uz
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Kanalga Telegram’da o‘tish

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 303
Obunachilar
+824 soatlar
-47 kun
-7130 kun
Postlar arxiv
🇱🇧🇮🇱 FPV (First Person Drone) በመባል የሚታወቁት ድሮኖች፣ የዓለምን የውጊያ መድረኮች እየለወጡ ናቸው። ከዩክሬን እስከ ማሊ፣ ከሩሲያ እስከ ሊባኖስ፣ በየትኛውም የዓለማችን የው
+3
🇱🇧🇮🇱 FPV (First Person Drone) በመባል የሚታወቁት ድሮኖች፣ የዓለምን የውጊያ መድረኮች እየለወጡ ናቸው። ከዩክሬን እስከ ማሊ፣ ከሩሲያ እስከ ሊባኖስ፣ በየትኛውም የዓለማችን የውጊያ መድረኮች፣ FPV ድሮኖች  የተፋላሚዎችን አቅም በማመጣጠን የጦርነት ዙሩ አክርረውታል። በዚህ በይበልጥ አናሳ ተዋጊዎች በኃያላን ላይ እንዲበረቱ ሆነዋል። ከ$30 - $300 ዶላር የሚሸጡ ናቸው። የሊባኖሱ ሂዝቦላ ከሌሎች አንፃር ዘግይቶም ቢሆን ድሮኖቹ ውጤት እያስገኙለት ይመስላል። ከእስራኤል ጋር በሚያደርገው ውጊያ፣ ድሮኖችን፣ ነጠላ ወታደሮችን እና የጦር ቁሳቁሶችን ለመምታት ጥቅም ላይ በማዋሉ፣ በዚህም በእስራኤል ጦር ላይ ያልተጠበቁ ጉዳቶችን በማድረሱ፣ ዛሬ የይህን ምክኒያት በማድረግ ከአንዳንድ የደቡብ ሊባኖስ ግዛቶች ሊወጣ መሆኑን ጦሩ ተናግሯል።

🇮🇷 🇴🇲 🇾🇪በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሙስሊሙ ዓለም፣ 'በጥሩ የምታዩት ሀገር' ለተባለው ጥያቄ፣ አብዛሃኛው ሕዝብ በደረጃ ኢራንን፣ የመንን እና ዖማንን በአብላጫ ድምፅ የመረጠ እንደሆነ ያ
🇮🇷 🇴🇲 🇾🇪በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሙስሊሙ ዓለም፣ 'በጥሩ የምታዩት ሀገር' ለተባለው ጥያቄ፣ አብዛሃኛው ሕዝብ በደረጃ ኢራንን፣ የመንን እና ዖማንን በአብላጫ ድምፅ የመረጠ እንደሆነ ያሳያል፣ እንደዚህ የሕዝብ አስተያየት መመዘኛው ውጤት።

🇮🇷❌🇺🇸🇮🇱 - የኢራን ኤሮስፔስ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መጂድ ሙሳቪ ለአሜሪካውያን፡
- በአካባቢው ውስጥ የጦር ሠፈሮቻችሁን ዕጣ ፋንታ አይተናል፣ የጦር መርከቦቻችሁን ዕጣ ፋንታም በቅርቡ እናያለን።

