uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Kanalga Telegram’da o‘tish

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
195
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-730 kun
Postlar arxiv
"አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የኾኑ ሰዎች (ያጠሩታል)፡፡" [ሱረቱ አንኑር: 37] ሱፍያን አስሰውሪ ረሒመሁሏህ ይህችን አንቀጽ ሲያብራሩ፦ "ይገዛሉ እንዲሁም ይሸጣሉ፤ ግዴታ የሆኑትን ሶላቶች [ስግደቶች] በህብረት [በጀማዓ] ከመስገድ የሚተው አልነበሩም" ይላሉ። [ሒልየቱል አውሊያእ]

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦  “እወቁ! ከመልካም ስራዎቻችሁ ሁሉ በላጩ ሶላት ነው።” ( ሶሂህ አልጃሚዕ)

"... በአላህ ይሁንብኝ! ባንተ አማካኝነት አንድ ሰው አላህ ቢያቀናልህ ላንተ ከቀያይ ግመሎች የበለጠ ነው።” የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

"*የተውሂድ ጮራ ሲፈነጥቅ የሽርክ ፅልመት የገባበት ይጠፋል *የሱና ነፋስ ሲነፍስ ቢዳዓ የዶጋመድ ይሆናል *ትልቅ ክፍልን የሞላ ጨለማ አንድ ክብሪት ድራሹን እንደሚያጠፋው የተረጋገጠ ነው። ~ከኛ የሚጠበቀው በሽርክና በቢዳዓ ጨለማ ላይ የተውሂድና የሱና ሻማ መለኮስ ብቻ ነው!!"

እስልምና አውሮፓን እያጥለቀለቃት ነው። የኢድ ሶላት በሩሲያ ሞስኮ

ስለ እውቀት በኡስታዝ ኸድር አህመድ አልከሚሴ ሃፊዘሁላህ 🎓በወሎ_ወረኢሉ https://t.me/YewereiluMuslimoch/6144

#እውነታው ይኸው ነው‼ """"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" ኢትዮጵያ ውስጥ በኢስላም ስም የተተደራጄ ወይንም እነርሱ በሚሉት ወሀብያ ስም የተደራጄ አንድ ታጣቂ አንድ የፖለቲካ አደረጃጄት የለም! በኢስላም ስም የማታገል የሚገድል የሚያሳድድ የሚያወድም አንድ ሀይል የለም አንድ እንኳ!!! በኢስላም ስም እጅ የቆረጠ የለም! በኢስላም ስም አንበርክኮ የረሸነ የለም! በኢስላም ስም " በስመአብ ብለህ እረ¶¶¶ደው " እንዳሉት ያደረገ የለም! ኢትዮጵያ በሙስሊም ትመራ ብሎ የታገለ አንድ ሀይል የለም! ግና በተቃራኒው ከወለጋ እስከ አክሱም ፤ ከወሎ እሰከ ጎጃም ፤ ከጎንደር እስከ መተከል በኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት ፅንፈኞች የሚገደለው የሚጨፈጨፈው የሚሳደደው ሙስሊሙ ነው። መስጅዱ እንደ ሻማ የሚነድበት ፤ እየታገተ ከፍሎም የሚገደልበት ሙስሊሙ ነው! ንብረቱን ጥሎ የሚሰደደው ፤ ሀገር አልባ የተደረገው ሙስሊሙ ነው! አፈጠርክ ሰገድክ መቃብር ቀበርክ ተብሎ የሚረሸነው ሙስሊሙ ነው! ግና መታኝና አለቀሰ ቀደመኝና ከሰሰ እንዲሉ ራሳቸው ገድለው አሳደው አፈናቅለው መልሰው " ወሀብያ አራ¶¶ጅ¶ጅ" ነው ይሉናል። አያፍሩም። መሳጅዶቻችንን አውደመው ራሳችሁ አወደማችሁት ይሉናል። ቁርአናችንን ቀዳደው ራሳችሁ ቀዳዳችሁት ይሉናል! እስኪ የትኛው በማን የሚመራው የወሀብያ ድርጅት አጠቃችሁ ብላችሁ ጠይቋቸው ! አይመልሱላችሁም መልስ የላቸውምና! እኛን በሀይማኖታችን ያጠቁናል። ከዚያ እነርሱ በብሔር ግጭት ሲጠቁ ወሀብያ ብለው ይሰይሙና በጋራ ዘመቻ ይከፍታሉ! ለነርሰሱ መከላከያው ወሀብያ ነው ፣ ፖሊሱ ወሀብያ ነው ! መንግስቱ ወሀብያ ነው! አርሲ ላይ እስኪ አንድ ሙስሊም የትጥቅ ድርጅት ያሳዩንና እንፈር!! ኧረ እንቅፋት ራሱ ቢመታቸው ወሀብያ ነው! በተረት ተወልደው በተረት አድገው በተረት በሚገድሉ አካላት ጋር እንዲንኖር ፈረደብን። ተናግሮ ሊግባቧቸው የማይችሉ የ 15ኛው ክፍለ ዘመን ነዋሪያን እንኳ ለመሆን የማይመጥኑ አካላት ጋር መቁሰል እጣፈንታችን ሆነ! ሙስሊሙ ድምፁን አጥፍቶ ከመስራት ከመነገድ ውጭ እዚህች ሀገር ላይ በሚደረገው የቆሸሸ መገዳደል ውስጥ እንደ ሀይማኖት እጁን አላስገባም። የትኛውም የኢስላም ሀይማኖት መሪ ተገዳደሉ ብሎ አልባረከም! አላደረገም ! ይህንን ያውቁታል። ማን በየእምነት ተቋማቱ ጅምላ መሳሪያ አሽጎ እያሰለጠነ ለሽብር እንደሚያውል ያውቁታል! ሁሉም ያውቀዋል! እሺ ከነዚህ ጋር እስከመቼ ስንቆስል እንኑር!!!!

