cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
1 342 000Obunachilar
+76924 soatlar
+3 0427 kunlar
+25 15330 kunlar
Po'stilar arxiv
" ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " - ሞህሰን አል-ማንዳላዊ የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ። እንዲሁም፦ - ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ - ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ - ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች - ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። " በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፎቶ፦ ፋይል #Iraq @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
#Ethiopia " የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዟል " - የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት " ለ2ኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ እንዲሆን እያደረገው " ነው ሲል ገለጸ። የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዘዋልም ብሏል። ማህበሩ ምን አለ ? - በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። - እነዚህ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸው በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። - በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው። እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። - የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ የቦንዳ ልብሶች ተሞልተዋል። - የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገቡ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል። - ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ (በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ። በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ይደርስባታል። - ህገወጥ በሆነ መንገድ የሚገቡት ልብሶች ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸውን ቀጥለዋል ለኪሳራም እንዲዳረጉ እያደረገ በመሆኑ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረብን ቢሆንም ምላሽ አላገኘንም። ምንጭ፦ #የካፒታል_ጋዜጣ @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
#ኢራቅ የኢራቅ ፓርላማ ፫ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ ማርቀቋን ቢቢሲ ዘግቧል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ። በአዲሱ ሕግ ፦ ➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ ➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤ ➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤ ➡️ " ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል። እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገባ ፥ መጀመሪያ ላይ ረቂቁ ግብረሰዶማውያን #በሞት_እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ ነው የተሻሻለው። የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል። #አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል የሕጉን መፅደቅ ተቃውማለች " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ተቃውማለች። " ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች። የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች ቢቢሲ እና ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
#FakeNews🚨 አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም። ከወራት በፊት መሰል የፈጠራና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ የ #የሶማሊያ አክቲቪስቶችና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሰሞኑን ዳግም የፈጠራ ወሬዎችን ፅፈው ማሰራጨትን ይዘዋል። እያሰራጩ ካሉት ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ አንዱ " በአዲስ አበባ የተለየ ሁኔታ እንዳለ ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደጨመረ፣ በየቦታው ወታደሮች እንደተበተኑ " የሚገልጽ ነው። ይህ ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ አንዳችም የተለየ የወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም። ምንም እንኳን ጉዳዩ ውሸት ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ሀሰተኛ መረጃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ፣ እያጋሩት እንደሆነ መመልከት ተችሏል ስለሆነም ጥንቃቄ አድርጉ። #AddisAbaba #Ethiopia @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው በቀን በ12 ብር በወር በ350 ብር ብቻ ! ተወዳጁን ሀገርኛ ድራማዎችን እና መዝናኛዎችን የምናገኝበት አቦል ቲቪ ከሜዳ ወደ ጎጆ ፓኬጅ መጣ! ምን ይሄ ብቻ ኒክ ጁኒየር በአማርኛ፥ ዚ-ዓለም የተከታታይ ድራማ ቻናል እና ሌሎችም የዲኤስቲቪ ቻናሎችን በጎጆ ፓኬጅ ያገኛሉ። አሁን ጎጇችን ሞላ፤ በወር 350... በቀን 12ብር ብቻ #DStvEthiopia #AbolTV #NickJrAmh #TraceMuzika #Zeeዓለም
Hammasini ko'rsatish...
🥰 1
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ጾም 8ኛ ሳምንት) ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣዔ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም  " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው። ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡  ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል። በዐብይ ጾም ከሰርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሣዔ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ካህናት መስቀል በእጃቸው አይዙም፣ አያሳልሙም ፣ ይፍቱኝ ተብሎ ወደካህን አይቀረብም፤ ይህ ሳምንት የጌታን የመጨረሻው ስቃይ የሚታሰብበት ነው። #TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
426🙏 30🥰 25🕊 12👏 8😡 5😢 3🤔 2😱 2
#ሆሣዕና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2016 ዓ/ም ሆሣዕና በዓል አስመልክተው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተገኝተው ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል። ቅዱስነታቸው ፤ የዛሬው የሆሣዕና በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይ አእሩግ እና ሕጻናት " ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም " በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል መሆኑን አስረድተዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ሰሙነ ህማማትንም  አስመልክተው ለመላው ምዕመናን አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው ፦ " ሰሙነ ሕማማትን እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አስጀምሮ እንዲያስፈጽመን ለብርሃነ ትንሳዔው እንዲያበቃን እግዚአብሔር አምላካችንን እንለምነዋለን። ሰሙነ ሕማማትን ሁላችንም በየአካባቢያችን ባለው ቤተክርስቲያን ተገኝተን ሰሞነ ሕማማትን ፣ ስግደቱን ፣ ጸሎቱን፣ ልመናውን በሕብረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችን እንጸልያለን። በጸሎታችን ደግሞ ያለውን ችግር ሁሉ እንዲያስወግድልን ፦ - #ሰላሙን፣ - #ፍቅሩን፣ - #አንድነቱን እንዲሰጠን የሁላችንም ጸሎትና ምኞት ነውና እግዚአብሔር አምላካችን ከዚያ ያድርሰን ሰሙነ ሕማማቱን በሰላም ያስፈጽመን። " #TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
116🙏 13🕊 4🤔 1😭 1
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች  ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
Hammasini ko'rsatish...
15🕊 4🤔 2😭 1
#RoseWood ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ ሼልፎችን ከሮዝዉድ ፈርኒቸር  ይዘዙ 👌 ለ ወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉልን  🙌 ሮዝዉድ ፈርኒቸር  📲 0905848586 ኣድራሻ  :  📍4ኪሎ ኣምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ                   📍 እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል Showroom Location 👇 https://goo.gl/maps/X6Q2exa7dfvjBPvWA ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ  👇 https://t.me/R0seWood https://t.me/R0seWood
Hammasini ko'rsatish...
#ጥንቃቄ🚨 " ማህበረሰቡ ያለበትን #የቤት_እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ - ቴሌኮም ጋር በመተባበር 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው " እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም #ሀሰተኛ ነው። በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወረው መልዕክት አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን #ለማጭበርበር የፈጠሩት ነው። " ሼር ብቻ እያደረጋችሁ የቤት ባለዕድለኛ ሆኑ ፣ ተሸለሙ " የሚሉት መልዕክቶች በሁለቱም ተቋማት እውቅና የሌላቸው የአጭበርባሪዎች ስራ ናቸው። " ቤት ታገኛላችሁ ሼር አድርጉ " እንዲህ የሚባል ነገር የለም። ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፤ መሰል #በውሸት የተሞሉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን እንድትጠነቀቁ ከዚህ ቀደም በዛ ያሉ መልዕክቶች ተለዋውጠናል ፤ በቂ እውቀትም አላችሁ። ምናልባት እንዲህ ያለን ሀሰተኛ መልዕክት አምኖ የሚጭበረበር ወዳጅ ዘመንድ እንዳይኖራችሁ አስገንዝቧቸው። #TikvahFamily @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉም አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትም ፈተና በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብሏል። ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጿል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸው ተገልጿል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ተብሏል። #MoE @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...