الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Kanalga Telegram’da o‘tish
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
2 159
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+1817 kun
+41530 kun
Postlar arxiv
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ሀያ_ሦስት(⓶⓷)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #ተስኒም ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
የሕሊና ጽልመትና የድልብ ድልብ መቅሰፍት
የሰው ልጅ በዱንያ ላይ የሚያጋጥመው መከራ አንዳዴ ገላን ብቻ ሳይሆን ነፍስን የሚቀጠቅጥ "ዱብዳ" ሆኖ ይመጣል። እኔም ዛሬ ምንም ያህል "አቋቁመዋለሁ" ብዬ ብታገልም፣ ጉልበቴ ተብረከረከ፤ ያ ያመንኩት ወንድነቴም በክህደት ፊት ከዳኝ።
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ለሰለፍያ ወጣቶች ትልቅ ትምህርት ያለው፤ እውነተኛውን አዛኝና #ሐያል ጌታ #አላህን ትቶ፣ በፈራሽና በበስባሽ ፍጡር ውበት ላይ ተንጠልጥሎ "የሕይወት ግንብ ልቀልስ" ቢል፣ ቤቱ እንደ አህያ ቆዳ ጅብ በጮኸ ቁጥር ይበታተናል።
አላህን በመፍራትና በተቅዋ ያልተገነባ የውሸት ማንነት፣ በመከራው ቀን እንደ አሸዋ ተራራ ይናዳል።
ነገሩ እንዲህ ነው... የአገሬ ሰው ሲተርት "ፍየል እሳት ወልዳ አትልሰው ፈጃት"አትቶውው ቸገራት ይላል። እኔም ዛሬ የሐራም ፍቅር እሳት ሆኖብኝ፣ በዱኒያ ላይ በጸጸት ጅራፍ እየተገረፍኩ ነው። "ዛሬው እንዲህ ካቃጠለኝ፣ ነገ የሞት መጋረጃ ተገፎ ወደ መቃብር ስወርድና የመጨረሻይቱ ዓለም ስትመጣ ምን ይውጠኝ ይሆን? ዋ ነፍሴ! ዋ ኪሳራሽ!" እያልኩ በሕሊናዬ ዐውድማ ላይ እቆዝፋለሁ።
የተስኒም "የመከራ ድግስ" ቀን ወለደና፣ ከተወሰኑ ቀናት ዝምታ በኋላ በአጭር ቴክስት በሩን በፊቴ ላይ ዘጋችው። "ምንም አላጠፋህም፤ የኔ ችግር ነው፤ የትዳር ጥያቄህንም ውድቅ አድርጌዋለሁ፤ የራስህን መንገድ ምረጥ" የሚል መራራ ቃል ደረሰኝ። ምን ልበል? ምንስ ልመልስ?
አላህ እንዲህ ይላል፦
إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ}
٢. {وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ}
٣. {ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيكُمْ وَأَنَّ اللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّامٍ لِّلْعَبِيدِ}
٤. {وَلَوْلَا أَن تُصِيبَهُم مُّصِيبَةٌ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ فَيَقُولُوا رَبَّنَا لَوْلَا أَرْسَلْتَ إِلَيْنَا رَسُولًا}
٥. {مَّا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ}
٦. {أَوْ يُوبِقْهُنَّ بِمَا كَسَبُوا وَيَعْفُ عَن كَثِيرٍ}
٧. {فَكَيْفَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ ثُمَّ جَاءُوكَ يَحْلِفُونَ بِاللَّهِ إِنْ أَرَدْنَا إِلَّا إِحْسَانًا وَتَوْفِيقًا}
