cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Dagi mu💜💖💑😜

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
156
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🔶ክፍት የስራ ቦታ🔶 ✅ዋና ፋይናንስ ማናጀር💸 ✅ፃታ. ሴት 🙎 ✅ሰፈሯ ሰሚት ኮንደምንየም የሆነ🏘 ✅ሆቴል ላይ ወይም ካፎ ከ 2 አመት በላይ የስራ ልምድ ያላት🏨 ✅በሙያው ድግሪ እና ከዛ በላይ ያላት 👩‍🎓 ✅ደሞዝ በስምምነት💵 📲 0936689368 📲 0912124984 📲 0940428246 ወይም @fegegitawechu ቴሌክራም ላይ ዶክመንታችሁን መላክ ትችላላችሁ
Hammasini ko'rsatish...
የቆሰሉት ተመራቂ ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። በትግራይ ክልል ዓዲመስኖ በተባለው ቦታ ላይበታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የቆሰሉ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል። የቆሰሉትና ከጥቃቱ አካላዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደ አዲስ አበባ ከገቡት ሃያ ስምንቱ ተመራቂዎች ትላንት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲያርፉበት ካዘጋጀላቸው ሆቴል ድረስ በመሄድ አመሻሹ ላይ የቆሰሉትን ተማሪዎች የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደወሰዷቸው የሆስፒታሉ ክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት አሳውቀዋል። ዶክተር ይርጉ ሶስቱ በጥይት አጥንታቸውን ስለተመቱ ተኝተው እየታከሙ ነው ብለዋል። ቀሪ አምስት ቁስለኞች በተመላላሽ መታከም እንደሚችሉ ዶክተር ይርጉ ገ/ህይወት ገልፀዋል። ቆስለው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ካሉ ተመራቂዎች መካከል ስድስቱ በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ፍንጣሪ ያገኛቸው ናቸው ተብሏል፡፡ ተመራቂዎቹ እንደተናገሩት ያረፉበት "ካሌብ ሆቴል" ምግብ ሆስፒታል ድረስ እያመላለሰላቸው ነው፡፡ ተመራቂዎቹ ከደረሰባቸው ጥቃት ባሻገር ንብረታቸውን በመዘፈረፉ የካሌብ ሆቴል ሰራተኞች ገንዘብ አዋጥተው ቅያሪ ቲሸርት ገዝተው እንደሰጧቸው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 @fegegitawechu @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
13 ቀናት የቀሩት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና... በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 ዓ/ም ሳይሰጥ የቀረው የ2012 የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29 ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል። ኢቢስ ቲቪ ከቀናት በፊት ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወረቀቶች ማተም እንዲጀመር ትዕዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ትዝእዛዝ የተሰጠው ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ሲሆን ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 የፈተና እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች በመላ ሀገሪቱ ባሉ ፈተና ጣቢያዎች ይሰራጫሉ ተብሎ ይጠበቃል። በፀጥታ በኩልም ከፈተናው ስርጭት ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰላማዊ እንዲሆን ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ እየተሰማ ነው። የ2012 ፈተናን 450 ሺህ ተማሪዎች እንደሚወስዱት ይጠበቃል። ፈተናው ረጅም ጊዜ በመዘግየቱ በተማሪዎች ላይ እንዲሁም በወላጆች ላይ ከፍተኛ የስነልቦ ጫና መፍጠሩ ሲገለፅ ቆይቷል። አሁን ፈተናው ሊሰጥ 13 ቀናት ብቻ ነው የቀሩት። ተፈታኝ ተማሪዎች እያደረጋችሁት ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል? ወላጆች ልጆቻችሁ ለፈተናው ብቁ ሆነው እንዲቀርቡ እያደጋችሁት ያለው የስነ ልቦና ዝግጅትስ እንዴት ይገለፃል ? ት/ ቤቶች ተማሪዎቻችሁ ፈተናውን በውጤት ያጠናቅቁ ዘንድ ምን አስተዋፅኦ እያደረጋችሁ ነው ? ሀሳብ ያላችሁ በአስተያየት መስጫው ማካፈል ይቻላል። @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
ኦሮሚያ ለሲዳማ ክልል 100 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደሚያበረክት ገለፀ። በዛሬው ዕለት በሀዋሳ "ጉዱማሌ" እየተካሄደ በሚገኘው የሲዳማ ክልል ይፋዊ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሚያ ክልል ለአዲሱ የሲዳማ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደሚያበረከት ገለፁ። የክልሉ ፕሬዜዳንት በስነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ወቅት ነው ይህን ይፋ ያደረጉት። @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
ሲዳማ ክልል - 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ በዓል ! ነገ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ይፋዊ የምስረታ በዓል ይከበራል። በዚህ የክልል ምስረት ይፋዊ በዓል ላይ ለመታደም በርካታ የፌደራል እንዲሁም የክልል መሪዎች ሀዋሳ ገብተዋል። የሲዳማ ክልል ሀዋሳ ነዋሪዎች ፣ የከተማው አመራሮች እንግዶቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ። ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር @fegegitawechu @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
😀😂😋😋🤓🤔😷🙈🙊🙆🏿🤦🏻ol Join 👇👇 @fegegitawechu @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
እጅግ አደገኛ ናቸው የተባሉ የዘረፋ እንዲሁም የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ተያዙ ! የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ አካባቢዎች በቡድን በመደራጀት የዘረፋ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 53 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ እጅግ አደገኛ እና ደጋጋሚ ወንጀል ፈፃሚዎች መሆናቸውን ከጣት አሻራ ሪከርዳቸው ማረጋገጥ እንደተቻለ ተገልጿል። ከተጠርጣሪዎች መካከል ለ55 ፣ ለ30 እና ለ10 ጊዜ የወንጀል የጣት አሻራ ሪከርድ የተመዘገበባቸው መገኘታቸውን ታውቋል። በ4 ቡድን የተደራጁ 36 ተጠርጣሪዎች በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች ባንክ ቤትን ጨምሮ በተለያዩ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥናት በማድረግ እና በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የወንጀል ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው 4 ሽጉጦች ፣ የካዝና መሰርሰሪያ እና ለወንጀል ተግባራቸው የሚገለገሉባቸው ሌሎች ቁሳቁሶች እና ተሽከርካሪዎች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ሙሉ በሙሉ ሊያዙ መቻላቸውን እና 14 የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ፖሊስ ገልጿል @fegegitawechu @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
979 የመትረየስ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ። በአርባ ምንጭ ከተማ በሼቻ ቀበሌ ዶይሳ ቀጠና ወጣት ማዕከል መንደር በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 979 የመትረየስ ጥይት በወጣቶች ወንጀል መከላከል ስራ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ። እንደ አርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ኃይለሚካኤል ጉላንታ ገለፃ ፥ ከትላንት በስቲያ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ40 ደቂቃ በሰላምና ፀጥታ አደረጃጀት መንደሩን በወንጀል መከላከል ስራ ሲጠብቁ በነበሩት ወጣቶች ተሳትፎ ተጠርጣሪ አቶ ታማኝ ዳቲኮ የተባለ ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ ከአርባ ምንጭ ወደ ጉማይዴ ሲያንቀሳቅስ የነበረውን 979 የመትረየስ ጥይት በቁጥጥር ስር አውለዋል። የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች እስካሁን ላደረጉት እና እያደረጉ ላሉት አስተዋፅኦ ምስጋና ቀርቦላቸዋል። መሰል ወንጀል መከላከልና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግም ጥሪ መቅረቡን የአርባ ምንጭ ከተማ ኮሚኒኬሽን ገልጿል። @fegegitawechu @dagi_mu
Hammasini ko'rsatish...
😂😀 Join👇 @fegegitawechu
Hammasini ko'rsatish...
1.82 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.