cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ! . ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤ ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
9 494
Obunachilar
-1024 soatlar
-437 kunlar
-8330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

. ጥሩው ነገር ግን እዚህ መድረሳችሁ ነው፡፡ዩኒቨርሲቲ የቀለም ትምህርት ብቻ ሳይኾን ሕይወትን የተማራችሁበት፣ከሰው ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል ያወቃችሁበት፣ የሕይወት ዘመን ጓደኞች ያፈራችሁበት፣ ከቤተሰብ ርቃችሁ ብዙ ነገር የተጋፈጣችሁበት ሥፍራ እንደመኾኑ ይኽን ሁሉ ይዛችሁ እዚህ መድረሳችሁ ሊያኮራችሁ ይገባል! ተስፋ ሳትቆርጡ፣ የጀመራችሁትን ሳታቋርጡ እዚህ ስለደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ለራሳችሁ ሞራል ሥጡ! በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! . (#ፈይሠል_አሚን) . @huluezih @huluezih
Hammasini ko'rsatish...
ለተመራቂዎች:- . • ዩኒቨርሲቲ ስትገቡ የቀይ ዳማ መልክ ይዛችሁ ገብታችሁ እንደ ዳማ መጫወቻ ጥቁርና ነጫጭባ ኾናችሁ የወጣችሁ… • የካፌ ምግብ ጨጓራችሁን አስረጅቶ በከዘራ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ጨጓራ ባለቤት ያደረጋችሁ. . . • 4 D 3C እና 2 F በመያዝ በቀጣይ ዓመት Add ለማድረግ ወደ ዪኒቨርሲቲ የምትመለሱና ቤተሰብ ጉዱን ሳያውቅ በሬ ጥሎ የደገሰላችሁ ተመራቂዎች. . . • ሁሌ ከክላስ እየቀራችሁ፣ አስተማሪ ለምን ክላስ እንደማትገቡ ሲጠይቃችሁ ‹‹ብዙ ትኩረት መሣብ ስለማልወድ ነው!›› ስትሉ ተማሪዎች…. . • አንዳንድ የሰላም መደፍረስ ያለባቸው ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ ካጠናችሁት ኮርስ በላይ ስልታዊ ማፈግፈግና ወታደራዊ ስትራቴጂ ተምራችሁ የወጣችሁ. . . • የበሶ ውለታ ያለባችሁ ተመራቂዎች. . . • በቴንሽንና በተመጣጠነ ምግብ እጦት ፈተና በደረሰ ቁጥር ፌንት እየበላችሁ ብዙ ተሸካሚ ወንድምና እህቶች ያፈራችሁ. . . . እናም ሌሎችም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንኳን ለዚህ አበቃችሁ. . .እንኳን ደስ አላችሁ! . በተለያየ ዓመትና በተለያየ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብንማርም ሁላችንም ዩኒቨርሲቲ የገባን ተማሪዎች አንድ ዓይነት ታሪክ እንጋራለን፡፡ በዚህም ምክንያት ወጣቶች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እስኪወጡ ድረስ ምን ሊገጥማቸው ይችላል የሚለውን በመጽሐፍ መልክ በማዘጋጀት ትውልዱን ከመደናገር ለመታደግ አስቤያለሁ፡፡ርእሱም ‹‹እኛም እንናገር፣ተመራቂ አይደናገር!