አዎን! እኔም ዛሬ የወንጀሌን ጽዋ ደህና አድርጌ እየጎነጨሁ ነው። "ሳትታወር አትታወር" እንደሚባለው፣ በስሜት ታውሬ ሳለሁ ዛሬ በፈተና መብረቅ ነቃሁ።
የሕሊና ጽልመትና የድልብ ድልብ መቅሰፍት
የአገሬ ሰው ሲተርት «የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ» ይላል። እኔም በስሜት አውሎ ንፋስ ታውሬ፣ የፍጡርን ፍቅር እንደ ዘላለም መጠጊያ ቆጥሬ በከንቱ ስዘፍን ኖሬያለሁ። ነገር ግን ጌታዬ አላህ ከሕልሜ የሚቀሰቅስበት የግርፋት ጅራፍ ፍጹም የተለየ ነበረ።
ገና በተስኒም የክህደት ቁስልና በብሎክ ሰቀቀን ሕመም ውስጥ ሆኜ፣ ሌላ የሞት ሞት የሆነ፣ ሕሊናን የሚያደነዝዝ ድልብ ድልብ መርዶ እንደ ሰማይ መዓት በደጃፌ ላይ ተከታተለ። ያቺ ዓለሜ፣ ልጇ ተሳክቶለት በጥሩ ሕይወት ላይ እንድታይ ሌሊትና ቀኑን በዱዓ የምትደክመው ውድ እናቴ፣ በከባድና በአስፈሪ ሕመም ውስጥ መሆኗ በስልክ ተነገረኝ።
'አግባ ልጄ፣ በስደት አገር በባዕድ ምድር አትከራተት፣ የቤትህ ምሰሶ ይቆም ዘንድ አትባክን' እያለች የምትማጸነኝ እናቴ፤ ሕልሟን ሳላሳካላት፣ የልጅነት ወጓን ሳላሳያት በፊት የናፈቀኝ አባቴ ጉዞውን ወደ አኼራ አድርጎ ቀደመ። አሁን ደግሞ እናቴን... አባቴን ሕልሙን ሳላሳየው እንዳጣሁት ሁሉ፣ እሷንም በሕመም ልቀማት ይሆን? የሚለው ሥጋት እንደ ሾርጣ ብትር ገላዬን ቀጠቀጠው።
ምን ይሄ ብቻ! መዓቱ በየአቅጣጫው በሩን ሰብሮ ገባ። ያቺ ከጨለማ ጉዞ፣ ከስደት ቃጠሎና ከጭቃ አሮቃ እንደ ሰበብ ሆና ያወጣችኝ፣ ወስዳ አሳድጋ ለቁም ነገር ያበቃችኝ ውድ እህቴ፣ የአእምሮ በሽተኛ ሆና እንደምትባዝን መርዶ መጣ።
ምን ይሄ ብቻ! ታላቅ ወንድሜ በድንገተኛና በከባድ በሽታ የሞት አፋፍ ላይ ሆኖ፣ በሕይወትና በሞት መገናኛ መስመር ላይ ሆስፒታል መተኛቱ ተነገረኝ። በአንድ በኩል የተስኒም ፍቅር ክህደት፣ በሌላ በኩል የቤተሰቦቼ መበታተን ተደራርበው እንደ እግር እሳት ያቃጥሉኛል። ይሄ ሁሉ መከራ፣ ይህ ሁሉ የዱብዳ ሰንሰለት በአንድ ሰዓት፣ በአንዲት ቅጽበት ውስጥ ይፈራረቃል፤ ኢሏሂ!
አንዳንዶች ይህንን መከራ አይተው አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል ሊሉ ይችላሉ፦
(وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰلِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰتِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ” (አል-በቀራህ፡ 155!
ላላላላ! የኔን ማንነትና የኔን እውነተኛ ውድቀት የሚገልጸው ይህ የፈተናና የምንዳ አንቀጽ አይደለም። እኔማ በራሴ ስህተት፣ በገዛ ወንጀሌና በሐራም ፍቅር ዳክሬ የጌታዬን ድንበር የጣስኩ አጥፊ ነኝ። የኔን ትክክለኛ የሕይወት ቅጣትና የሰቀቀን ማሳያ የሚገልጸው የአላህ ጽኑ ቃል ይህ ነው፦
\وَمَنۡ أَعۡرَضَ عَن ذِكۡرِی فَإِنَّ لَهُۥ مَعِیشَةࣰ ضَنكࣰا وَنَحۡشُرُهُۥ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ أَعۡمَىٰ ” (ጣሃ፡ 124)
ወልኢያዙ ቢሏህ
----
“አንድ ባሪያ ከአላህ ትእዛዝ ዞር ብሎ፣ ልቡን በሐራም ፍቅርና በፈራሽ ፍጡር ላይ ሲያንጠለጥል፣ አላህ ዱንያን በምላሱ ላይ መራራ፣ ሕይወቱንም በቅጣትና በጭንቀት የተሞላች ጠባብ ያደርግባታል። በሀብትና በምቾት መሃል ቢሆን እንኳ፣ ነፍሱ ግን በሰቀቀን እሳት ትለበልባለች።” እኔም ዛሬ የሆነው ይኸው ነው፤ ከአላህ ዚክርና ከተውሂድ መስመር ርቄ በሴት ፍቅር ስንከራተት፣ ጌታዬ ሕይወቴን በጠባብ ጽዋ ቀዳልኝ።
...