🇺🇦❌🇷🇺 - የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ዛሬም፣ በሩሲያ ፐርም (ከዩክሬን 1,500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ) ላይ ጥቃት ሰነዘሩ። የነዳጅ መሠረተ ልማቶችም አውድመዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሩሲያ እጅግ አክሳሪ ጥቃቶችን በኃይል መሠረተ ልማቶቿ ላይ እያስተናገደች ትገኛለች። የዩክሬን ድፍረት እና ሩሲያ ግዛት ጠልቆ በመግባት ማጥቃት ተባብሶ ይገኛል። የሩሲያ አክቲቪስቶች ዛሬም ቁጣቸውን 'ለዘብተኛ' ባሉት የፑቲን አመራር ላይ አድርገው ታይተዋል። የጦሩ ትዕግስት 'እየተሟጠጠ' ነው የሚሉት እነዚህ ድምፆች ፣ እንዲህ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች የሚቀጥሉ ከሆነ የፑቲን ውድቀት ምክኒያቶች ሊሆኑ ይችላሉ እያሉ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው። በሌላ በኩል የሩሲያ መንግሥት እየደረሰበት ላለው የመሠረተ-ልማት ጥቃቶች 'አንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች' ተጠያቂ ናቸው ከማለት ውጭ፣ ለማስቆም ተጨባጭ እርምጃ ሲወስድ አይስተዋልም። በግንባር ያለውም ውጊያ ባለበት የቆመ ሲሆን፣ ሁለቱም ኃይሎች በያዙት ሥፍራ ፀንተው ከመዋጋት ውጭ አንዱ አንዱን ወደ ኋላ ሊገፋው አልቻለም።

🇺🇸🇮🇷 — የአሜሪካ ግዙፉ አይሮፕላን ጫኝ መርከብ፣ The USS Gerald R. Ford፣ 'እጅግ አስፈላጊ' ለተባለ ጥገና መካከለኛው ምሥራቅን ለቅቆ ወደ አሜሪካ ሊመለስ መሆኑን Washingt
🇺🇸🇮🇷 — የአሜሪካ ግዙፉ አይሮፕላን ጫኝ መርከብ፣ The USS Gerald R. Ford፣ 'እጅግ አስፈላጊ' ለተባለ ጥገና መካከለኛው ምሥራቅን ለቅቆ ወደ አሜሪካ ሊመለስ መሆኑን Washington Post ዘግቧል። አሜሪካ በቀጣይ ኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ እየተቃረበች ነው በሚባልበት በዚህ ሰዓት፣ የዚህ መርከብ ወደ አሜሪካ መመለስ በቀጠናው በሚገኘው የጦር ኃይል ላይ ከፍተኛ ክፍተትን ይፈጥራል ተብሏል፣ እንደ ዘገባው።

🇺🇸🇮🇷❗️ትኩስ - Axios እንደዘገበው፡ ትራምፕ በኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚችል አዳዲስ ወታደራዊ እርምጃዎች ከCENTCOM አዛዥ አድማይራል ብራድ ኩፐር እና ጄኔራል ዳን ኬይን ሐሙስ መረጃዎች
🇺🇸🇮🇷❗️ትኩስ - Axios እንደዘገበው፡
ትራምፕ በኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚችል አዳዲስ ወታደራዊ እርምጃዎች ከCENTCOM አዛዥ አድማይራል ብራድ ኩፐር እና ጄኔራል ዳን ኬይን ሐሙስ መረጃዎችን እና ትንታኔዎችን ይቀበላል። ትራምፕ እገዳውን እንደ ዋና መሳሪያ አድርጎ የሚመለከተው ቢሆንም፣ ኢራን ከያዘችው አቋም ወደ ኋላ የማትል ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ አያፈገፍግም። እቅድ አውጪዎች፣ ኢራን በአሜሪካ ኃይሎች ላይ የበቀል እርምጃ ብትወስድ አደጋው ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን እየገመገሙ ናቸው።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ዛሬም ከ 2 ሺ በላይ መርከቦች እና ከ 20 ሺ በላይ መርከበኞች፣ ማለፊያ አጥተው በሆርሙዝ ወሽመጥ ተቀምጠዋል። በመቶ ቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት የቀጠናው የንግድ ዝውውር፣ ኪሳራ በል
🇮🇷⚡️🇺🇸 ዛሬም ከ 2 ሺ በላይ መርከቦች እና ከ 20 ሺ በላይ መርከበኞች፣ ማለፊያ አጥተው በሆርሙዝ ወሽመጥ ተቀምጠዋል። በመቶ ቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት የቀጠናው የንግድ ዝውውር፣ ኪሳራ በልቶታል።