›› የሚል ነው፡፡ . ከመጀመሪያው ስንጀምር. . . ሁላችንም ዩኒቨርሲቲ እንደደረሰን ስናረጋግጥ መጀመሪያ ላይ መጥተው ‹‹ምትፈልገውን ማንኛውም ነገር ካለ ንገረኝ! አትደብቀኝ! እኔ አሟላልሃለሁ!›› የሚሉ አጎቶችና አክስቶች አሉን፡፡ እንዲህ ካሉን በኋላ ግን ጠፍተው የምርቃታችን ቀን ነው በዓይነ ሥጋ የምናያቸው፡፡ አንዳንዴ ቸግሮን ስንደውልላቸው የማይገናኝ ምክንያት የሚያቀርቡ ዘመዶች ሁላችንም ጋር አሉ፡፡ ደውለን ‹‹የምትፈልገው ነገር ካለ ንገረኝ ብለኸኝ ነበር….›› ስንል ‹‹እቴኑ እኮ ሞተች!›› ብለው ወሬ የሚያስቀይሱ ዘመዶች እናንተ ጋር ብቻ ሳይኾን እኛም ጋ ነበሩ፡፡ ዘመን አይሽሬ ናቸው፡፡ . እንደ ልማዳቸው የምርቃት ቀን ይመጡና ‹‹እንኳን ለዚህ አበቃህ! አሁን ሥራ ነው ሚያስፈልግህ…..በሰው በሰው አፈላልገን አንድ ቦታ እንሸጉጥሃለን!›› ብለው ሌላ ቃል ይገቡልሃል፡፡ ከዚያ አንተ በባስና በባቡር እየተሸጎጥክ ሥራ ፈልገህ ስታጣ ደውለህ…ቃል ገብተህ ነበር ስትለው. . .እንደ ልማዱ ‹‹እቴኑ እኮ ሞተች!›› ብሎ ወሬ ያስቀይሳል፡፡ እኔ ፍሬሽ ተመራቂ እያለሁ ይኼን የሚነግረኝ ሰው ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር፡፡ . የዚህ ዘመንን የዩኒቨርሲቲ ሕይወት ከእኛ ዘመን ትንሽ የሚለየው ሁለት ነገር ይመስለኛል፡፡አንደኛው በፊት ዩኒቨርሲቲ ገብተን ስንወጣ ነበር የምንመረቀው….አሁን አሁን ደሞ ቤተሰብ መርቆን ካልገባን በሰላም ለመውጣት እንቸገራለን፡፡ . ሌላው ልዩነት ዩኒቨርሲቲዎች አዳዲስ ተማሪዎችን ለመጥራት የሚያወጡት ማስታወቂያ ይመስለኛል፡፡ ሐገሪቱ ባለችበት ሁኔታና እውነታ ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎች አሁን አሁን ተማሪ አጠራራቸው ራሱ ያስደነግጣል፡፡ . ‹‹ማስታወቂያ ደብረ-ጤዛ ዩኒቨርሲቲ ለደረሳችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፡- ‹‹ደብረ-ጤዛ ዩኒቨርሲቲ የቀጣይ ዓመት መደበኛ ተማሪዎችን ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ተቀብሎ የሚመዘግብ በመኾኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፎችን በመያዝ፣ ከላይ ከተጠቀሰው ውጪ አንሶላ፣ብርድልብስ፣ ሻንጣ እና በቆይታችሁ የምትጠቀሟቸውን ተጓዳኝ ምግቦች ሽፍታዎች ሊቀሟችሁ ስለሚችሉ ባትይዙ ይመረጣል፡፡በማስታወቂያ ላይ የተጠቀሱትን አሟልታችሁ ፈጣሪ ብሎ ድንገት በሕይወት ወደ መመዝገቢያ ስፍራው ከደረሳችሁ በአስቸኳይ የምናስተናግድዎ ይኾናል(በሕይወት ካለን!)፡፡ፈጣሪ በኪነ-ጥበቡ ይጠብቃችሁ!