uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

Alex Abreham - በነገራችን ላይ

Alex Abreham - በነገራችን ላይ

Kanalga Telegram’da o‘tish

በገበያ ላይ የሚገኙ የአሌክስ አብረሃም መፅሐፍት ዝርዝር 1- አልተዘዋወረችም 2- ከዕለታት ግማሽ ቀን 3- ዙቤይዳ 4 - ዶክተር አሸብር 5 - እናት ሀገር ፍቅር 6 - አንፈርስም አንታደስም 💚💛❤️ Official Fan Channel ! አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው:: Contact me @akexeth

Ko'proq ko'rsatish
7 204
Obunachilar
-124 soatlar
+47 kun
+1630 kun
Postlar arxiv
በዚች ዓለም ላይ ብቸኛው "ሚራክል መኒ" ደመወዝህ ነው። አስበኸዋል .... በአመት 58 ሚሊዮን እስከ 60 ሚሊዮን ሰዎች ​በሰዓት 6,500 ሰዎች ​በደቂቃ 110 ሰዎች ​በሰከንድ 2 ሰዎች ይሞታሉ!! በቃ ሰበቡ ምንም ይሁን ይሞታሉ! ስልህ ከደመወዝህ አንድ ሰከንድ በፊት ከሞቱት 2 ሰወች አንዱ አንተ አልነበርክም! በዚህ ሁሉ ሬሳ ላይ ተረማምደህ አነሰም በዛም ስትቆጥራት ተዓምሩ አይገርምህም? በእርግጥ አከራይህ ሲቀበሉህ እርሳቸውም ይሄን ሁሉ የፍፃሜ ሞት አልፈው ነው። ተቃቅፋችሁ እንኳን አደረሰን መባባል አለባችሁ😀 አውቃለሁ ይሄ አያፅናናህም። ግን ይችን ፅሁፍ በስንት ሰከንድ ጨረስካት? በ2 ሰው አስላው ፤ አንተ ግን አሁንም አለህ...እንደውም ኮሜንት ልትፅፍ ነው...ገፊ ነገር ነህ ልበል?😀

ኢትዮጵያ ሄጀ ነበር ክፍል 3 " ወደገደለው ግባ እንጅ የምን ዳር ዳር ነው ኢትዮጵያን እንዴት አገኘሀት?" የሚል ተደጋጋሚ ኮሜንት አግኝቻለሁ። ዌል እንግዲክ ሐሳብን በነፃነት የመጠቀም መብቴን በመጠቀም ስለኢትዮጵያ ዋና ትዝብቴን እንደሚከተለው በዝርዝር ፅፊያለሁ። ሁሉም ለየራሱ በሚገባው መንገድ እንደሚያነበው ተስፋ አለኝ። ሰማንያ እንላለን እንጅ 130 ሚሊየን ቋንቋ ያለን ህዝቦች ሁነናል፣ ሁሉም ለማንም የማይገባ ሸክም ሸክሙን የሚገልፅበት ቋንቋ አለው። ማንም የማንንም ቋንቋ አይሰማም ግን ይገበዋል። እኔ ቦሌ ስደርስ እንደቪዛ ለግሌ የተሰጠኝ ቋንቋ ይሄ ነው። የእናንተን ኮሜንት ላይ አየዋለሁ! መልካም ንባብ! ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ (▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢) ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢🙏 ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢8? ▢▢▢ ▢▢ ▢▢ 27▢▢! ▢▢▢▢▢▢😀 ▢▢▢▢▢ (▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢) ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢▢▢▢፤ ▢ ▢▢ ▢▢▢፤ ▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢▢▢▢29? 27? ▢▢▢! ▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢... ▢▢▢ ▢▢... ▢▢▢▢.... ▢▢▢ ▢▢▢....▢▢▢ ▢▢... ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢🤔 ▢▢▢▢▢ (▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢) ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢▢ ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢ ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢ ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢💀 ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢ ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢4▢▢? ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢😀 ▢▢▢▢▢ (▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢) ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢🙏 ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢8? ▢▢▢ ▢▢ ▢▢ 29 ▢▢! ▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ (▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢) ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢▢▢▢፤ ▢ ▢▢ ▢▢▢፤ ▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢▢▢▢29? 27? ▢▢▢! ▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢... ▢▢▢ ▢▢... ▢▢▢▢.... ▢▢▢ ▢▢▢....▢▢▢ ▢▢... ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢🤔 ▢▢▢▢▢ (▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢) ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢▢ ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢? ▢▢! ▢▢▫▫...▢▢▢▢...▢▢▢▢...▢▢! ▢ ▢▢▢ ▢▢▢▢▢▢ ...▢▢▢▢▢▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢▢ ▢▢ ▢▢▢▢! ▢▢▢▢▢▢....▢▢▢▢4▢▢?🤐🤐 አሜን🙏

