የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 290
Obunachilar
+124 soatlar
-157 kun
-8430 kun
Postlar arxiv
4 290
🇮🇷⚡️🇮🇱🇺🇸 “እውነታውን መጋፈጥ እና በእውነተኛው ዓለም ውስጥ ማሰብ እና መኖር አለብን ብዬ አስባለሁ” — አራግቺ ትራምፕ አያቶላ ሞጅታባ ካሜኒን ለመገናኘት መፈለጉን በተመለከተ።
4 290
🇷🇺🇺🇦⚡️ — የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን፦ ሁለት ዓመታት። በትክክል እስከ ቀኑ — ሜይ 20፣ 2024። የአቶ ዘለንስኪ የሥራ ዘመን አብቅቷል። የፕሬዝዳንትነት ስልጣኑ አብቅቷል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ሰዎች በዩክሬን ስለሚካሄደው ምርጫ ማውራት ጀምረው ነበር። አሁን ስለዚህ ጉዳይ ምንም ዜና አንሰማም። ምርጫ ያካሂዳሉ ወይስ አያካሂዱም? ይህ አስፈላጊ ስለሆነ እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ አለብን። ማንም ስለሱ አያወራም።
ጦርነቱን የማያቆመው፣ በጦርነት ሰበብ ሥልጣን ላይ ለመሰንበት ነው። ዛሬ ጦርነቱ ቢቆም፣ ነገ እንደሚወርድ ያውቀዋል።
4 290
🇷🇺🇺🇦⚡️ — የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ስለ ዘሌንስኪ፦
እሱ አይሁዳዊ ነው። አያቱ ናዚዎችን እየተዋጋ እንደነበር ታስታውሳላችሁ። አሁን በመቃብሩ ውስጥ እየተገላበጠ ይመስለኛል።
4 290
🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን ዘለንስኪ ፑቲንን ማስፈራራቱን ቀጥሏል። 'ለሩሲያ ሳይሆን ለራስህ፣ ለግልህ፣ ደህንነት ፍራ!' ብሎታል።
አንተ ራስህ፣ በግልህ፣ በራስህ አእምሮ፣ ይህንን ጦርነት ለማቆም ጊዜው አሁን ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ካልደረስክ፣ እመነኝ፣ ዩክሬን ለመኖር ስትል መታገሏን ትቀጥላለች። የሚደግፉንን እናገኛለን፣ አንተ አታገኝም። ያንን አረጋግጥልሃለሁ። ለራስህ ህልውና፣ ለሩሲያ አይደለም፣ ለራስህ፣ በጣም ጠንክረህ መታገል ይኖርብሃል። በድጋሜ፣ ለሩሲያ ሳይሆን፣ ለግል ህልውናህ! ይህን እኔ አይደለሁም የምለው፣ ይሄ ከዩክሬን የመጣ ስጋት አይደለም፣ ከየት እንደመጣ በደንብ ታውቀዋለህ። አዎ፣ የሩሲያ ታሪክ እውነታዎች እንደዚህ ናቸው፣ ሩሲያ ስትደክም፣ ለውጥ ይከሰታል።”
4 290
🇺🇸🚫🇮🇱❗️— ቶማስ ማሲ የUSS Liberty መርከበኞችን ለማክበር እና ለመዘከር በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ንግግር ለማድረግ አቅዷል።
💬 በX ገፁ ላይ የሚከተለውን ጽፏል፡-
በጁን 8 1967፣ ሆን ተብሎ በእስራኤል በተቃጣ ጥቃት የሞቱትን እና የቆሰሉትን የUSS Liberty ጀግኖች ሠራተኞችን እና የሠራዊቱን አባላት ለማክበር እና ለማስታወስ በጁን 8፣ 2026 በምክር ቤቱ ወለል ላይ እናገራለሁ።የUSS Liberty ክስተት፣ በስድስት ቀኑ ጦርነት ወቅት፣ በጁን 8 ቀን 1967፣ በእስራኤል አየር ኃይል ተዋጊ አውሮፕላኖች እና በእስራኤል ሰርጓጅ መርከብ በዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ቴክኒካዊ የምርምር መርከብ፣ USS Liberty ላይ፣ የተደረገ ጥቃት ነበር። ጥቃቱ 34 የባሕር ኃይል አባላትን ገድሏል፣ 171 አባላትን አቁስሏል፣ እንዲሁም መርከቡን ክፉኛ አውድሟል። ይህ ጥቃት፣ ዛሬ ድረስ አሜሪካ ውስጥ በእስራኤል ላይ ቁጣን የሚቀሰቅስ ክስተት ነው። በተለይ አሁን፣ በአሜሪካ ፀረ-እስራኤል ስሜት በተንሰራፋበት ወቅት ላይ፣ ክስተቱ አዲስ መልክ ይዞ ብቅ ብሏል። ማሲ፣ የMAGA አባል ሲሆን፣ ባለፈው ወር በተካሄደው የኮንግረስ ምርጫ፣ የኬንተኪ ግዛት የተወካዮች ምክር መቀመጫውን፣ በእስራኤል በሚደገፍ እጩ ተሸንፎ መቀማቱ የሚታወስ ነው።
4 290
🎙️ 🇺🇦 ዘለንስኪ ለፑቲን ደብዳቤ ጽፏል። ከኢራን ጋር በጣም ስለተጠመድክ፣ እርሱ ከፑቲን ጋር ለብቻ መገናኘት ይፈልጋል። ትክክል ነው?