🇺🇸🛢 "አሜሪካ በከፍተኛ ደረጃ ነዳጅ እየሸጠች መጋዘኖቿንም እያራገፈች ነው፣ ዕድሜ ለእስያ ሀገራት ይሁንና።" አሜሪካ በኢራን ላይ ባደረገችው እገዳ ምክንያት፣ የአሜሪካ የንግድ ፔትሮሊየም ክምች
🇺🇸🛢 "አሜሪካ በከፍተኛ ደረጃ ነዳጅ እየሸጠች መጋዘኖቿንም እያራገፈች ነው፣ ዕድሜ ለእስያ ሀገራት ይሁንና።" አሜሪካ በኢራን ላይ ባደረገችው እገዳ ምክንያት፣ የአሜሪካ የንግድ ፔትሮሊየም ክምችት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ባዶ እየሆነ ነው። አሁን የኢራንን ዘይት ማግኘት የማይችሉ የእስያ ገዢዎች ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካን ዘይት ለመግዛት የሰጡትን ምክር እየተከተሉ የአሜሪካንን ዘይት ለመግዛት በመጋፋት ላይ ናቸው። የዚህ የጎንዮሽ ጉዳት አሜሪካውያን የጋዝ ዋጋ ሊጨምርባቸው እና በቅርቡ በነዳጅ ማደያዎች እና በአውሮፕላን ማረፊያዎች የነዳጅ እጥረት ሊያጋጥማቸው ይችላል፣ ልክ በተመሳሳይ መልኩ እያንዳንዱ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገር ላለፉት ሁለት ወራት ሲያየው እንደቆየው።

🇺🇸🇮🇷⚡️ — CENTCOM ኮማንደር አድማይራል Brad Cooper: በአሁኑ ወቅት የኢራን አገዛዝ መሸጥ የማይችለው 69 ሚሊዮን በርሜል ዘይት የጫኑ 41 መርከቦች አሉ። እነዚህን በማገዳችን ባ
+1
🇺🇸🇮🇷⚡️ — CENTCOM ኮማንደር አድማይራል Brad Cooper:
በአሁኑ ወቅት የኢራን አገዛዝ መሸጥ የማይችለው 69 ሚሊዮን በርሜል ዘይት የጫኑ 41 መርከቦች አሉ። እነዚህን በማገዳችን ባሉበት ቆመዋል። ይህ፣ የኢራን አመራር በገንዘብ ሊጠቀምበት የማይችልበት ከ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ብር ነው። በዚህ፣ እገዳው በጣም ውጤታማ እንደሆነ ማየት ይቻላል። የአሜሪካ ጦር ኃይሎች ይህን ግዳጅ እስከመጨረሻው ለማስፈጸም ቁርጠኛ ናቸው።

⚡️🇮🇱🇵🇸 የእስራኤል ቻናል 14: የእስራኤል ባሕር ኃይል በጋዛ ሰርጥ ላይ ያለውን የባሕር እገዳ አጠናክሮ መቀጠሉን ያስታወቀ ሲሆን ወደ ግዛቱ ሰብዓዊ ዕርዳታ ጭነው እየመጡ ባሉ መርከቦች ላይ
⚡️🇮🇱🇵🇸 የእስራኤል ቻናል 14: የእስራኤል ባሕር ኃይል በጋዛ ሰርጥ ላይ ያለውን የባሕር እገዳ አጠናክሮ መቀጠሉን ያስታወቀ ሲሆን ወደ ግዛቱ ሰብዓዊ ዕርዳታ ጭነው እየመጡ ባሉ መርከቦች ላይ በመሳፈር መቆጣጠር ጀምሯል።