ኢትዮጵያ ሄጀ ነበር ! ክፍል ሁለት (አሌክስ አብርሃም) የመጀመሪያወቹ ቀናቶች ድካምና የእንቅልፍ መምታታት ስለነበር ቅዠት የሚመስሉ ነገሮችን ብፅፍ ታገሱኝ! ቅዳሜ ቀን አዲስ አበባ ገብቸ ቅዳሜ ሌሊት አስገራሚ ዝናብ ዘነበ። ዶፍ! አንዳንዶች እንደሚሉት የአዲስ አበባ ህዝብ ሙቀቱና የኑሮ ውድነቱ ተባብሮ ልብሱን ሊያስጥለው ደርሶ ነበር። እንደውም እየጣለ ነበር። ኮፍያውን...ጃኬቱን፣ ቀሚሱን፣ ሱሪውን...ነጠላውን ሂጃቡን ...መነፅሩን ሂውማን ሄሩን...ይሉኝታውን....እያወለቀ ልክ ዝናቡ ሲዘንብ ቀዝቀዝ ስላለ ሙሉ ልብሱን መጣሉን ለጊዜው ትቶ እንደአዳምና ሂዋን ቅጠል አገልድሞ በየመንገዱ ታየ። ኑሮው በዚህ ከቀጠለ ያች ገመናውን የሸፈነባትን የደመወዝ፣ የመደጋገፍ፣ የተስፋ ቅጠሉን ጥሎ አደባባይ ሊወጣ ይችላል። በርግጥ ብዙሀኑ ራቁቱን ሲሄድ ካፖርት ደርበው የሚንጎማለሉም አይተናል። እንቅልፌ ስለተምታታ እንደዛ ታይቶኝ ይሆን? በቀጣዮ ቀን ቡና ልጠጣ ወጣሁ....በመንገዴ ሁለት ሊስትሮወች ተጣልተው በቡርሽ፣በጫማ፣ በሊስትሮ ሳጥን ፣ በቀለም ቆርቆሮ ይፈነካከታሉ። ሕዝቡ እንደፊልም ከቦ ያያል። እንደውም ተመልካቹ "ያንኛው ስታይሉ እንደሰኢዶ ይሄኛው እንደጆኒ ነው " ምናምን ይባባላል። የላብ አደሮች Jujutsu! በነገራችን ላይ ይሄ Jujutsu የሚሉት ስፖርት ለኢትዮጵያዊያን በትክክለኛ ጊዜ የመጣ የስፖርት ዓይነት ነው። ኑሮውን ገላጭ! ሕዝቡ ከኑሮ ጋር ጁጁትሱ ገጥሟል፣ ግጥሚያው እንደሩጫ መስመር፣ እንደኳስ ጥብቅ ሕግጋትና ጨዋነት ፣ እንደቦክስ ሞገስ ያለው ፍልሚያ የለውም። አንገት መቆልመም፣ ትናጋን ማናጋት፣ እጅና እግር መስበር፣እግር ከወርች መቆላለፍ፣ አገጭ ማጣመም፣ አፍንጫ ማወላገድ ፣ ቅንድብን ባይበሉባ መላጨት፣ አይንን ማጠናገር፣ ፈ* ማስ*ሳት፣ ግሳት ማስገሳት .... ወገብ ይዞ መዛዛት፣ አከርካሪን መስበር... በማንኛውም መንገድ የለት ቁርስና ድል ማገኘት ነው። ማን አሸነፈ እንጅ እንዴት አሸነፈ አይባልም። ተነካካህ ተብሎ ቀይ ካርድ በሚመዘዝበት ዘመን ያደግን ልጆች ቢሸክከንና ክብረነክ ነገር ቢሆንብን አይፈረድብንም። የሆነ ሆኖ ሁለቱ ሊስትሮወች የተጣሉት የሆነን ሰውየ ጫማ እኔ ልጥረግ እኔ በሚል ነበር። የገረመኝ ግን ሁለቱም ተደባዳቢ ሊስትሮወች የለበሱት አንድ አይነት ቲሸርት መሆኑ ነበር፤ ጀርባው ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው"

