cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

FastMereja.com

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
37 077
Obunachilar
+7124 soatlar
+457 kunlar
+32630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዘማሪ ዲያቆን ይገረም ጸጋዬ አረፈ #FastMereja ዘማሪ ዲያቆን ይገረም ጸጋዬ ለአገልግሎት በተጠራበት ቦታ ሁሉ ገጠር ከተማ ሳይለይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራትም ጭምር ቤተክርስቲያንና ምዕመናንን ሲያገለግል ሲታዘዝ የነበረ መልካም አገልጋይ እንደነበር በቅርብ ወዳጆቹ ተነግሯል። ነፍስ ይማር ‼ **** ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇 ❗https://t.me/fastmerejahttps://t.me/fastmereja
Hammasini ko'rsatish...
😢 44
Photo unavailableShow in Telegram
ከ13 ሚለየን ብር በላይ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ በቴሌብር የዲጂታል አማራጭ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተቋም ግንባታ ፕሮግራሙ ከአገልግሎት የሚሰበሰቡ ክፍያዎችን ወደ ዲጂታል የክፍያ ስርዓት ማሸጋገር አንዱ እቅድ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል። በዚሁ መሰረት ከቴሌብር ጋር በጋራ በተጀመረው ስራ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ 13,083,547.85 ብር በዲጂታል መሰብሰብ መቻሉ በዛሬው ግመገማ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል። የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ስራ አስፈፃሚዎች እና የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት በተደረገው የስራ ግምገማ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ድረስ ያለው የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። ሃላፊዎቹ ባጠረ ግዜ ተቋሙ የዲጂታል አማራጩን ለመተግበር ያሳየው ቁርጠኝነት ለሌሎች ተቋማት አርዓያ እንደሚሆን ገልፀው በቀጣይ ሙሉ ለሙሉ የሚሰበሰበውን ገቢ ወደ ዲጂታል ማሻገሩ ላይ ትኩረት አድርግ አሁንም ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በውይይቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንደገለፁት በቀጣይ ዓመት ተቋሙ ሙሉ ለሙሉ ከገንዘብ ንክኪ ነፃ በመሆን የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን ሙሉ ለሙሉ በመተግበር የተቋሙን የዲጂታል ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። በሪፖርቱ የነበሩ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች ተለይተው የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ የተሰጠበት ሲሆን የዲጂታል አማራጩን በመተግበር አዲስ ከተማ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ የተሻለ አፈፃፀም ማሳየታቸው ተመላክቷል። **** ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇 ❗https://t.me/fastmerejahttps://t.me/fastmereja
Hammasini ko'rsatish...
👍 10
Photo unavailableShow in Telegram
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀች #FastMereja በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች። ፋስት መረጃ የእግቱን መልዕክት እንደተመለከተው ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች። ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች። ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች። **** ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇 ❗https://t.me/fastmerejahttps://t.me/fastmereja
Hammasini ko'rsatish...
👍 14👎 5👏 5
Photo unavailableShow in Telegram
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀች #FastMereja በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች። ፋስት መረጃ የእግቱን መልዕክት እንደተመለከተው ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች። ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች። ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች። **** ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇 ❗https://t.me/fastmerejahttps://t.me/fastmereja
Hammasini ko'rsatish...