"እማዬ... የኔ ውድ እናት! ፍላጎትሽን ሳልሞላ፣ በሐራም ፍቅር ወጥመድ ተጠልፌ፣ ጌታዬን አስቆጥቼ እንዴት ፊትሽን አያለሁ?" ብዬ ለነፍሴ ጮኽኩባት። "ተይ ነፍሴ ሆይ እረፊ! ጌታሽን አታስቆጭ፣ ታማኝ የለምና በዲንሽ ላይ እንደ ዘበኛ ቁሚ!" አልኳት።
ተስኒም በሯን ዘጋች - ተስፋዬም ጠወለገ፣
እናቴም ታመመች - ሕመሟ አደገ፤
በሐራም መንገድ ላይ - ስንት ዘመን ባከንኩ፣
ከጌታዬ ርቄ - ለካስ ተሸነፍኩ።
የሴራው መጋረጃና የክብር መርገፍ
#በሚል_ይቀጥላል_ክፍል_(⓶⓸)
👁የምን ፈቀቅ ፈቀቅ ነው የገጠር ልጆች በዚች ያልተጫወተ አለ ብየ አላምንም ?! 💯💯 አትንጫጩ ወፍጮ ቤት ስኔድ ትምርት ቤት ስኔድ በየ መንገዱ እየደፋን ተላቅመናል ኧሯ ተውጂ ውሸትም ልክ አለውኮ
ታቋታላቹህ ወይ?!🕶🕶 በዚች ኪሳራ ድፊት የተጫወተው ማነው በሬ ዶሮ እያለ😂✍️ መገን ያ ደጉ ጊዜ አቺ ከጠፋሺበት ሰአት ጀምሮ ነገራቶች ተመሰቃቅለዋል💦✍️
سُبْحَانَ اللَّهِ
سُبْحَانَ اللَّهِ
سُبْحَانَ اللَّهِ
الْحَمْدُ لِلَّهِ
الْحَمْدُ لِلَّهِ
الْحَمْدُ لِلَّهِ
اللَّهُ أَكْبَرُ
اللَّهُ أَكْبَرُ
اللَّهُ أَكْبَرُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
እንደምን ነህ መንግስት!?
--------------------------
ትሻላለህ ብሎ ህዝቡ እንደመረጠህ፡
ግፍን አሳየኸው ከሁሉም አብልጠህ፡
በጣፋጭ ንግግር በሳቅ እያዋዛህ፡
በብልፅግና ስም ብልግናን አበዛህ!!
እንደምነህ መንግስት ተመቸህ ስልጣኑ፡
አያሳዝንህም !?ህዝቡ ለመሆኑ፡
መሀል ከተማ ላይ ሜካፕ እየሰራህ!!
ሰላም የሌለበት ሀገር እየመራህ፡
በሰፊው ህዝብህ ላይ ስንት ነገር ሆነ፡
አልገባኝም እኔ ያንተ መንግስትነት ለማን እንደሆነ፡
#ፋኖ እሚባል አውሬ ደንብሮ ሲወረን፡
አንተም እንደ መንግስት በድሮን ስትወግረን፡
በሁለታችሁም ህዝባችን አለቀ፡
በጦር የተረፈው በኑሮ ደቀቀ፡
ወጣቱ በሀገሩ እየተሳቀቀ፡
አንገት እየደፋ በስደት ለቀቀ፡
...ህዝቡ...!!
በታጣቂ ሀይሎች ሌት ቀን ይረሸናል፡
በስልጣን ሱሰኞች ድንገት ይታፈናል፡
ወንጀል እየሰራን አምላክ አምፀናል፡
ከሀጢያት መላቀቅ ሱስ ሆኖ ከብዶናል፡
አጋቹ በዝቶብን ተደነጋግሮናል፡
ይባስ አሁን ደግሞ ዝናብ ጠፍቶብናል፡
አንተ ግን እንደት ነህ⁉️
ሀበሻን ስንት አመት ቀጥቅጠህ ገዛኸው!?
