✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Kanalga Telegram’da o‘tish
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
193
Obunachilar
-224 soatlar
-47 kun
-630 kun
Postlar arxiv
"(የዱንያ )ሰዎች ሁሉ በእንቅልፍ ላይ ናቸው።ነገር ግን ሲሞቱ ይነቃሉ!!"
(ከሰለፎች)
......
ቀድሞ ለመንቃት ግን..ስንት ሟችን ይሆን ማየት የሚያስፈልገን?!
حَتَّى إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ
لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ
አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡
«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡»
المؤمنون99-100
☑️ #የጤና #አዳም #የተለያዩ #የጤና #ጥቅሞች
====
✍ጤና አዳም በጡንቻ ላይ የሚያጋጥም ሕመምን፣ ውጥረትንና በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥም ሕመምን የማርገብ ሁኔታ ያለው ሲሆን፤ መጠቀም ያለብን ግን
የእፅዋት ባለሙያን በማማከር መሆን አለበት።
✍በሻይ መልክ መጠቀም ለሽንት ቧንቧ፣ ለአንጀትና በአጠቃላይ ለደንደኔ ኢንፌክሽን መድኃኒት መሆን ይችላል።
✍ጤናአዳም ለምግብ መመረዝ በተለይ ደግሞ ሳልሞኔላ የተባለውን ባክቴሪያና ሌሎች አደገኛ ተህዋስያን ሊከላከለን ይችላል።
✍ከዚህ በተጨማሪ ጤና አዳም የፀረ ባክቴሪያ ባሕሪ ስላለው ልንጠቀመው እንችላለን።
✍ይህ እጽ ነርቮችን የማረጋጋት ኃይል ማለትም የአራጌነት (Sedative) ባሕሪ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፤ በመሆኑም የእንቅልፍ ማጣት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ብንጠቀመው ሊያረጋጋን ይችላል።
✍ጤና አዳም በአንጓ (መገጣጠሚያ) ላይ የሚያጋጥም ብግነትን ሰከን የማድረግ ኃይል ስላለው ችግሩ ያለበት ሰው አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ በሻይ መልክ ቢጠጣ እፎይታን ሊያገኝ ይችላል።
✍የጤና አዳም ዘይት በዘመናዊው ዓለም ለሳሙናዎችና ለኮስሞቲክስ ምርቶች ጥሩ መዓዛ ጥቅም ላይ ይውላል፤ ይህ ዘይት መጠኑ ሲበዛ የመርዛማነት ባሕሪ ስላለው በቀጥታ በቆዳ ላይ በጥቅም ላይ አይውልም።
✍ነገር ግን ተመጥኖ ለቆዳ የተለያዩ ጥቅሞች እንዳስገኘ ትናቶች ያሳያሉ፤ ይኸውም የፀረ-ፈንገስ ባህሪ ስላለውና ቆዳን የማጥራት አቅም ስላለው ነው።
☑️ #የጤና_አዳም_የጎንዮሽ_ጉዳት
======
ከጤና አዳም የሚወጣው ዘይት በሰውነት ላይ በቀጥታ ከተጠቀምን ሰውነት ውኃ ሊቋጥር እንዲሁም ሊቀላ ይችላል፤ በከፍተኛ መጠን ከተጠቀምነው ደግሞ የሰውነት መመረዝ ሊያከትል ይችላል።
በተለይ ደግሞ ፅንስ ያላቸው እናቶች በከፍተኛ መጠን ከተጠቀሙት ፅንሳቸውን ሊያስወርድ ይችላል፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የጨጓራ ሕመም ሊያስከትል ይችላል።
ይህም በመሆኑ በዘመናዊው ዓለም የጤና አዳም የሕክምና አገልግሎቱ የተገደበ እየሆነ መጥቷል።
ከጤናዳም የሚገኘው ዘይት በብዛት ከተወሰደ ውርጃ ሊያስከትል ይችላል።
#የጤና_አዳም_የጤና_በረከቶች🌻
======
