Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
Kanalga Telegram’da o‘tish
- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
761
Obunachilar
+2324 soatlar
+1617 kun
+36130 kun
Postlar arxiv
ጥሪ ለቻናል ባለቤቶች!
ወደ 500 ብሎም ወደ አንድ ሺ subscribers ለመድረስ የምናደርገውን ጉዞ በፍጥነት ለማሳካት የቴሌግራም ወይም የፌስቡክ ቻናል ያላችሁ ሰዎች
@usmanoman ላይ አናግሩኝ። ወይም ☝️ከላይ የተያያዘውን ቻሌንጅ ቻናላችሁ ላይ አጋሩ
ጀዛከላሁ ኸይረን!
to join usmanic islamic psychology 👇
https://t.me/usmanic_psychology
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 3. ሩህ /رُوح (መንፈስ)
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ሩህን በጣም በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ሩህ የሰው ልጅ መሠረታዊ
❮Essence❭ የማንነቱ ረቂቅ ክፍል ሲሆን ከማይታየው አለም ጋር ያለው የግንኙነት መስመር የተዘረጋበት ሚስጢራዊ መገለጫው ነው።
ስነመለኮታዊ እሳቤውን ስናይ:- ሩህ ሳናይ ከምናምንባቸው አበይት የእምነት ክፍሎች አንዱ ሲሆን አላህ ምንነቱን ምስጢር አድርጎ ከፍጡራን የደበቀው የስውሩ አለም እውነታ እንዲሁም ከሩህ አላህ የሰው ልጆች ላይ በመንፋት ሰው መሆንን ያላቀበት የክብር መገለጫ ነው።
ሩህ በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ጥናት ውስጥ:-
የምእራብያውያን ሳይኮሎጂ በክህደት ቆርጦ ከጣላቸው የሰው ልጆች የተፈጥሯቸው ምንነት የመኖራቸው መሠረት የሆነውን ሩህ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ማዕከላዊ የትኩረት አካሉ አድርጎ የሰው ልጆችን ወደ ላቀ የስብእና የማንነት ብቃት የህሊና እና የአይምሮ ጤንነት እንዲመለሱ ሀያል የመዳን መሣሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል።
ሩሀችን ከአላህ ጋር ባላት ትስስር የጎደላትን ነገር በመመርመር ሰዎችን በመንፈሳዊ እና ሀይማኖታዊ መመሪያዎች ከፍተኛ አምልኮአዊ ጥራት ላይ በማድረስ ሁለንተናዊ ደህንነታቸው ወደ ተፈጥሯዊ ጤናው የሚመለስበት ህክምናዊ ጥበቦችን የሚጠቀም አንድ አበይት የጥናት መስክ ነው።
✍️
ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል...
1, ከሁሉም አይነት የህይወት ጭንቀቶች እፎይታ ለማግኘት የሚያግዝ ዱአ:-
اللّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْهَمِّ وَالْحَزَنِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ جُبْنِ وَبُخْلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ وَقَهْرِ الرِّجَالِ
"አላህ ሆይ እኔ ከሃዘን እና ከጭንቀት ፣ አቅም ከማጣት እና ከስንፍና ፣ ከፍርሀት እና ከስስት ፣ በእዳ ከመያዝ እና ከሽንፈት በአንተ እጠብቃለሁ።"
የዚህ ዱአ ስነልቦናዊ ጠቀሜታዎች
-ጭንቀትን ያስወግዳል
- ስሜታዊ መረጋጋትን ይለግሳል
- ሀይል እና አቅም በመስጠት ችግሮችን ጥሶ የማለፍ አቅም ይሰጣል።
የሰው ልጅ ፈተናዎች እና የቁርአን ማፅናኛዎች
ሱራ አልበቀራህ 2:286
አላህ ነፍስን ከምትችለው በላይ አያስገድዳትም...
