uz
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Kanalga Telegram’da o‘tish

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 310
Obunachilar
-524 soatlar
-227 kun
-8430 kun
Postlar arxiv
🇺🇸 አዲስ የአሜሪካ ፓስፖርት የትራምፕን ፎቶዎች ያሳያል። ‹‹እንኳን ደህና መጣህ፤ መልካም ሁን (ትበጠብጥና ዋ!)›› ይላል።
🇺🇸 አዲስ የአሜሪካ ፓስፖርት የትራምፕን ፎቶዎች ያሳያል። ‹‹እንኳን ደህና መጣህ፤ መልካም ሁን (ትበጠብጥና ዋ!)›› ይላል።

🇻🇪 ቬኔዝዌላ፣ በፊት እና በኋላ።

+3
የአሜሪካ ወታደሮች፣ ከ1990 ወዲህ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ቬኔዝዌላ ገቡ። *-*-*- በነገራችን ላይ ብዙ ሀገሮች የአሜሪካ ወታደሮች በሀገራቸው እንዲሰፍሩላቸው ለአምላካቸው ይጠልያሉ። ሳዑዲዎች፣ ኳታሮች፣ ኤሜሬቶች፣ ባሕሬኖች፣ ኩዌቶች፣ ዮርዳኖሶች፣ ግብጦች፣ ቱርኮች፣ ማሌዢያዎች፣ አዘርባጃኖች፣ ጅቡቲዎች አሜሪካ በሀገራቸው እንድትሰፍር ለአላህ ይጠልያሉ። ጠሎታቸው ተቀባይነት አግኝቶ ሰፍረውላቸዋል። ጃፓኖች፣ ኮሪያዎች፣ ፊሊፒኖች፣ ታይዋኖች፣ ሲንጋፖሮች ለቡዳ ይጠልያሉ። ተሰምቶላቸው ሰፍረውላቸዋል። ጀርመኖች፣ ፖላንዶች፣ እንግሊዞች፣ ጥልያኖች፣ ስፔኖች፣ ሮማኒያዎች፣ ግሪኮች፣ ፖርቱጋሎች፣ ኮሶቮዎች …ኧረ የነዚህማ አያልቅም … ኖርዌዮች፣ ኢስቶኒያዎች፣ አይስላንጆች፣ ስዊድኖች፣ ቤልጄሞች … ኧረ አግዙዥ … ብቻ በአውሮፓ ሁሉም ለፖፓቸው፣ ለማርቲን ሉተር ይጠልያሉ እንዲያሰፍርላቸው። ተቀባይነት አግኝቶ ሰፍረውላቸዋል። አሜሪካ እንደዚህ ናት፣ በብዙዎች ዓይን። በሰላም አስገብተህ ካሰፈርካታ፣ ብሩንም፣ ሥራውንም፣ ጥበቃውንም ታመጣልሃለች። እነሱ የማይወዱት ጠብ ነው፣ ጠብ አይወዱም። የሚሉትን መስማት ይገባል። አይ ካልክ፣ ይጣሉሃል፣ ጥሩ አይመጣም። አሁን እስቲ ማን ይሙት ኢትዮጵያ ልምጣና ልስፈር ብትል፣ ጠቅላዩ በደስታ ራቁቱን ለአንድ ዓመት አይዘልም? ተዚህ አንጣር ቬኔዝዌላ ደስተኛ ናት ከመጠን በላይ።

