cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኢብኑ ሰኢድ

«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡፡ ዩሱፍ 108 ~~~~~~~~

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
812
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ከውሸት እንራቅ!! ~ 🔻ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦[አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል።] ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
Hammasini ko'rsatish...
🚫መውሊድ ቢድዓ ነው‼️ #መ መለያ ምልክት የሙብተድዕ አርማ #ው #ውስጡን_የገነባ_በኹራፋት_ኮርማ #ሊ ሊያጠወልግ ክብሩን የኢስላሜን ውበት #ድ ድብቅ መርዙን ሊረጭ ሊያስቀረኝ ራቁት #ቢ ቢያግበሰብስ ሙክት ሺወችን ቢያበላ #ድ ድቤውም ቢያጓራ ቢወገር በዱላ #ዓ ዓይኑ እስኪቀላ ቢቅም ቢያመነዥክ #ነ #ነውና_ቢድዓ_የድን_ጠላት_እሾክ #ው ውስጣችን ቁልፍ ነው🔐
Hammasini ko'rsatish...
መውሊድ.mp316.39 MB
01:09
Video unavailableShow in Telegram
2.77 MB
03:00
Video unavailableShow in Telegram
2.23 MB
   የመልካም ነገር መክፈቻ ሁን !!   ነቢዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰላም እንዲህ ይላሉ " إِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلْخَيْرِ مَغَالِيقَ لِلشَّرِّ،  "ከሰዎች መካከል ለኸይር መክፈቻ ቁልፍ የሆንና ሸርን ደግሞ የሚዘጋ አለ።" እንደዚሁም وَإِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلشَّرِّ مَغَالِيقَ لِلْخَيْرِ،  "ከሰዎች መካከልም እንደዚሁ የሸርን በር የሚከፍቱ ወይንም ለሸር በር መከፈት ምክንያት የሆኑ ቁልፎችና የኸይር ወይንም የመልካም ነገር በር መዘጋት ምክንያት የሆኑ ቁልፎች አሉ።" فَطُوبَى لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الْخَيْرِ عَلَى يَدَيْهِ، "የኸይርን በር መክፈቻ በእጁ ያደረገለት ሰው፤ ይህ ትልቅ እድል አግኝቷል።" وَوَيْلٌ لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الشَّرِّ عَلَى يَدَيْهِ " "የሸር ቁልፎችንም በእጁ ያደረገበት ሰውም ወየውለት!።" ይላሉ። ኢብኑ ማጃህና ሌሎች ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል   
Hammasini ko'rsatish...
🌾አሰላሙዐለይኩም ወራሐምቱሏሂ ወበረካቱህ 〰〰〰 ጥያቄ 🔸ሴት ልጅ ግሩፕ ከፍታ ወንዶችንም ሴቶችንም ማስተማር እና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ረድ መስጠት ከነሱ ጋር መከራከር ትችላለችን? አንዳንዴ በፅሁፍ አንዳንዴ በሪከርድ እየገባች 〰〰〰 መልስ:-በሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ ~ https://telegram.me/daruselam
Hammasini ko'rsatish...
4.07 MB
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦ "ነቢዩ( ﷺ) ተሳዳቢ፣አስቀያሚ ንግግርን ተናጋሪ ሆነ ተራጋሚ አልነበሩም።" 📚【ቡኻሪ ዘግበውታል】
Hammasini ko'rsatish...
01:44
Video unavailableShow in Telegram
👉የሰዎችን አቋም ምንፈትነው በአህሉ ሱና ኡሱል ወይም በኢማምነታቸው ጥርጥር የሌለባቸውን መሻኢኾች ኢማም አህመድ ኢማም ሻፊዒ ኢማም ማሊክን ይመስል ነው። 👉በመንደር ሼኽና ኡስታዝ የሰውን ሱንይነት መፈተን አትችልም። ✍Dawud Ali AbuAsiya
Hammasini ko'rsatish...
