cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የሱና ኡስታዞች ትምህርት ብቻ የምላክበት

فاعلم أن العبادة لا تسمى عبادة إلا مع التوحيد، كما أن الصلاة لا تسمى صلاة إلا مع الطهارة. فإذا دخل الشرك في العبادة فسدت، كالحدث إذا دخل في الطهارة. ( القواعد الأربع: ٧) 40 ምንጭ (Arba Minch) ✍️ ابو بلال حسين محمد

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 084
Obunachilar
-124 soatlar
-37 kunlar
-1030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🎙 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)  ተቀርተው የተጠናቀቁ ሙሉ ዱሩሶችን በቀላሉ ለማግኘት  ሊንኩን ይጫኑት 0⃣1⃣ ኪታቡ ተውሒድ ፈውዛን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4860 0⃣2⃣ ኡሱሉ ሱና ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሃምበል 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1760 0⃣3⃣ ቀዋዒዱል አርባኣ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5459 0⃣4⃣ አርባዒን አነወዊያ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1802 0⃣5⃣ ሀዚሂ ደዕወቱና ወአቂደቱና 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4588 0⃣6⃣ ኩን ሰለፊየን አለል ጃዳህ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2030 0⃣7⃣ ሚን ዑሱል አቂደቱል አህለ ሱና ወል ጀማዓ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4545 0⃣8⃣ ዓቂደቱል አህሊ ሱናቲ ወልጀማዓሕ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2068 0⃣9⃣ አቂደቱ ሰለፍ ወዓስሓቡል ሓዲስ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5195 1⃣0⃣ ሰላሰቱል ኡሱል (ኡሱሉ ሰላሳ) 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5483 1⃣1⃣ ፈትሁ ረቡል በሪያ ቢተልኺሲል ሃመዊያ (ተልኺስ)👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2562 1⃣2⃣ ኪታቡ ተውሒድ ሙሓመድ አብዱል ወሓብ👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2644 1⃣3⃣ሸርህ አቂደቱል ዋሲጢያ ሊል ሀሊል ኻራስ👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5450 1⃣4⃣ ዑምደቱል አሕካም ሚን ከላሚ ኸይሪል አናም👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2984 1⃣5⃣ ሸርሁ መንዙመቱል ሓዒያ ሸይኽ ፈውዛን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3207 1⃣6⃣ አል ኡሱል ሚን ዒልመል ኡሱል 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3265 1⃣7⃣ ሸርሑ ሙስጦለሁል ሓዲስ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3428 1⃣8⃣  ኹዝ አቂደተከ ሚነል ኪታቢ ወሱነቲ ሰሒሓ 👇https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3461 1⃣9⃣ ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3497 2⃣0⃣ ሙምቲዕ ሸርሑ አል አጅሩሚያ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3749 2⃣1⃣ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ ሊል ዑሰይሚን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3882 2⃣2⃣ ተብሲሩል ኸለፍ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4885 2⃣3⃣ ኢስቲቅባሉ ሸህሪ ረመዷን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3925 2⃣4⃣ ሚንሐጅ ፊርቀቱ ናጂያ ወጧኢፈቱ መንሱራ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3985 2⃣5⃣ ኹላሰቱል ኑሪል የቂን ጁዝ —1 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4025 2⃣6⃣ ተብሲሩል ባዲዒን ቢስጢላሓት አል ሙሓዲሲን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4073 2⃣7⃣ ቀዋዒዱል ሙስላ ፊ ሲፋቲላሂ ወዓስማኢል ሑስና👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4125 2⃣8⃣ ረውደቱል ባዲዒን ሚን አሓዲሲ ሰይዲል ሙረሰሊን👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4145 2⃣9⃣ ብሉግ አል መራም ሚን አዲለቲል አሕካም👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4448 3⃣0⃣ ተንቢሑ ዘዊል አፍሐም ኢላ ረእቢ ሰድኢ ወልዊአሚ አላ መንሐጅ ሰለፊል ኪራም👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4515 3⃣1⃣ ኡሱሉ ሲታ ሊል ዑሰይሚን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4578 3⃣2⃣ ሸርህ ከሽፉ አሹብሀት 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4669 3⃣3⃣ ተቅሪቡ ተድሙሪያ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4790 3⃣4⃣ አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ ሸይኽ ፈውዛን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5041 3⃣5⃣ ነዋቂዱል ኢስላም ሊሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5064 3⃣6⃣ ጂናየቱ ተመዩዕ አለል መንሀጂ ሰለፍ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5086 3⃣7⃣ ቱህፈቱ ሰኒያ ሸርህ መንዙመቱል ሓኢያ 👇 https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/5142 ይቀጥላል…  ይቀጥላል……
Hammasini ko'rsatish...
