cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ተዋህዶ ሃይማኖቴ_Orthodox

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። #ተወህዶ ሃይማኖቴ #የዘላለም ቤቴ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማግኝት ቻናሉን ይጎብኙ ለማንኛዉም ሀሳብ ጥቆማ 📩 @orthodoxemnete_bot ላይ ብያስቀምጡ ይደርሰናል ✞ ማንም እንዳያስታቹ ተጠንቀቁ ማቴ 24:5✞

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
225
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ወይም ለቤተክርስቲያንህ መባን መጻሕፍትንም ለሚሰጥ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስስለታለሁ። ገድልህንም የሚጽፈውን፣ ወይም የሚያነበውን፣ የሚሰማውን፣ ወይም የሚገዛውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ"። ❤ ከዚህም በኋላ ብዙዎች ከንጉሥ ሠራዊትና ከሕዝቡ ተሰብስበው በንጉሡ ላይ እንዲህ ብለው ጮኹበት "አንተ ከሀዲ እግዚአብሔር ያጥፋህ ከጠላቶቻችን ያዳነንን ኃያልና ጽኑዕ የሆነውን የከበረ ቴዎድሮስን ታሠቃየዋለህና" ይህንንም ብለው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ያን ጊዜም ንጉሥ ተቆጥቶ ሁሉንም አስገደላቸው ሰማዕትም ሆኑ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ አዘዘ የብረት ዐልጋም አምጥተው ቅዱሱን በላዩ አስተኙት ከበታቹም እሳትን አነደዱ ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ ጸለየ "አቤቱ ፈጣሪዬ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ምድጃ እንደ አዳንካቸው አድነኝ ። ወዲያውኑም ያ እሳት ጠፋ እንደ ንጋት ጊዜ ቊርም ሆነ። ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የተሰጠህ ሆይ ጽና በርታ" ያን ጊዜም ቅዱሱ ተነሥቶ በንጉሡ ፊት ቆመ እንዲህም አለው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖኛልና አንተ ከሀዲ እፈር" አለው። የንጉሡም የጭፍራ አለቃ ይህን በአየ ጊዜ "ክቡር ቴዎድሮስ ከሚያመልከው ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ ጮኸ ርሱንም ራሱን አስቆረጠውና በሰማዕትነት ሞተ። ❤ ቅዱስ ቴዎድሮስንም ብዙ ከአሠቃየውና ማሠቃየቱ ከሰለቸው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም እንዲአቃጥሉ አዘዘ። በጌታችንም ፈቃድ ከእናቱ ደጅ ወስደው እራሱን ቆረጡ ከእርሱም ደም፣ ወተትም ፈሰሰ ታላቅ እሳትም አንድደው ሥጋውን በውስጡ ጨመሩ እሳቱም ከቶ አልነካውም። እናቱም ለወታደሮች ብዙ ወርቅ ሰጥታ ሥጋውን ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው እስከ መከራው ፍጻሜም በቤቷ ውስጥ አኖረችው። ❤ ከዚያ በኋላም አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩለት ስብጥ በሚባል በአባቱ አገርም በተሠራች ገዳም ሥጋውን አኖሩ ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ተደረጉ ታላቅ ፈውስም ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በበሰማዕቱ ቅዱስ ቴዎድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ሰላም ለቴዎድሮስ ማር። ሊቀ ሠራዊት ክቡር። በረድኤተ አምላክ ባሕቲቱ እምሕዝበ በርበር። መስተጽዕናነ አፍራስ አኅለቀ ለእለሂ ዘእግር። እስከ ኢያትረፈ ነፋጼ ለዝክር"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 20። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ሕገ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ። ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ። ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ"። መዝ18፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ6፥35-48። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። @sigewe
Hammasini ko'rsatish...