– ከዚህ አያ የምንማረው የሚገጥመን ሁሉም ፈተና እኛ ልንሸከመው የምንችለው ብቻ እንደሆነ ይገልፃል።
ሱራ አል ሸርህ 94:5-6
..."በእርግጥም ከመከራ ጋር እፎይታ/እረፍት አለ።
– ይህ አያ ችግር ብቻውን እንደማይመጣ ችግር ውስጥም እረፍት እና ሰላም ተጣምሮ እንደሚገኝ ያስታውሰናል
የሰው ልቦና (የስነ - ልቦና) ሀኪሙ ነቢዩ (ﷺ)
ሰውየው መጣ! ፍትወት ባነደደው ድምፀት ፣ ፍላጎት ባናረው አንደበት 'ዝሙት ይፈቀድልኝ' አላቸው።
አልተቆጡትም ፣ አማከሩት ፣ ሰሙት። በእናቱ እና በእህቶቹ ይህ ነገር ቢደረግ ይወድ እንደሆነ ጠየቁት (ይህ cbt/cognitive behavioral therapy ይለዋል የዘመኑ ስነልቦና) እንደማይወድ ነገራቸው። እንደዛ ማሰቡንም ፣ ምኞቱንም ተፀየፈ።
ከዛም ልቡ ላይ እጃቸውን አሳርፈው ዱአ አደረጉለት። ይህ መንፈሳዊ ህክምና ይባላል በእስልምና ወይም በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ -
ከዛም በኋላ ዝሙትን በጣም ጠላ።
የተሳካ የማማከር የማከም እና የማዳን አገልግሎት።
ይህን ነው ኢልመ ነፍስ/ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ። ኢስላማዊ መሠረት ይዘን ነው የተነሳነው።
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ አጭር ፅሁፎች
ክፍል 1 ፊጥራ 👈
ክፍል 2. ነፍስ 👈
ክፍል 3. ሩህ
ሌሎች እስካሁን የተለቀቁ የቻናሉ ጠቃሚ ፅሁፎች
- የመፅሐፍ ሽያጭ
የስነልቦና ጥያቄ ና መልሶች (case studies)
ጥያቄ 1
ሙስሊም የ 31 አመት ሴት ስሆን እስካሁን የትዳርን ወግ አላየሁም።
መልስ .1
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች የጋብቻ እድሜ ድሮ ከነበረበት በብዙ እጥፍ ከፍ ብሏል።
ጥያቄ ሁለት
አሰላሙአለይኩም እኔ የ 27 አመት ወጣት ወንድ ነኝ።በአንድ አሳሳቢ ነገር ተለክፍያለው።
መልስ ሁለት ክፍል 1
በአይን የሚገባው የዘመኑ አደገኛው እፅ (የፖርን ፊልም)
መልስ/ ክፍል ሁለት
ይህን የወንድማችንን ጥያቄ በሁለት ዙር እንድናየው ያስገደደን ነገር...
የሚስጥራዊነት ደህንነት ማስታወሻ/ confidentiality alert
እዚህ ጋር ለህዝብ የምናቀርባቸው ታሪኮች በራሳቸው በባለታሪኮቹ ፍቃድ ወይም ተጠይቀን ነው።
በውስጥ የሚሰሩ የማማከር ስራዎች ምስጢራውነታቸው የተጠበቀ መሆኑንን በጥብቅ እናስታውሳለን።
ታሪኳን ካነበባችሁ በኋላ ትክክል ነው የምትሉትን ውሳኔ ምረጡ (ምርጫው ከአምስት ቀን በኋላ ይዘጋል)
+1
ታሪክ ሁለት
የእህታችን ልብ የሚነካ ታሪክ! እንደዚህ አጋርታናለች።ካነበባችሁ በኋላ ሃሳባችሁን ከታች የምናያይዘው poll/መምርጫው ላይ አስፍሩ።
ለእህታችን የቀረበ የማጠቃለያ ተጨማሪ የመፍትሔ ሀሳብ እና መልስ