🇱🇧🇮🇱 ሰበር ዜና! የሊባኖስ መንግሥት ከእስራኤል ጋር ስምምነት ከተፈራረመ በኋላ የቤሩት መንግሥት መቀመጫ፣ ሴራይል፣ በተናደደ ሕዝብ እንደተከበበ አሁን እየተሰራጨ ያለው ቀረጻ ያሳያል። ቤሩት
+4
🇱🇧🇮🇱 ሰበር ዜና! የሊባኖስ መንግሥት ከእስራኤል ጋር ስምምነት ከተፈራረመ በኋላ የቤሩት መንግሥት መቀመጫ፣ ሴራይል፣ በተናደደ ሕዝብ እንደተከበበ አሁን እየተሰራጨ ያለው ቀረጻ ያሳያል። ቤሩት፣ ከእስራኤል ጋር ማዕቀፉን በይፋ መፈራረሟን የሚገልጽ ዜና ከተሰማ በኋላ ተቃዋሚዎች የሊባኖስ መንግስት መቀመጫ የሆነውን ሴራልን ከብበዋል። የሕዝብ ቁጣም በዋና ከተማው በፍጥነት እየተስፋፋ ነው። በተፈረመው ሰነድ መሠረት፣ የሊባኖስ መንግሥት ሂዝቦላን እና ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ታጣቂ ቡድኖችን በራሱ መሬት ላይ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለማስፈታት ቃል ገብቷል። ይህ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ እና ብቻ፣ IDF፣ ደረጃ በደረጃ፣ በራሱ ጊዜ፣ ፓይለት ዞኖች በሚባሉት በኩል የሚወጣ ይሆናል። አሜሪካ አጠቃላይ ሂደቱን ትቆጣጠራለች። እስራኤል በበኩሏ ትጥቅ ማስፈታት መጠናቀቁን ካረጋገጠች በኋላ በራሷ የጊዜ መስመር ብቻ ትወጣለች። እስራኤል የፈረመችው ምንም አስገዳጅ ነገር የለም። *-*-* የሊባኖስ ጉዳይ ይገርማል። በአንድ በኩል ሂዝቦላ ተዋግቶ በኢራን ዲፕሎማሲያዊ ጡንቻ እስራኤልን ያስታግሳል፣ በሌላ በኩል የሊባኖስ መንግሥት ይወጣና፣ መንግሥት ነውና፣ በጎንዮሽ፣ ከእስራኤል ጋር አፍራሽ የተባለን ስምምነት ተፈራርሞ ይመጣል። አስቸጋሪ ነው።

🇻🇪 የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ፣ በቬኔዝዌላ እስካሁን 50 ሺ ገደማ የሚደርሱ ሰዎች እንደጠፉ ናቸው -- ፕሬዝዳንት ዶልሲ ሮድሪገዝ። በእስካሁኑ አሃዝ፣ ከ1 ሺ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተረጋግጧል።
🇻🇪 የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ፣ በቬኔዝዌላ እስካሁን 50 ሺ ገደማ የሚደርሱ ሰዎች እንደጠፉ ናቸው -- ፕሬዝዳንት ዶልሲ ሮድሪገዝ። በእስካሁኑ አሃዝ፣ ከ1 ሺ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተረጋግጧል።

🇮🇱❌🇱🇧 የእስራኤል ጦር የኢጎዝ ኮማንዶ ወታደሮች፣ ዛሬ ጠዋት በማንዛላ አቅራቢያ፣ ሰባት የሂዝቦላህ አባላትን፣ የእስራኤል የፀጥታ ቀጠና ውስጥ መሳሪያ ሲያጓጉዙ ነበር በማለት፣ በአየር ድብድባ መግደሉን አስታወቀ። 

🇮🇷⚡️🇺🇸 CENTCOM፣ በትናንትናው ዕለት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ለመታችው መርከብ አፀፋ፣ በኢራን የተለያዩ ወታደራዊ ዒላማዎችን መምታቱን ተናገረ።
🇮🇷⚡️🇺🇸 CENTCOM፣ በትናንትናው ዕለት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ለመታችው መርከብ አፀፋ፣ በኢራን የተለያዩ ወታደራዊ ዒላማዎችን መምታቱን ተናገረ።

🇺🇸⚡️ዋና MAGA እና የቀድሞ ኮንግረስ አባል፣ ማርጆሩ ቴይለር ግሪን፣ ማርክ ሌቪን 'በእስራኤል ውስጥ በቋሚነት እንዲቆይ' ነገረችው ‹‹እኔ የማነጋግራቸው አሜሪካዊያን አንዳቸውም፣ አሜሪካ ለእስ
🇺🇸⚡️ዋና MAGA እና የቀድሞ ኮንግረስ አባል፣ ማርጆሩ ቴይለር ግሪን፣ ማርክ ሌቪን 'በእስራኤል ውስጥ በቋሚነት እንዲቆይ' ነገረችው ‹‹እኔ የማነጋግራቸው አሜሪካዊያን አንዳቸውም፣ አሜሪካ ለእስራኤል ስትል ጦርነት እንድትቀጥል የሚጠይቅ የለም። አሜሪካውያን ሰላምን እና ብልጽግናን የሚፈልጉት ለኤፕስቲን ክፍል ሳይሆን ለራሳቸው ነው።' ለውጭ እርዳታ መስጠት እና የውጭ ጦርነቶችን መደገፍ No More! *-*-*- ይህን ያለችው አይሁዳዊው ዋና የጦርነቱ አቀንቃኝ እና ታዋቂ የአሜሪካ የሬዲዮ ውይይት አዘጋጅ የሆነው፣ ማርክ ሌቬን፣ እስራኤል ሄጄ ያነጋገርኩት ሁሉ አሜሪካ ለምን አትዋጋልንም፣ ምን እየሰራች ነው? ብለውኛል ማለቱን ተከትሎ ነው። ማርጆሪ ቴይለር ግሪን፣ በመልሷ፣ "ይሄ እኮ አሜሪካ ነው፣ ታዲያ ምን ይጠበስ" ማለቷ ነው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ማርክ ሌቬንን በተለያየ ጊዜ ያወደሰው ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጦርነት የሚያደርገውን ግፊት እንዲያቆም አስጠንቅቆታል። በአሜሪካ፣ ፀረ- እስራኤል አመለካከቶች በሁሉም የሕብረተሰቡ ክፍል እያየለ መጥቷል።