›› . እንዲህና መሰል መከራዎችን አልፎ የተመረቀ ተማሪ በምርቃቱ ቀን ምንም ቢያደርግ ወዙ ሊመጣ አይችልም፡፡ ሁላችንም በምርቃታችን ቀን ሰቀቀኑ አክስቶንና አጥቁሮን፣በዲፌንስ ድንጋጤ ዓይናችን ቦግ ብሎ ቀርቶ፣አስተማሪ ሚመስል ሰው ባየን ቁጥር እየተደናበርን…… በምርቃታችን ቀን የተመረቀ ሰው ሳይኾን የመረቀነ ሰው ነው ምንመስለው፡፡ . ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርሲቲ የሔድኩት የኦረንቲየሽን ቀን ነበር፡፡ሁሉም ዲፓርትመንቶች በተወካያቸው በኩል አዳዲስ ተማሪዎች እንዲቀላቀሏቸው ሲያማልሉ ደረስኩ፡፡ እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የመጀመሪያውን ሳክስ እና ግነት የምትሰሙት ኦረንቲየሽን ላይ ነው፡፡ በስስ ጎናችን በኩል ጀንጅነው፣ ሥራ አለ ብለው ያለ ፍላጎታችን ዲፓርትመንታቸውን እንድንቀላቀል የማይሉት ነገር የለም፡፡ የዚያን ቀን የአርኪዮሎጂ ዲፓርትመንትን ወክሎ የመጣው ሰውዬ እንዲህ አለ፡- ‹‹እንግዲህ እኛ ብዙ ራሳችንን ማስተዋወቅ የለብንም፤ጥሩ ነገር ማስታወቂያ አይፈልግም፡፡ የእኛ ዲፓርትመንት በጣም ሰፊ የሥራ ዕድል ያለው ዘርፍ ነው፡፡ እንደምታውቁት እስካሁን ሉሲ ብቻ ናት ሙሉ ለሙሉ የተገኘችው፡፡ገና አባትና እናቷ፣ ባለቤቷ እና ጎረቤቶቿ ስላልተገኙ እናንተ እነሱን በማግኘት ከበርቴ ልትኾኑ የምትችሉበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ የእኛ ተማሪዎች ጥንታዊ ቅሪተ-አካሎችን ለማግኘት የልምምድ ቁፋሮ በሚያደርጉበት ወቅት በድንገት ነዳጅ አግኝተው የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ሕይወት ቀይረዋል፡፡ ስለዚህ እናንተም ከጸጋ በረከቱ ትቋደሱ ዘንድ እነሆ ተቀላቀሉን!›› . እውነት ነዳጅ አገኛለሁ ብለህ ስትገባ ….ራስህን አስተማሪው ጀሪካን ሰጥቶ ለመኪናው ነዳጅ እንድታመጣ ሲልክህ ታገኘዋለህ! . በመጨረሻ የሚመር እውነት ሹክ ልበላችሁ፡፡ አሁን እየተሰማችሁ ያለው ስሜት እኛም ስንመረቅ ተሰምቶናል፡፡አሁን እያሰባችሁ ያላችሁትን ነገር እኛ አስበነው ነበር፡፡ ከምታስቡት ሐሳቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- ‹‹አሁን ተመርቄያለሁ! ሥራ ይዤ ለፍቶ ያስተማረኝን ቤተሰቤን እየደጎምኩ፣ ከማገኘው ደሞዝ ቆጥቤ ዕዳዬን ከፍዬ ማስተርሴን እቀጥላለሁ!›› ብላችሁ የምታስቡ አላችሁ አይደል? . ሌሎቻችሁ ደሞ ‹‹ትምህርቱ ይበቃኛል፣ የራሴን ነገር ጀምሬ…ድርጅት አቋቁሜ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል እፈጥራለሁ›› ብላችሁ እያሰባችሁ ነው፡፡ . የተቀራችሁት ደሞ ‹‹ስኮላርሺፕ አግኝቼ…ከሐገር ወጥቼ፣ በአውሮፓ ወይ በአሜሪካ ትምህርቴን ተምሬ፣ጥሩ ሥራ ይዤ ከኢትዮጵያ ሚስት አስመጥቼ ጥሩ ቤተሰብ መሥርቼ እኖራለሁ!›› እንደዚህ የምታስቡ አላችሁ አይደል! ይኼን ሐሳባችሁን እኛ ስንሰማ ምን እንደምንል ታውቃላችሁ? ‹‹ወላሂ! ኧረ? እንደዛ ነው!›› . ሐቅ ሐቁን እናውራ ከተባለ….