3.34 MB
🌾የጁምዓ እለት ትሩፋት ☞የጁምዓ እለት የሳምንቱ ምርጥ ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ «አላህ ዘንድ ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋልና በዚህ እለት ስራዎቻችንን ይበልጥ ማሳመር ይገባናል። 📚صححه الألباني في السلسلة الصحيحة - رقم: (1502) صحيح الجامع -  رقم: (1098) ☞የጁምዓ እለት በጀማዓ (በህብረት) የተሰገደ የፈጅር ሰላት ከየትኛውም ወቅት ሰላት በላጭ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ «አላህ ዘንድ በላጩ ሰላት በጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብህ ሰላት ነው።» ብለዋልና ከየትኛውም እለት በበለጠ ቀድሞ ለመገኘት መጣር ይበልጥ ያስመነዳል። 📚السلسلة الصحيحة - الألباني صحيح - رقم: 1566 ☞የጁምዓ እለት ከሌሎች ቀናት በበለጠ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት የማውረጃ ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ «በጁምዓ ቀንና በጁምዓ ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ያወርዳል።» ብለዋልና ትንሽ ሰርተን ከአስር እጥፍ በላይ ለማግኘት ከወዲሁ እድሉን እንጠቀም። 📚صحيح الجامع  الألباني حسن - رقم: 1209 ☞የጁምዓ እለት መኖሩም መሞቱም ለሙስሊሙ ፀጋ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ «ማንኛውም ሙስሊም የጁምዓ ቀን ወይም የጁምዓ ሌሊት የሞተ እንደሆን አላህ ከቀብር ፈተና ሳያድነው አይቀርም።» ብለዋል።  ስለዚህ በመጀመርያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን ☞አርካኑል ኢስላምን በስርዓቱ የተገበረ ሙስሊም እንሁን። ☞በማስከተልም አላህ በራህመቱ ከቀብር ፈተና እንዲጠብቀንና ለዚህ ሰበብም እንዲያበቃን ሁሌም እንለምነው። 📚حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره ☞የጁምዓ እለት የሳምንቱ ከኃጢኣት መንፂያ ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ «ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱት በስተቀር አምስቱ ሰላቶች እንዲሁም ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ያለውን ኃጢኣት ያብሳሉ።»¹ በሌላ ዘገባም «ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ላለው ማበሻ ናቸው።»² ብለዋል።   ስለዚህ ከከባባድ ወንጀሎች በመራቅ ወይም ተውበት በማድረግ፣ አምስቱን እለታዊ ሰላቶች ጠብቆ በመስገድና የሳምንቱን ልዩ የስብስብ ቀን የጁምዓን ሰላት በመስገድ ተጨማሪ ግድፈቶቻችንን እናፅዳ። ¹📚صحيح مسلم - رقم: (233) ²📚الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110) ☞ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የመከባበርያ ቀን ነው። ሁሉም ሙስሊም ክቡር ነው። ሀብታም ከድሃ ታላቅ ከታናሽ፣ ገዢ ከተገዢ የሚለይበት ቦታ አየደለምና መስጂድ ሲደርስ ያገኘበት ክፍት ቦታ ሊቀመጥ ይገባዋል እንጂ ማንንም አስነስቶ ወይም እንዲነሳ አስደርጎ ሊቀመጥ አይገባውም።  የአላህ መልእክተኛ ﷺ «አንዳችሁ በጁምዓ ቀን ወንድሙ የተቀመጠበት ቦታ ሊቀመጥ ብሎ እንዳያስነሳው። ነገር ግን ሰፋ ሰፋ አድርጉ ይበል።» ብለዋልና ኢማሙ ኹጥባ ያልጀመሩ እንደሆነ ሰዎችን እንዲጠጋጉለትና እንዲሸጋሸጉለት በስርዓት ማግባትም ይችላል። 📚صحيح مسلم - رقم: (2178) ☞ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የፅዳት ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ «አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ማለታቸው ተዘግቧል። 📚صحيح البخاري - رقم: (882) ☞ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የቁርኣን ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቀጣዩን ብለዋል☞ «በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» 📚حسنه الألباني في تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116) በሌላም ዘገባ እኛ በተለምዶ ሐሙስ ማታ በምንለው የጁምዓ አጥቢያ ምሽቱን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው አጅሩ እጅግ በጣም ሰፊ ነው። «ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል። 📚صححه الألباني في صحيح الترغيب -رقم: (736) ☞በተጨማሪም የጁምዓ እለት የማንንም ክብርና መብት የማንጥስበት፣ ከውስጥም ከውጭም በወሬም ሆነ በሌላ ጉዳይ ሰውን እንዳንረብሽ የተከለከልንበት ልዩ ቀን ነው። ይህንንም ለዒባዳ ብለን መስጂድ እንኳን መጥተን ክፍት ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ እየተረማመድን እንዳንሄድ ከልክለውናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንል ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወት ተከልክለናል። ማንኛውም ሰው በጁምዓ እለት ወደ መስጂድ ሲመጣ ክፍት ቦታ ከፊትለፊቱም ሆነ ከጎኑ ክፍተት እንዳይኖር ወደፊት መጠጋትን የመሰለ እንደገባ በማመቻቸት መቀመጥ አለበት። ምክንያቱም ከኋላ የሚመጡት ቦታ ፍለጋ ስህተት እንዳይፈፅሙና ክብሩንም እንዳይነኩ ይረዳልና። በመሰረቱ ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ መረማመድ ተከልክለናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንልም ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወትም ተከልክለናል። ባጠቃላይ የሰው ትከሻ አትርገጥ~እንዳትወራገጥ አርፈህ ተቀመጥ~በፀጥታ አድምጥ ለጌታህ እጅ ስጥ   اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه أجمعين
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.