ይህንን ሚስኪን ዑማ ስንት ፌክ ሰራኸው!?
በኑሮ ውድነት ህዝቡ እየታመሰ፡
አመታት አለፉት ሰላም ከቀመሰ፡
አንተ በአንደበትህ ሰላም ትለናለህ፡
በጀርባ በድሮን ሲቪል ትፈጃለህ፡
ተዋናኝ ነህና ቀልድ ትችላለህ!?
👉ጤናህን ደህና ነህ!?
እንደምን ይዞሀል ይሄ መንግስትነት፡
እኛ ግን ከብዶናል ኑሮና ሰውነት፡
ከሁሉም በላይ ግን ሰላም እርቆናል፡
ከቤት ወጥቶ መግባት እጂጉን ናፍቆናል፡
ፀባይህ ብዙ አይነት ተቀያሪ እንደ እስስት፡
ንግግርህ ጣፋጭ ተደማጭ በስስት፡
ንፁሀን በመግደል መስመር የምትስት፡
ኮሪደር ወዳጁ እንደ ምን ነህ መንግስት!!
....ኸረ የሰላም ያለህ ..!?
...ኑር.✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
ፈጥኖ የመለስ Add የሚለውን በመንካት ምርጥ ቻናል ይሸለም
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
የመግሪብ ሶላት ስንት ረከዓ አለው
ذكريات الطفولة وحبها البريء لا يُنسى أبداً؛ مهما غابوا وطال الزمان يبقى حنينهم في القلب غصة لا تفارقنا💧ذكريات حب الطفولة لا تموت حين وقع بلا إدراك ثم عاد متأخراً بعد النضج، أدمى القلب بحنينه المؤلم فصار كل منهما يستذكره بوجع صامت💔
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
+1
أولئك الأبطال الذين سخروا أقلامهم وأوقاتهم لنصرة السنة، فهم كالأسود في حماية العقيدة، وشوكة لا تُزايل حلوق أهل الأهواء والبدع، وحصن حصين لدين الله المتين
✍✍✅
كالأسود
لا يهابون الباطل إذا انتفش
كالشوكة
لا يستطيع أهل الأهواء أن يبتلعوا بدعهم بسهولة
كالحصن
يأوي إليه طلاب الحق إذا كثرت الفتن
نفع الله بهم ورفع قدرهم
እነዚያ እስልምናን (ሱናን) ለመርዳት ብለው እስክሪብቶዎቻቸውን እና ጊዜያቸውን የሰጡ ጀግኖች እምነትን በመጠበቅ ረገድ እንደ አንበሳ ናቸው በስሜታዊነት እና በፈጠራ (በቢድዓ) ላይ ለተሰማሩ ሰዎችም በጉሮሮአቸው ላይ እንደተሰካ እሾህ (እንቅፋት) ናቸው ለጠንካራው የአላህ ሃይማኖትም የማይበገር ምሽግ ናቸው።
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
🙌ለሽያጭ የቀርብ አስቾካይ እስላማዊ ትlየቴሌግራም ቻናል
እጃችን ላይ 1 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉5k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
سَيِّدُ الاسْتِغْفَارِ
أَللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ
ልቦች የሚመኙትን ነገር ይለምናሉ
አሏህ ደግሞ በሚሻላት እና በሚበልጠው ነገር ይመልስላታል አላሀምዱ ሊሏህ ወሏሂ🌸
🌸 አሏህ የልቦቻችሁን የውስጥ ፀሎት ሰምቶ፣ ከምኞታችሁ በላይ በረከትና እጅግ ውብ በሆነው ምላሽ ያስደስታቹህ ቤተሰብ🤲
