አል-ኢትቃን ኢስላማዊ አካዳሚ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ የአል-ኢትቃን ኢስላማዊ አካዳሚ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
210
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
+130 kun
Postlar arxiv
ልቤ ሆይ!!
~
ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ
ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ ያስፈራኛል - በጧትም በማታ
እጄ ሆይ ተመከር - "እጄን በ’ጄ" እንዳልል - በሚያስጨንቅ ቦታ
እግሬ እግር አታብዛ - ታዋርደኛለህ - በጭንቁ ቀን ለታ
አዋጅ ሰምቻለሁ - እጅግ የሚያስፈራ - ከሰማዩ ጌታ።
(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 7/2016 )
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
የወቅቱ ቅዝቃዜና ክረምት ሰበብ አይሁናችሁ፤ አልጋ ላይ ተኝቶ የሚጠበቅ ስኬት የለም። ተነሱና ህልማችሁን ለማሳካት በብርቱ ስሩ!
http://t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
የምናውቀው ነገር ትንሽ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የማናውቀውን ነገር ስለምንረሳ ነው ብዙ ጊዜ የምንሳሳተው። ትልቁ አደጋ ያልተማርንበት ነገር ብቻ አይደለም፤ ተምረናል ብለን የምናምነው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው። ብዙ ጊዜ ሌላው ላይ ስንፈርድ ራሳችን ገና ያልደረስንበት ደረጃ ላይ ቆመን ነው። ዕውቀት ያለ ትህትና ትዕቢት ብቻ ይሆናል፣ ትህትና ያለ ዕውቀት ደግሞ ድክመት። ሁለቱ ተጣምረው ብቻ ነው ብልህ ሰው የሚሰሩት። ራስህን ያላወቅህ ቀን ብቻ ነው ራስህን ያወቅህ የመሰለህ ቀን።
➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
قال الفضيل بن عياض"بقدر ما يصغر الذنب عندك، يَعْظُمُ عند الله. وبقدر ما يَعْظُمُ عندك، يَصْغر عند الله."“ኃጢአት አንተ ዘንድ ትንሽ በሆነ መጠን አላህ ዘንድ ይገዝፋል። አንተ ዘንድ በገዘፈ መጠን ደግሞ አላህ ዘንድ ትንሽ ይሆናል።” ➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy ➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
በጣም የጎዳን ሰው እንዲጸጸት አንፈልግም፤ እንዲረዳን አንመኝም። ዝም ብሎ እንዲረሳን ብቻ ነው የምንሻው። በቃ ትርፍ ልብ የለንምና ያለውን እንድናስታም አሁን ላይ የምንፈልገው ማንም የማይፈርድብንንና የማይወቅስብንን የማዳመጥ ዓለም ብቻ ነው፤ ማንም የማይጠይቀን፣ ማንም የማይነካብን ያቺ ጠባብ ጥግ... እሷ ነች የእኛ ዓለም! አንዳንድ ህመሞች በጊዜ ሂደቶች ውስጥ ብቻ የሚያገግሙ ናቸው።➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy ➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
╭─━─━─༺༻─━─━─╮
1 ደቂቃን ከአላህ ቃል ጋር ➊➎
╰─━─━─༺༻─━─━─╯
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