የኬንያው ፕሬዝዳንት የጫት ዕገዳን በመቃወም ምርቱን እንደሚያስፋፉ ተናገሩ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አንዳንድ የአገሪቱ ግዛቶች በጫት ሽያጭ መጠቀም ላይ ያጣሉትን አወዛጋቢ ዕገዳ ውድቅ በማድረግ ምርቱ እንዲስፋፋ እንደሚያደርጉ አስታወቁ። ኬንያ ውስጥ ጫት መቃም እየጨመረ ላለው የአእምሮ ጤና ችግር፣ ለወንጀልን መስፋፋት እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ምክንያት ነው ተብሎ ይታሰባል። በኬንያ የባሕር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ሦስት ግዛቶች ባለፈው ሳምንት ጫት መሸጥ እና መቃምን ካገዱ በኋላ ጫት በሚያምርቱ አካባቢዎች ቁጣን ቀስቅሷል። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ግን ጫት ሕጋዊ ምርት መሆኑን ጠቅሰው ሽያጩም መከልከል የለበትም በማለት የግዛቶቹን እርምጃ ተቃውመዋል። ሙጉካ በመባል የሚታወቀው የጫት ዓይነት ርካሽ እና ጠንካራነቱ የሚነገርለት ሲሆን ሞምባሳ፣ ኪሊፊ፣ ታይታ ታቬታ እና ክዋሌ በተባሉት የባሕር ዳርቻ ግዛቶች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። ባለፈው ሳምንት የሞምባሳ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልሰዋማድ ሸሪፍ ናሲር ሙጉኮ የተባለው የጫት ዓይነት በተለይ በወጣቶች ላይ ባለው ጎጂ ውጤት ምክንያት ወደ ግዛታቸው እንዳይገባ፣ እንዳይዘዋወር፣ አዳይሸጥ እና እንዳይቃም ከልክለዋል። አስተዳዳሪው እንዳሉት ሞምባሳ ውስጥ በሚገኙ የሱስ መገገሚያ ማዕከላት ከሚታከሙት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የጫት ሱሰኞች ናቸው። በተመሳሳይም የኪሊፊ እና ታይታ ታቬታ ግዛቶች አስተዳዳሪዎችም በጫት ሽያጭ እና አጠቃቀም ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ አሳውቀዋል። ይህ የግዛቶቹ ውሳኔ ጫቱ በሚመረትበት ኢምቡ ግዛት ያሉ ገበሬዎችን እና ነጋዴዎችን ተቃውሞ ቀስቅሷል። ውሳኔው ተግባራዊ ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ ሥራቸውን እንዲያቆሙ እንሚያስገድዳቸው ገልጸዋል። ጫት ከሚመረትበት ግዛት የመጡ የማኅበረሰብ መሪዎች በጫት ላይ የተጣለውን ዕገዳ በተመለከተ ሰኞ ዕለት ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተወያይተዋል። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “ጫት [ሙጉካ] በሕግ የታወቀ ነው፤ ስለዚህም ከአገሪቱ ሕግ ተቃራኒ የሆኑ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ብሏል። ፕሬዝዳንት ሩቶ እንዳሉት ጫት በአገሪቱ ሕግ እንደ አንድ ምርት የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚህ የበጀት ዓመት በአገሪቱ ያለውን የጫት ምርት ለማስፋት መንግሥታቸው 3.7 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመድብ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ ሁለት የመብት ተከራካሪዎች ግዛቶቹ በጫት ላይ ያጣሉትን ዕገዳ ተቃውመው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ሞምባሳ ውስጥ የተጣለው የጫት ዕገዳ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ባለፈው አርብ ከ10 በላይ የጫት ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል። ዕገዳው ከበርካታ የሃይማኖት ተቋማት ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ በሞምባሳ ያሉ ሙስሊም መሪዎች ጫት ከተከለከሉ ዕጾች መካከል እንደመደብም እየጠየቁ ነው። ምንም እንኳን የኬንያ ብሔራዊ ፀረ ዕጽ ተቋም በጫት ላይ ዕገዳ ባይጥልም፣ ቅጠሉ በውስጡ በያዛቸው ንጥረ ነገሮች ምክንያት ጎጂ ብሎ ለይቶታል። ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው
Hammasini ko'rsatish...
