uz
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Kanalga Telegram’da o‘tish

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 293
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-217 kun
-9130 kun
Postlar arxiv
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በርካታ ፍንዳታዎች በኢራን እየተሰሙ ናቸው፣ የአሜሪካ ድሮን በሁለተኛ ትልቁ ከተማዋ፣ በኢስፋሃን፣ ባሁኑ ሰዓት ይበራል፣ እንደ አካባቢው ምንጮች።
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በርካታ ፍንዳታዎች በኢራን እየተሰሙ ናቸው፣ የአሜሪካ ድሮን በሁለተኛ ትልቁ ከተማዋ፣ በኢስፋሃን፣ ባሁኑ ሰዓት ይበራል፣ እንደ አካባቢው ምንጮች።

—❗️🇮🇷/🇮🇱/🇱🇧 ኢራን በቤይሩት ላይ የሚደረግ ማንኛውም የእስራኤል ጥቃት ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው እና 'የዲፕሎማሲያዊ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ከመስመር ሊያወጣ' እንደሚችል ለአሜሪካ አስጠን
—❗️🇮🇷/🇮🇱/🇱🇧 ኢራን በቤይሩት ላይ የሚደረግ ማንኛውም የእስራኤል ጥቃት ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው እና 'የዲፕሎማሲያዊ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ከመስመር ሊያወጣ' እንደሚችል ለአሜሪካ አስጠንቅቃለች – አል ጀዚራ

ደረቱን ለአርሴናል የሚሰጠው ኢትዮጵያዊ ትውልድ። ምግብ ውስጥ ነው ወይስ ውሃ ውስጥ ነው ማምከኛውን የጨመሩበት?

🇺🇸🇸🇦 — ሳዑዲ ዓረቢያ አጥፍቶ ጠፊ ድሮን ልትሠራ ነው። ፋብሪካው በሪያድ አቅራቢያ በመገንባት ላይ ይገኛል። በአሜሪካ ክፍለ ሀገር በUTAH ውስጥ በተመሠረተው Vector Defense እና በ
🇺🇸🇸🇦 — ሳዑዲ ዓረቢያ አጥፍቶ ጠፊ ድሮን ልትሠራ ነው። ፋብሪካው በሪያድ አቅራቢያ በመገንባት ላይ ይገኛል። በአሜሪካ ክፍለ ሀገር በUTAH ውስጥ በተመሠረተው Vector Defense እና በሳዑዲ በቅርብ ጊዜ በተቋቋመው SR2 Defense Systems መካከል፣ SR2Vector የተባለ የጋራ ጥምረት በመፍጠር፣ ለሳዑዲ ዓረቢያ ድሮን ሊሠራ ነው። ይህ ድሮን ለሀገር ውስጥ አገልግሎት የሚውል እና ለአጋር ሀገራት የሚላክ ነው የተባለ ሲሆን፣ የኢራን ሸሂድ ድሮንን እንደ መነሻ እና ማበረታቻ ወስዶ ተመሳሳዩን እንደሚያመርት ተናግረዋል። ፋብሪካው፣ በአሁኑ ሰዓት በሪያድ አቅራቢያ እየተገነባ ይገኛል። ድሮኑ እስከ 1,500 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሉ ኢላማዎችን የመምታት አቅም ሲኖረው፣ ይህም በግምት ከሳዑዲ ዓአረቢያ ሰሜን ምስራቅ የባሕር ዳርቻ እስከ ቴህራን ካለው ርቀት ጋር የሚዛመድ ነው። ፕሮጀክቱ በሳውዲ አረቢያ በቪዥን 2030 ስር የአካባቢውን የመከላከያ ማምረቻ ለማስፋፋት ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አካል ነው። 

