን ስጋት ለማስወገድ በየሶፉ ጣልቃ አስገብተን ብናቆማቸው ችግር የለውም፡፡ https://t.me/AlIkhilasmedresa
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AI-IKHILAS
ሴት በጀናዛ ላይ መስገዷ እንዴት ይታያል? አንዲት ሴት ወደመስጊድ በመሄድ በሟች ላይ መስገድ ትችላለች? በቤቷ ውስጥ በእርሱ ላይ ብትሰግድ ይበቃላታል? ከሁለቱ የቱ ነው በላጩ? መልስ፡- በቤቷ በእርሱ ላይ መስገዷ በላጭ ነው፡፡ ከቤቷ ወጣ ከሰዎች ጋር ብትሰግድም ችግር የለውም፡፡ ነገር ግን ከእኛ ዘንድ ይህ ነገር የታወቀ አይደለም፡፡ በተለይም ሟች ቤተሰብ ከሆነ በላጭ የሚሆንላት ወደመስጊድ ወጣ መስገዷ ሳይሆን ከቤት መስገዷ ነው፡፡ ሟቹ ከውጭ ከሆነ ሶለተል ጋኢብ (የርቀት ሶላት) መስገድ አይገባትም፡፡ https://t.me/AlIkhilasmedresa
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AI-IKHILAS
ልቦና በህይወትና በሞት ደረጃ ከሆነ ልቦችን በሶስት ከፍለን መመልከት አንችላለን፡- 1. ሰላማዊ የሆነች ቀልብ፡ በማንኛውም መልኩ ሰላማዊ የሆነችና ሽርክ የሌለባት ቀልብ ነች፡፡ ይልቁንም በመውደድ፣ በፍላጎት፣ በመመካት፣ ተጸጽታ በመመለስ፣ በመዋደቅ ፣ በመፍራት እና በተስፋ አላህን ጥርት አድርጋ ታመልካለች ፡፡ ከወደደች ለአላህ ብላ ትወዳለች ፤ ከጠላች ደግሞ ለአላህ ብላ ትጠላለች ፤ ከሰጠች ለኣላህ ብላ ትሰጣለች ፤ ከከለከለች ደግሞ ለአላህ ብላ ትከለክላለች ፤ በማንኛውም ነገሯ ዳኛዋ በረሡል صلى الله عليه وسلم ላይ የወረደው ህግ ነው ፤ በዓቂዳም በንግግርም በተግባርም ከአላህ ህግ ውጭ ሌላን አታስቀድምም፡፡ 2. የሞተች ቀልብ፡ ምንም ህይወት የሌላት ነች ፤ ጌታዋን አታውቅም፣ አትገዛም ፣ ትእዛዙን አታከብርም፣ አላህ የሚወደውን አትሰራም፤ ይልቁንም የአላህ ቁጣ እና ጥላቻ ቢኖርበት እንኳ ከስሜቷ ጋር ነው የምትንቀሳቀሰው ፤ ፍርሃቷም፣ ተስፋዋም፣ ውዴታዋም ጥላቻዋም፣ ማላቋም ማዋረዷም ከአላህ ውጭ ነው፡፡ ስትወድም ስትጠላም ስትሰጥም ስትከለክልም ለስሜቷ ነው፡፡ ስሜትና የዱንያ ፍላጎቷ ኢማሟ (መሪዋ) ፤ ማህይምነት ሹፌሯ ፤ ዝንጋቴ መርከቧ ነው፡፡ 3. ህይወትና በሽታ የተቀላቀለባት ቀልብ፡ ይህች ቀልብ ሁለት ገጽታዎች ያሏት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ አንድኛው ገጽታ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛው ገጽታ ያሸንፋታል፡፡ እርሷ ከሁለቱ ወዳሸነፈው ትሆናለች ፡፡ በውስጧ የአላህ ውዴታ፣ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ተወኩል አላት፡፡ ይህ የህይወት ገጽታዋ ነው ፤ ስሜት፣ ምቀኝነት፣ ኩራት፣ በራስ መደነቅ እና የበላይነትን መፈለግ የጥፋትና የክስረት ገጽታዋ ነው፡፡ https://t.me/AlIkhilasmedresa
Hammasini ko'rsatish...