ኢትዮጵያ ሄጀ ነበር! (አሌክስ አብርሃም) እንዴት ከረማችሁ? ከዚህ ሰፈር ዞር ብየ ቆየሁ። እንኳን ሌላ ሰው የራሳችሁ አንገት ተጠምዝዞ ቢዞር የማታስታውሱበት ፋታ የማይሰጥ ትርምስ ፣ እና ሰበር ዜና ውስጥ ናችሁና መጥፋቴ ብዙም እንዳልተሰማችሁ አውቃለሁ። እንደውም "መጣ ደሞ ሊጨቀጭቀን" ባትሉ ነው! ተሰምቷችሁ ለጠየቃችሁኝ ግን ምንድነው የምትነዘንዙኝ ሰው ማረፊያ ያጣል እንዴ የምል ነጭናጫ አይደለሁም 😀 አመሠግናለሁ🙏 ለማንኛውም የኖርኩ ኑሬ ድንገት በዚህ ሰዓት ተነስቸ ኢትዮጵያ መሄድ የጤና ነው? ሰው ማለት አገሩን በሰላም ጊዜ ብቻ የሚወድ አይደለም(ዘራፍ) ከረዢም ጊዜ በኋላ ነው የሄድኩት! መቸስ ያየሁ የሰማሁትን አካፍል ዘንድ ወዳጃዊ ግዴታ አለብኝና እንደሚከተለው በክፍል በክፍል አቀርባለሁ። ክፍል አንድ የተሳፈርኩበት ግዙፍ ኤርባስ አውሮፕላን ኢራን ከተኮሰቻቸው ሰላሳ ሮኬትና 25 ድሮኖች መካከል አልፎ የምትቀጠቅጣቸውን ሶስት የአረብ አገራትን አቋርጦ እኩለ ሌሊት ላይ አዲስ አበባ ደረሰ። ወቅቱ የኢራን ሮኬቶች እንደአገራችን ሴቶችና ወንዶች ወደሁሉም አረብ አገራት በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር። አንድ ድሮን ከተሳፈርኩበት አውሮፕላን ጎን እየተምዘገዘገ መጣና ካሜራውን ዞር አድርጎ በመስኮት አየኝ ፣ ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን ፤ አመጣጡ የሰላም አልነበረም...ግን ፍጥነቱን ቀነስ አድርጎ "ውይ በሞትኩት፤ አንተ አሌክስ አይደለህም እንዴ? በዚህ ክፉ ቀን ምን ክንፍ ጣለህ? የሳዲቅ ሂዳያት ፣የነፊርዶውሲ የነ ሳዲ ሺራዚ የአገሬ ፀሐፍት መንፈስ አንተ ላይ ታየኝ፣ እኔማ አንተን ...አድርጌ ድል ራቱ ከምባል በቃ በሰላም ግባ እዚህ ውቂያኖሱ ላይ እፈጠፈጣለሁ" አለና ለሚከተሉት የሚሳኤልና ድሮን መንጋ "አቅጣጫ ቀይሩ" ብሎ አዞ ቁልቁል ወረደ ....አንዳንዶቹ ኳታር፣ አንዳንዶቹ ሳኡዲ፣ አንዳንዶቹ ኩዌየት ብዙወቹ ኢስራኤል ካለፕሮግራማቸው አረፉ። ያው ጉራ እንዳይመስል ለማንም አልተናገርኩም። ዓለም እንደፈለገ ይተንትን። ቆንጆ ቆንጆ ዘጠኝ ሆስተሶች በየተራ እየመጡ ስላተረፍከን እናመሰግናለን እያሉ በሽሚያ እያቀፉ ሲስሙኝና "የቀረውን ስንደርስ እናወራርዳለን" ሲሉኝ "የቀረው ምንድነው?" ልል ስል ከእንቅልፌ ነቃሁ። አፍንጫቸው ላይ መተንፈሻ የተገጠመላቸው ወፍራም ሰውየ እያንኮራፉ በክንዳቸው ወድቀውብኛል። ሳልተኛ በፊት ለህክምና የሆነ አገር ቆይተው እየተመለሱ መሆናቸውን ነግረውኝ ነበር። ኤዲያ! አዲስ አበባ መድረሳችን በፓይለቱ ሲታወጅ በናፍቆት ሰፍ ብየ በመስኮት በኩል ወደታች ተመለከትኩ ፤ ምን አየሁ? ምንም አላየሁም! ምክንያቱም ኳስ ሜዳ የሚያክለው የአውሮፕላኑ ክንፍ ከልሎኝ ነበር። በክንፍ በኩል ያውም ተጨማሪ ሒሳብ ከፍየ መሳፈሬ ቆጨኝ። አዲስ አበባን ከሰማይ ላይ በምሽት የማየት ፍላጎት ነበረኝ። ድሮም ኳስ ስጨዋት በክንፍ በኩል ነበር አሰላለፌ። መንግስት ልማቱ መብራቱ የማይታያቸውን ሰወች ሁሉ ፀረ ልማትና ምቀኛ አድርጎ ማየት የለበትም የምለው ለዚህ ነው¡ ብዙ ምክንያት ይኖራል። ይልቅ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ክንፍ አልባ አውሮፕላኖችን ቢጠቀም፣ አልያም ክንፎቹ ልማቱን እንዳይከልሉ ከመስተዋት የተሰሩ ኤር ባስ በትዕዛዝ ቢያሰራ የሚል ቅን ሐሳብ አለኝ¡ እንደሀሳብ! አብራሪው አውሮፕላኑን ቦሌ ላይ አሳረፈው ከማለት አነቦጨው ቢባል ልክ ይመጣል። እንዴ ፓይለት ከመሆኑ በፊት አጥፍቶ ጠፊ ድሮን አብራሪ ነበር እንዴ? አስተራረፍማ የኢትዮጵያ ፓይለቶች ይምጡብኝ። ዞሮ ዞሮ ያው በሰላም ቦሌ አፍን። ... ሻንጣየን ተቀብየ ዲያስፖራ እንዳልመስል የተቻለኝን መጎሳቆል ከከወንኩ በኋላ ከቦሌ ወጣሁ። አሁን ኢትዮጵያን በግላጭ የማየት ጊዜው ሆነ...

አስመሳይ!

በዚች ፈንዲሻ የሆነች ልጅ ቀናችሁን ጀምሩ። ከጃንሆይ ወዲህ እንዲህ የሳቀ ኢትዮጵያዊያዊ አላየሁም😁 እንደምን ሰነበታቹ 🙌

መልካም አዲስ ዓመት!
መልካም አዲስ ዓመት!

በየትኛው ዕድሜ እንሰደድ? (አሌክስ አብርሃም) አንድ ቀን ዶክተር ፍስሃ ጋር እያወራን  ትክክለኛ ለስደት ጥሩ የሆነ እድሜ  የትኛው  ነው አለኝ....አሰብኩ.... ከ1- 15ዓመት ? የህፃንነት ውብ ዕድሜ ጭቃና ውሃ መራጨቱ ትንንሽ እግሮች የአገራቸው አቧራ ላይ መፈንጠዣቸው ፣ በተወለዱበት አገር ቋንቋ መዝሙሮቹ ተረቶቹ... በቁንጥጫ መመዢለጡ በቀበቶ መዢለጡ የህይወት ትንሽ ህመም ፍቅር የወለዳት ከወላጅ የምትበረከት መንገድ መሪ ቁንጥጫ.... ከ15 -20 ውብ እድሜ ባዮሎጅ ባህል ከወፍጮቤቱ ኋላ ያለው ሰፈር ውስጥ የምትኖረው ጠይም ልጅ እና ወዘተ ተባብረው የሆነ ገነት የሚፈጥሩበት የምንፈቀርና የምናፈቅርበት እሳትነት። እሳት ውቅያኖስ ከተሻገረ ምኑን እሳት ሆነ? ከ20-30 ዮኒቨርስቲው፣ የአገር ፖለቲካው፣ አብዮቱ፣ ንብቡ ፣ ተስፋው፣ መማሩ፣ መመረቁ፣ ትንታግነቱ ፣ ውበቱ ትዳሩ ወግ ማረጉ ህዝብህ ጋር .... 30-50 ቁም ነገሩ የስራ እድገቱ፣ ስልጣኑ ፣  የልጆችና የትዳር የአባትነትና የማዕረግ ቤት መስራቱ ፣ ዕድሩ መሃበሩ .... ከ50- 70 ሽምግልናው ፣ ማስታረቁ፣ የልጅ ልጁ አንቱታው ዕቁቡ የወገብ ህመሙ ደም ግፊቱ ሽበቱ፣ ማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ቦታ ቀበሌው ስብሰባው ምክሩ .... የሰው ልጅ ፈፅሞ መሰደድ የሌለበት ፍጡር ነው። ምንም ያህል ቁሳዊ ለውጥ ቢመጣም ስሩን ትቶ የተሰደደ ዛፍ ቆንጅ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ወይም ማገዶ እንጅ ዛፍ አይሆንም። በስንት ዓመቴ ልሰደድ ጥያቄ አይደለም ፣በስንት ዓመትህ ጠቅልለህ ትመለሳለህ ግን የሁሉም ስደተኛ የዕድሜ ልክ ጥያቄ ነው!