🇺🇸 ትራምፕ፦ ምን እየሰሩ እንደሆነ በትክክል አውቃለሁ። ቢገናኙ ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ይገናኙ፣ ችግሮቻቸውን ይፍቱ። ማድረግ አለባቸው።
4 290
🇷🇺🇺🇦⚡- የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ለሩሲያው ፑቲን ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል። ክሬምሊን ደብዳቤውን እንዳየው እና ፑቲን በቅርቡ ስለሱ መልስ እንደሚሰጥ ተናግሯል።
ስለ ኔቶ፣ ጂኦፖለቲካ እና የሩሲያ ቋንቋ ምንም ብትል — ይህ ጦርነት የአንተ የግል ምርጫ ነው። እውነተኛ ምክንያት የሌለው ጦርነት። ታሪክ እንደዚያ ነው የሚያስታውሰው። ከዩክሬን ሙሉ የሆነ ተቃውሞ አልጠበቅክም እና ነገሮች እስከዚህ ድረስ እንደሚሄዱ አልተነበይክም። ነገር ግን ዛሬ ሁላችንም እዚህ አለን — በአምስተኛው ዓመት፣ በለየለየት ጦርነት ውስጥ። ዩክሬን ነፃነቷን ትጠብቃለች እና ታቆያለች፣ ሌሎች ትንበያዎች ቢኖሩም። ከጦርነቱ ለመውጣት አትፍራ — አሁን ከእናንተ የሚፈለገው ዋናው ነገር ይህ ነው። እኛ በዩክሬን ውስጥ ዘላቂ ጦርነት አንፈልግም። ያለ ጦርነት በጣም የተሻለ እንደሆነ በደንብ እናውቃለን። ላለፉት 26 ዓመታት እንዳደረግከው፣ ካሁን በኋላ የሩሲያውያንን ታማኝነት መግዛት ለመቀጠል በቂ ገንዘብ እና የፖለቲካ ስልጣን አይኖርህም። ይህን እንዳታገኝ እናደርግሃለን። ዓለም ስለዚህ ጉዳይ እንዲያውቅ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን። አንተ እራስህ እንደምትለው — 'ሁሉም ነገር መመዝገብ አለበት።' በአሁኑ ጊዜ ለ2027 እና ለ2028 የጦርነት እቅዶችን እየገመገምክ እንደሆነ የሚያሳዩ የደኀንነት ሰነዶችን አይተናል። ቤላሩስን ወደ ጦርነቱ የበለጠ ለመጎተት ትፈልጋለህ፣ እና አሁን ለዚያም እንድንዘጋጅ ተገድደናል። ዩክሬን በእኛ እና በእናንተ መካከል በሚደረግ ውይይት ጦርነቱን ለማቆም ሃሳብ አቅርባለች። ስብሰባ እንድናደርግ እጠቁምሃለሁ። የጦርነት እና የሰላም ጥያቄዎችን ለመፍታት በባህላዊ መንገድ መሪዎችን የሚያስተናግዱ ሀገራት አሉ። ስዊዘርላንድ፣ የአረብ ዓለም ሀገራት — ብዙዎች ይህንን ስብሰባ ማስተናገድ ይችላሉ እና ይፈልጋሉ። ለስብሰባ፣ ሞስኮ አልመጣም!" -
4 290
🇪🇹⚡️የሰው እዳ ባለመከፈል ኢትዮጵያ ልትከሰስ ነው።
የኢትዮጵያ ዩሮቦንድ አበዳሪዎች ያልተከፈለ ዕዳን በተመለከተ መንግሥትን ለመክሰስ የሕግ ሂደት መጀመራቸው ተዘገበ‼️
የኢትዮጵያ የዩሮቦንድ አበዳሪዎች ቡድን፣ መንግሥት ያልከፈለውን የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በተመለከተ ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸውን የሕግ ሂደት በይፋ መጀመራቸው ታውቋል።
ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ እነዚህ አበዳሪዎች በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ክስ ለመመሥረት ማቀዳቸውን የሚገልጽ የቅድመ-ክስ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ለኢትዮጵያ መንግሥት ልከዋል።
መንግሥት ደብዳቤው እንደደረሰው ለማሳወቅ 14 ቀናት ተቆርጦለታልም ተብሏል።
ዕዳውን ላለመክፈል የሚልመጠመጠው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከእንግዲህ የሚያበድረው ሀገር ወይም ተቋም የማግኘት ዕድሉ ቀጭጯልም፣ ተብሏል።
እንደ መረጃዎች፣ መንግሥት ዕዳውን በመቅረፍ ላይ በየወሩ ወርሃዊ ክፍያ ጣል ጣል ማድረግ እንኳ አቅቶታል።