በተማርንበት ሙያ ላንሠራ እንችላለን፡፡ በኢንጂነሪንግ የተመረቀ ጓደኛዬ በሐገሪቱ ሁኔታ ምክንያት እሳት የላሰ ደላላ ኾኗል፡፡ ከየት እንዳመጣው ባላውቅም አሁን እንደሱ ሰውን የማሳመን ችሎታ ያለው ሰው የለም፡፡ ባለፈው የኾነ ቤት ሊያከራይ ደንበኞችን ይዞ ሲሔድ ቤቱ ሽንት ቤት የለውም፡፡ ‹‹ቤቱ እኮ ሽንት ቤት የለውም!›› ሲሉት ‹‹ችግር የለውም! ለጊዜው በዳይፐር ትጠቀማላችሁ!›› ብሏል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የድመቴ ጉዳይ! . "ድመትህን ጨክነህ አባረርከው?" የሚሉ ጥያቄ የሚመስሉ ውንጀላዎች ደርሰውብኛል😄 እርግጥ ተገቢ ጥያቄያዊ ውንጀላ ነው። ቢኾንም ግን እኔ ለዓመታት እንደ ልጄ አቅብጬ ያሳደግኩትን ድመት፣ በተመጣጠነ ምግብ እና በተመጣጠነ እንቅልፍ አሞላቅቄ ያኖርኩትን ድመት፣ መክሬ እና ዘክሬ ለአቅመ አዳም ያደርስኩትን ድመት. . . ሚስት አገባሁ ብዬ ባባርር ሚስቴ ራሱ ምን ትላለች? "ለድመትህ ካልኾንክ ለእኔም አትመለስም?" ብላ አትሰጋምን? . የተፈጠረው ነገር አሳሳቢ ነው። ድመቴ ግቢውን እንደ ግቢው ቆጥሮ አከራዬም እኔም ጋር እየተመላለሰ በነፃነት የሚኖር ቀበጥ ድመት ነው። አሁን ግቢውን እንደምለቅ ስታውቅ ድመቱን ይዤው እንደማልሔድ አስጠንቅቃ ነገረችኝ። ምክንያቷ ደሞ "ድመቶች አዲስ ቦታ የመልመድ ችግር ስላለባቸው ወደዚህ ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት የመኪና እራት ይኾናል("የመኪና እራት" ማለት ግን ምን ማለት ነው? መኪና ነዳጅ እንጂ ድመት አይበላም ልበላት እንዴ?🙄 ፣ በዚያ ላይ ደሞ ይኼ ግቢ ካለ እሱ አይኾንም ጭር ይላል!" የሚል ነው መከራከሪያ ነጥቧ! ተከራክራኛለች። . እኔ አዲሱን ቤት ለመልመድ ተቸግሮ የመኪና እራት ቢኾን የሚለው ቢያሰጋኝም፣ ያሳደግኩትንና እኔን ብሎ ያን ግቢ የለመደን ድመት ጥዬ መሔድ አልችልም። ድመቴን እስካልሠጠሽኝ ድረስ የቤቱን ቁልፍ አልመልስም በማለት ክርክሩን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋግሬዋለሁ። ይኽ የድመት ይገባኛል ጥያቄ እየከረረ ሔዶ ፍርድ ቤት እንዳይደርስ በመስጋት ላይ እገኛለሁ😁 (አስባችሁታል ለድመት ጠበቃ ሳቆም😅) . በርግጥ አከራዬ ለድመቱ የተለየ ፍቅር አላት፣ ትንከባከበዋለች። ግን እኔ ደሞ እዚህ ድረስ አብሬው የመጣሁትን ድመት ጥሎ መውጣት ያስወቅሰኛል። እስቲ እንወያይበት....እርስዎ ቢኾኑ ምን ያደርጋሉ?😁 . @huluezih @huluezih
Hammasini ko'rsatish...
ትዳር መያዜን ሰምታችሁ ግሩፕ ውስጥ መልካም ምኞታችሁን የገለፃችሁልኝ ሰዎች እንደ ቤተሰብ የምንቆጣጠርበት ቻናል ውስጥ ማሳወቅ እንደነበረብኝ እንዲሰማኝ አድርጋችሁኛል። ምንም እንኳ የግል ጉዳይ ቢኾንም ከግል ሕይወት በመነሳት የምጽፋቸውንም ጽሑፎች ስታነቡ፣ስትነጋገሩበት፣ሐሳብ ስትጨምሩበት ቆይታችኋል። በዚህም ምክንያት አሁን ማግባቴን እንደ ቤተሰብ ቆጥሬ ለመናገር ተገድጃለሁ። አከብራችኋለሁ🙏
Hammasini ko'rsatish...