በተለይ ኑሮ ጋር እየታገሉ ገና በሁለት እግራቸው ለመቆም የሚሞክሩ ሰወች ሲጋቡ መፅሐፍ ቅዱስ ስጦታ የምታበረክቱ ሰወች ጥሩ ነውኮ...ግን መጥበሻ፣ ብረት ድስት፣ የአልጋ ልብስ፣ ብር ምናምን ብትጨምሩበት🙏 ሁለት ሚስኪኖች ተጋብተው አንድ አይነት 16 መፅሐፍ ቅዱስ ስጦታ እንደተቆለለባቸው ሲናገሩ ሰምቸ ነው። ፅደቅ ላለው አንዱ ይበቃል። ኧረ የምድሩንም እየተደጋገፍን ወገኖች። ክርስቲያን ከሆኑ መቸስ ቤታቸው መፅሐፍ ቅዱስ ይኖራል። ባይኖሩም ማግኘቱ ከባድ አይደለም። ይመስለኛል ብዙ ሰው እቤቱ ገና ያልተነበበ አዲስ መፅሐፍ ቅዱስ አለው ስጦታ ከመግዛት ያችን ወስዶ ይሰጣል። "ከምድርና ከሰማይ የከበደውን የአምላክ ቃል በዚህ ዕለት ስሰጣችሁ ለእናንተ ካለኝ ፍቅርና ምንም ስጦታ ከማይመጥነው ወዳጅነቴ...." ከሚል ስብከት ጋር። ይሄ የኔ ቢጤን እግዚአብሔር ይስጥህ ብለን እንደምናባርረው ያለ ነገር ነው።

የ130 ሚሊየን ነብያት አገር የደፈሩት መድረክ ላይ ወጡ እንጅ 130 ሚሊየኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነብይ ነው። ላረጋግጥላችሁ? ለምሳሌ በቅርቡ አገራችን ላይ ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ አካታች እና ፍፁም ሰላማዊ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን የአፍሪካ ህብረት የታዘበው ምርጫ መካሄዱ ይታወሳል። እሽ ይሄን የምታነበው ወይም የምታነቢው እህትና ወንድሞች በዚህ ምርጫ ቀድማችሁ ማን እንደሚያሸንፍ ውስጣችሁ ተንብዮ ነበር ወይስ አልተነበየም? ተንብዮ ነበር! ትንቢታችሁ ተሳሳተ? አንድም ኢትዮጵያዊ አልተሳሳተም። ጃሉድ ራሱ በትክክል ተንብዮ ነበር። የ130 ሚሊየን ነብያት አገር። ፕሮፌሳይ ሻርፕ ሹተር ሜጀር ዋን ፕሮፌት...ፕሮፌሳይ!

አንዳንድ ወላጆች ከበድ ያለ ጠባብነት አለባቸው። (አሌክስ አብርሃም) ስለግ*ብረሰ* ዶም፣ ስለሱስ፣ ስለልቅ ወሲብና ስለተለያዮ ከባህል እና ከሰብአዊነት ስላፈነገጡ የስነምግባር ጉዳዮች መስፋፋት ሲነሳ "እግዚአብሔር ይመስገን እኔ ልጀን ቅዱስ ማንትስ የክርስትያን ት/ቤት አስገብቻለሁ፣ አልሃምዱሊላሂ ልጀ የሚማረው የሙስሊም ትምህርት ቤት፣ የካቶሊክ የፕሮቴስታንት.... አገር ከተበላሸ እንኳን ሐይማኖት መር ትምህርት ቤት፣ ቤተ ክርስቲያንና መስጅዶች ራሳቸው የወመኔ መናህሪያ ነው የሚሆኑት። ድራግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወዘተ በስፋት እምነትን ተገን አድርገው ስንቱን ሲያጠፉት አላነበባችሁም? መጥፎ አገር ላይ የትኛውም ጥሩ ተቋም ቢመሰረት ሰወችን አይታደግም። ከ12 ዓመት በፊት የአንድ ኢንተር ናሽናል ስኩል ተማሪ ያለችኝን አልረሳም "ሽመልስ ሀብቴና እኛ ጋ 'የሚነፋው' ኳሊቲ ይለያያል" የኳሊቲ ጉዳይ ነው። መፍትሄው ልጆችን በእምነት በባህልና ማንነታቸው ማሳደግ እጅግ ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ግን ከየትኛውም የእምነት የዘርና የኑሮ ደረጃ አጥር በላይ አገር የምትባል ነገር ስለመገንባት ማሰብ አለብን። እንደአገር የሚወጡ ፖሊሲወች አሰራርና ህገወጥነቶችን ልጅን ቅዱስ ማንትስ አጥር ውስጥ በማቆየት አንታደገውም። ትልቅ ማህበራዊ ውዥንብር እና የተሳሳተ የመደገፍያ ግንብ ነው። ክንፍ ያለን ቅዱስ ብንሆን ራሱ የተሻለ አገር ከሌለን የትኛውም እምነት ከባርነት ስነልቦና፣ ከማንነት አልባ ባዶነት ከጥፋትም አይታደገንም!! ከሁሉም ነገር በፊት አገር!!