ሶለዋት ማውረድን እዳረሱ
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.🎀☕🍫
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ሀያ_ሁለት(⓶⓶)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #ተስኒም ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
የተስኒም ዝምታና የነፍስ ጦርነት
"መቼም ስሟ ማን ይሆን? ብላችሁ እንደምትጠባበቁ አውቃለሁ፤ ስሟ ተስኒም ይባላል። ልክ እንደ ስሟ ውብና ጥሩ መዓዛ ያላት እንስት! ለብዙ ጊዜ ጠፍታ ከቆየች በኋላ፣ በድንገት ባለችበት ሆና ሎኬሽኔን ጠየቀችኝ። ከዚያም የልቤን በር የሚያንኳኳ፣ ነፍሴን የሚገዛ ታላቅ ስጦታ አበረከተችልኝ። በርግጥም ስጦታ መሰጣጠት ፍቅርን ያለመልማል እንደሚባለው፣ ያ ስጦታዋ የደስታን ጥግ አሳይቶኛል። አሏህ ኸይር ጀዛዋን ይክፈላት።"
በዚህ" ደስታ ውስጥ "እያለሁ ቀናቶች" ይነጉዳሉ!! የተስኒም ዝምታ የምድር" ድባቡን እዬቀዬረው" መጥቷል።
በዱባይ ምድር አዲስ ሕይወት ብጀምርም፣ ልቤ ግን በተስኒም ቃል ኪዳን ታስሮ ነበር። ነገር ግን እንደ ቀድሞው ማንነቴ አልነበርኩም፤ ካለፈው ስህተቴ ተምሬያለሁ። ከአይከል ጋር በሳዑዲ ምድር ሳለን፣ ሌሊቱ ሲነጋ ቀኑም ሲመሽ በስልክ ሽቦ ላይ ተንጠልጥለን፣ ወሬያችን እንደ አሸዋ በዝቶ፣ ራሳችንን በሐራም አጥር ውስጥ አዝረከርከን ነበር። ወሬ ቢበዛ በአህያ አይጫንም እንዲሉ፤ ያ ሁሉ ወሬ መጨረሻው ክህደት ሆነ።
አሁን ግን ተስኒም ጋር ስመጣ፣ መንገዴን ቀየርኩ። እሷ ጠንካራ የሱና እንስት ናትና፣ እኔም ለሷ የሚመጥን የጽናት ዓምድ ለመሆን ወሰንኩ።
ያለ አግባብ መላላጥን፣ በስሜት መጋለብንና ራስን ማርከስን ተውኩት። ሆኖም ግን ነፍሴ እንዲህ እያለች ትሞግተኛለች፦ "ይህ መቀየርህ በእውነት ለአላህ ብለህ (ለኢኽላስ) ነው ወይስ ተስኒምን ለማግኘት የለበስከው ሌላ የሽንገላ ካባ?" ይህ በውስጤ የሚለበልብ የነፍስ ጦርነት እረፍት ነሳኝ።
ቀናቶች ይነጉዳሉ፤ በዱባይ አውራ ጎዳናዎች ላይ ግን ደስ የማይል ድባብ መጣ። ተስኒም ዝምታን መረጠች። ያቺ የነፍሴ ተስፋ፣ የቤቴ ምሰሶ ትሆናለች ብዬ ኒቃብ በእጆቼ ያዘጋጀሁላት ዕንቁ፤ ድንገት ድምፅዋ ጠፋ። "የሙሐመድ ልጅ ሆይ! ምን ነካህ? አሁንም ሰውን ማመን? አሁንም ቃል ገባችልኝ ብለህ ልብህን መስጠት?" እያልኩ ራሴን በጥርጣሬ ጅራፍ እገርፋለሁ።
"በሐላል አጥር - ነፍሴን ባስርም፣
የተስኒም ዝምታ - ሆነብኝ ገሃነም፤
ልቤ ቢቆስልም - አይታረምም፣
ዳግም ለመውደድ - አይሰለቸውም።"
ከለታት በአንዱ ቀን... ከሥራ ዛለኝ ብዬ፣ የዱባይን ግለት ተሸክሜ ወደ ቤቴ ስመለስ፤ አይኔ ማየት የሚከብደውን፣ ሕሊናዬ ሊሸከመው የማይችለውን ያንን አስደንጋጭ ትዕይንት ተመለከተ። ያኔ ዓለም በላዬ ላይ ዞረችብኝ፤ ልቤም ዳግም ተጠለፈ።
አቤት የሰው ልጅ ምስጢር! አቤት የፍጥረት ተለዋዋጭነት! ያ ሁሉ የኢብኑል ቀይም መድኃኒት፣ ያ ሁሉ የይቅርታ ደብዳቤና የኒቃብ ስጦታ... መጨረሻው እንዲህ ባለ ድንገተኛ ድንጋጤ ሊደመደም ነበር?