*-*-*-
በኮሰመኑ እና ያለ ፍትህ በታጎሩ የፖለቲካ እስረኞች ላይ የ14 ቀን፣ የ20 ቀን ቀነ ቀጠሮ የሚቆርጠው መንግሥት፣ ይኸው፣ በሌላው ዓይን የኮሰመነ እና ዕዳውን መክፈል የማይችል ደሃ ነው።
'ገንዘቡን ውሃ በልቶታል' የሚባለው ይሄ ነው፡
$1ቢሊዮን ዶላሩ እርግጠኛ ነኝ የገፈርሳና የአባ ሳሙኤልን ወንዝ በተቆፈረ ቦይ ለማስኬድ ፈሰስ የተደረገው ነው።
የፈለገ ሜካፕ ብትለቀለቁ፣ በአበዳሪዎቻችሁ ፊት ሁሌም የገረጣቹ ናችሁ። ራሳችሁን ሁኑ!
4 290
🇱🇧🇮🇱⚡️- "የነቢያትገዳዮች በመሬታችን ላይ አይመሰረቱም፣ ወራሪዎቹን ከመሬታችን እስክናስወጣ እና ጥቃታቸውን እስከምናስቆም ድረስ፣ እንዋጋቸዋለን።"
- የሂዝቦላ ዋና ፀሐፊ ናይም ቃሴም።
4 290
🇷🇺❗️ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ 'የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ መሰረታዊ መፍትሄ የሚያገኘው የፍልስጤም ግዛት ሲፈጠር መሆኑ የሩሲያ አቋም ነው።
4 290
🇮🇱🇮🇷⚡️- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቆንስላ ጉዳዮች ቢሮ በምዕራብ እስያ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ሊከሰቱ ለሚችሉ ግጭቶች "የበለጠ ጥንቃቄ" እንዲያደርጉ አሳስቧል፣ የደህንነት ሁኔታው "ውስብስብ ሆኖ በፍጥነት ሊለወጥ ይችላል"ም ብሏል።
ባህሬን፣ እስራኤል፣ ዌስት ባንክ፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በደረጃ 3 ላይ ናቸው — ጉዞዎን እንደገና ያስቡ (እሄዳለሁ ቢሉ፣ ሆድዎን ይቁረጦት)
— ኢራን፣ ኢራቅ፣ ሊባኖስ፣ ሶሪያ፣ ጋዛ እና የመን በደረጃ 4 ላይ እንደቆዩ ነው — አይጓዙ (እግርዎን አያንሱ)
4 290
🇰🇵 በሰሜን ኮሪያ የመንግሥት ሚዲያ፣ ኪም ጆንግ ኡን የኒውክሊየር የጦር መሳሪያ ማምረቻ ማዕከልን ሲጎበኝ የሚያሳይ ምስል አውጥቷል።
ባለሙያዎች ለሮይተርስ እንደተናገሩት፣ በምስሉ የሚታየው በዮንግቢዮን ውስጥ ያለው ዋና ተቋም ሊሆን ይችላል ብለዋል። የደቡብ ኮሪያ ጦር ሠራዊት በበኩሉ፣ ምስሉ በሴንትሪፊጅ ላይ የተመሠረተ የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋም መሆኑን አስረድቷል።
*-*-*
አንዱን ቦንቧን ብቻ ለኢራን በተውሶ ብትሰጣት ብላችሁ አስቡት፣ የኢራንን ዝንብ እሽ የሚል አይኖርም ነበር። ለዚሁም ተከብረዋል፣ ዕድሜ ለባለስቲክ ሚሳዬል ቴክኖሎጂያቸው። ስትይዙ ነው የምትከበሩት። ታጠቁ ወገኖቼ፣ በያላችሁበት! ስትታጠቁ ማንም እየተነሳ አይፈነጭባችሁም።
4 290
🇸🇴⚡️ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት፣ ሀሰን ሼክ መሐመድ፣ በቀድሞው የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ሸሪፍ ሼክ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀሰን አሊ ኬይር ላይ፣ በቤታቸው ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተሰበሰቡበት ከብቦ ተኩስ እንዳስከፈተባቸው፣ እነሱንም ልትገለብጡኝ ነው ብሎ እንደከሰሳቸው የሱማሌ ሚዲያዎች እየዘገቡ ናቸው።