የሆነ ጊዜ ነዳጅ የሚባለው አስቀያሚ ቅርናታም ድፍድፍ ከሽንትቤት ፍሳሽ በላይ ፀያፍ ቆሻሻ መሆኑ አይቀሬ ይመስለኛል። ዓለማችን ወደኤሌክትሪክና ኒውክሌር ኢነርጅ ፊቷን ማዞሯ አይቀርም። (ቱ ምናለ በሉኝ😁) ያኔ የነዳጅን መቶ እጥፍ ተወዶ ዙፋኑ ላይ የሚነግሰው ምን ይመስላችኋል? ውሃ! የአለማችን ውቂያኖሶች ሁሉ ውሃ እንደወርቅ የሚነጠርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ይልቁንም እግዜር አንጥሮ ንፁህ ውሃ ያሸከማት አገራችን ያኔ የማንም አይን ማረፊያ ትሆናለች። አለም ባግበሰበሰችው የስልጣኔ ጉርሻ ስትታነቅ እጇን ወደቡትሊያችን መዘርጋቷ አይቀርም። እኔ መሪ ብሆን ግብፅን ችላ ብየ መቶ ተጨማሪ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ነበር የማስጠናው። በውሃ ዙሪያ ብቻ የሚያስተምሩና የሚያጠኑ አንድ ሶስት ዮኒቨርስቲወችን ነበር የምገነባው። ከቦኖ ውሃ እስከአገር አቋራጭ ወንዞቻችን ጋር በተያያዘ ጉዳይ የውሃ ማህንዲሶችን ነበር የምመድበው። የውሃ ጥበቃ ላይ ከትራፊክ ህግ በላይ ነበር የምጋደለው። ካለአግባብ ወንዝ በመሻገር ሁሉ ልቀጣ እችላለሁ። (ማውራት እንደመስራት ባይቀልም) ትንቢቴ ካልተፈፀመ የልጅ ልጆቻችሁ ውሸታም ነብይ" እንዲሉኝ የአደራ ደብዳቤ ፅፋችሁ ሙቱ። ለምን እርግጠኛ ሆንክ ካላችሁኝ በሰፊው አብራራለሁ።

እናቴዋ ዛላ! ​(አሌክስ አብርሃም) ​ትምህርት ቤቶች ዕድሚያቸው የገፉ ልጆችን ከሕፃናት ጋር ቀላቅለው ማስተማር የለባቸውም የሚል ፅኑ እምነት አለኝ። ሕፃናቱን እንዳልነበሩ አድርገው ነው የሚያበላሿቸው፤ አደገኛ ነገር ነው። ወላጆች ይህንን ነገር በዝምታ ማለፍ የለባቸውም፤ ትምህርት ቤቶችም ጭምር። በእኛ ጊዜ የተለመደ ነበር፣ አሁን ግን እንጃ! ​አምስተኛ ክፍል ሆነን፣ እንዴት እንደሆነ እንጃ፣ ትልልቅ ልጆች ወደ ክፍላችን ገብተው ከኋላ ተቀመጡ። ድምፃቸው የጎረነነና የተስረቀረቀ ጎረምሶች ነበሩ። ሦስቱ እስከ አሁን አይረሱኝም። መዓዛ የምትባል፣ ማርያም ፊቷ ላይ አራት ቦታ ላይ የሳመቻት ድምቅ ያለች ቀይ ልጅ፣ ሕፃን ሕፃን የማትሸት፣ አጠገባችን ስትቀመጥ ሽቶና የላብ ጠረን ከላይዋ ላይ የሚተን ልጅ፤ ማስቲካ ከአፏ የማይለይ፣ ደግሞ ስታላምጥ «ቀጭ ቀጭ» የምታደርግ... በመጀመሪያው ቀን «ራሳችሁን አስተዋውቁ» ሲባል፣ «መዓዛ እባላለሁ፤ የምሠራው ቢዝነስ ነው» አለች እየተሽኮረመመች። «ቢዝነስ» የሚለውን ቃል መጀመሪያ የሰማሁት ከእሷ ነው። ደግሞ «ተማሪ ሥራ አለው እንዴ?» ብለናልም።​ቆይታ፣ በተለይ የሳይንስ ትምህርትን ትደፍነው ጀመር። «እንዴት ነው የደፈንሽው?» አልናት በልጅነት ጉጉት። «ወንድ ያችን ነገር ካገኘ... ሂሂሂሂ...» ነበር መልሷ። ያች ነገር ምን እንደሆነች ለማወቅ የደከምነው ድካም! በኋላ፣ እዚያ ፊቱ የማይፈታው የሳይንስ አስተማሪያችን ጋር የሆነ አልጋ ቤት ሲገቡ የአልጋ ቤቱ ባለቤቶች ልጅ አይቶ ነገረን (ጠባብ ከተማ!)። ቆይቶ ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች አወቅን። በከተማችን ውስጥ ማታ ማታ ሴቶች ለዚሁ ሥራ የሚቆሙበት ሰፈር አለ፤ እኔ ራሴ አንዴ አየኋት። ከእህቴ ጋር ዘመድ ቤት አምሽተን በታክሲ እየተመለስን ነበር። እያለፍን ያኔ ያየኋት መዓዛ (በውልብታ ቢሆንም) ያ ቀይ ፊቷ ከመንገዱ መብራት ጋር በአእምሮዬ ላይ ታትሞ ቀርቷል። በደንብ የታተመው ደግሞ በግርምት አንገቴ እስኪሰበር ዙሬ በታክሲው መስኮት መንገድ ላይ ወደተደረደሩት ሴቶች ስመለከት፣ መብረቅ የሚያስንቅ የእህቴ ጥፊ ጭንቅላቴን 360 ዲግሪ አዞረው (ቸንቧ!)። ከዚያ ቀን ጀምሮ ሰፈሩን እራሱን ዙሬ ባይ፣ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዓምድ ሆኜ የምቀር ነው የሚመስለኝ። ሴተኛ አዳሪ ምን እንደሆነችም ያወቅነው ያኔ ነው። የሚገርመው፣ ብዙ ሴት ተማሪዎች ነፍሳቸው እስኪወጣ መዓዛን ይወዷት ነበር። አረማመድና አወራራቸው፣ ማስቲካ አለማመጥና አሳሳቃቸው ሁሉ እንደ እሷ ሆኖ ነበር። ነፍሳቸውን ይማረውና እሷም፣ የሳይንስ አስተማሪያችንም መሞታቸውን አሥረኛ ክፍል ሆነን ሰማን። ​ሁለተኛው ልጅ ታጋይ ነበር፤ ዕድሜው 20 ገደማ የሚሆን። አስተማሪያችንን ሁሉ የሚቆጣ፣ በማትስ ክላስ ሳይቀር «ዲሞክራሲ!» የሚል ነበር። ሰብስቦ ስለ ትግል ያወራናል፦ «አነጣጠርኩና ቃታ ስስብ ጠላት ጭንቅላቱ እንደ ሰርዲን ተነደለ... ደሙ ፊን ብሎ ... አንጎሉ...» እያለ ምድረ ሕፃን ስንቃዥ እናድራለን። አስታውሳለሁ እኔ ራሱ ሌሊት ስጨነቅ ነበር የማድረው። ለቤተሰብ ደግሞ አንናገርም። አፋችሁን ከፍታችሁ ወሬ ብለው እኛው ላይ ይዞሩብናል። ​ሦስተኛው ልጅ ከገጠር የመጣ ነበር፤ ያኔ ዕድሜው 17 ወይም 18፣ ኧረ ቀንጭሮ ነው እንጂ 25ም ሊሆን ይችላል። ወሬው ሁሉ የወሲብና የሴት ሰውነት ነው። ደግሞ የክፍል አለቃ ነበር። ((አሁን ላይ ሳስበው ከከሰዓት ፈረቃ በኋላ «የቤት ጠረጋ» የሚባል ፕሮግራም ነበር፤ በየሳምንቱ የመማሪያ ክፍል እናፀደለን። ይሄ ልጅ ደጋግሞ ከኋላ የሚያስቀረው ሴቶችን ብቻ ነበር። ልጆቹ አንዳንዶቹ ያለቅሱ ነበር፣ ግን ጊዜው እንደ አሁኑ አልነበረም። አሁን ላይ አስባለሁ፣ ደፍሯቸው ይሆን? ያኔ ምንም አይገባንም ነበር።)) ​አንድ ቀን የማትስ አስተማሪያችን ቲቸር ፀሐይ ብላክቦርድ ላይ «ሒሳብ» ብላ ልትጽፍ ስትንጠራራ፣ ድብልቅ ባለ ድምፅ ምላሱን «ጧ» አድርጎ አጣጣመና «እናቴዋ ዛላ!» አለ። ዛላ ማለት ሰውነት፣ አቋም ማለት ነው። ለመደብን! ምድረ ማቲ ሬንቦውንም ቡርስሊንም ስናይ «እናቴዋ ዛላ!» እንላለን። ​አንድ ቀን «120» ፕሮግራም ላይ ቴሌቪዥን እያየን፣ የሆነች ገጸ ባህሪ(መሠረት መብራቴ ትመስለኛለች) ስትንጠራራ «እናቴዋ ዛላ!» አልኩ። ከእናቴና ከእህቴ እኩል የተወረወሩ ነጠላ ጫማዎች ጎንበስ በማለቴ በባዶ አየር ላይ ተጋጩ (አልበርት አንስታይን ራሱ «በሚሊዮን የብርሃን ዓመት አንዴ የሚከሰት ግጭት» እንዳለው በኋላ ፊዚክስ ስማር ደረስኩበት 😁)። ((((((((​ቁም ነገሩ፣ በዕድሜ የጎረመሱ ልጆች በልዩ ሁኔታ የሚማሩበት ፕሮግራም ሊመቻችላቸው ይገባል እንጂ ከሕፃናት ጋር ተቀላቅለው መማር የለባቸውም!!))))))