የቃላት መርገፍና የብሎክ ሰቀቀን
፼
፦ የቃላት መርገፍና የብሎክ ሰቀቀን
የተስኒም ዝምታ... ዝምታ ብቻ አልነበረም፤ በውስጡ የሞት አዋጅን የታቀፈ "ዱብዳ" እንጂ። ያቺ እንደ ጨረቃ የምትበራው የሱና እንስት፣ ድንገት የብርሃን በሯን ዘጋችው። የሕይወቴ መቃን ጨለመ፣ የመኖር ለዛው እንደ መጸው ቅጠል ረገፈ፣ የነፍሴም ጥንካሬ እንደ ሸረሪት ድር ተበጠሰ። ወንጀሌ... ያ በስደት ማኅደር ያከማቸሁት ድልብ ድልብ ስህተቴ፣ ዛሬ በፈተና ጽዋ ተቀድቶ መጣና የሕሊናዬን ዐውድማ አወደመው።
ታላቁ ዐሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) በማጅሙዕ አል-ፈታዋ ላይ እንዲህ ይላሉ፦ “አንድ ባሪያ ከአላህ ውጭ ባለ ፍጡር ላይ ልቡን ሲያንጠለጥል፣ አላህ በዚያው በወደደው ፍጡር አማካኝነት ልቡን እንዲሰበርና እንዲቀጣ ያደርገዋል። ይህ የጌታ ፍትሃዊ ቅጣት ነው፤ ነፍስ ወደ እውነተኛው መመለሻዋ ወደ አላህ ብቻ እንድትሸሽ የሚያደርግ ማንቂያ ነው”።
ነገሩ እንዲህ ነው... ተስኒም፣ ያወራናቸውን የቃል ኪዳን ትርክቶች፣ ተስፋን ያሰነቁኝን የቴክስት መስመሮች ሁሉ በአንዲት ቅጽበት አጠፋችው።
በሯን በ"ብሎክ" (በእገዳ) ቆልፋ፣ እኔን በናፍቆትና በግራ መጋባት ሸለቆ ውስጥ ብቻዬን ጣለችኝ። ሀቂቃ ደነገጥኩ! "አምኜሽ እንጂ ምን አጠፋሁ? አፍቅሬሽ እንጂ ምን በደልኩ?" ብዬ በባዶ ቤት ጮኽኩ። ግን ምላሽ የለም።
ይህ የልብ ስብራት አላህ በቁርኣኑ የጠቀሰውን ታላቅ ሀቅ ያስታውሰኛል፦
وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
(አል-ሹራ፡ 30)
አይ... ዝም ብላማ አትሄድም! የሆነ የከፋ ነገር አጋጥሟት ይሆናል ብዬ በሰው ስልክ ደወልኩ። ድምጯን ስሰማ ልቤ ሊቆም ደረሰ፤ እሷ ግን የእኔ መሆኔን ስታውቅ ስልኩን "ትርቅ" አድርጋ ዘጋችው። ሰማዩ ተደፋብኝ! ሰብእናዬ ረከሰ፣ ማንነቴ ዛለ። ለሊቱ ፅልመቱን (ጨለማውን) አወረሰኝ፤ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ያ በበረሃው ጥይት ያልፈራው ወንድነቴ፣ ዛሬ በአንዲት ሴት ዝምታ ፊት አቅመ ቢስ ሆኖ ተንበረከከ።
ታላቁ ዐሊም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) "ዛድ አል-መዓድ" በተባለው ኪታባቸው ላይ እንዳሰፈሩት፦ “የፍቅረኛሞች ትልቁ ቅጣትና ሲኦል መለያየትና መካድ ሳይሆን፣ ጥፋታቸውን ሳያውቁ በዝምታ ግንብ መታጠራቸውና መገፋታቸው ነው”። ያኔ የተስኒም ዝምታ ለእኔ ይኸው የነፍስ ቅጣት ሆነብኝ።
በማግስቱ ዳግም ስሞክር፣ "አትደውል!" የሚል መራራ ትእዛዝ መጣ። መረረኝ! የቃላት ድርቅ መታኝ። ስሜቴ እንደ ሻማ ቀለጠ፣ ገላዬም እንደ በረዶ ቀዘቀዘ። "አሳዝኛት ይሆን?" በሚል የሞኝ ተስፋ፣ ደም እንባ እያፈሰስኩ መጠበቅ ጀመርኩ።
ነገር ግን የዝምታዋ ምስጢር፣ የብሎኳ መዘዝ ሌላ ገጽታ ነበረው። ነገሩ እንዲህ ሆነ...