🇷🇺⚡️ - ሩሲያ በረጅም ጊዜ ውስጥ ለኔቶ ስጋት ሆና ትቀጥላለች ሲል የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩቴ ተናገረ። በአሁኑ ጊዜ የሩስያ ጦር የውጊያ ልምድ በጦር ሜዳ በንቃት እያገኘ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቶ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ኔቶ ለ"መከላከል" የሚያስፈልጉትን "ንብረቶች እና አቅም" ይጎድለዋል ብሏል፣ የኔቶ ዋና ፀሃፊ በንግግሩ።

🇮🇷🇾🇪🇵🇰🇱🇧🇮🇶🇧🇭 በመላው የሺዓ እስልምና ዓለም፣ ዛሬ እና በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት፣ አሹራ የሚባል ትልቅ ሃይማኖታዊ በዓል ይከበራል። በሺዓ እስልምና፣ አሹራ (የሙሀረም 10ኛው
+8
🇮🇷🇾🇪🇵🇰🇱🇧🇮🇶🇧🇭 በመላው የሺዓ እስልምና ዓለም፣ ዛሬ እና በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት፣ አሹራ የሚባል ትልቅ ሃይማኖታዊ በዓል ይከበራል። በሺዓ እስልምና፣ አሹራ (የሙሀረም 10ኛው ቀን) በጣም የተከበረው የሀዘን ቀን ነው። በ680 ዓ.ም በካርባላ ጦርነት የኢማም ሁሴን (የነቢዩ ሙሐመድ የልጅ ልጅ) እና ባልደረቦቹን ሰማዕትነት ያስታውሳል። ለሺዓዎች፣ ከአምባገነንነት ይልቅ ለፍትህ የመጨረሻውን አቋም ይወክላል። አብዛኛዎቹ የነቢዩ ቤተሰቦች እና የልጅ ልጆቻቸው የተገደሉት፣ በዘመኑ በነበሩ ኸዋሪጆች (የተክፊር/ወሃቢ አያቶቻቸው) በኢራቅ ካርባላ አቅራቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ ካርባላ ለሺዓዎች መካቸው ሆናለች። እንደ ኢራቅ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ዘገባ፡ እስከ 12 ሚሊዮን ሃይማኖታዊ ተጓዦች በካርባላ ይጠበቃሉ። ብዙዎች፣ የዛሬ ተክፊር እና ወሃቢዮች፣ የነቢዩን ልደት (መውሊድን) የማያከብሩት፣ እንደ ቀደሙት ኸዋሪጆች፣ ለእሳቸው ባላቸው ሥር የሰደደ ጥላቻ ነው ይላሉ። በባሕሬን፣ በየመን፣ በሊባኖስ፣ በኢራን፣ በኢራቅ፣ በፖኪስታን እና በሌሎች ሺዓ እስልምና እምነት ተከታዮች በሚበዙባቸው ሀገራት፣ በዓሉ በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት ይከበራል።