የ ተጠናቀቁ ሙሉ ደርሶች በ ኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ከሚሴ(አቡ ሓቲም) የተቀሩ ደርሶች

በድጋሜ የተቀራ አዲስ ደርስ ኪታቡ ተውሒድ ፈውዛን ሙሉ ደርስ  👆👆 ⌚️ ከ 00 እስከ 68 ✍ የኪታቡ ፀሓፊ = ሸይኽ ፈውዛነል ፈውዛን በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)

https://t.me/ABUJUWEYRIYAA

https://t.me/ABUJUWEYRIYAA

#ክፍል_22 #ብዥታዎችና_መልሶቻቸው የአላህን የትነት በተመለከተ ሁለት የተራራቁ አፈንጋጭ አንጃዎች አሉ ብለናል፡፡ አንዱ ፅንፍ አላህ "ሁሉም ቦታ ይገኛል" የሚል ፈጣሪን ከፍጡር ጋር የሚያመሳስል ቆሻሻ እሳቤ ሲሆን ሌላኛው ፅንፍ ደግሞ "አላህ የትም የለም" የሚል የንግግሩ አንድምታ ከናካቴው "ፈጣሪ የለም" ወደሚል የሚያመራ አራቋች እሳቤ ነው፡፡ ሁለቱም ፅንፎች እውነታውን በማስተባበል ላይ እና መረጃዎችን በመጠምዘዝ ላይ የተካኑ ናቸው፡፡ ሁለቱም ፅንፎች ሐቅን የያዙ ሰዎችን "አመሳሳይ" እያሉ በመወንጀል አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱም ፅንፎች የዒልመልከላም ውጤቶች ናቸው፡፡ ሁለቱም ፅንፎች የሚያንቀሳቀሱት በኢስላም ስም ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ፅንፎች በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ የተጋረጡ አደጋዎች ናቸው፡፡ ኢብኑልቀይዪም ረሒመሁላህ እንደሚሉት "አራቋች ምንም የሌለን ነገር ነው የሚያመልከው፡፡ አመሳሳዩ ደግሞ ጣኦትን ነው የሚያመልከው፡፡ የተውሒዱ ሰው ግን መልካም ስሞችና የላቁ መገለጫዎች ያሉትን፣ ምንም የሚመስለው የሌለውን ጌታ ነው የሚያመልከው፡፡" (አስሶዋዒቁልመሐርሰላህ፡ 1/148) እነዚህ አስተሳሰቦች በቁርአንም በሱናም የሌሉ ከቀደምት ታላላቅ ትውልዶችም ዘንድ የማይታወቁ መጤ አስተሳሰቦች ናቸው፡፡ የእነዚህ አመለካከቶች አራማጆች መጤ ሀሳብ ስላመጡ አያፍሩም፡፡ ይልቁንም ቁርአንና ሱናውን ተከትለው ሐቁን የሚያስተጋቡትን በክህደት ይወነጅላሉ እንጂ፡፡ በርግጥ ይሄ የቢድዐህ ባለቤቶች መታወቂያ ነው፡፡ ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንደሚሉት "የቢድዐህ ሰዎች #መታወቂያ እንግዳ የሆነ አባባል ወይም ተግባር ያመጡና በዚያ ላይ ሰዎች እንዲከተሏቸው ማስገደድ ነው፡፡ ከዚያም በሱ ላይ (የተቀበላቸውን) ይወዳጃሉ፡፡ የተዋቸውን ደግሞ ጠላት ያደርጋሉ፡፡" (አልፈትዋ፡ 6/339) ሐቁ ደግመን ደጋግመን እንዳየነው ከሁለቱ መሀል ነው፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ ቀደም ብለን ያሳለፍናቸው ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃዎችና የቀደምት ምሁራን አባባሎች ለሁለቱም አፈንጋጭ እሳቤዎች በቂ መልስ መያዛቸው ይሰመርበት፡፡ ይህን በሚገባ ከያዝን በኋላ አሁን ደግሞ ሁለቱን አደገኛ እሳቤዎችና ብዥታዎቻቸውን በመጥቀስ በየተራ መልስ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ ~~ኢንሻአላህ ይቀጥላል~~ ✍️ #አቡ_ቢላል_ሁሴይን 📚 (ተውሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ገጽ 113-114)📚 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ከኪታቡ ተውሂድ ደርስ (ከክፍል-31) የተወሰድ ከዚህ ርዕስ ስር:- باب قول الله تعالى፡ {حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ} فيه مسائل በኃላ 👉 ስለ ሸኽ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት በሰፊው የተወሳ የሆነ 🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏሂ] 👉የድምጽ file🎙 bit.ly/4cugRnv 🎙 📱 @Twehid12 📱 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Hammasini ko'rsatish...