👍 14👎 9 2
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ኤርትራዊያን በእስራኤል ዉስጥ በፈጠሩት ግጭት አንድ ሰዉ መሞቱ ተሰማ በደቡብ ቴል አቪቭ በኤርትራ መንግስት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚ ስደተኞች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው በስለት ተወግቶ መሞቱን ፖሊስ እና የህክምና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል። የማጌን ዴቪድ አዶም አምቡላንስ አገልግሎት እንደገለጸው በግጭቱ ሌሎች አምስት ሰዎች ቆስለዋል ያለ ሲሆን ሶስቱ በከፋ ሁኔታ ዉስጥ እንደሚገኙ ገልጿል። ፖሊስ ግጭቱን ተከትሎ ከ20 የሚበልጡ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቆ በነፍስ ግድያ የተጠረጠረውን ግለሰብ እያጣራ  መሆኑም ተዘግቧል። ቀደም ሲል በእስራኤል እና በሌሎችም የአዉሮፓ ሀገራት በኤርትራውያን ስደተኞች መካከል ተመሳሳይ ሁከት ሲፈጠር ታይቷል። ይህም ማለት ባለፈው መስከረም በቴል አቪቭ ውስጥ ቢያንስ 170 ሰዎች እና የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ የተጎዱበትን ከፍተኛ ግጭት እንተጠበቀ ሆኖ እንደማለት ነዉ። በተጨማሪም በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በደቡብ ቴል አቪቭ በመሰል ጥቃት ስደተኛ ለገዥው የኤርትራ መንግስት ደጋፊ ነበረች የተባለች ሴት በስለት መገደሏ ተነግሯል። በተመሳሳይ በናታኒያ አንድ ኤርትራዊ በስደተኞች መካከል በተደረገው ግጭት በጦርነቱ ተወግቶ ተገድሏል። በዚህ ሁካታ ዘጠኙ ተጎድተዉ አንድ ሰው በከባድ ቆስሎ ነበር ሲል ብስራት ሬዲዮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። **** ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇 ❗https://t.me/fastmerejahttps://t.me/fastmereja
Hammasini ko'rsatish...
😢 5👍 1
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተሸላሚው ሺሃብ ሱሌይማን #FastMereja እንኳን ደስ አለህ ሺሃብ ሱለይማን የ2024 STRIDE ሽልማት በወጣቶች ዘርፍ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተሸላሚ በመሆንህ እንኳን ደስ አለህ። በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ እየሰራህ በምትገኝበት ዘርፍ በአፍሪካ ብሎም በአለም ተጽኖ መፍጠር የሚችል አቅም እና የወደፊት ተስፋ እንዳለህ አምናለሁ። ደስ ብሎኛል!
Hammasini ko'rsatish...
👍 20 3
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ ግንቦት 21 ቀን 2016 ቅዱስ ፓትርያርኩ በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተናገሩት
Hammasini ko'rsatish...
😢 41👍 9 3
አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ለ1 አመት የሚያገለግል ድምፅ አልባ ጄኔሬተር የፈጠረው የወለጋው ፌዴሳ ሹማ። #FstMereja ፌዴሳ ሹማ ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን፣ በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያው ይታወቃል፡፡ ይህን የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራውን የመብራት መጥፋት እና መቆራረጥ ብዙ ጊዜ አስተጓጉሎበታል። "ችግር ብልሃትን ይወልዳል" እንዲሉ ወጣቱ ሥራውን በተደጋጋሚ ላስተጓጎለበት ችግር መላ መዘየድ እንዳለበት አሰበ፤ አስቦም ወደ ተግባር ገባ። ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ወጣት ፌዴሳ ሹማ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት መሣሪያ የፈጠራ ባለቤት ነው፡፡ ፈዴሳ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በሚመራው ልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሐ ግብር ተሳትፎው ባገኘው ስልጠና እና ሙያዊ ድጋፍም ቴክኖሎጂውን ይበልጥ አዘምኖ መሥራት ችሏል። ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ለፍሪጅ እና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስ እና በገመድ እና ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው። አንዴ የያዘውን ኃይል ደጋግሞ እያደሰ (recycling) ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን ብቻ ሣይሆን ምን አልባትም በዓለማችን ላይ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት መፍጠር እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል። ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅም እና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ ያረጋገጠው። በዚህም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው ሰው መሆኑን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ የሚያመላክተው ሲል ኢቢሲ ዘግበዋል። አሁን ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወጣቱ የራሱን ኩባንያ የሚከፍትበትን እና ቴክኖሎጂው በስፋት ተመርቶ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሚቻልበትን ሁኔታ ላይ እየሠራ ይገኛል ተብሏል። **** ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇 ❗https://t.me/fastmerejahttps://t.me/fastmereja
Hammasini ko'rsatish...
👏 60👍 21