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሐምሌ ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋር ወደ መቅደስ ለተወሰደችበት ቀን መታሰቢያ በዓልና ለታላቁና ለክቡር ለሆነ ለሠራዊት አለቃ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ቴዎድሮስ ለዕረፍት በዓለ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከታአኪጦስ፣ ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ ጢሞቴዎስ ከሙሴ፣ ከኢየሉጣ ከመታሰቢያቸውና ከሕፃኑ ከቅዱስ ቂርቆስ ጋር በሰማዕትነት ከአረፉ ከአራት መቶ አራት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የሠራዊት አለቃ ሰማዕቱ ቅዱስ ቴዎድሮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ። አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች። ❤ ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው። ❤ ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቴዎድሮስንም ጠርቶ "ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ" አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ ይበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና"። ንጉሡም "እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ" አለው። ❤ በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም "የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና" አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ ደሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በእግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም"። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ "ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ" አላቸው። እነርሱም "ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን" አሉት እርሱም "ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ" አላቸው። "ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ" አሉት። ❤ ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ "ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው ጌታዬ አምላኬ ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን"። ❤ ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በመስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ "እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ" እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ። ❤ አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው። ❤ በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው። ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል እግዚአብሔርም ይበቀልላታል" አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው። ❤ ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው "አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል"። ❤ በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት። በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው "ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ" እነሆ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ "መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማውን ለሚያጠጣ፣
Hammasini ko'rsatish...
🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨 ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል ፲፱ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡ ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ። ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡ ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ ዚቅ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። መልክአ ቂርቆስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡ ዚቅ ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር። ወረብ ኢየሉጣ ወለደት/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ። ዚቅ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት። ወረብ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/ ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ። ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ። ዚቅ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡ ወረብ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/ ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡ ዚቅ በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡ ወረብ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/ ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/ መልክዐ ኢየሉጣ ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡ መልክዐ ገብርኤል ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ። ዚቅ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት። ወረብ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/ እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/ ምልጣን፦ ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ አመላለስ: ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/ ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/ ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ እስመ ለዓለም ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡ አመላለስ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/ ወረብ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/ እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE 💚 •✥•@Tewahido_enate•✥•💚 💛 •✥•@Tewahido_enate•✥•💛 💖 •✥•@Tewahido_enate•✥• 💖
Hammasini ko'rsatish...
ገብርኤል በሰማይ ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር/2/ ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር/2/ ትፀንሺ ሲልክ በከበረ ዜና ይሁንልኝ አልሽው ትውልድ እንዲፅናና ከገብርኤል ሰምተው መላዕክቱ ሁሉ ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ ብፅሂት እንላለን እኛም አደግድገን የራማውን ልዑል አብነት አድርገን / አዝ ======= ስርሽ በምድር ነው ሀረግሽ በሰማይ ንፁህ መሶበ ወርቅ የተመላሽ ሲሳይ የማህፀንሽ ፍሬ በላነው ጠጣነው በኤፍራታ ሰምተን በዱር አገኘነው የተሰወረውን መና በልተነዋል ከተመረጡት ጋር ብፅሂት ብለናል /አዝ ======= ከተፈጥሮ በላይ ፅንስን ያዘለለ የእሳት ምሰሶ ባንቺ ተተከለ የእግዚአብሔር ሀገሩ የእንጀራ ቤታችን ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን ብፅይት እንላለን እኛም አደግድገን ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን / አዝ ======= ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዪት ሰዉና መላዕክት አብረው አከበሩት የጥሉ ግርግዳ በልጅሽ ፈረሰ በዳግማዊት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ እጅ እንነሳለን ሁነን በትህትና ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነው እና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE 💚 •✥•@Tewahido_enate•✥•💚 💛 •✥•@Tewahido_enate•✥•💛 💖 •✥•@Tewahido_enate•✥• 💖
Hammasini ko'rsatish...