የአሁኑ ፕሬዝዳንት የስልጣን ዘመን ባሳለፍነው ወር የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ስልጣኑን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ተብሏል። በዚህም የተነሳ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስተር ከተለያዩ አጋሮች ጋር ሆነው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ሕገ መንግሥቱን አክብሮ ከስልጣን እንዲወርድ ሲወተውቱት እንደከረሙና፣ በመጨረሻም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ጦር እንዳዘመተባቸው ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት በሞቃዲሾ ያለው ከፍተኛ ውጊያ እንደቀጠለ ሲሆን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በቶሎ ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ፣ 'አደጋ ውስጥ ነን' በሚል ርዕስ በፃፈው መግለጫው ተማጽኗል።
4 290
🇸🇴⚡️- በሞቃዲሾ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የተኩስ ልውውጥ እና ከፍተኛ ፍንዳታዎች በመሰማት ላይ ናቸው። የተኩስ ልውውጡ እኩለ ሌሊት የጀመረ ሲሆን እስካሁን አላባራም።
4 290
🇪🇹 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ከ DC United ጋር በዋሽንግተን ዲሲ ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በቪዛ መሰረዝ ምክኒያት መሰረዙ ተሰምቷል።
ምክኒያቱ፣ ኢቦላ ይዛችሁብን እንዳትመጡ የሚል ነው።
የአፍሪካ ሕብረት፣ ኢትዮጵያን ለኢቦላ ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ 10 ሀገሮች አንዷ አድርጓታል።
*-*-*-
አሜሪካ ለመጥፋት አቅደው በሶ፣ በርበሬ ያዘጋጁት እና ቤተሰቦቻቸውን ተላቅሰው የጨረሱት ተጨዋቾች ናቸው የሚያሳዝኑኝ። የማይገኝ ዕድል ነው ያመለጣቸው።
4 290
🇺🇸🇮🇷⚡️ — የኢራን የፓርላማ ብሔራዊ ደህንነት ኮሚሽን ኃላፊ ኢብራሂም አዚዚ፣ ለኋይት ሃውስ ምክትል የስታፍ ኃላፊ እና የትራምፕ ረዳት ዳን ስካቪኖ 'የብልቃጥ አሸዋ ሰዓት አልቋል' GIF፣ ምላሽ ሰጥቷል፦
'ምን እንደሚሆን እንያታለን!'
4 290
🇺🇸 ትራምፕ፣ እራሱን በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ “ካሉት ምርጥ ባለ ምጡቅ አእምሮዎች አንዱ” ሲል ጠርቶታል።
ትራምፕ "እኔ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ካሉት ምርጥ ባለ አእምሮ ስብዕናዎች አንዱ” ነኝ ብሏል።
*-*-*
የሰለጠኑ ሀገር መሪዎች አንዱ ደስ የሚለው ነገራቸው ግን፣ እንዲህም ብለው፣ ዶክተሮችን ሰብስበው ስለ ሕክምና ሳይንስ የውስጥ ደዌ ሌክቸር ላድርጋችሁ አይሉም። እሱ እሱ እንደኛ ያሉ የደሃ ደሃ ሀገር መሪዎች የሚያደርጉት ነው።
4 290
በአሜሪካ MAGA ውስጥ፣ ፀረ-እስራኤልነት ተስፋፍቷል። ይህ የመነጨው በእስራኤል ውስጥ የክርስትና እምነት ከፍተኛ ጫና እና በደል ውስጥ ያለ መሆኑ እየታወቀ ከመጣ በኋላ ነው።
4 290
🇰🇼🇮🇷🇺🇸| IRGC ትናንት ስለ ፔትርዮት ሚሳዬል ማባረቅ የጻፍኩትን አረጋግጧል። ኩዌቶች የራሳቸውን ቦሌ እራሳቸው ናቸው የመቱት።
በኩዌት አውሮፕላን ማረፊያ T1 ተርሚናል ላይ የደረሰው ውድመት በአሜሪካዊው የፓትሮይት ሚሳዬል ብልሽት ምክንያት እንደሆነ ደርሰንበታል። IRGC ምርመራ እንዳካሄደ፣ እና ጦሩ በዚህ ዒላማ ላይ እንዳልተኮሰ እና የኩዌት አየር ማረፊያ የተሳፋሪ ተርሚናል ውድመት የተከሰተው፣ የአሜሪካ ፓትሮይት ሚሳዬል ወደ ራሱ አዙሮ በመተኮሱ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። አደጋው የደረሰው የኢራን ሚሳይሎችን እጠልፋለሁ ብሎ ወደ ራሳቸው ዞሮ በመፈንዳቱ ምክኒያት ነው።