—❗️🇮🇱/🇱🇧/🇮🇷 ትኩስ ዜና፦ እስራኤል በቤሩት ላይ ጥቃቶችን የሚያካትት 'የእሳት ቀስቶች ዘመቻ' ያለችውን እቅዶችን አጽድቃለች። በጥቂት ሰዓታት ድብደባ ትጀምራለች ተብሏል። እስራኤል፣ የአሜሪካ እና ኢራንን የድርድር ሂደት እንዲህ ባሉ እርምጃዎች ማደናቀፍ የፈለገች ይመስላል። ጦርነቱን ለማቆም አንዱና ዋነኛው የኢራን ቅድመ ሁኔታ ወይም በድርድሩ መካተት አለበት የምትለው፣ የሊባኖስ ጉዳይ ነው። 'በሊባኖስ ላይ የሚደረገው ጥቃት መቆም አለበት' የሚለው ነው።

🇱🇧⚡️🇮🇱 ቤሩት፣ ሕዝቡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስራኤል ልትደበድብ ነው በሚል ከተማውን ለቅቆ እየወጣ ነው።

❗️❗️ይሄ፣ በጋዛ በጥቂት ወራቶች የተፈጸመ ነው፣ ከምድረ ገጽ ደልዛቸዋለች እስራኤል። ይሄን አይቶ ዘር ማጥፋት ወይም ጀኖሳይድ አይደለም የሚል አይኖርም። በሀገራችን ኢትዮጵያም፣ ይህ በብዛት ተፈጽሟል፣ ዛሬም እየተፈጸመ ያለ ነው። ባለፉት አንድ አሥርተ ዓመታት፣ የሕዝብ ፍጅቶችን መስማት የሁል ጊዜ መደበኛ መረጃ ነው። ሕዝብ ድለዛ በተለያዩ ቦታዎች ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአብዛኛው ገጠር ውስጥ ስለሚኖር፣ በሞንታርቦም ተጩኾለት ሁኔታው ሳይሰማ ቢቀር እንጂ፣ የማይታወቅ አይደለም። እጅግ ብዙ የገጠር መንደሮች፣ በእንዲህ ያለ ሁኔታ፣ ከነ ሕዝባቸው፣ መንግሥት ባነሳሳቸው በዘር ጥላቻ የታወሩ ሰዎች፣ ሙሉ በሙሉ ተደልዘዋል። በከተማዎች እምብርትም፣ ከጋዛ የበለጠ ሕዝብ ጎዳና ወድቆ ለማኝ ሆኗል። እንደ ጋዛ በግላጭ የሚታይ ስለሆነ የሚካድ ነገር አይደለም። ሀገሮች 'ኢትዮጵያን እንዳትመስሉ' ማለት ጀምረዋል፣ ሲያስጠነቅቁ ሕዝባቸውን።

🇺🇸❌🇮🇷❗️— በThe Atlantic መሠረት፣ የትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርገው ጦርነት ግልጽ እና የተቀናጀ ስትራቴጂ ባለመኖሩ ወደ ደስ የማይል እና አሳፋሪ ሽንፈት እየተጓዘ ነው። ➡ በጣም
🇺🇸❌🇮🇷❗️— በThe Atlantic መሠረት፣ የትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርገው ጦርነት ግልጽ እና የተቀናጀ ስትራቴጂ ባለመኖሩ ወደ ደስ የማይል እና አሳፋሪ ሽንፈት እየተጓዘ ነው። ➡ በጣም የቅርብ አጋሮቹ እና የፖለቲካ ደጋፊዎቹ እንኳን በኢኮኖሚያዊ እና በወታደራዊ መዘዞቹ ላይ ያላቸውን አስደንጋጭ ስሜት ገልጸዋል። ➡️ ዋይት ሃውስ በፍጹም ግራ መጋባት ውስጥ ተይዟል — ውድ እና ዋጋ የሚያስከፍልን የተጓተተ ጦርነት መቀጠል ወይስ አሳፋሪ ስምምነቶችን መቀበል? በሚሉ የድንጋይ አጣብቂኞች መካከል ገብቷል።