በሰዎች መካከል ትልቁ ፀብ መጣላት ሳይሆን፣ 'ግድ የለሽ' መሆን ነው። ደጋግመህ የሰጠከው ዕድል፣ ደጋግመህ ያሳየከው ትዕግስት በከንቱ ሲባክን፣ መጨረሻው ግድየለሽነት ይሆናል። መጥላት ሳይሆን መታከት! ለአንድ ሰው ሲከፋው መከፋት ካቆምክ፣ ሲደሰት ደስታህ ካልሆነ... ያኔ ነፍስህ ያንን ሰው ቀብራዋለች ማለት ነው። አሁን ለሚመጣውም 'እንኳን መጣህ'፣ ለሚሄደውም 'መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ' የምንለው ለዛ ነው።
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
የስደት ህይወት የከበደው በስራው ብዛት ብቻ አይደለም ይልቁንም "ደህና ነኝ" በሚለው ንግግር ውስጥ በተደበቁ ማንም ሰው በማያውቃቸው የብቸኝነት ህመሞች ነው። ስደት ሀገርን ትቶ መውጣት ብቻ ቢሆን እድል ነበር ግን እሱ ራስንም መተው ነው፤ ስደት ማለት ማንነትን ደረጃ በደረጃ መልቀቅ ነው። ናፍቆት ላይ ናፍቆት ተደራርቦ መጨረሻ ምን እንደተናፈቀ እንኳ ይረሳል:: ስቃዩ ትልቅ መሆኑ ብቻ ሳያንስ ስለ እውነት የሚረዳ አለመኖሩ ደግሞ ከባድ ያደርገዋል :: ግን አልሐምዱ ሊላህ ይህ ብቸኝነት ራስን ብቻ ሳይሆን፣ አላህንም ይበልጥ እንድታውቅ ያደርጋል። ማንም በሌለበት የመከራ ምድር ላይ ቆመህ ስትጸልይ ብቸኝነትን ወደ ቀረቤታ የሚቀይር ኃይል እንዳለ ያስተምራል።
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
╭━─━─━─༺༻─━─━╮
ከአላህ ቃል ጋር ➊➍
╰━─━─━─༺༻─━─━╯
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
هذا هو اليقينእንደ ህፃን ብንሆን... አየር ላይ ተወርውሮ የሚስቅን ህፃን አስተውለህ ታውቃለህ? ያለው ባዶ ከፍታ ላይ ነው፤ ከታች የሚጠብቀው መሬት ደግሞ ሲበዛ ጠንካራ ነው። እሱ ግን በሳቅ ይፈነድቃል፤ ምክንያቱም የሚይዘው እጅ ላይ ሙሉ እምነት አለው። አኺል ከሪም፣ "ጉልበቴ ደከመ፣ ፀሎቴ ጠፋ፣ እድሌ ተበላሸ" ብለህ ከልክ በላይ በመጨነቅ ሁሉም ነገር በአንተ ጥንካሬ እንደሚሳካ አታድርገው። አምላክህ ከእናትም በላይ ነውና አንተ እንደ ህፃኑ ሁን። እስካሁንም ያቆመህ ያንተ መያዝ ሳይሆን የእሱ አለመልቀቅ ነው። እውነተኛ እረፍት የሚገኘው ከችግር በመሸሽ ሳይሆን፣ በባለቤቱ ትከሻ ላይ በማረፍ ነው። እርግጠኝነት ማለት መጨረሻውን ማወቅ አይደለም፤ መጨረሻውን የያዘውን ማወቅ ነው። ሰላም ማለት የሁኔታዎች መስተካከል ሳይሆን፣ በሁኔታዎች መሃል የሚጠብቅህን ኃይል ማመን ነው። ➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy ➦ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
ሰምታችኋል!!
አሳልፉ ኖርማል ማሳለፍ ብቻ ሳይሆን - ከስልካችሁ በጆሮ ስፒከሩ በኩል እስኪወጣ በደንብ አሽቀንጥሩት¡ በጥቅሉ ደግሞ የተባለውን ነገር ተግባራዊ እናድርግ፤ ማህበራዊ ሚዲያን መናቅ አያስፈልግም። ስንቶች ጠፍተውበታል ስንትች ተስተካክለውበታል። የመልካሙም ሆነ የክፉው ሰበብ ደግሞ የእኛ እይታ፤ ላይክና ሼር ነው።
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
╭━─━─━─༺༻─━─━╮
1 ደቂቃን ከአላህ ቃል ጋር ➊➌
╰━─━─━─༺༻─━─━╯
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
➤ t.me/AL_ItqanIslamicAcademy