እህታችን በዚህ አጭር የአለም ቆይታዋ የአባቷ ሞት ፣ ሁለት ያልተሳኩ ትዳሮች እና ሌሎችም በዙ የህይወት ውጣ ውረዶችን አልፋለች።
በቅድሚ አላህ ታላቅ ትዕግስትን እና መፅናናትን እንዲለግስሽ እንማፀነዋለን ፤ ጉዳዮችሽንም ገር ያደርግልሽ። በመቀጠል ህይወትሽን የሚመለከቱ የተወሰኑ ነጥቦች ለማየት በአላህ ፍቃድ እንሞክራለን።
እህታች ካጋጠማት ያልተጠበቀ የህይወት ምስቅልቅል ለማምለጥ ብላ የገባችበት 2 ትዳር ሁለቱም ሳይሳኩ መቅረታቸው ሌላ ተደራቢ የህይወት ሸክም እና ጫና ፈጥሮባታል። ትዳርን የሚያህል ብዙ ማሰብ እና በትክክል የመወሰንን አቅም የሚጠይቅ የህይወት ምእራፍ በለጋ እድሜዋ እና በችኮላ መግባት ትልቅ አደጋ ያለው ውሳኔ ነበር።
በሁለት ያልተሳኩ ትዳሮች ውስጥ ማለፍ ደግሞ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይሆንም። ይህም ለራስ ያለን ግምት በማዛባት በራስ መተማመንን (self-esteem) ሊጎዳ ይችላል።
ውሳኔዎቻችን ፦ አስተዳደጋችንን ፣ ተፈጥሯዊ የማንነት ዝንባሌያችንን ፣ እና አስተሳሰባችንን... ይመስላሉ። አንዳንድ ሰዎች ለደረሰባቸው ችግር አቋራጭ መፍትሔ ሲፈልጉ ( ትዳርን ፣መሠደድን ፣ መለያየትን ...)ሌሎች ደግሞ መሠረታዊ ለውጥ በማድረግ ህይወታቸው በአካባቢያቸው እና በራሳቸው ላይ በመስራት ከራሳቸው አልፈው ለሌላው ሰው ተፅፃኖ ማድረስ የሚችል ማንነት ይገነባሉ።
የእህታችን ህይወት ላይ ተደጋጋሚ ሁለት በችኮላ የተወሰኑ ውሳኔዎች በጉልህ ይታያሉ። የዚህ ምክንያት ካለችበት የኑሮ ጫና ሁኔታ ከግል ባህሪዋ እና ከሌላም ምክንያት ሊቀዳ ይችላል።
መንስኤው ምንም ይሁን በትክልል ሳያስቡ በፍጥነት አንዱን ጥሎ ሌላን ቶሎ ለማንሳት
መሯሯጥ ተመሳሳይ ጥሩ ያልሆነ ውጤትን ማስከተሉ አይቀርም።
በመንታ መንገድ መሀል ላይ የቆመችው እህታችን አሁን የዩኒቨርስቲ ነጥብ ቢመጣ ግቢ ልግባ ወይስ ወደ ቀጣይ የትዳር ምእራፍ ልሻገር ? የሚል 'መወሰን የሚያስቸገር' ያለችው ሁኔታ ውስጥ እንደወደቀች ትናገራለች።
እህቴ ሆይ! ህይወት በሁለት አማራጭ ብቻ የተከበበች ጠባብ የትግል ሜዳ አይደለችም።ወይ ማግባት ወይ መስራት ወይ መማር ወይ አለመማር ብቻ በሚል የታጠረችም አይደለችም ።
ህይወት ፈርጀ ብዙ እና የተለያዩ ነገሮችን በተመሳሳይ ጊዜ በብቃት የማካሄድ የምትፈልግ የፍልሚያ ስፍራ ነች።
በህይወትሽ ላይ ያለፈው ሁሉ አላህ የወሰነው ነው እና በፀፀት ራስሽን ሳትቀጪ ማዕበሉ እያናወጠሽም ቢሆን ቆም ብለሽ በተረጋጋ መንፈስ እና በጥሞና ስለ ቀጣይ የህይወት እቅዶችሽ በተረጋጋ መንፈስ ለማሰብ ሞክሪ።እቅዶችሽን ፃፍያቸው።
ትምህርትሽ ሳይቆም የምትሰሪበት ፣ ራስሽን የተለያዩ ከህሎቶች የምታሰለጥኝበት ፣ዲንሽን የምትማሪበት መንገድ አመቻችተሽ ራስሽን በእውቀት እና በ ክህሎት የተሟላች ልበ ሙሉ እና የምትፈልገውን የምታውቅ ሴት ለመሆን ራስሽ ላይ ሳታቋርጪ ስሪ።