🇮🇱⚡️🇱🇧 የውጊያ ጨዋታ ቀያሪዎቹ የሂዝቦላ FPV ድሮኖች፣ ዛሬ፣ በጨለማ ማየት በሚያስችላቸው thermal imagery በመጠቀም፣ በደቡብ ሊባኖስ የእስራኤል ወታደሮችን ሲያድኑ ታይተዋል፣ ቡድኑ በለቀቀው ቪዲዮ መሠረት። የእስራኤል ጦር ቀን ቀን ድሮኖቹን በመፍራት ብዙውን እንቅስቃሴውን በምሽት ገድቦ ነበር የቆየው። ቡድኑ፣ ባለፈው ሳምንት፣ እንዲሁ፣ በ150 ዶላር FPV ድሮኖች $150 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሦስት የእስራኤል IRON DOME ሲስተሞችን ሲያወድሙ የሚያሳይ ምስል ለቆ ነበር። በዚህም የተነሳ፣ በእስራኤል ጦር ውስጥ፣ እነዚህ ድሮኖች እያመጡ ያሉትን ለውጦች በተመለከተ ከፍተኛ መደናገጥ አለ።

🇮🇷 ኢራን ከፍተኛ ደረጃ ያለው ዩራኒየም ከሀገሪቱ ለማውጣት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች፤ በአንድ ቅድመ ሁኔታ፦ ወደ አሜሪካ ሳይሆን ወደ ቻይና መሄድ አለበት። አል ሃዳት ከፍተኛ ምንጮችን በመጥቀስ እንደገለጸው።

🇮🇷🇺🇸🇮🇱 — የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፦ 'ሌሎቹ ቢፈልጉ ከእስራኤል ጋር ይደመሩ፣ እኛ እንቀነሳለን።' 'የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ 'እስራኤልን' አይቀበልም፣ በጭራሽ አይቀበልም! ምክንያቱም ሕገ-ወጥ እና ወራሪ አካል በመሆኗ። ስለዚህ፣ በቀጠናው ውስጥ የአለመረጋጋት እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ትልቁ ምንጭ ከሆነ አገዛዝ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መፍጠር አይቻልም። ለሺዎች ዓመታት የኖረ ሥልጣኔ ባለቤት ለሆነችው ኢራን፣ የዘር ማጥፋት ከምትፈጽም 'ሀገር' ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወይም ሌላ ማንኛውንም ግንኙነት ከመፍጠር ይልቅ በሙሉ ሰውነቷ ሰማዕት መሆን ይሻላታል።'

🇸🇦 የሳዑዲ ዓረቢያ ያልተገደበ እና እንደልብ የነበረው የገንዘብ ፈሰስ፣ ዛሬ የለም BBC ከጥንት ጀምሮ አምባገነን መሪዎች ያለ ጠያቂ እና ያለ ተቀናቃኝ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በስማቸው በመቅረጽ ሠ
+3
🇸🇦 የሳዑዲ ዓረቢያ ያልተገደበ እና እንደልብ የነበረው የገንዘብ ፈሰስ፣ ዛሬ የለም BBC ከጥንት ጀምሮ አምባገነን መሪዎች ያለ ጠያቂ እና ያለ ተቀናቃኝ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በስማቸው በመቅረጽ ሠርተው ያልፋሉ። በኋላ እነዚህ ግዙፍ ሥራዎች 'እከሌ የሠራቸው' እየተባሉ ይወደሱበታል። እንዲህ ያሉ ከሺ ዓመታት በፊት የተሠሩ ትልልቅ ቅርሶች ዛሬም በመካከለኛው ምሥራቅ ቆመው ይታያሉ፣ እንደ BBC ዘገባ። በዘመናችን፣ በዚሁ አካባቢ፣ በስማቸው የሚተውት ዘርፈ- ብዙ ዘመናዊ ግንባታዎችን እና ፕሮጀክቶችን፣ ገደብ እና ተቆጣጣሪ በሌለው የገንዘብ ፍሰት እንደሚገነቡ በየጊዜው ከሚያውጁ መሪዎች አንዱ፣ የሳዑዲው ሙሐመድ ቢን ሠልማን ነው። የእሱን የአገዛዝ ስልት እና በዚህ በኩል ያለውን የሳዑዲን ትራክ ሬከርድ የሚያውቁ ኤክስፐርቶች እንደሚሉት፣ ሀገሪቱ በአብዛኛው የምታውጃቸው ሕዝባዊ ፕሮጀክቶች፣ ከሚጠራው የገንዘብ ፍሰት አንፃር፣ 'ከቅዠት ያላለፉ' ናቸው ይላሉ። "ፕሮጀክቶች ከልዩ ፌሽታና ድምቀት ጋር ይታወጃሉ፣ በመነጋታው የሉም" "ለዚህ ምክኒያቱ" ይላሉ እኒህ ኤክስፐርቶች፣ "ሳዑዲ እንዳለፉት ጊዚያት ዛሬ ላይ እንደ ልቧ የምታወጣው ገንዘብ የላትም።"

🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ በለጠፈው ረጅም ጽሑፉ፣ ከትናንት በስትያ በስልክ ያዋራቸው የአረብ ሀገሮች፣ የፖኪስታን እና የቱርክ መሪዎች ሳያቅማሙ በፍጥነት ከእስራኤል ጋር በአብርሃም ጎጆ (Abra
🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ በለጠፈው ረጅም ጽሑፉ፣ ከትናንት በስትያ በስልክ ያዋራቸው የአረብ ሀገሮች፣ የፖኪስታን እና የቱርክ መሪዎች ሳያቅማሙ በፍጥነት ከእስራኤል ጋር በአብርሃም ጎጆ (Abraham Accord) ውስጥ እንዲጠቃለሉ እና እንዲደመሩ አሳስቧል። በዚህ ጉዳይ 'ወገቤን ማለት' የለም፣ ብሎ የዛተው ትራምፕ፣ እነዚህ ሀገሮች ይህን ነገር እንደ ትንሹ ግዴታቸው ወስደው ሊወጡት የሚገባ ኃላፊነት ነው ብሏል።

🇸🇦🤝🇮🇱 ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሳዑዲ ንጉሥ መሐመድ ቢን ሠልማንን ሳዑዲ ዓረቢያ ከእስራኤል ጋር "ቀለበት እንድታስር" እና ወደ አብርሃም ጎጆ (Abraham Accord) እንድትገባ መጠየቁ ተሰ
🇸🇦🤝🇮🇱 ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሳዑዲ ንጉሥ መሐመድ ቢን ሠልማንን ሳዑዲ ዓረቢያ ከእስራኤል ጋር "ቀለበት እንድታስር" እና ወደ አብርሃም ጎጆ (Abraham Accord) እንድትገባ መጠየቁ ተሰማ። ትራምፕ፣ ሳዑዲን ጨምሮ፣ የገልፍ አረብ ሀገሮች በአብርሃም ማህበር ጥላ ሥር (Abraham Accord) ከእስራኤል ጋር እንዲደመሩ እና የሚሽኮረመሙትን ነገር እንዲተው ትናንት በዋይት ሃውስ በነበረው የስልክ ስብሰባ እንደነገራቸው ተዘግቧል። ከኢራን ጋር ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ለማግኘትና፣ ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ ለመወያየት የመጡት የአረብ ሀገሮች፣ በትራምፕ ምክረ-ሐሳብ ደርቀው እንደቀሩና አፍረውም እንደነበር Axios ዘግቧል።

🇮🇷 PressTV፦ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ ሊባኖስ እንደ ሞባይል ስልኮች፣ GPS ሲስተሞች እና የቼሪ ቲማቲሞች ላሉ ፈጠራዎች እስራኤልን ማመስገን አለባት በማለቱ መሳቂያ ሆነ። በውነቱ፣
🇮🇷 PressTV፦ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ ሊባኖስ እንደ ሞባይል ስልኮች፣ GPS ሲስተሞች እና የቼሪ ቲማቲሞች ላሉ ፈጠራዎች እስራኤልን ማመስገን አለባት በማለቱ መሳቂያ ሆነ። በውነቱ፣ እስራኤል በተሰረቁ የፍልስጤም መሬቶች ላይ ከመመስረቷ ከ 1,200 ዓመታት በፊት የቼሪ ቲማቲሞችን ያለሙት ቀደምት የአሜሪካ ተወላጆች (Native Americans) ነበሩ።

🇪🇹⚡️ በወለጋ ክፍለ ሀገር፣ ምሥራቅ ወለጋ በሚባለው ክፍል፣ ኪረሙ አጋምሳ አካባቢ፣ ዛሬ ቀኑን ሙሉ፣ በአምሃራ ታጣቂዎች (ፋኖ) እና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ ነበር ሲሉ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዚህም፣ የማዕከላዊ እዝ አመራርን ጨምሮ ከ100 በላይ የመንግሥት ወታደሮች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተሰምቷል። ውጊያው፣ እስከዛሬ በቀጠናው ከተደረጉ ውጊያዎች የከፋ ነበር ተብሏል።

ለእንግሊዝ እርድ የቀረበው ኢትዮጵያዊ በሬ።
ለእንግሊዝ እርድ የቀረበው ኢትዮጵያዊ በሬ።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ቅድም እንዳልኩት ነው፣ ኢራኖች ሲበዛ ተጠራጣሪ ናቸው፣ መጠራጠራቸው ትክክል ነበር፣ ጠቅሟቸዋል። አሜሪካ ተንሸራታለች። ትናንት ያሉትን፣ አላልንም ብለው አሁን እየሸመጠጡ ነው። **
🇮🇷⚡️🇺🇸 ቅድም እንዳልኩት ነው፣ ኢራኖች ሲበዛ ተጠራጣሪ ናቸው፣ መጠራጠራቸው ትክክል ነበር፣ ጠቅሟቸዋል። አሜሪካ ተንሸራታለች። ትናንት ያሉትን፣ አላልንም ብለው አሁን እየሸመጠጡ ነው። ** — አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለFOX NEWS እንደተናገረው፣ ምንም ስምምነት “ዛሬም ሆነ ነገ” አይፈረምም፣ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጨረሻ ውጤት ለመድረስ ለሂደቱ ተጨማሪ ቀናት ለመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጿል። ባለሥልጣኑ እንደተናገረው፣
የአስተዳደሩ አካሄድ “አቧራ (ዩራኒየም) ከሌለ፣ ዶላር የለም” በሚለው ፖሊሲ እየተመራ ነው፣ ይህም ማለት፣ ኢራን ግዴታዎቿን ሙሉ በሙሉ ካላሟላች የማዕቀብ እፎይታ ወይም የገንዘብ ጥቅማጥቅሞችን አታገኝም ማለት ነው። በተብላላው የዩራኒየም ክምችት እና የሆርሙዝ መተላለፊያ እንደገና መከፈት ላይ፣ መግባባት ተደርሷል፣ የመጨረሻው የቃላት አጻጻፍ ግን አሁንም በድርድር ላይ ነው። ድርድሮች ካልተሳኩ ወይም እንደ “መጥፎ ስምምነት” የሚቆጥሩትን ነገር ካስገኙ፣ አሜሪካ ወታደራዊ ጥቃቶችን ለመቀጠል ዝግጁ ነች።
5,6,7 ቀን ነው ያላቸው፣ ይፍጠኑ!

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 'በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው የመግባቢያ ስምምነት ሊሰረዝ ይችላል።' ይህ የተዘገበው በኢራን የዜና ኤጀንሲ ታስኒም ነው። ከዚህ ቀደም የኢራን ምንጮች በአሜሪካ አቋም ለውጥ ምክንያት በድርድሩ ላይ ከባድ ቀውስ እንደተፈጠረ ዘግበው ነበር። ይህ የተባለው፣ ዛሬ ይፈረማል ተብሎ የነበረውን የመግባቢያ ሰነድ፣ ትራምፕ፣ 'እንደገና በክለሳ ልየው እና እንወስናለን' በማለት ቃሉን ካፈረሰ በኋላ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጨምሮ፣ የእስራኤል መንግሥት፣ የተደረሰበት የመግባቢያ ሰነድ ኢራንን አሸናፊ የሚያስመስል ነው፣ በማለት ከባድ ትችት በዋይት ሃውስ ላይ መሰንዘራቸው ይታወቃል።

🇮🇷 ኢራኖች፣ እንዲያውም በቃ ትተነዋል ብለው ደረሱበት ከተባለው ስምምነት ሊያፈነግጡ ነው። ይህን ያሉት፣ ጥሩ ያልሆነ፣ የመደባበቅ ነገር ከአሜሪካና እስራኤል "እየሸተተን ነው" ካሉ በኋላ ነው።