ቀርተሻል መሰለኝ! . (#ፈይሠል_አሚን) . በዚህ ፉንጋ ክረምት በዝናብ. . . በካፊያ. . . በውርጩ ስልተ-ምት፤ ሐምሌ ባጨቀየው፣በረጠበው ኮረት፤ እየጠበቅኩሽ ነው በቃሌ መሰረት! (ዘይግተሻል!) . ደሞ ነገር በላሁ ደርሶ አብሰለሰለኝ፤ ሲሉ እንደሰማሁት ቀርተሻል መሰለኝ! . ግዴየለም! ጡር እና ግፍ ሳትፈሪ ከቀረሽም ቅሪ! ልቤ ነግሮኝ ነበር፣ፊቱንም ስትቀጥሪኝ፤ ብቻ መቅረትሽን ነይና ንገሪኝ! . ("የቀሩት" ናቸው የሚያሳምሙን!🙂 . @huluezih @huluezih
Hammasini ko'rsatish...
#ላሽ_ታግ-Time . ቢንቢ ትሙት የት አባቷ! . ሌሊቱን ሙሉ ከቢንቢ ጋር የማያባራ ጦርነት ገጥሜ ሳልተኛ ነው ያደርኩት! ቢንቢዎች ሰይጣን መረጃ ለመሰብሰብ የሚጠቅማባቸው መሣሪያዎች ስለሚመስሉኝ በጣም ያስጠሉኛል። አዕምሯቸውን ለእኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ካላዋሉት ለምን ጨለማን ተገን አድርገው፣ ለሊትን መርጠው ጆሮ ላይ ብቻ የተቃጣ ጥቃት ይፈጽማሉ ታዲያ? ፀረ ሰላም ነፍሳት ናቸው! . ገና መብራቱን ከማጥፋቴ አንድ የሳንቾ ዓይነት ድምጽ ያለው ጎልማሳ ቢንቢ ቀኝ ጆሮዬ ላይ የመክፈቻ ንግግር 'ሚመስል ነገር አደረገብኝ። ችላ ብዬ...ጆሮዬን በብርድ ልብሴ ሸፍኜ ተጠቅልዬ ተኛሁ። አልመች ያለው ይኽ ጎልማሳ ቢንቢ ተናዶ ሔደና ተጨማሪ የቢንቢ ኃይል አስከትሎ መጥቶ፣ ብርድ ልብሴ የማያቆመውን ድምጽ ማጉያ በመጠቀም በሙሉ ባንድ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ጀምሮ "ለሰው ልጆች ሰላም" በሚል ህብረ ዜማ ጫፉን ከያዝኩት እንቅልፍ አቆራረጡኝ። ይኽን ጊዜ ነው እንግዲህ ብልጭ ያለብኝ! . መብራቱ አብርቼ ዋጋቸውን ልሠጣቸው ስል ከአካባቢው ተሰወሩ። እኩይ ዓላማ እንዳላቸው ማረጋገጫው መብራት ሲበራ መሰወራቸው ነው! የሠሩት ሥራ ወንጀል ባይኾን ለምን ይጠፋሉ? ከእልህ አስጨራሽ ክትትል በኋላ ሁለት ቢንቢዎችን በቁጥጥር ሥር አውዬ አስከሬናቸው ለገናዥ እንዳይመች አድርጌ በትራስ አፍኜ ጨፈለቅኳቸው። . አንድ ሰውዬ "ቢንቢዎች ለምንድነው ጆሮ ላይ ብቻ 'ሚጮሁት?" ተብሎ ተጠይቆ "እና ቂጥህ ጆሮ የለው!" ማለቱ ትዝ ይለኛል። እኔ እንቅልፌን ሰውቼ የደረስኩበት ነገር "ሰው ከእንቅልፍ የሚያገኘውን ፍሰሃ ለማኮላሸትና ቀኑ እንዲዛባ ለማድረግ" መኾኑን ተረድቻለሁ! እሱ እንዳለው ያ ጠላቱ ቢንቢ ይሙት የት አባቱ! #ሞትለቢንቢ . @huluezih @huluezih
Hammasini ko'rsatish...