ድግምት ነው! ትላንት ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ በደረቅ ሌሊት በሬን ከፍቸ ወጣሁና ቁሜ መንደሩን ስቃኝ ኤሎን መስክ የሚባለው ሰውየ ነጭ ጅብ እየጋለበ ሲያልፍ አየሁት... እንደውም የግራ እጁን አንስቶ ፈጣን ሰላምታ ሰጠኝ። ለነገሩ ቴስላ ትራክ የሚባለው መኪና ቅርፁ የጅብ መምሰሉ ያለነገር አይደለም። ያንን በየሲግመንድ ፍሩድ ሳይኮአናሊሲስ የተጠመቀ ጓደኛየን ስነግረው "አብርሽ የሆነ ነገር አናትህ ላይ ወጥቶ እያቃዠህ ነው አበርክተህ ተቃቀፍ" አለኝ። የሚቀፍ ይቀፍህ! ድሮም ከዛሬ ሳይኮ ምናምኒስት እማማ ዝናሽ ይሻላሉ። .... ቁም ነገር ግን ጓዶች...ሁሉም ገንዘብ የራሱ የሆነ አቅም አለው። ይሄ ዶላር የሚሉት ነገር ግን የሆነ ድግምት ነገር ነው። ባብራራላችሁ ደስ ይለኝ ነበርኮ ችግሩ ድግምትን የሚያውቀው ደጋሚው ብቻ ነው። እንዴት አድርገው ነው ዓለምን እግር ከወርች ያሰሩበት በፈጠራችሁ? እሽ 1944 የማንትስ ውል የሚል ነገር ተዋዋሉና ዶላር ነው ቋንቋችን አሉ! ይሄን ሁሉ አመት ወርቅ ቢባል ነዳጅ፣ ሚሊታሪ ቢባል ሲቪል፣ ሰላም ቢሆን ጦርነት ዶላር ምንተዳው! ስለዶላር ብዙ ኢኮኖሚስቶች፣ የፋይናንስና የታሪክ ባለሙያወች የሰጡትን ሌክቸር ሰምቻለሁ፣ የፃፉትን አንብቢያለሁ የደረስኩበት ድምዳሜ ዶላር ድግምት ነው የሚል ነው😁 ቀልድ እንዳይመስላችሁ ዶላር ከኤቲኤም ማሽን ስታወጡ (የሀብታም ምሳሌ ሰጠሁ ይቅር በሉኝ እኔም Bilal M Guwale ባለፈው ሲያወጣ ነው የሰማሁት ) ብቻ ስታወጡ ማሽኑ ተረረረረረረረ አይልም። በጥሞና ከሰማችሁት ያንደርብ... ያንጀርብ... የዠዣጥ... ያናዢጭ... ብሎ ዶላር ይሰጣችኋል። ወደቁም ነገሩ...😁 ይታያችሁ ዶላር የዓለማችን ውዱ ገንዘብ አይደለም! እንደውም 10ኛ ደረጃ ላይ ነው። የአንድ ገንዘብ "ውድ መሆን" እና "ኃያል መሆን" የተለያዩ ናቸው። የሌሎቹ ሀገራት ገንዘብ ዋጋቸው ከፍ ያለ ቢሆንም፣ የዓለም ንግድ የሚሽከረከርበትን የደም ዝውውር የተቆጣጠረው ግን የአሜሪካ ዶላር ነው። ወረቀቱ ከአሜሪካ ይሄዳል ነዳጅና ወርቅ ሆኖ ይመለሳል። እና ይሄ ድግምት አይደለም? የኩዌት ዲናር ዶላርን ሶስት እጥፍ ይበልጠዋል። ​የባህሬን ዲናር የኦማን ሪአል፣ ​የዮርዳኖስ ዲናር፣​የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ​የካይማን ደሴቶች ዶላር(የት ናት አሁን ይች በፈጠራችሁ?) ፣​የጀርሲ ፓውንድ ፣​የስዊዘርላንድ ፍራንክ፣​ዩሮ ....ብላችሁ ​የአሜሪካ ዶላር ነው የሚመጣው። ወደገባየው ስትመጡ ይሄ ሁሉ "ጨዋ" ነው፤ ለዶላር ይንበረከካል። ነገሩኮ ያው ሳይንስ ነው፤ መቸስ አሳምረው ቀምረውታል። ግን ይሄን ያህል ጊዜ ዓለማችን ላይ ዋጋውም ክብሩም ሳይነካ የተዘባነነ ነገር አለ ወይ? ደግሞኮ ብዙ አገራት ይነጫነጫሉ ይሄን ነገር ይቃወማሉ፣ ግን የሚነጫነጩት ራሱ ዶላር ከፍለው ነው። (አዙረውባቸው ነዋ) እኔ አሁን የምፈልገው Abdulkadir Hajj Nureddin ይሄን ነገር ትፈስርልናለህ ወይስ ወርልድ ቢዝነስ ሴንተርን ጠበል እንርጨው? ወይ ደህና ደህና አሊም ይዘን እናስቀራበት?