🇺🇸⚡️🇮🇷 Rep. Pat Ryan (D-NY)፣ በኩዌት ለተገደሉት 6 የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላት Pete Hegseth ን ተጠያቂ በማድረግ መረጃ ለቋል። Pete Hegseth ወታደሮቹ በሞቱበት ሥፍራ በቂ ጥበቃና መከላከያ እንደሌለ እያወቀ፣ ወደ ሥፍራው ልኳቸዋል በዚያም በኢራን ሚሳዬሎች እንዲገደሉ ሆነዋል ብሏል። ባሁኑ ጊዜ ከዚያ የጦር ሰፈር በሕይወት የተረፉ ወታደሮች የጦር ኃይሎች ሚንስትሩን፣  Pete Hegseth ን ተጠያቂ እያደረጉ ናቸው።

🇺🇸🇮🇷⚡️ - Rep. Seth Moulton:ኢራን የሆርሙዝ ባህርን የመዝጋት አዝማሚያ እንደነበራት ታውቃለህ?  Secretary of War Pete Hegseth: በደንብ!  Seth Moulton: ታዲያ እንደዛ ከሆነ፣ ለምን አሜሪካ ያላትን አንድ ለናቱ የባሕር ፈንጂ ማጽጃ መርከብን ጦርነቱ ከመጀመሩ ከሳምንታት በፊት ወደ ሲንጋፖር ላክህ?

🇺🇸🇮🇷⚡️ — Secretary of War Pete Hegseth ዛሬ ስለ ኢራን ጦርነት በኮሚቴ ምርመራ ወቅት ከተናገረው፡
በዚህ ያላችሁ ዲሞክራቶች አሜሪካ ጦርነቱን እንድትሸነፍ ትፈልጋላችሁ። ጠላት የሚፈልገውን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በወታደሮቻችን ላይ ስትነዙ ትውላላችሁ። በዚህ ጦርነት 'አረንቋ ውስጥ ገብተናል' እያላችሁ ስትለፈልፉ ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማችሁም። 'አረንቋ' የኔ ትውልድ በኢራቅ እና አፍጋኒስታን ያሳለፈው ነው፣ ለዓመታት መውጣት አቅቶን የዳከርንበት ነው። የኢራን 'አረንቋ' አይደለም። የሁለት ወር ጦርነት እንደዚያ ሊባል አይችልም። ነገር ግን ትራምፕ ላይ ያላችሁ ጥላቻ ስላሳወራችሁ፣ ምንም ነገር ታወራላችሁ።

+2
🇮🇱 ⚡️🇱🇧 እንደ ዩክሬን እና ሩሲያ፣ የሂዝቦላን ድሮን በመፍራት፣ እስራኤልም የጦር መኪኖቿን፣ ታንኮቿን እና ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሁሉንም ዓይነት መሳሪያዎቿን ወንፊት አልብሳ ልትንቀሳቀስ መሆኑ ታውቋል። በዩክሬን ሎጀስቲክ የሚያልፍበትን መንገድን ጭምር ከጥቃት ለመጠበቅ፣ ከዳር እስከ ዳር  ተወጥሮ በሚለብስ የዓሣ ማጥመጃ መረብ መሸፈን በድሮን ዘመን የተለመደ ሆኗል።

🇮🇱⚡️ኔታንያሁ ሕገ ወጥ የሲጋራ እና የሻምፓኝ ስጦታዎችን ተቀብሏል በሚል ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል። - ከእስራኤል ቢሊየነር Arnon Milchan, ወደ $200,000 ዶላር የሚጠጋ የቅንጦት ዕቃዎች ተቀብሏል በሚል ነው። የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኔታንያሁ ላይ የተመሠረተው ክስ ውድቅ መሆን እንደሌለበት እና መቀጠል እንደሚገባው ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። በኔታንያሁ ላይ የተከፈቱት ክሶች ብዙ ጊዜ ሥልጣኑን አደጋ ላይ የጣሉበት ሲሆን፣ በጦርነት ምክኒያት በሚታወጅ የአደጋ ጊዜ አዋጆች የፍርድ ሂደቱ ሲቋረጥ እና ሲራዘም ቆይቷል። በእስራኤል ተቃዋሚ ፖርቲዎች ኔታንያሁ በሙስና ወንጀል ከሥልጣን እንደሚወገድ ተስፋ ያደርጋሉ።

🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፐዝሽኪያን ለኢራን መገናኛ ብዙሃን ስለ ኻሚኒ ሞት ዛሬ የተናገረው፡ "ትልቅ ኪሳራ ነው፣ በምንም ነገር አናካክሰውም። እሳቸውን በማጣት ከደረሰብን ህመም እና ስቃይ
🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፐዝሽኪያን ለኢራን መገናኛ ብዙሃን ስለ ኻሚኒ ሞት ዛሬ የተናገረው፡ "ትልቅ ኪሳራ ነው፣ በምንም ነገር አናካክሰውም። እሳቸውን በማጣት ከደረሰብን ህመም እና ስቃይ መውጣት አንፈልግም።"

🇮🇷❌🇺🇸 - ትኩስ፡ የኢራን የጸጥታ ምንጭ ለፕረስ ቲቪ፡ የኢራን ጦር ኃይሎች ትዕግስት ወሰን እንዳለው እና ዋሽንግተን እገዳዋን ከቀጠለች አሳማሚ ምላሽ አስፈላጊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። 🔹የኢራን ጦር ኃይሎች ያሳዩት ትዕግስት ለዲፕሎማሲ እድል ለመስጠት እና ዋሽንግተን የኢራንን ሁኔታ እንድትረዳ ጊዜ ለመስጠት ታስቦ ነበር። 🔹 የአሜሪካ ግትርነት በዚህ ከቀጠለ እና የኢራን ፍላጎት ውድቅ ከተደረገ፣ ጠላት በቅርቡ ለእገዳው የተለየ ምላሽ መጠበቅ አለበት።

🇦🇪 UAE ከተጨማሪ ዓለም አቀፍ ተቋማት እወጣለሁ በማለት እያስፈራራች ነው። ትናንት ከዓለም የነዳጅ አምራቾች ማህበር (OPEC) አባልነት ራሷን ማስወጣቷ ይታወቃል። UAE በተምሳሌነት እየተከተለች ያለችው ሀገር እስራኤል ይመስላል። እንዲህ ዓይነቱን እንቅስቃሴ፣ እስራኤል ከዓለም አቀፍ ተቋማት ራሷን በማግለል፣ ያለ ተያዥ እና ሀይ ባይ፣ ከተጠያቂነት ርቃ የፈለገችው ለማድረግ ረድቷታል።

🇪🇬 🇦🇪 የኤሜሬት ተፅእኖ ፈጣሪ፣ መጅድ አል አምሪ፣ እንዲህ ሲል በ X አካውንቱ ላይ ጽፏል፡ "ባሁኑ ጊዜ በዚህ ግጭት 'ገለልተኛ ነኝ' ብሎ የሚል ካለ፣ ከጠላትህ ጎን ነው። ወራዳ ስለሆነ ግ
🇪🇬 🇦🇪 የኤሜሬት ተፅእኖ ፈጣሪ፣ መጅድ አል አምሪ፣ እንዲህ ሲል በ X አካውንቱ ላይ ጽፏል፡ "ባሁኑ ጊዜ በዚህ ግጭት 'ገለልተኛ ነኝ' ብሎ የሚል ካለ፣ ከጠላትህ ጎን ነው። ወራዳ ስለሆነ ግልፁን አይናገርም።" ታዋቂው ግብፃዊ የጥበብ ሰው አምር ዋቂድ፣ ለመጅድ እንዲህ ሲል መልሶለታል፡ "አትጨነቅ፣ እኛ ገለልተኛ አይደለንም - ሁላችንም ከኢራን ጎን ነን!"

250 ድሮኖች በዚህ ሰዓት ከዩክሬን ተነስተው ወደ ሩሲያ እየበረሩ ነው።
250 ድሮኖች በዚህ ሰዓት ከዩክሬን ተነስተው ወደ ሩሲያ እየበረሩ ነው።