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ "ሰው ከሚወደው ጋር ነው።" [ቡኻሪና ሙስሊም)

የሰዎችን ስራ የወደደ የውመልቂያማ ከነሱ ጋር ይቀሰቀሳል። የሉጥ ሚስት ሊዋጥን "ግብረ ሰዶማዊነት"ባትፈፅመውም ከሚፈፅሙት ሰዎች ጋር ስለነበረችና ስራቸውን ስለወደደች ከነሱ ጋር ትቀሰቀሳለች። ከኢብኑ ተይምያ ንግግር የተወሰደ Ibnu Heyru

ሙዚቃ ሳይሆን ቁርአን የልብ መርጊያ መድሃኒት وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا وَادْعُوهُ خَوْفًا وَطَمَعًا إِنَّ رَحْمَتَ اللَّهِ قَرِيبٌ مِّنَ الْمُحْسِنِينَ (الأعراف)

#ሙስሊሞች #ለዘመናዊ #ስልጣኔ #ያበረከቱት #አስተዋፅኦ እነ ፍራንሲስ ቤከን በሙስሊም ሊቃውንት የቤተሙከራ ጥናት የተገኙ ሳይንሳዊ እውነታወችን ከአረብኛ ቋንቋ ወደ እንግሊዝኛ ተርጉመው እስካቀረቡበት ጊዜ ድረስ አውሮፓ የእውቀት ምንጭ አልነበራትም። ውድ የሂራ በተሰቦች:- አሁን ሙስሊሞች ለአለም ያበረከቷቸውን ሳይንሳዊ ግኝቶች አንድ ሁለት ብየ ላጫውታችሁ። 1. የአረብኛ ቁጥሮችን (1,2,3..) ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም ያስተዋወቁት ሙስሊሞች ናቸው፣ 2. የሂሳብ ስሌት የሆነውን algebraን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም ያስተዋወቁት ሙስሊሞች ናቸው፣ 3. በኮምፒውተር ቋንቋ ጉልህ ፋይዳ ያላትን ዜሮ (0)ን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም ያስተዋወቁት ሙስሊሞች ናቸው፣ 4. የመጀመሪያው የህክምና ኢንሳይክሎፒዲያ የተዘጋጀው በኢብኑ ሲና ነው። ይህ መፅሀፍ ''አል ቃኑን ፊ ጠቢብ'' ከሚል አረብኛ ስያሜ ወደ ''Canon of Medicine'' ተተርጉሟል። 5.ኢብኑ ሲና ከ700 በላይ የመድሀኒት አይነቶችን እስከ አጠቃቀም መመሪያቸው ለሰው ዘር አበርክተዋል። 6. ራዚ የተባሉት አሊም 100 የህክምና መፅሀፍትን እና የፈንጣጣ (smallpox) መከላከያ መድሀኒትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም አስተዋውቀዋል፣   ክፍል ሁለት ይቀጥላል...