ድንግል_ማርያም_ብዬ_ሊቀ_መዘምራን_ኪነጥበብ_@DNZEMA_ዜማ_ቅዱስ_ያሬድ.mp33.94 MB
#ሃያል_ነህ_አንተ ሃያል ነህ አንተ ሃያል ደጉ መልአክ ገብርኤል ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት አንተ ተራዳን በእውነት #አዝ በዱራ ሜዳ ላይ - ገብርኤል ጣኦት ተዘጋጅቶ - ገብርኤል ሊያመልኩት ወደዱ - ገብርኤል አዲስ አዋጅ ወጥቶ - ገብርኤል ሲድራቅ እና ሚሳቅ አብደናጎ ፀኑ፤ ጣኦቱን እረግጠው በእግዚያብሄር አመኑ #አዝ ተቆጣ ንጉሱ - ገብርኤል በሶስቱ ህፃናት - ገብርኤል ጨምሯቸው አለ - ገብርኤል ወደ እቶን እሳት - ገብርኤል ከሰማይ ተልኮ ወረደ መላኩ፤ ከሞት አዳናቸው በሳት ሳይነኩ። #አዝ ከእቶኑ ስር ሆነው - ገብርኤል ዝማሬ ተሞሉ - ገብርኤል ገፍተው የጣሏቸው - ገብርኤል በእሳቱ ሲበሉ - ገብርኤል አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር፤ አዩ መኩአንንቱ የእግዚአብሄርን ክብር። #አዝ ናቡከደነፆር - ገብርኤል እጁን ባፉ ጫነ - ገብርኤል ሰለስቱ ደቂቅን - ገብርኤል ከእሳት ስለአዳነ - ገብርኤል ይክበር ጌታ አለ የላከ መላኩን፤ ሊአመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE 💚 •✥•@Tewahido_enate•✥•💚 💛 •✥•@Tewahido_enate•✥•💛 💖 •✥•@Tewahido_enate•✥• 💖
Hammasini ko'rsatish...
ድንግል_ማርያም_ብዬ_ሊቀ_መዘምራን_ኪነጥበብ_@DNZEMA_ዜማ_ቅዱስ_ያሬድ.mp34.05 MB
#አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት_ዘገዳመ_ዋሊ (ዋልድባ ገዳም) ❖ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የቅዱሳት መካናትን የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት። ✞☞ "ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!! ☞ እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተስፋ ሐዋርያት ዘዋልድባ በዓለ ዕረፍት በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!! ፠ በባለቤቱ በመድኃኔዓለምና በእናቱ በእግዝትነ ማርያም በ3 ዓ.ም ተባርኮ የተገደመው ታላቁ ዋልድባ ገዳም በርካታ ቅዱሳን የፈለቁበት መካነ ግሑሣን ነው። እነዚህ ቅዱሳን አንዳንዶቹ ለጸሎትና ለበለጠ ተጋድሎ፣ ሌሎቹ ለበረከት፤ ገሚሶቹም ለሱባዔ ወደ ቦታው ሄደው ለብቃት ደረጃ የደረሱበትና በጸጋ ላይ ጸጋ ያገኙበት ቦታ ነው። ከእነርሱም አብዛኞቹ ቅዱሳን በተለያዩ ገዳማቸው ስማቸው ይዘከራል፡፡ ነገር ግን በዋልድባ ኖረው ስማቸውና ዝክራቸው በዋልድባ የሆነላቸው ዐበይት ቅዱሳን አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ዐበይቶቹ፦ ☞ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ ☞ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ዘዋልድባ፣ ☞ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘዋልድባ፣ ☞ አቡነ ገብረ መስቀል ዘዋልድባ፣ ☞ አቡነ ሚናስ ዘዋልድባ፣ ☞ አቡነ ዘጰራቅሊጦስ፣... ይገኙበታል፡፡ #አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት_ዘዋልድባ (ዘገዳመ ዋሊ) ፠ የጻድቁ አባታቸው መብዓ ሐዋርያት፣ እናታቸው ወለተ ሐዋርያት ሲሆኑ የተወለዱት ሽሬ አካባቢ ነው። የአባታቸው መካነ ትውልድ ሰሜን ጎንደር ሲሆን የእናታቸው ደግሞ ትግራይ ሽሬ ነው፡፡ ፠ ጻድቁ አባታችን ሰነ 20 ቀን በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እጅ ነው የመነኰሱት። በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት የነበሩ ጻድቅ ሲሆኑ፤ ዐፄ ልብነ ድንግል ወደ ዋልድባ ሄዶ በረከትን ተቀብሏል፡፡ ጻድቁ በአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትእዛዝ መሠረት ከአቡነ ሳሙኤል ቀጥለው በገዳመ ዋሊ የተሾሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት በአቡነ ሳሙኤል መቃብር ላይ የፈለቀውን ጠበል ለአትክልት አንድ ጊዜ ብቻ በማጠጣት ለብዙ ጊዜ ዳግመኛ አያጠጡትም ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ በዋልድባ አካባቢ ያለው የለምነት ምሥጢር ይኸው እንደሆነ ይነገራል፡፡ ፠ የአባ ነፃ ማኅበርንም በገበዝነት ያስተዳደሩ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በዚህም አበ መነኰሳት (አበ ማኅበር) በመባል ይጠራሉ፡፡ ገዳመ ዋሊ ከመግባታቸው በፊት ገለባ፥ ሣር እየበሉ፥ ውኃ እየጠጡ፤ ለሌሎች ወንድሞቻቻው ግን እንጀራና ጠላ ያዘጋጁ ነበር፡፡ ነገር ግን ዘንዶ መጥቶ ያዘጋጁትን ጠላ ላይ መርዙን ተፋበት፤ እርሳቸው ግን መርዙን እየቀመሱ አወጡት፤ ዘንዶውንም የጠጣውን እንዲያፈስ አስደረጉት፡፡ ፠ በዚህ ጊዜ አንድ ኅርመተኛ አይቶ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ምግቤ ሣርና ገለባ ነው ይላሉ እንጂ፤ ጠላ ይጠጣሉ ብሎ አማቸው፤ እርሳቸው ግን ለማኅበሩ ጥቅም ይህን ነገር እንዳደረጉ ቢናገሩም ሊያመኗቸው ስላልቻሉ እንደ ማኅበረ ዶጌ ጽዋ፥ የጠጣሁባት ጽዋ ትናገር ብለው፤ ጽዋዋም ከውኃ ውጭ ጠላ አልጠጣብኝም ብላ እንድትመሰክር ያደረጉ አባት ናቸው፡፡ ፠ አንዲት እርጉዝ ጅብ ልጇን ስትወልድ የምትበላው አለመኖሩን አይተው፤ አርባጫውን (ምስጥ/ኵይሳ/ የበላውን ቀይ አፈር) ባርከው ሥጋ አርገው አርሰዋታል፡፡አቡነ ያዕቆብ ዘወለቃ ዘቀዳሚት ደብረ ከርቤም የተራበች ጅብ አፍ አውጥታ መራቧን ነግራቸው፤ እንደ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ዘዋልድባ በተአምራት መግበዋታል፡፡ ፠ ጻድቁ በርካታ ቅዱሳንን የወለዱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አቡነ ምስራቃዊን ያመነኰሱ አባት ናቸው፤ ፠ ታላቁ ገዳማቸው አባ ነጻ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ በዋልድባ ቅጥር ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከአብረንታንት የማይሰሬ ወንዝ እንደተሻገሩ የ3 ሰዐት የዕግር ጕዞ ፤ ወይም በወልቃይት መዘጋ መስመር በኩል ደግሞ፤ በማይጋባ ከተማ የዛሬማን ወንዝ እንደተሻገሩ በአንድ ሰዐት የእግር ጕዞ ላይ የሚገኝና ልቡናን የሚመስጥ ቦታ ነው፡፡ ፠ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ልዩ ስሙ «አባ ነፃ» በተባለው ቦታ ገዳማቸውን ከመሠረቱ በኋላ በዋልድባ ያለውን የአንድነት ማኅበሩን በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረውታል፡፡ በጣም ብዙ መነኮሳትንም አፍርተዋል፡፡ ፠ በአስደናቂው