ትዳር ትልቅ የነፍሶች መስከኛ የልቦች መረጋጊያ ደሴት ሁለት ልቦች በፍቅር የሁለት አለም ደስታቸውን የሚገነቡበት የትውልድ መፍለቂያ የተቀደሰ ማእከል እንጂ ከሆነ ነገር የሚያመልጡበት መሸሸጊያ ስፍራ ሊሆን አይገባውም። ከሆነም መጥፎ ውጤት ያስከትላል።
አሁን ያለሽበት ሁኔታ ባትወጂውም የነገን ተስፋሽን ለመስራት ጥሩ መሠረት ነው እና ከእናትሽ ጋር ሁነሽ ራስሽን እያበቃሽ ከሷ ተሞክሮዎች እየተማርሽ ትምህርትሽን በአቅራቢያ ቦታ እየተማርሽ ከአላማሽ የሚያሰናክሉ ለሀራም ጥያቄዎች በርሽን ቆልፈሽ በፆም እና በስግደት ታግሰሽ ይህን ጊዜ ለማሳለፍ እና በጥራት ማሰብ የምትችይበት የህሊና አቋም ላይ ለመድረስ ጥረት አድርጊ።
ከዚያ የሚሆንሽን ሰው በትክክል መምረጥ እና ማወቅ የምትችይበት የአስተሳሰብ እድገት ላይ ስትደርሺ ሁሉም ነገር ጊዜውን ጠብቆ ይሆናል። አትዘግዩ ፣ አትቸኩዪ በመሀከል ያለው ተረጋግቶ አሰቦ የመወንን ልምድ አዳብሪ።
አላህ መልካም ትዳርን ለእህቶቻችን በሙሉ ይስጣቸው!!
በኮሜንት ሀሳብ በመስጠት እና ምርጫ መስጫው ላይ በመምረጥ ለተሳተፋችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን በአላህ ስም አቀርባለሁ።
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።ምስጢራዊነቱ
"የፊታቸው ሰማይ ላይ ፈገግታ የማትጠልቅ የዘውትር ፀሀይ ነበረች ፥ ገፃቸው ለተመለከታቸው በሙሉ ደስታን የሚያጋባ የሀሴት ድግስ ነው። በትህትና የተቀመረ የማማር አክሊልል ደፍተዋል ፣ በነቢይነት ስክነት ሞገስ እና በሰውነት ጨዋ ማንነት ገፃቸው የረጋ ነው...።"
(መሰል ውብ አንቀፆችን ስለ ውዱ ነብይ (ﷺ) የሚያገኙበትን 'ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ' መፅሐፍ በመግዛት ከመልእክተኛው ጋር በጥልቀት እና በውበት ይተዋወቁ።)
የኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፌ እስኪደርስ እቺ ስለ ውዱ ነቢይ (ﷺ) በውብ ቋንቋ እና በጥልቅ ሀሳብ የከተብኳትን መፅሀፍ ውሰዱ።
ርእስ= ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ
ፀሀፊ = ኡስማን ሙስጠፋ
የህትመት ጊዜ= ነሀሴ 2017 ዓ.ል
መፅሐፉን ለማግኘት በቴሌግራም ዩዘርኔም @usmanoman ወይም በስልክ 0921390122/ 0912027023 ላይ ያናግሩን
መልስ/ ክፍል ሁለት
ይህን የወንድማችንን ጥያቄ በሁለት ዙር እንድናየው ያስገደደን ነገር ነገሩ ከግለሰብ ችግር በላይ የሆነ የማህበረሰቡ ህመም እና የ
ሁሉንም በነፍስ ወከፍ የሚነካ ጉዳይ ስለሆነ ነው።
ግን አሁን ግለሰባዊ ትኩረት ሰጥተን ለዚህ ጥያቄ መልስ በመስጠት ለጊዜው ይህን ጉዳይ እንቋጨው።