ብልህነት ማለት.mp36.82 KB
Photo unavailableShow in Telegram
ልብ 'ሚነካ ገዢ!🥺 . የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የኾነው ይኽ ወጣት "በ500 ብር መጽሐፍ መግዛት ባልችልም ሕልምህን እውን ለማድረግ ያለኝን 400 ብር ልኬያለሁ" ብሎኛል። ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበር የተሰማኝ። ዙሪያዬ ላይ በቅርብም በሩቁም የማውቃቸው ብቻቸውን መጽሐፉን አሳትመው ከሽያጩ ያወጡትን ወጪ መሸፈን የሚችሉ በርካታ ሰዎች አሉ። በእዚህ ዓይነት መነጽር ነገሩን ዐይተው ለማበረታታት የጋረዳቸው ግርዶ ስላለ እንጂ! ይኽ መጽሐፍ ለህትመት በቅቶ ለንባብ ሲደርስ የእንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ውለታ ልረሳው አልችልም። አልቅስ አልቅስ የሚያስብል ማበረታቻ ነው። ከገዛኸው መጽሐፍ በላይ ቅንነትህ ለእንደኔ ዓይነት ሰዎች ትልቅ ማነቃቂያ ነው። ለአንተ ሲል ያሳክልኝ🙏 በሙሉ ልቤ አመሠግናለሁ። . አሁንም ቅድመ-ሽያጩ እንደቀጠለ ነው! 1000413125654 Feysel #ሰንባች
Hammasini ko'rsatish...
ልቤ ግን እንዴት ነው? . (#ፈይሠል_አሚን) . አፈነኝ. . . አሰረኝ. . .የጥያቄ ግርዶ. . . "ሰው እንዴት ይሔዳል? ድንገት እንደ መርዶ?" . የኾነው ሁሉ ኾኖም. . . ልቤ ተከተለሽ! (አይገርምም?) ከክህደትሽ ይልቅ ውህደትሽ ተጫነው፤ አንቺ ተዘቅዘቂ! ልቤ ግን እንዴት ነው? . @huluezih @huluezih
Hammasini ko'rsatish...
አዝናለሁ አልወደቅኩም! . (#ፈይሠል_አሚን) . አንድ ኀሙስ እንደቀረው፣ የብሶት ዜማ የማንጎራጉረው፤ ስለጠፋኝ አይደለም. . . መንገድ ስለቀረሁ! ቀናነት ሳይከብድ፣ መኾን ሲቻል መልካም፤ ተንኮል ለመጎንጎን፣ ለደከሙት ድካም. . . "እሪ!ኩም! ዘመዳ! "ዘመዳ እሪ!ኩም!" እኔ ግን. . . አዝናለሁ! አልወደቅኩም! . እበቅላለሁ እያልኩ. . . በአፍ-ጢሜ ስተከል፤ ማቆጥቆጥ ሲመስለኝ፣ ከሥሬ መነቀል፤ ከአረም ጋራ ኾነ. . . የእኔ አበቃቀል! ሆድ ባይብሰኝም. . . "እሪ!ኩም! ዘመዳ! ዘመዳ እሪ!ኩም!" አዝናለሁ! አልወደቅኩም! . ግፊያና ግፍተራ የፍቅር መሰለኝ፤ እኔ እንደሁ' ስወድ. . . ወትሮም ዓይን የለኝ! ዝቅ ማለት ጎዳኝ፣ መች ዐውቃለሁ ብልጠት? ላከበርኩት ሁሉ፣ማጅራቴን መሥጠት! ሰው ነኝና. . .ተጓዥ! መንገድ ነውና... ጎዝጓዥ! ሞክሬ. . ዳክሬ. . . ከጭቃ ውስጥ እሾህ አላመለጥኩም፤ ግን አዝናለሁ! አልወደቅኩም! . የሌላውን ወድቀት አስበልጦ 'ሚሻው፤ ካቲማው አያምርም ዳሩ መጨረሻው፤ቀ ብትካኑበትም...አጣጣል ብታውቁም፤ አዝናለሁ አልወደቅኩም! . @huluezih @huluezih
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.