ተጋድሏቸው የሚታወቁት ጻድቁ አባታችን በነብር ተቧጭረው እንደሚሞቱ አስቀድመው ተናግረው ስለነበር ነብሯ መጥታ ቧጨረቻቸው። ክቡር የሆነ ቃልኪዳንን ከጌታችን ተቀብለው በተወለዱ በ98 ዓመታቸው ሐምሌ 15 ቀን በዚች ዕለት ከሥጋ ድካም በክብር ዐርፈዋል። መቃብራቸው ለብዙ ዘመናት በተጋደሉበት በአባ ነጻ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ገዳም ይገኛል። ፠ ጻድቁ ከመቃብራቸው ላይ የፈለቀ ተአምረኛ ፈዋሽ ጠበልም አላቸው። የጻድቁ ደቀመዛሙርት የነበሩ መነኮሳት ይህንን ጠበል የቋርፍ ማዘጋጃ ለሚሆን አትክልት (ሙዝና ስኳር ድንች) አንድ ጊዜ ብቻ ያጠጡበታል፤ ከዚያ በኋላ ግን ደግመው ሳያጠጡት በጻድቁ በረከት አትክልቱ አድጎ ያፈራል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር። ለዘላለሙ አሜን! ★ ምንጭ፦ ዋልድባ ዋሊ ገጽ ❖ በመንፈሳዊ ጉዞዎቻችን መርሐ ግብራት በመሳተፍ ቅዱሳት መካናትን አብራችሁን ለመሳለም የምትሹ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ! ❖ ባላችሁበት አካባቢ በመመዝገብ (ትኬት በመቁረጥ) በየትኛውም የጉዞ መርሐ ግብራችን ለመሳተፍ፦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዋሽ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች በካሽ ወይም በሞባይል ባንኪንግ በሚከተሉት የመምህር አንተነህ ውብሸት አካውንቶች አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይንም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ። ☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899 ☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900 ❖ ይህን የመንፈሳዊ ጉዞ መልዕክት እርሶ በሚጠቀሙበት ድህረገጽ ላይ ሼር በማድረግ ይተባበሩን። ✞❖✞ ለበለጠ መረጃ፦ ☞ 0901070707 / 0911289877 / 0941960723 #ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ @Tewahido_enate
Hammasini ko'rsatish...
✏️@bisrategebrel📖 የእመቤታችን የከበረ ድንቅ ሥዕሏ ምሳሌ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታን የስቅለቱን ሥዕል እንደሣለ ሊቁ በመልክአ ሥዕል ላይ፦ "ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዐሞዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ" (ርኄና ቀናንሞ ሽቱ የተባለ ዮሐንስ ለሳመው ለልጅሽ ሥዕልና ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) እንዳለ በተመሳሳይ መልኩ ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ለመዠመሪያ ጊዜ የቅድስትድንግል ማርያምን ሥዕል የሣለ ነው የመልክአ ሥዕል ደራሲ ሊቁ፡- “ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ” (ከወንጌላውያን አንዱ ዐዋቂ ሉቃስ በእጅ ለሣላት ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) ብሏል። ❖ ይኽቺም የሣላት የእመቤታችን ሥዕል ከላይዋ ላይ ዘይት እየፈሰሰ፤ ወዝ እየወዛ ብዙ ተአምራትን ትሠራ ነበር፤ ሊቁም ከዚኽ ተነሥቶ፦ "ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማሕየዌ በጼዴንያ ወግብጽ ወአውኀዘት በኢሕሳዌ" (በጼዴንያና በግብጽ ያለምንም ሐሰት የሚያድን ወዝን ላፈሰሰች ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) በማለት ገልጾታል፨ ❖ ባለንበት ጊዜም በግብጽ በፓርት ሳይድ ቤተ ክርስቲያን ባለች የእመቤታችን ሥዕል ላይ መዐዛዋ እጅግ የሚደንቅ ዘይት የሚፈስስ ሲኾን እጅግ ብዙ ሕሙማን የሚፈወሱባት እንደኾነ ኼጄ አይቼያለሁ፨ ❖ ቅዱስ ሉቃስ አመቤታችንን ከተወደደ ልጅዋ ጋር የሣለ የመጀመሪያው እንደኾነ ዓለም ዐቀፍ የኦርቶዶክስ ሊቃውንት (The tradition of the Orthodox Church maintains that the first iconographer was the evangelist Luke, and that the first icon he painted under divine inspiration was of the Mother of God holding the Christ-child) በማለት ሲገልጹ፤ በሰማዕታት ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በመከራው ሰዓት በሚደበቁበት ግበበ ምድር (ካታኮምብ) ዋሻ ግድግዳ ላይ ቅዱስ ሉቃስ እንደሣላት እያስመሰሉ የእመቤታችንን ሥዕሏን ይሥሉ ነበር፡፡ ❖ ለምሳሌ በሮሜ ባለው 3 ክፍል ባለው የፕሪስኪላ ግበበ ምድር ዋሻ (The Catacomb of Priscilla on the Via Salaria) ውስጥ በ150 ዓ.ም. የተሣለ የእመቤታችን ሥዕሏ ተገኝቷል። በ3ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተሣለው ከ1700 ዓመት በላይ የመላው እመቤታችን ጌታን ዐቅፋው ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ሲያቀርቡለት የተሣለው ሥዕል በቫቲካን ሚዪዚየም ይገኛል፨ ❖ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ እንደምናነብበው በ460 ዓ.ም. ያረፈችው የንጉሥ ቴዎዶስዮስ 2ኛ ሚስት ኢውዶኪያ “መራሔ ፍኖት” ተብላ የምትጠራውን ቅዱስ ሉቃስ የሣላትን ሥዕል ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለንጉሥ አርቃዴዎስ ልጅ ለፑልቼሪያ ልካላት ነበር፤ በቅዱስ ትውፊት ቅዱስ ሉቃስ በዘመኑ የእመቤታችንን ሥዕሎችን የሣለ ሲኾን እነዚኽም የተለያዩ ጥንታውያን ሀገራት ውስጥ ሲገኙ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥንታውያን ገዳማት ውስጥ ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ሥዕላት በተለያየ ጊዜ እንደመጡ ሊቃውንት ይናገራሉ (Cormack, Robin (1997) Painting the Soul, Icones, p.46)፡፡ ❖ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ሠዐሊያን የእመቤታችን የተለያዩ ሥዕላቷን ሲሠሩ በታላቅ ጥንቃቄና አክብሮት ውበቷን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ክብሯን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ጥንካሬዋን በሚገልጽ መልኩ ነው፨ ❖ ይኸውም በግንባሯና በግራና ቀኝ ትከሻዋ 3 ከዋክብት ሲያደርጉላት ይኸውም በሦስት ወገን ጌታን ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችው ጊዜ፤ ከወለደችው በኅዋላ ድንግል መኾኗን ለመግለጽ ነው። ጥቂት መናገሯን ለማመልከት አፏን አነስ አድርገው ይሥላሉ፨ ❖ ድንግልም እናትም መኾኗን ለማመልከት ደናግል በእስራኤል የሚለብሱትን ሰማያዊ እና እናቶች የሚለብሱትን ቀይ ልብስ አጎናጽፈው ይሥሏታል፤ ዳግመኛም ያገኛት 5ቱን ዐዘናት በቀይ፤ አማናዊ ፀሐይና የዐጥቢያ ኮከብ የተባለ ጌታን የወለደች ዳግሚት ሰማይ መኾኗን ለማመልከት በሰማያዊ መጎናጸፊያ ይሥሏታል። ❖ በጽርዕ ጥንታዊ አሣሣል ከበላይዋ “MP OY”, የሚል ምሕጻረ ቃል ሲጽፉ በጽርዕ ማቴር ታዖስ “Mater Theos” ማለት እመ አምላክ ማለት ሲኾን በጌታ ሥዕል ጎን IC XC (ኢየሱስ ክርስቶስ) ብለው ይጽፉ ነበር፨ ❖ ከጥንት ጀምሮ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን ሥዕላት አሣሣል ትውፊት ብዙዎች ሲኖሩ ዋናዎቹ 5 ዐይነት ናቸው እነዚኽም፦ 1) መራሒት (The Guide; Hodigitria) - ይኽቺ ሥዕል ጌታን ዐቅፋ ወደ ርሱ ታመለክታለች (ትጠቁማለች)፤ ይኽም ወደ ዘላለማዊ ሕይወት መርቶ ያደረሰን መድኅነ ዓለም ልጇ እንደኾነ ለማመልከት የተሣለ ነው፨ 2) ርኅርኅት መሐሪት (Tender Mercy; Eleusa) የምትባለው ሥዕሏ - የአምላክ እናት ልጇን ይዛ ጌታም ፊቱን ወደ ርሷ አስጠግቶ እጁን በአንገቷ ላይ አድርጎ ይታያል፨ 3) መሐሪት (All Merciful, Panakranta) – ይኽቺ የእመቤታችን ሥዕል ጌታን በጭኖቿ ታቅፋ የኹለቱም ፊት ወደ ተመልካች እያየ ይሣላል፨ ይኽም ዳዊት እንደተናገረው ምሕረትን ለማሰጠት ከንጉሡ ልጇ ቀኝ ለምልጃ መቆሟን የሚገልጽ ነው፨ 4) ተንባሊት፦ (Intercessor, Agiosortissa) – የእመቤታችን እጆቿ ለምልጃ ተዘርግተው የሚታዩ ሲኾን ይኸውም ነቅታ ተግታ ማማለዷን ለመግለጽ ነው ፊቷ ወደ ግራ አግጣጫ መለስ ብሎ ይታያል፨ 5) ሰአሊት ወሰባሒት (Praying, - Oranta , Panagia) , ትእምርተ ድንግል (Lady of the Sign)- ሲሏት የእመቤታችን ከክንዶቿ ጀምሮ ባማረ በተንቆጠቆጠ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ጌታ በማሕፀኗ እያለ በክበብ ተደርጎ ሲሳል ይኸውም "ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ስሙንም ዐማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።" ብሎ የተናገረው(ትንቢተ ኢሳይያስ 7:14) የተፈጸመባት ይልቁኑ ዓለምን የያዘውን ጌታ በማሕፀኗ ይዛ አንገቷን ዘንበል አድርጋ ቅዳሴ መላእክትን ሰምታ ማመስገኗን ያመለክታል(Theology of the Icon by Leonid Ouspensky ISBN 0-88141-124-8) ❖ የመልክአ ሥዕል ጸሐፊ፦ "በኢትዮጵያ ወግብጽ ወሶርያ በአንጾኪያ ወሮም ለሥዕላትኪ ዘሀለዋ ማርያም ሰላም" (በኢትዮጵያና በግብጽ በሶርያ በአንጾኪያና በሮም ያሉ ለኾኑ ሥዕሎችሽ ሰላምታ ይገባል) እንዳለ። ቅዱስ ሉቃስ ሆይ ቅዱስ ወንጌልን በጻፈው እና የአምላክን እናት ሥዕሏን በሣለው እጅኽ እንድትባርከን እንለምንኻለን፡፡ (የቅዱሳት ሥዕላት ክብር በዘፀ 25:18-22, ዘፀ 26:1፤ ዘኁ 7:99፤ 1ኛ ነገ 6:29-32፤ ሕዝ 4:1፤ ገላ 3፡1) ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ በ ዲ/ን ቃለአብ ግርማ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች #share ☝☝☝☝☝☝ @Tewahido_enate @Tewahido_enate @Tewahido_enate
Hammasini ko'rsatish...