ብር ያስገኝ እንጅ ምንም ነገር ይሁን እሰራለሁ የሚሉ ሰወች የትም አይደርሱም!! ነገሩ የመቸገር ብቻ አይደለም፤ የመባከን የመግበስበስ በሽታም ነው። ለሆነ ነገር ሕይወትህን ጭምር እስከመክፈል የሚደርስ ፍቅር ይኑርህ። አንድ ነገር ላይ ዓይኖችህ ያተኩሩ፣ ኢላማ ይኑርህ እዛ ግብህ ላይ ለመድረስ ግን ማንኛውንም ነገር ስራ። በተለይ ይሄ ሶሻል ሚዲያና ድህነት ምንም ያልሆኑ ግን ሁሉንም ነገር ነን የሚሉ ማማሰያወችን ለጉድ እየፈለፈለብን ነው። የወሲብና ፖርኖግራፊ አስተማሪነትን ከሐይማኖት ሰባኪነት ጋር፣ ጋዜጠኝነትን ከካድሬነት፣ ትዳርን ከወንድ አተራማሽነት፣ በጎ አድራጊነትን ከሌብነት ጋር እኩል ሲያሳልጡት ስታይ አትገረምም ወይ ያ ጀመዓ?

ውድም! ብዙ ሰወች ብር ማግኘት የመጨረሻ ያስደስታቸዋል፤ የባንክ አካውንታቸው በሆነች ቁጥር ከፍ ሲል ሳይበሉ ይጠግባሉ ሳይ...ይረካሉ (ሳይጠጡ ለማለት ነው) የሆነ ሆኖ ብዙሃኑ የፋይናንስ ሰው የማይነግራችሁ እውነተኛው ደስታ ያለው ብር በማጠራቀም ውስጥ ባለው ጭንቀት የተሞላ መቆናቆን ሳይሆን ብር ማጥፋት፣ መክፈል፣ ቀልብ ለወደደው መዘርዘር፣ መመንዘር ላይ ነው። በተለይ ባጠፋኸው ብር ነገህ እንደማይበላሽ፣ ያወጣኸውን ያህል ወይም የበለጠ በቀላሉ የመተካት አቅሙ ካለህ፣ ማን ብር እንደማጥፋት! ውድም ርክት! ካርዱን ስትጭረው፣ ካሹን ስትዘረዝረው፣ ኤቲኤሙን ስታስተፋው ወዳጅህን "ስርዓት ያዝ እኔ ነኝ የምከፍለው" ስትል፣ ሳትከራከር ጠቅልይው ስትል፣ ነገ መለሰ አልመለሰ ሳትል ለተቸገረ ስትሰጥ...እውነተኛ ደስታ ያለው ብርን አፈር አባቱ አስበልተህ ለተፈጠረት ዓለማ ስታውለው ነው። ውድም! አስበው "ይችን ቆጥቤ ጫማ ብገዛ ፣ ይችን አጠራቅሜ መኪና ስትል ድፍት ብለህ "ውይ ትላንት ማዞሪያው ጋ እርጥብ ሲበላ አይቸው አልነበር ምን ነካው?" ሲሉህ😁 የሰው ልጅ የተፈጠረው ለማውደም ነው። መቆጠብ ማጠራቀም ይሉት ብሂል በኋላ የመጣ ጣጣ! "ለነገ አትጨነቁ" አለ ራሱ ጌትየው። እህሳ ብንል እያወደምክ ተመስገን እያልክ ኑር። አቦ የምታወድሙት ገንዘብ ከአውዳሚ ልብ ጋር ይስጣችሁ። ከየት አባቱ እያመጣ ነው የሚል ብስጩ ቢከባችሁም... ውድም!