🇮🇱⚡️ - የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ -
በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ በመከላከያ በጀት ላይ 350 ቢሊዮን ሸቃል ጨምረናል። እንዴት? ምክንያቱም እስራኤል በጦር መሳሪያ ምርት ውስጥ በተቻለ መጠን ነፃ እንድትሆን እና እራሷን እንድትችል እፈልጋለሁ። ጠንካራ እና በራስ የመተማመን ኢንዱስትሪ እፈልጋለሁ። አሁን ያለንን ጥምረት እንጠብቃለን እና እናሰፋቸዋለን (ከአሜሪካ ጋር)፣ ነገር ግን በመጀመሪያ ደረጃ, በራሳችን መቆም መቻል አለብን።

🇮🇱🇹🇷🇦🇲⚡️ - የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዴዎን ሳአር፣ የአርሜኒያን የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ወንጀልን በይፋ እውቅና ለመስጠት የካቢኔ ውሳኔ እሁድ እለት ለማቅረብ አቅዷል። ይህ
🇮🇱🇹🇷🇦🇲⚡️ - የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዴዎን ሳአር፣ የአርሜኒያን የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ወንጀልን በይፋ እውቅና ለመስጠት የካቢኔ ውሳኔ እሁድ እለት ለማቅረብ አቅዷል። ይህም ቱርክን የሚያስቆጣ እርምጃ ነው። ግን ምንም አታመጣም።

🇷🇺🇮🇷 መሳሪያ የጫነ ተብሎ የሚገመት ግዙፍ የሩሲያ ወታደራዊ አይሮፕላን ወደ ኢራን በመጓዝ ላይ ነው።
🇷🇺🇮🇷 መሳሪያ የጫነ ተብሎ የሚገመት ግዙፍ የሩሲያ ወታደራዊ አይሮፕላን ወደ ኢራን በመጓዝ ላይ ነው።

🇷🇺⚡️🇺🇦 Chita City, Zabaykalsky Krai, June 26th.
ከተማዋ በነዳጅ መጥፋት ምክንያት ሽባ ሆናለች። ሰዎች ከሌሊት ጀምሮ በነዳጅ ማደያዎች ውስጥ ተሰልፈው በመኪናቸው ውስጥ ተኝተዋል። ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ሰዎች ከ7-8 ሰአታት ወረፋ መጠበቅ አለባቸው። በዚህ ሁሉ ማዕቀብ፣ በዚህ ሁሉ መገለል ያልተንበረከክን፣ እኮ አሁን በድሮን ሽባ እንሁን? በግዙፍ ነዳጅ አምራቿ ሩሲያ፣ የነዳጅ ችግር ይፈጠራል ብሎ ማን ያስብ ነበር?

🇷🇺⚡️🇺🇦 የቀድሞው የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር (2010-2014) ኒኮላይ አዛሮቭ፣ ለTASS እንደተናገሩት: የኪየቭ አገዛዝ ከምዕራቡ ዓለም ድጋፍ ውጭ ወደ ሩሲያ ጥልቅ ጥቃት ሊጀምር አይችልም" ብለዋል።
አሁን፣ እነዚህን ሁሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች በሩሲያ ውስጥ ለኪየቭ አገዛዝ ጥቃት የሚያዘጋጁ ኃይለኛ የአሜሪካ አይቲ ኩባንያዎች ተቀላቅለዋል። የኪየቭ አገዛዝ እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞችን በራሱ ማከናወን እንደማይችል 100% እርግጠኛ ነኝ።

🇮🇱🇱🇧⚡️የእስራኤል ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ IDF ከደቡብ ሊባኖስ 'የጸጥታ ቀጠና' እንደማይወጣ ተናግሯል። 'ትራምፕ ወደ እኛ ቢቀርብ፣ ብለን እንነግረዋለን - 'እንዳትጠጋ!'

🇫🇷 በዛሬው ዕለት የፈረንሳይ ባሕር ኃይል፣ በዘርፈህ ብላ ስሌት መሠረት፣ የሩሲያን የነዳጅ ጫኝ መርከብ አግተው መውሰዳቸው ተሰማ። መርከቡ የተያዘው 'ማዕቀብ በመጣሱ' ነው በሚል ታፔላ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ የሆነው፣ በትናንትናው ዕለት፣ እንግሊዝ በተመሳሳይ የዛሬ ወር የያዘችውን የሩሲያ መርከብ ነዳጅ 'ሸጬ ብሩን ለዩክሬን ልሰጥ ጨርሻለሁ' ማለቷን ተከትሎ ነው። እንደ ሁሌውም፣ ፑቲንም ሆነ ክሬምሊን፣ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴራቸው በኩል፣ በሁለት መስመር ከማውገዝ በዘለለ፣ ያሉት የለም። *-*-*- የፑቲን ሩሲያ አረንቋ ውስጥ ነው ያለችው፣ በእንዝህላል አመራሮቿ የተነሳ። ፑቲን፣ ፈርቷል!