1
ከኪታቡ ተውሂድ ደርስ (ከክፍል-31) የተወሰድ ከዚህ ርዕስ ስር:- باب قول الله تعالى፡ {حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ} فيه مسائل በኃላ 👉 ስለ ሸኽ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት በሰፊው የተወሳ የሆነ 🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏሂ] 👉የድምጽ file🎙 bit.ly/4cugRnv 🎙 📱 @Twehid12 📱 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Hammasini ko'rsatish...
ሸኽ ሁሴን ትንቢት በኢብኑ ሙነወር.mp3

Shared with Dropbox

ሸኽ ሁሴን ትንቢት በኢብኑ ሙነወር.mp36.76 MB
#ክፍል_21 "#ጂብ_እስኪነክስ_ያነክስ" የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን በማስተባበል፣ ብዥታ በመርጨት ቀዳሚ የሆኑት ጀህሚያዎችና ሙዕተዚላዎች መነሻቸው አካባቢ ይህን ጥመታቸውን በገደምዳሜ ካልሆነ ወይም ሰዋራ ቦታ እየመረጡ ካልሆነ በቀር በግልፅ ለመናገር አይደፍሩም ነበር፡፡ ነገር ግን በጊዜው የነበሩ ምሁራን ተንኮላቸውን ስለተረዱ እነሱ ይፋ ሳያደርጉት በፊት ሲያጋልጧቸው ነበር፡፡ ይህን እውነታ ከሚያመላክቱ የቀደምት ምሁራን አባባሎች ውስጥ ጥቂቶቹን ብንጠቅስ፡ ➊. አዩብ አስሰኽቲያኒይ (131 ሂ.) ረሒመሁላህ ስለሙዕተዚላዎች እንዲህ ይላሉ፦ "#ሰዎቹ_ዳር_ዳር_የሚሉት #በሰማይ_ምንም_የለም_ሊሉ_ነው፡፡" (ሙኽተሶሩልዑሉው፡ 132) ➋.ሐማድ ኢብኑ ዘይድ አልበስሪይ ረሒመሁላህ (179 ሂ.)፦ "#ጀህሚያዎች_የሚዞሩት_በሰማይ #አምላክ_የለም_ሊሉ_ነው" ብለዋል፡፡ (አልሐመውያህ፡ 337) ➌. ዐባድ ኢብኑ አልዐዋም ረሒመሁላህ (185 ሂ.) ፦ "(አፈንጋጩን) ቢሽር አልሚሪሲንና ጓደኞቹን አናግሬያቸው ነበር፡፡ #የንግግራቸው_መጨረሻ '#በሰማይ_ምንም_የለም' #ወደ_ማለት #እንደሚያደርስ_አስተውያለሁ፡፡ ሊጋቧቸውና ሊዋረሷቸው አይገባም እላለሁ" ይላሉ፡፡ (ሙኽተሶሩልዑሉው፡ 254) ➍. ጀሪር ኢብኑ ዐብዲልሐሚድ አድዶቢይ ረሒመሁላሄ (188 ሂ.)፦ "የጀህሚያህ ንግግር መጀመሪያ ማር ነው፡፡#22 መጨረሻው ግን መርዝ ነው፡፡ #የሚጥሩት_በሰማይ_አምላክ_የለም #ለማለት_ነው" ብለዋል፡፡ (ሙኽተሶሩልዑሉው፡ 251) ➎. ዐብዱርረሕማን ኢብኒ መህዲ (198 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ጀህሚያዎች አላህ ሙሳን ያናገረ መሆኑንና #አርረሕማን_ከዐርሹ_በላይ #መሆኑን_ሊክዱ_ፈልገዋል፡፡ ተውበት እንዲያደርጉ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ከተመለሱ መልካም፡፡ ካልሆነ ግን አንገት አንገታቸውን በሰይፍ ሊመቱ ይገባል፡፡" (ሙኽተሰር አልዑሉው፡ 164) ➏. ወህብ ኢብኑ ጀሪር (206 ሂ.) ረሒመሁላህ፦ "ከጀህም አመለካከት ተጠንቀቁ!! እነሱ '#በሰማይ_ምንም_የለም' #ሊሉ ነው_የምጣጣሩት፡፡ ይሄ የኢብሊስ 'ወሕይ' እንጂ ሌላ አይደለም!! ይሄ ክህደት እንጂ ሌላ አይደለም" ብለዋል፡፡ (አልጁዩሽ፡ 145) ቡኻሪ በዘገቡት ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡ "#አፈንጋጭ_ጀህምያዎች_የምፈልጉት #እሱ_በዐርሹ_ላይ_አይደለም_ሊሉ #ነው፡፡" (ኸልቁ አፍዓሊልዒባድ፡ 30) ➐. አልሓፊዝ አቡ መዕመር አልቀጢዒይ (236 ሂ.) - ረሒመሁላህ (የቡኻሪ ሸይኽ ናቸው)፦"#የጀህሚያህ_ንግግር #መጨረሻው_በሰማይ_አምላክ_የለም #ማለት_ነው" ብለዋል፡፡ (ሙኽተሶሩልዑሉው፡ 188) ሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ "ጀህሚያዎች በዚህ ላይ ዳር ዳር ይሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰለፎችና ታላላቅ ምሁራን ስላሉ፣ የሱናህ ሰዎችም ብዙ ስለነበሩ በግልፅ አይናገሩም ነበር፡፡ ጊዜው በሄደ እና ታላላቅ ምሁራኑ ባለቁ ጊዜ እነዚያ ይጠቁሙትና ይዞሩበት የነበረውን ተከታዮቻቸው ግልፅ አወጡት፡፡" (አልጁዩሽ፡ 145) አላሁልሙስተዓን!! ______ #22 "መጀመሪያው ማር ነው" ያሉበት ምክንያት ልክ ዛሬ አሕባሾች እንደሚያደርጉት በተውሒድና አላህን በማጥራት ስም ስለሚያቀርቡት ነው፡፡ ______ ~~ኢንሻአላህ ይቀጥላል~~ ✍️ #አቡ_ቢላል_ሁሴይን 📚 (ተወሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ገጽ 112-113) 📚 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
07:19
Video unavailableShow in Telegram
አላህ ከአርሹ በላይ ነው የአብደላ አል ሀረሪ ሰዎች ጩኸት 🎤 ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ [ሀፊዘሁሏሂ] 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Hammasini ko'rsatish...
33.56 MB
#አላህ_የት_ነው? "አላህ የት ነው" ለሚለው የነብያዊ ጥያቄ "ሰማይ ላይ" ብለህ ከመለስክ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ፈተናውን አልፈሀል፡፡ ከዝንባሌያቸው የማይናገሩት ነብይ "አልፈሃል" ካሉህ ሚሊዮኖች ተሰብስበው "ወድቀሃል" እያሉ ቢያስተጋቡ አይጭነቅህ፡፡ ሙዓውያህ ኢብኑልሐከም አስሱለሚይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦ "በጀዋኒያህ እና ኡሑድ (ተራራ) መካከል በግ የምትጠብቅልኝ አንዲት አገልጋይ ነበረችኝ፡፡ አንድ ቀን ጎራ ስል ተኩላ አንዷን በግ ወስዷታል፡፡ መቼስ እኔም እንደማንኛውም ሰው፣ ሰው ነኝና አዘንኩኝ፡፡ እናም በጥፊ አጮልኳት፡፡ ከዚያም ወደ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጣሁና የሆነውን ስነገራቸው ጉዳዩን አከበዱብኝ፡፡ ይህኔ 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እንግዲያው ለምን ነፃ አላወጣትም?' ስላቸው [#ይዘሀት #ና] አሉኝ፡፡ ከሳቸው ዘንድ አመጣኀት፡፡ ከዚያም [#አላህ #የት #ነው?] ሲሏት 'ሰማይ ላይ!' አለች፡፡ [#እኔስ #ማነኝ?] ሲሏት 'እርሶ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነዎት' አለች፡፡ እሳቸውም [#ነፆ #አውጣት፡፡ #ምክንያቱም #እሷ #አማኝ #ነችና] አሉ፡፡ (ሙስሊም፡ 1227) #17 ይቺ ባሪያ በምን ምክንያት በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አማኝነቷ እንደተመሰከረላት፣ አልፋም ነፃነቷን እንደተጎናፀፈች ያስተውሉ፡፡ የተጠየቀችውን ሁለት ጥያቄዎች በትክክል በመመለሷ ነው፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች የመጀመሪያው ደግሞ "አላህ የት ነው?" የሚል ሲሆን የመለሰችውም "ሰማይ ላይ" ብላ ነው፡፡ ዛሬ ይሄ ጥያቄ ቢቀርብላቸው ፈተናውን የማያልፉ ከዚያም በላይ ጥያቄው እራሱ ጤነኛ አይደለም የሚሉ "የተማሩ" ሞገደኞች በዝተዋል፡፡ አልኢማም አዝዘሀቢይ ረሒመሁላህ በዚህ ሐዲሥ ስር እንዲህ ብለዋል፡"በሐዲሡ ውስጥ ሁለት አንኳር ነጥቦች ያሉ ሲሆን አንደኛው አንድ ሙስሊም 'አላህ የት ነው?' ብሎ መጠየቁ ሸሪዐዊ መሆኑ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ተጠያቂው 'ሰማይ ላይ' ብሎ መመለሱ ነው፡፡ እነኚህን ሁለት አንኳር ነጥቦች የተቃወመ እየተቃወመ ያለው ሙስጠፋን (ነብዩ ሙሐመድን) ነው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡" (ሙኽተሶሩልዑሉው፡ 81) ይቺ ባሪያ አንዳንዶች እንደሚሉት መናገር የማትችል ዲዳ አይደለችም፡፡ [#አላህ #የት #ነው?] ሲሏት "በሰማይ!" [#እኔስ #ማነኝ?] ሲሏት ደግሞ "የአላህ መልእክተኛ ነዎት" ማለቷ ሀሳቧን በትክክል የምትገልፅ ተናጋሪ እንደሆነች ያስረዳል፡፡ ______ #17 ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ ከዚህ ሐዲስ ስር እንዲህ ይላሉ፡ "ይሄ ሐዲስ ያለ ጥርጥር ሶሒሕ ነው፡፡ መሀይም ወይም ተንኮል ያነገበ የስሜት ተከታይ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን አይጠረጥርም፡፡ እነኚህ ግን ያሉበትን ጥመት የሚፃረር ግልፅ ማስረጃ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመጣላቸው ቁጥር መልእክቱን በመጠምዘዝ አልፎም በማራቆት ሊገላገሉት ይሞክራሉ፡፡ ይሄ ካላዋጣቸው ደግሞ ጥንካሬው ላይ ትችት ይሰነዝራሉ፡፡ ልክ እንደዚህ ሐዲስ፡፡ ይህ ሐዲስ የመጣበት ሰንሰለት ጤናማ ከመሆኑም ጋር፣ የሐዲሥ ምሁራንም እኔ እስከማውቀው ድረስ ያለ ምንም ልዩነት ሶሒሕነቱን መስክረዋል፡፡ ለምሳሌ ኢማሙ ሙስሊም በሶሒሕ ጥራዛቸው ዘግበውታል፡፡ አቡ ዐዋናህም በ "ሙስተኽረጃቸው"፣ በይሀቂይም እንዲሁ በ(#አልአስማእ፡ 422) ላይ "ሶሒሕ ነው ሙስሊም ዘግበውታል" ብለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር እንደ ከውሠሪ ያሉ ጭፍንነት ያጠፋቸው ሰዎች ግን "መምታታት አለበት" በሚል ሙግት ሶሒሕነቱን ሊያጠራጥሩ ሞክረዋል፡፡ ይህ የሆነው እንግዲህ ከተለመደው የሐዲሥ ጥናት ባፈነገጠ መልኩ ጠንካራውን ሰነድ ልዩነት ካለው ከደካማው ጋር ለንፅፅር ለማቅረብ ነው፡፡" በአፊል ተነካክቶ የተወሰደ፡፡ (ሙኽተሰሩልዑሉው፡ 82) ሙስሊም፣ ኢብኑ ዐዋናህ፣በይሀቂና ሸይኩልአልባኒይ ይህን ሐዲስ "ሶሒሕ" ማለታቸው የማይዋጥለት ካለ ኢብኑ ሐጀርም ተመሳሳይ ብይን ሰጥተዋል፡፡(ፈትሑልባሪ፡ 13/359) (ተውሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ገጽ 84-87)
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
09:07
Video unavailableShow in Telegram
ወንጀሎች ሲበዙ አጭር ምክር 🎤  ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ [ሀፊዘሁሏሂ]
Hammasini ko'rsatish...
41.32 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.