የወለደች ሴት አግባ! (አሌክስ አብርሃም) ትዳር ብዙ ግላዊና የወል ምርጫዎች ያሉት ጉዳይ ነው። ግን በፍቺም ይሁን በሌላ ምክንያት ልጅ ብቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶችን እንደማግባት ጀነት የለም። የሕይወትን ትርጉም በሚገባ የተረዱ፣ ሕፃን ሕፃን የማያጫውታቸው፣ በክፉም በደጉም የትዳርን ጫና መቋቋም የሚችሉ፣ ከሚስትነት በላይ የእናትነት ክብርና የሰውን ልክ ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለሚደረግላቸውም ለሚያደርጉትም ነገር በምስጋና የተሞሉ፣ በሁሉም ነገር በመቶ የኮሌጅ ድግሪ የሚመነዘር በተግባር የተፈተነ ክህሎት ያላቸው፣ ስህተትና ቸልተኝነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ለሚያደርጉት ነገር ጥንቁቅ የሆኑ ምርጥ ፍጥረቶች ናቸው። ልጅ በሚባለው በር በኩል ከራስ ወዳድነት ወጥተዋል። ለአካባቢያቸው ለቤተሰብ ህያው ናቸው። ​ይሁንና ያልወለዳችሁ ሴቶች ከጋብቻ ውጭ እንዳትሞክሩት። እነዚህ ሴቶች ለዚህ ማንነት የሚበቁት እናንተ በቀላሉ የምታልፉትን የሕይወት መንገድ በብዙ እጥፍ የስጋና የስነ-ልቦና ስቃይ አልፈው ነው። ብዙዎቹ ብዙ የደከሙለትን ነገር መንገድ ላይ ትተውታል፤ መድረስ ከሚገባቸው ቦታ ሳይደርሱ ወርደዋል። ይሁንና ሌላ የተከበረ ማንነት ላይ ደርሰዋል።

ቴምር ሪል ስቴት የሀብታሙ ሃደራን የግጥም መድብል መፅሐፍ ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ለመቶ ሰወች ይሸልማል። እንዲሁም የመረጥኳቸውን መፅሐፍት ለአንባቢወቸ እንድሸልም የቴምር ሪል ስቴት ሴልስ ማን የሆነው አብርሃም ተስፋየ ነግሮኛል። ቴምሮች ከስነፅሁፉ ቤተሰብ ጋር የበለጠ በመስራት አዲስ ፈር ቀዳጅ እየሆኑ ነው። ምክንያቱም ንባብን በማበረታታት የሪል ስቴት ሳይቶቻቸውን ማስተዋወቅ ስለሚፈልጉ ነው። ማሳሰቢያ ከቴምር ሪል ስቴት ለማሰታወቂያ ሰባራ ሳንቲም አልተቀበልኩም! መፅሐፍ ገዝተው ደራሲወችን ያበረታታሉ፣ በዚህ በጎ ስራቸው ደራሲያን አንባቢወች ይጠቀማሉ። እኔም ማስታወቂያቸውን ያለምንም ክፍያ እለጥፍላቸዋለሁ።(የሪል ስቴት ማስታወቂያ እየሰራህ ነው ብር አበድረን፣ ባለአንድ መኝታ ከሳርቤቱ ሳይት አበድረን ምናምን እንዳትሉኝ😁) ቴምር ሪል ስቴቶች የላኩትን ማስታወቂያ እነሆ። ቴምር ሪል ስቴት በመሃል ከተማ ሳር ቤት አደባባይ እንዲሁም በቡልጋሪያ አፍሪካ ህብረት አዲስ ሳይቶች አሉት...ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ አፓርታማዎችን በተለያየ የ ካሬ አማራጭ ከ20 % ወይም ከ 1.5 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ወይም ከ 5.2 ሚሊዮን ብር ጠቅላ ዋጋ ያቀርባል። ፒያሳ አደባባይ ግንባታቸው 50% በላይ የተጠናቀቀ ከ 20 ካሬ ጀምሮ ዘመናዊ የንግድ ሱቆች አሏቸው። ቴምር ሪል እስቴት በ11 ዓመት 10ፕሮጀክት ጥንቅቅ አድርጎ ያስረከበ ግዙፍ ታማኝ ተቋም ነው * ምንም ዓይነት የዋጋ ግሽበት አይመለከተዎትም እንዲሁም ቀስ ብለው ካለ ምንም ወለድ በ ሶስት ዓመት ከፍለው ያጠናቀቃሉ ብሏል። በውጭ አገራት ለምትኖሩ ያሉበት አገር በ DHL ልከን እናስፈርመዎታለን ቅድመ ክፍያ ከተከፈለ በኋላ ቀሪው በግንባታ ሂደት በ16 ዙር ከፍለው የሚያጠናቅቁበት የአከፋፈል ስርዓት ተመቻችቷል። * የምንሸጣቸው ቤቶች ሁሉንም ነገር ያሟሉ ዘመናዊ አፓርታማዎች ናቸው ሳርቤት እና ቡልጋሪያ ቤቶቹ የሚከራዩት በዶላር ስለሆነ ለኢንቨስትመንት በጣም አዋጭ ናቸው ሳርቤት በዚህ ዋጋ አፓርታማዎችን ማግኘት አይታሰብም ብለዋቸኋል። ለማንኛውም መረጃ Abreham Tesfaye ን አግኙት ብዙ ዝርዝር ብዙ አማራጭ አለው። ወይም በዚህ ደውሉለት 0910798353 / 0908770077 https://wa.me/251910798353?text ወደመፅሐፍ ሽልማት! ....የሐብታሙ ሐደራን መፅሐፍ መሸለም የሚፈልግ ኮሜንት ላይ አለሁ ማለት ብቻ ነው።