🇫🇷 በዛሬው ዕለት የፈረንሳይ ባሕር ኃይል፣ በዘርፈህ ብላ ስሌት፣ የሩሲያን የነዳጅ ጫኝ መርከብ አግተው መውሰዳቸው ተሰማ። መርከቡ የተያዘው 'ማዕቀብ በመጣሱ' ነው በሚል ታፔላ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ የሆነው፣ በትናንትናው ዕለት፣ እንግሊዝ በተመሳሳይ የዛሬ ወር የያዘችውን የሩሲያ መርከብ ነዳጅ 'ሸጬ ብሩን ለዩክሬን ልሰጥ ጨርሻለሁ' ማለቷን ተከትሎ ነው። እንደ ሁሌውም፣ ፑቲንም ሆነ ክሬምሊን፣ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴራቸው በኩል፣ በሁለት መስመር ከማውገዝ በዘለለ፣ ያሉት የለም። *-*-*- የፑቲን ሩሲያ አረንቋ ውስጥ ነው ያለችው፣ በእንዝህላል አመራሮቿ የተነሳ። ፑቲን፣ ፈርቷል!

🇩🇪 "ሩሲያ አታሸንፍም" መርዝ። የጀርመኑ ቻንስለር፣ ፑቲን በግንባር ቀደምትነት የሚደረገውን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በያዘው አፍራሽ ሚና የሚቀጥል ከሆነ፣ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫ
🇩🇪 "ሩሲያ አታሸንፍም" መርዝ። የጀርመኑ ቻንስለር፣ ፑቲን በግንባር ቀደምትነት የሚደረገውን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በያዘው አፍራሽ ሚና የሚቀጥል ከሆነ፣ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚጨምር አስፈራርቷል። "ለሩሲያ ግልጽ ምልክት እየላክን ነው፣ ድርድር ለመጀመር፣ የፊት መስመሩን (የግንባር ጦርነቱን) ለማቀዝቀዝ እና ግድያውን ለማስቆም ጊዜው ደርሷል" ብሏል። አያይዞም፣ "ሩሲያ በዚህ ጦርነት አታሸንፍም! አውሮፓ ለዩክሬን የሚያደርገው ድጋፍ አሁንም የማይናወጥ ነው። በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ለመጨመር ዝግጁ ነን" ሲል መርዝ ተናግሯል። ይህን ያለው፣ የአውሮፓ ሕብረት ለዩክሬን ተጨማሪ $90 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ፣ በመጪው የአንካራ የኔቶ ስብሰባ ላይ ለማወጅ እንደተዘጋጀ በገለፀበት መግለጫው ላይ ነው።

🇩🇪 "ሩሲያ አታሸንፍም" መርዝ የጀርመኑ ቻንስለር፣ ፑቲን በግንባር ቀደምትነት የሚደረገውን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በያዘው አፍራሽ ሚና የሚቀጥል ከሆነ፣ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና
🇩🇪 "ሩሲያ አታሸንፍም" መርዝ የጀርመኑ ቻንስለር፣ ፑቲን በግንባር ቀደምትነት የሚደረገውን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በያዘው አፍራሽ ሚና የሚቀጥል ከሆነ፣ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚጨምር አስፈራርቷል። "ለሩሲያ ግልጽ ምልክት እየላክን ነው፣ ድርድር ለመጀመር፣ የፊት መስመሩን (የግንባር ጦርነቱን) ለማቀዝቀዝ እና ግድያውን ለማስቆም ጊዜው ደርሷል" ብሏል። አያይዞም፣ "ሩሲያ በዚህ ጦርነት አታሸንፍም! አውሮፓ ለዩክሬን የሚያደርገው ድጋፍ አሁንም የማይናወጥ ነው። በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ለመጨመር ዝግጁ ነን" ሲል መርዝ ተናግሯል። ይህን ያለው፣ የአውሮፓ ሕብረት ለዩክሬን ተጨማሪ $90 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ፣ በመጪው የአንካራ የኔቶ ስብሰባ ላይ ለማወጅ እንደተዘጋጀ በገለፀበት መግለጫው ነው።