ወንድሜ አሁን አንተን ይመታህ ፍላፃ አለም ላይ ብዙ ቢሊዮን ሰዎች እየተሰቃዩበት ቤተሰቦች እየፈረሱበት እና ማህበረሰብን ጥልቅ ዝቅጠት ውስጥ ከቶ ጥቂት ሺ ስግብግብ ሰዎችን ሀብታም በሚያደርግ የሰዎችን ገላ ሽጦ ገንዘበ ለማግኘት በተፈጠረ የህሙማን የቁማር ንግድ ነው።
አንተ ውስጥ የሚታየው ትልቁ ተስፋ ያልሞተችው የህሊናህ ደውል እና ራሷን ወቃሽ ነፍስ ናት።በክፉ አዛዧ ነፍስ ተጠልፎ በመውደቅ እና ራሷን በምትወቅሰው ነፍስ መሀከል ተነስቶ መንገድን የመቀጠል የተውበት/የንስሀ ምልልስ ይታይብሀል።
የወጣትነት ስሜትህ እና አለማግባትህ ለዚህ ተደጋጋሚ ስህተትህ በሰበብነት የሚጠቀሱ ጉዳዮች ቢሆኑም ለሁሉም የወንጀል መዳረሻዎች መፍትሄ አቅጣጫ ያስቀመጠው ኢስላም ያላገቡት የምግብ ሚዛናቸውን በመጠበቅ በፆም እንዲሁም እይታቸውን በማስተካከል ስሜታቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ ይመክራል።
አላህ መልካም ትዳር እስኪለግስህ ድረስ በፆም የሚገኘውን ስሜት የመቆጣጠር አካላዊ እና መንፈሳዊ ጥቅም ለማግኘት ሞክር/ታገል።
በአይንህ የሚገቡ መሰል በተጨባጩ አለምም ሆነ በሞባይል የምታየችውን ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮች አላህን ተመርኩዘህ ለማቆም ወስን።
ትእግስት እና ጥራት ያለው ሶላትም ስሜትን ለማረቅ ታላቅ መፍትሔ ነው።
ብቸኝነትህን የምታጠፋበት ኑሮ የሚጋራህ ሷሊህ/በጎ መንገድ የሚመራህ የወንድ ጓደኛ ቢኖርህ ብቻህን ሆነህ ለሰይጣን ሹክሹክታ እና ከነፍስ ወስዋስ ከመጋለጥ ራስህን ትታደጋለህ።
አስተዳደግህ ጥሩ የኢስላም መሠረት ያለው መሆኑን የጠቀስክ ሲሆን ለዚህም የወላጆችህ ወይም የአሳዳጊዎችህ ውለታ የላቀ መሆኑን ያሳያል።
ያንተ ታሪክ ግን የሚያስተምረን በቀና መስመር ውስጥ ማደግ ብቻ ከወንጀል የፀዳ ህይወት ለመምራት መሠረት እንጂ ዋስትና መሆን እንደማይችል ሲሆን። ድሮ ወደነበርክበት የፊጥራ/ተፈጥሯዊ የንፅህና እና የኢማን ጥንካሬ ለመመለስ ደጋግመህ በንስሐ ውሃ እየታጠብክ ነተውበትህን መንገድ ሳታቋርጥ ቀጥል።
ሰይጣን ተስፋ ሊያስቆርጥህ ደጋግመህ መውደቅህን ያስታውስህ ይሆናል ግን ተንኮሉን በ 'አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም እየታገልክ ፣ በ ቁል አኡዙዎች እየታከምክ ፈጅር ቢያመልጥህ ዙህርን እየሰገድክ አሱር ቢያልፍህ መግሪብን እየታገልክ ቋሚ የሆነ የአሰጋገድ ስርአት ውስጥ እስክትገባ ድረስ ሙከራህን ቀጥል ፤ ሶላትህን ባለማቆም ራስህን አግዝ።
በዱአ በርታ። አላህ ወጣቶቻችንን ከዚህ አጀገኛ እፅ ይሰውርልን።መልካም ትዳርም ይሰጣቸው።ይስጠን።
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን
ወደ ማለዳ አካባቢ እንዳለው ሰላም አዘል የንጋት ድባብ የህይወታችን ምሽትም የራሱ ንጋት አለው።
ኢንሻአላህ!