======      ወገኔ ሆይ! አሕመድን መሆን ቢያቅትህ አቡል ሀይሠምን መሆን አያቅትህ!! ===== የኢማሙ አሕመድ ልጅ የሆኑት ዐብደላህ እንዲህ ይላሉ:– አባቴን ብዙ ጊዜ "አላህ ሆይ! አቡል ሀይሠምን ማረው" ሲሉ እሰማቸው ነበር። "አባቴ ሆይ! አቡል ሀይሠም ማነው?" ስላቸው እንዲህ አሉኝ:– "አንድ ከዘላኖች የሆነ ሰው ነው። ፊቱን አላየሁትም። ከተገረፍኩበት ቀን ቀድሞ በነበረው ሌሊት በጠባብ ጨለማ ክፍል ውስጥ አስገቡኝ። የሆነ ሰው በእጁ ነረተኝና "አህመድ ኢብኑ ሐንበል ነህ አንተ?" አለኝ። "አዎ" አልኩት። "ታውቀኛለህ?" አለኝ። "አይ" አልኩት። "እኔ ሌባው፣ አስካሪ መጠጥ ጠጪው፣ ሽፍታው አቡል ሀይሠም ነኝ። በተለያየ ጊዜ 18,000 አለንጋ እንደተገረፍኩ ከአሚረል ሙእሚኒን መዝገብ ላይ ተመዝግቧል። እኔ በሸይጧን መንገድ ላይ ሆኜ ይህን ሁሉ ችያለሁ። ስለዚህ አሕመድ አንተ በአላህ መንገድ ላይ ነህና ታገስ!!" አለኝ። · አስረውኝ ግርፋቱ በተጀመረ ጊዜ አለንጋው ጀርባየ ላይ ባረፈ ቁጥር የአቡል ሀይሠምን ንግግር እያስታወስኩ ለራሴ "አሕመድ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ ታገስ!" እለው ነበር። ★ (አሕመድ) ኢብን ሐንበል መሆን ካልቻልክ አቡል ሀይሠምን ሁን!! ★ ጥፋት ላይ የሰመጥክ ብትሆን እንኳን ሐቅን ውደድ!! ★ ወንጀል ላይ የተነከርክ ብትሆን እንኳን ለጌታቸው ታዛዥ የሆኑትን ውደድ!! ★ ሸይጧን የፈለገ ካንተ ቢያገኝ ለአላህ ሁን!! [መናቂቡል ኢማም አሕመድ: 450–451] [አስሶፍዋ: 1/485] ከዐረብኛ የተመለሰ IbnuMunewor

Repost from N/a
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በረመضاን ተቋርጦ የነበረው የመዝሀበ ሻፊዕያ ኪታብ ሙራጅዓችን ከነገ ጀምሮ ስለሚጀመር ሙራጅዓውን ለሚፈልጉ እሕት ወድሞች አሳውቋቸው ሸር አድርጉላቸው ስዓቱ ከዝሁር በኋላ 7:00በኢቶ 1:00በሳኡድ የሙራጅዓው ጉሩፕ 👇👇 https://t.me/+1cTEA2oSw8pjZjU0

የእምነት ወሳኝነት ~ በ240 ሂጅሪያ የሞቱት ታላቁ ዓሊም ዐብዱሰ፞ላም ኢብኑ ሰዒድ ሰሕኑን አልቀይረዋኒ ረሒመሁላህ በአንድ ወቅት ኢብኑል ቀሷ፞ር ዘንድ ገቡ። ታሞ ነበር። • “ምንድነው ይህ ሁሉ ጭንቀት?” አሉት። “ሞት መጣ! ወደ አላህ መጓዝ!” አለ። - “በመልእክተኞች፣ ሞቶ በመነሳት፣ በምርመራ፣ በጀነትና በእሳት፣  - ከዚህ ህዝብ በላጩ አቡበክር፣ ከዚያም ዑመር እንደሆኑ፣  - ቁርኣን የአላህ ንግግር እንጂ ፍጡር እንዳልሆነ፣  - አላህ በቂያማ ቀን እንደሚታይ፣  - እርሱ ከዐርሹ በላይ ከፍ ያለ እንደሆነ የምታምን አይደለህ?  - መሪዎች ቢበድሉ እንኳን ሰይፍ አንግበህ አትወጣባቸውም አይደል?” አሉት። “አዎ ወላሂ!” አለ። “ሙት ስትፈልግ፣ ሙት ስትፈልግ!” አሉት። [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 12/67] በዚህ ዐቂዳ ላይ ከሆነ የምትሞተው ተረጋጋ፣ ምን አስጨነቀህ? እያሉት ነው። መከራ ማለት ሙሲባ ማለት ዐቂዳን ሳያስተካክሉ መሞት ነው። የዐቂዳችንን ነገር ዘወትር እንከታተል። IbnuMunewor