👍 መደመጥ ያለበት የባለትዳሮች ሀቅ የተዳሰሰበት ሙሀደራ ነው የሴቶች ሀቅ ከባሎቻቸው ማግኘት ያለባቸው ሀቅ የተጠቀሰበት ት/ት ነው ይደመጥ!!! ይደመጥ!!! ይደመጥ!!! ይደመጥ!!! https://t.me/sunah123
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AI-IKHILAS
Photo unavailableShow in Telegram
ቁርኣንን ከምናልቅበት መንገዶች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1- ቁርኣንን ከመተው ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ 2- ቁርኣንን ተገቢ የሆነ ንባብ ለማንበብ ከነፍሳችን ጋር መታገል፡፡ 3- የቁርኣንን ሸሪዓዊ ብይን መውደድ ፣ ቁርኣን ለመጣበት መልዕክት ተገዥ መሆን፣ በሰዎች ንግግር የአላህን ቃል አለመቃረን፡፡ 4- ቁርኣንን ለአላህ ብሎ እንጅ ለይዩልኝና ታዋቂነትን ለመፈለግ ብሎ አለመቅራት፡፡ 5- የቁርኣን ባለቤት የሆነውን አላህ ክብር ማወቅ፡፡ 6-ቁርኣን ከንግግሩ ሁሉ በላጭ መሆኑን ፤ እርሱን የመሰለ ከዚህ በፊት ያልነበረ ፣ ለወደፊትም ሊኖር እንደማይችል ማመን፡፡ 7- በቁርኣን ፍቅር ልባችንን ማስዋብ፡፡ 8- ቁርኣን ጉድለት የሌለበት ፤ እርስ በርሱ የማይቃረን ፤ በማንኛውም መልኩ ሙሉ መሆኑን ማመን፡፡ 9- ከቁርኣን አንድንም ሳንቃወም ሙሉ በሙሉ መቀበል፡፡ 10- በቁርኣን ከማሾፍ መጠንቀቅ፡፡ 11- ቁርኣን በዱንያም ይሁን በአኼራ ለሰው ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ሰብስቦ ይዟል ብሎ ማመን፡፡ 12- ቁርኣንን ለማያውቀው ህብረተሰብ ማብራራት፤ የቁርኣንን ጽንሰ ሐሳብ ለማጣመም የሚሞክሩ መሰሪዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ፡፡ 13- ቁርኣንን የጠላት መጫወቻ አለማድረግ፡፡ 14- ጀናብተኛ ሆኖ ቁርኣንን አለመቅራት ፤ ንጹህ ሆኖ እንጅ ቁርኣንን አለመንካት ፡፡ 15- እግር ወደቁርኣን ባለመዘርጋት ፤ ቁርኣንን ልክ እንደትራስ ባለመደገፍ ፤ ቁርኣንን ምድር ላይ ባለመጣል የቁርኣንን ክብር መጠበቅ፡፡ 16- ግንዛቤን አጥርቶ ንጽሕናን ጠብቆ እና ሙሉ ፍላጎት ኖሮት ቁርኣንን መቅራት፡፡ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዘሁሏህ አጭር ፅሁፍ የተወሰደ 👇👇 https://t.me/AlIkhilasmedresa
Hammasini ko'rsatish...
🟢የ.የሕያ አል ሐጁሪ ጭፍን ተከታይ የሆነው ከማል ሙሀመድ የተባለው ግለሰብ ለተናገረው ደካማ ንግግር ምላሽ 👉የተነሳውን ነጥብ ሸፍነህ ያልተነሳውን አታንሳ። 👉 በሀቅ ላይ ከሆነ ስምምነት ተፈላጊ ነው። 🟢የተነሱት ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች 👌የሰሊም ተልቢሶች 👌የኡማው መለያየት ሰበቦች 👌የሰሊም ሁኔታና የእናንተ አቀባበል። ወዘተ ነበሩኮ ከኩራትና እልህ ውጡና ለሀቅ እጅ ስጡ ሂዝቢያንም ራቁ። 🎙በኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (ሀፊዘሁላህ) https://t.me/Abuhemewiya
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AI-IKHILAS
“የሱና ሰዎች ለሱና ሲሉ የሰዎችን ንግግር ይተዋሉ የቢደዓ ሰዎች ደግሞ ለሰዎች ሲሉ ሱናን ይተዋሉ” ኢብኑል ቀይሚ ( ረሂመሁሏህ) https://t.me/sunah123
Hammasini ko'rsatish...
አቡ ኢልሐም አስ_ሰለፊ (የኡስታዝ ሙሀመድ ኑር)ያለቁ ና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል። 👇👇👇👇👇

https://t.me/sunah123