"ብዕሯ ተሰበረ - ቃሏም ደበዘዘ,፣
የተስኒም ጽላሎት - ተስፋዬን አነዘ፤
አፍቃሪ ልብ ይዞ - መከራ መጋት፣
ሆነብኝ ዛሬ - የነፍሴ ቅጣት።"
የሕሊና ጽልመትና የድልብ ድልብ መቅሰፍት
ክፍል ⓶⓷
~ ~~~~ይቀጥላል>
+1
ኢላሂ አንተ እርፍ የምልበት የራሴ የሆነ ሰፊ ሲሳይ ስጠኝ ከሰው ቤት ድካም ሀሳብ አላቀኝ እህቶቼን የቤት እመቤት አድርጋቸው ያረብ የሁላቺንም ህልም ነው ግን ......?
:::::::::::::::::::::::::::::
ዱንያ አንዳንድ ጊዜ ላትሞላ ትችላለች? ምኞትና እቅድ ይዘገዩ ይሆናል? ነገር ግን ቆራጥነትና ጥረት አላማውን ሳይመታ አይቀርም። ኢንሻአሏህ በአሏህ ፍቃድ
ዛሬ በሌሎች ቤት በውልና በስራ እየደከማችሁ ያላችሁት ነገ የራሳችሁ ቤት ንግስት ሆናችሁ በክብር ለመኖር መሆኑን ፈጽሞ አትርሱ። ኢንሻአሏህ
رَبِّ اجْعَلْنِي وَقَصْرِي مِنْ بُيُوتِ العِزِّ وَالسَّعَادَةِ، وَيَسِّرْ لِي أَمْرِي، وَاكْتُبْ لِيَ النَّجَاحَ وَالفَلَاحَ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ، وَاجْعَلْنِي مَلِكَةً فِي بَيْتِي آمِنَةً مُطْمَئِنَّةً🍃🤲🤲
የዲኑ አስተማሪነትና የሰዎች እውነት፡ ሸሪአችን ባልን ማክበር፣ ፈገግ ማለት፣ መታዘዝ እና መልካም ማድረግ ታላቅ ምንዳ የሚያስገኝ የኢባዳ መንገድ እንደሆነ ይነግረናል።
ነገር ግን ችግሩ ያለው ዲኑ ላይ ሳይሆን፣ የዛሬን ሰዎች (ባሎች) አእምሮና ሥነ-ምግባር ላይ ነው።
የተገላቢጦሹ እውነታ፡ ዛሬ ላይ ብዙዎች (ሁሉም ባይሆኑም) ሩህሩህ፣ ታዛዥና አሳቢ የሆነችውን ሴት ዋጋ ከፍ አድርገው ከማየት ይልቅ፤ እንደ ድክመት ይወስዱታል። ቆንጆውን አቀራረብና ንጹህ ፍቅር “ሞኝነት” አድርገው ይተረጉሙታል።
✍🕶የአመለኛ ሴቶች ተሰሚነት፡ በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ላይ ለጥንቃቄና ለክብር የሚጨነቁ፣ ንገረኝ ላስቸግርህ የማይሉትን ትተው፤ ነጭናጫ፣ አመለኛ እና ራስ ወዳድ የሆኑትን ሴቶች የሚመርጡ ባሎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እጅግ አሳዛኝ ነው
በቃ ይሄነው እውነታው ወዳጆቸ ለባል ታዛዝ መሆኑን እየነቀፍኩኝ ሳይሆን ባሎቺን ቢመክሩልን ኡስታዞች አንዳድ የብእር ባለቤት ጥበበኛ የሆኑ እህቶች እላለሁኝ እባካቺሁ ባሎችን ምከሩልን ብዙ ጊዜ አስተምሮቱ ለሴቶች ነውውውውውው
ሸሪአ ያዘዘዉን መታዘዝ እጅ እኛ የሰወችን ልቦለድ ስሜት አንከተልም ያሉትን ይበሉ ምን አገባኝ አኼራን እያስታወስን ሰው ዱንያ ላይ አዉርቶ ለሚቀር ምን ደነቀሽ