አንዲት አሮጊት ስዑዲያዊት ለህክምና ግብፅ ሀገር ሄዳ የተለያዩ ቅርሶች ጎበኘች። ከጎበኘቻቸው ቅርሶች መካከል የሐሰን ኢብኑ ዓሊይ ቀብር ይገኝበታል። ሰዎች፦"ያሀጃጃህ ይህ የሁሰይን ቀብር ነው ለምኚው ሃጃሽን ያወጣልሻል!" አሏት እርሷም እንዲህ ስትል መልስ ሰጠቻቸው፦ "የአያቱ ቀብር እኛ ጋር ነው አንድም ቀን ለምነናቸው አናቅም!!"

ለዱአቶች ማዘን.mp31.56 MB

#ከደጋጎቹ_ቀዬ ~ የሕያ ብኑ ኻሊድ አልበርመኪይ (190 ሂ.) በየወሩ አንድ ሺህ ዲርሃም ለሱፍያን ብኑ ዑየይናህ (198 ሂ.) ይደጉማቸው ነበር። በዚህ የተነሳ ሱፍያን - ረሒመሁላህ - እንዲህ እያሉ ዱዓእ ያደርጉለት ነበር፦ "اللهم إنه قد كفاني المؤونة، وفرغني للعبادة، فاكفه هم آخرته".. "አላህ ሆይ! እሱ የኑሮ ጣጣዬን በመሸፈን ለዒባዳ ነፃ አድርጎኛልና የኣኺራውን ሃሳብ አንተ ሸፍነው።" የሕያ ሲሞት ጊዜ ከጓዶቹ ውስጥ አንዱ በህልም አይቶት "አላህ እንዴት አደረገህ?" ብሎ ሲጠይቅ "በሱፍያን ዱዓእ ሰበብ ማረኝ" እንዳለው ተናግሯል። [አልቢዳያ ወኒሃያ፡ 13/679] = Ibnu Munewor