በስስ አንጀታቸው ስለሚለማመኑት ስለ አክሱም እና ባህርዳር እናቶች ብለህ ስለሰላማችን ተማለደን። ~~~~~~~~~~~~~~~ እውነት ነው መቅደስ ከሆነች ሀገር የዲያቢሎስ ግብርን የሚያስንቁ ፍጥረታት ወጥተውብናል። እውነት ነው ከቃልኪዳኗ ሀገር ለክፋት የተማማለ የሰው ዘር ተገኝቷል። እውነት ነው ከአባቶቻችን የተረከብናት ንጽኃን ምድራችንን የደም ምድር ፤የኃጢያት አውድማ አድርገን አቆሽሸናታል ነገር ግን ነነዌን ስለጥቂቶች ደጋጎች ብለህ እንደማርካት እናውቃለን። ሕዝበ እስራኤል ስለአብርሃም እና ይሳቅ ደግነት ስትል በብዙ ምህረት እና ቸርነት ተመልክተሃቸው ከጥፋት እንዳዳንካቸው ተምረናል። እባክህን ...የእኛን የትዕቢተኞችን ቃል አትስማብን፤የቃየልን የመገዳደል መንፈስ የተላበስነውን የዘመኞችን መፍቴሄ አትመልከተው። ይልቁንስ ..ከእነዚህ እናቶች ስስ አንጀት የሚወጣውን ተማጽኖ ስማልን፤ እልፍ ኃጢያታችንን ስለደጋግ እናቶች እና አባቶች ትንሽዬ ጽድቅ ብለህ እለፈን ። ሀገራችንን ባርክልን ።ሕዝባችንንም አድን። ተሰብስበው ነበር ተበተኑ ከሚል የሴጣን መሳለቂያ ቃል ጠብቀን። እንደ ባቢሎናውያን የአንድነት ቋንቋችንን አትደባልቅብን፤እንደ ቃየል ልጆች ተቅበዝባዢ አታድርገን። እንደ ናቡክደነፆር አውሬነትን አታልብስብን ሠላም ለሀገራችን ገፃችንን #like እና #follow መልእክታችንን #share ያድርጉ // በአንዲት ቅድስት ቤተክስቲያን እናምናለን // ወስብሐት ለእግዚአብሔር ደቡብ ኢትዮጽያ -አርባምንጭ
Hammasini ko'rsatish...
በጉራጌ ሀገረስብከት የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ኦርቶዶክሳዊ ተማሪዎች ሚኒስትሪ መፈተናቸውን ምክንያት በማድረግ ጉባኤ በመስራት ምዕመናኑን ወንጌል እንዲማሩ አደረጉ ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ አሁን አሁን የብሔራዊም ሆነ ክልል አቀፍ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ዩኒፎርም በማቃጠል፣የመፈተኛ ሽታቸውን አብዝተው በመቅደድ እና ዓለማዊ መልክ ባለው ክንውን በእዛ ደረጃ ያለው የትምህርት ጉዟቸው መቋጨቱን ያበስራሉ። በጉራጌ ሀገረስብከት በእነወሪ ወረዳ ቤተክህነት ውስጥ በጃፈራ ቅድስት አርሴማ ሰንበት ትምህርት ቤት የታቀፉት የእንደጋኛ ጮራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ግን የሚኒስትሪ ትምህርታቸው መፈታናቸው በማስመልከት የአከባቢውን ምዕመናንን በማሰባሰብ መንፈሳዊ ጉባኤ ሰርተው ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመዋል። እንዲህ አይነት ልምዶች ቢስፋፉ ትውልድ በዘመናዊነት ስም በበዓዳን አስተሳሰብ የመዋጡን ዕድል ይቀንሰዋል። ለተፈተኑ ተማሪዎች የጥረታቸውን ውጤት ያገኙ ዘንድ ምኞታችን ነው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.