"....እሷ ከተስተካከለች አካል በሙሉ ይስተካከላል እሷ ከተበላሸች አካል በሙሉ ይበላሻል" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 2. ነፍስ
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ነፍስን በጣም በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ነፍስ ምንድነው?
ነፍስ 'ራስ' (self or soul) ማለት ነው። ወይም በኢስላማዊ የሳይኮሎጂ ትርጓሜው 'የውስጥ ዝንባሌ' ወደ ማለት የቀረበ ትርጓሜ አለው።
ነፍስ በተለያየ የእድገት እርከን ውስጥ የምታልፍ ሲሆን እነዚህም በ3 ተከፋፍላወ ቁርአን ላይ በሚከተለው መንገድ ይገኛሉ።
የነፍስ ደረጃዎች
1. ነፍሱል - አል - አማራ:- ('አዛዥ ነፍስ') ወደ መጥፎ ዝንባሌዎች እንዲሁም ወደ ሀጥያታዊ ሀሳቦች የምትመራ ስትሆን ዝቅተኛውን የነፍስ ደረጃ ትወክላለች። ስጋዊ እና ደመ ነፍሳዊ ፍላጎቶችን ሰዎች እንዲፈፅሙም ትጎተጉታለች።
2, ነፍስ አል - ለዋማህ:- ራሷን ወቃሸ ነፍስ - ከፍ ያለ የሰውን ልጅ ንቃት ስትወክል ድክመቷን እና ወንጀሎቿን የምታውቅ ፣ ስህተት ላይ ስትወድቅም ራሷን የምትወቅስ ራስ አወቅ እና ሞራል ገዝ የሰው ልጅ የህሊና ደውል ድምጽ ናት።
3, ነፍስ አል - ሙጥመኢነህ:- የሰከነች ነፍስ - ይህ ውስጣዊ ህብረት እና ሰላም የሚገኝበት ከፍተኛው የመንፈስ ልህቀት እና ራስን የመግዛት ደረጃ ነው።
ከምእራብያውያን ስነልቦና አንፃር ይህ አስተሳሰብ ሲታይ:-
እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስት የነፍስ እድገት እርከን ሀሳቦች ከ ሲግመንድ ፍሩይድ id, ego እና super ego ጋር በቀጥታ አያይዘው የሚተረጉሙት ሰዎች አሉ። የተወሰነ የፅንሰ ሀሳብ መመሳሰል ባይጠፋም ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ላይ ይህ ፅንሰ ሀሳብ መንፈሳዊ ይዘቱ እና አምላካዊ መሠረቱ ጠንካራ ሲሆን የሲግመንድ ሀሳብ ግን ከምድር እና ከስጋዊነት ገደብ ያልተላቀቀ አካላዊ/bodily እና አይምሯዊውን የሰው ልጅ ስሜታዊ እና ሞራላዊ እድገት የሚገልፅ የተገደበ የአስተምህሮ ዘርፍ ነው።
በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ውስጥ የ ነፍስ ጥናት
ደረጃ በደረጃ የሰውን ልጅ በነዚህ እርከኖች ተጉዞ ከፍተኛውን የመስከን/ሙጥመኢና (tranquility) ከፍታ ላይ እንዲወጣ ማስቻል መንፈሳዊ ንቃት እና እርካታ ላይ በማድረስ ከፈጣሪው እና ከራሱ ጋር ያለውን ህብረት የሚያሳድግበት እርከን ሲሆን ፤ በወንጀል ድጋሚ ወደ ታች ቢወርድም ወደ ቀመሳት የስክነት የከፍታ ጣእም ሳይሰለች እንዲመላለስ የማድረግ ራስን ከመጥፎ ባህሪያት እና መንፈስን ከወንጀል የማፅዳት/ተዝኪያ የትግል መንገድ/ሱሉክ ነው።
✍️
ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል...