ውድ ቤተሰቦቻችን ተጠንቀቁ ! በቅርብ ጊዜ የጓደኞቻችሁን ወይም የምታውቋቸው ሰዎች ስም የዋትስአፕ (WhatsApp) አካውንቶችን በመጥለፍ / Hack በማድረግ የገንዘብ ማጭበርበር ድርጊቶች በስፋት እየተፈጸሙ ይገኛሉ። ማጭበርበሪያው እንዴት ነው እየተፈጸመ ያለው ? አጭበርባሪዎቹ የቅርብ ጓደኛችሁን ወይም ደግሞ የምታውቁትን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ የእነሱን ምስል እና ስም በመጠቀም መልዕክት ይልኩላችኋል። " የባንክ ትራንስፈር ሊሚት ስለሞላብኝ፣ ለአንድ ሰው አሁን 50,000 ብር (ወይም ሌላ መጠን) ላክልኝ፤ ነገ ጠዋት እመልስልሃለሁ " የሚል አስቸኳይ ጥያቄ ያቀርባሉ። ብሩን የምትልኩበትን የማታውቁትን ሰው ስም እና የባንክ አካውንት ይልኩላችኋል። እናተም " ጓደኛዬ ተቸገረ ፤ ነገ ይመልሳል " ብላችሁ ትልካለችሁ። ከዛም ሰውየው የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል። ለምሳሌ ከቀናት በፊት አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በዚህ መንገድ 50 ሺህ ብር ተጭበርብሯል። ወንጀለኞች የሰዎችን አጣዳፊ ችግር እና መተማመን ለክፉ ዓላማቸው ስለሚጠቀሙበት ማንኛውንም የገንዘብ ዝውውር ከማድረጋችሁ በፊት ደውሎ ማረጋገጥ ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ ነው። ለጥንቃቄ ፦ 1. በዋትስአፕ የገንዘብ ጥያቄ ሲቀርብላችሁ፣ መልዕክቱን የላከው ሰው ትክክለኛ ጓደኛችሁ መሆኑን ለማረጋገጥ በስልክ መስመር ደውላችሁ አነጋግሩት። 2. ወደ ስልካችሁ የሚመጣን ማንኛውንም የSMS የማረጋገጫ ኮድ ለማንም ሰው  በፍጹም አትስጡ። 3. በዋትስአፕ ሴቲንግ ውስጥ በመግባት 'Two-Step Verification' ማብራታችሁን እርግጠኛ ሁኑ። የዋትስአፕ አካውንታችን ይጠለፋል ? አዎ ይጠለፋል ፤ ነገር ግን አጠላለፉ እንደ ኮምፒውተር ቫይረስ በቀጥታ ሲስተሙን ሰብሮ በመግባት ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ ተጠቃሚውን በማታለል የሚፈጸም ነው። ° የSMS ኮድ ማጭበርበር ፦ ይህ አሁን ላይ በብዛት ማጭበርበር እየተፈጸመበት ያለው መንገድ ነው። አጭበርባሪው የእንተን ስልክ ቁጥር ተጠቅሞ ዋትስአፕ ለመክፈት ይሞክራል፤ ከዚያ ዋትስአፕ ለእናተ የማረጋገጫ ኮድ ይልካል። አጭበርባሪው በተለያየ ዘዴ ለምሳሌ ፦ " ኮዱ በስህተት አንተ ጋር ስለሄደ ንገረኝ " በማለት ያንን ኮድ ይቀበላችኋል። ኮዱን ካገኘ በኋላ የናተን ዋትስአፕ በራሱ ስልክ ላይ ይከፍተዋል። ° ዋትስአፕ ዌብ ፦ አንድ ሰው ስልካችሁን ለአፍታ አግኝቶ በዋትስአፕ ዌብ አማካኝነት የQR ኮዱን በራሱ ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ስካን ካደረገ አናተ የምትልኳቸውና የመጡላችሁ መልዕክቶች በሙሉ በቀጥታ ማየት ይችላል። ° ስፓይዌር ፦ ይህ እጅግ በጣም የላቀ ጠለፋ ነው። ስልካችሁ ላይ አደገኛ ሊንኮችን ስትነኩ ወይም ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎችን እንደ እነ GB WhatsApp ስትጭኑ ስልኩ ውስጥ የሚቀመጥ ሰላይ ሶፍትዌር መልዕክቶችህን ለሌላ አካል ሊያስተላልፍ ይችላል። እንዴት መከላከል ይቻላል ? 1. ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) ፦ ወደ Settings > Account > Two-Step Verification > Enable ማድረግ። የራስህን የ6 አሃዝ ሚስጥር ቁጥር (PIN) መፍጠር። ይህ ካለ አጭበርባሪው የSMS ኮዱን እንኳ ቢያገኝ ይህንን PIN ካላወቀ አካውንቱን ሊከፍተው አይችልም። 2. Linked Devices መፈተሽ ፦ ዘወትር Settings > Linked Devices የሚለውን በመጫን አናተ የማታውቁት ኮምፒውተር ወይም ስልክ መኖሩን አረጋግጡ። ካለ "Log Out" አድርጉት። 3. ኮድ ለማንም አትስጡ ፦ ማንኛውንም ዓይነት የ6 አሃዝ ቁጥር በSMS ሲመጣላችሁ ለሰው አትናገሩ። በቀጣይ ደግሞ ይፋዊ ባልሆኑ የቴሌግራም አፕሊኬሽኖች (በሶስተኛ ወገን የቴሌግራም አፕሊኬሽኖች) ስለሚመጣ መዘዝ ፣ ቴሌግራም እያስተላለፈ ስላለው ማስጠንቀቂያ ፣ ያለ ሰዎች ፍቃድ ስለሚካሄድ እንቅስቃሴና የማጭበርበር ስራዎች ዝርዝር መረጃ እንልክላችኃለን። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሚያዚያ 3 ቀን 2018