ጤና አዳም (Ruta chalepensis) ውልደቱ አውሮፓ ባልካን አካባቢ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው ሩታ ቻለፐንሲስ (Ruta chalepensis) ይሰኛል፡፡ፀረ- ባክቴሪያ፣ፀረ-ፈንገስ፣ፀረ- መርዝማ እና ፀረ- ውክሳጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በአውሮፓ የባህል ሕክምና ውስጥ ገናና ስም አለው፡፡ ዛሬም ቢሆን በአውሮፓ ባህላዊ ሕክምና ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
✍በኢትዮጵያ የባሕል ሕክምና ጤና አዳም ለሆድ ሕመም፣ ለተቅማጥ፣ ለጆሮ፣ ለልብ ሕመም፣ ለኪንታሮት፣ ለኢንፍልዌንዛና ከአንጀት መታወክ ጋር ለተያያዙ በሽታዎች አገልግሎት ላይ ይውላል።
✍የደረቀው ፍሬ ከተፈጨ በኋላ ተፈልቶ በመጠጣት ለተቅማጥ ሕክምና ሲውል፤ ቅጠሉ ከተከተከተ በኋላ በውኃ ተደርጎ ለሕፃናት ሆድ ሕመም ይሰጣል። ተክሉ ተድጦ ሲልም ደግሞ ለኪንታሮት በሽታ ይወሰዳል።
✍በሰሜን አፍሪካ በሚገኙ አገሮች ደግሞ ከተክሉ ተዘፍዝፎ የሚገኘው ፈሳሽ ለጉንፋን፣ ለጆሮ ሕመምና ለአንጀት መታወክ ይወሰዳል።
✍የጤና አዳም ሽታ በጣም ጠንካራ በመሆኑ ሰዎች ጊንጦችን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይጠቀሙታል።
✍በአልጀሪያ ሰዎች ተክሉ ከተዘፈዘፈ በኋላ የሚገኘውን ፈሳሽ በጠብታ መልክ በአፍንጫ ይወስዳሉ፤ በተለይ ለሕፃናት ይህ ሕክምና የሚሰጠው ለሚያስመልስና ትኩሳት ላለበት ነው።
✍ጤና አዳም በአንዳንድ የዓለም ሀገራት መርዛማ እንስሳት(ለምሳሌ በእባብ) ለተነደፍን ማርከሻ ይጠቀሙበታል።
☑️በመሆኑም ጤናአዳም እንደ ቀንድ አውጣና ሦሥት አፅቄ ያሉ ነፍሳትን የማራቅ አቅም ስላለው በጓራችን ቢኖር ተመራጭ ነው፤ እንዲሁም ለቁንጫ መድኃኒት ነው።
በሸዕባን ፆም ማብዛት
~
ያለነው የሸዕባን ወር ላይ ነው። ይሄ ወር ፆም ማብዛት የሚወደድበት ወር ነው። እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡-
كان يصوم شعبان إلا قليلاً
“(ነብዩ ﷺ) ሸዕባንን ጥቂት ሲቀር እንዳለ ይፆሙት ነበር፡፡” [ሙስሊም፡1156]
=
IbnuMunewor
ወሳኝ በሆኑት የህይወትህ ውጣ-ውረዶች ላይ ያልሆኑ ሰዎችን አታማክር።ልምዱ ያላቸውን፣በእድሜ የገፉ፣በእውቀት የደረጁ፣ሶላትን በአግባቡ የሚሰግዱ አማኞችን ማማከርን የመሰለ ነገር የለም።
وَالَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِرَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَمْرُهُمْ شُورَى بَيْنَهُمْ..
أَنْت لَا تَخْسَرُ شَيْئًا بِحُسْنِ الظَّنِّ،
وَلَكِنَّك تَخْسَرُ كَثِيرًا بِسُوءِ الظَّنِّ.
የአፍር እና የሶማሌ(ኢሳ ጎሳ) ጦርነት ግን ለምን?
ሐጅ በሽር ዳውድ እንዲህ በማለት ታሪካቸውን ያካፍሉናል። በሐይማኖት ሳቢያ የደረሰብኝ ግፍ ሁሉ ተሰማኝ አንገፈገፈኝና በእርሻ ስራ ለመሰማራት ወሰንኩ። ከአፍር ባለሀብቶች ጋር ተስማማሁ እና በሐረር ውስጥ በምትገኝ የረር በምትባል ትንሽ ከተማ በኩል አድርጌ ወደ እርሻው ለመሔድ እዛች ከተማ ደረስን። እንዳጋጣሚ ለሶስት ቀን ያህል ቆየን።
እዚያም የአፋርና የኢሳ ጎሳዎች በጥይት ሳይሆን በአይኖቻቸው በጨለማ ሳይሆን ጥርር ባለው ቀን ከከተማው ውጭ ሳይሆን እዛው ከተማ ውስጥ የሚገዳደሉ ይመስላሉ።
ጋዜጠኛ ነኝ በማለት ወደ አውራጃው አስተዳደር ኮሎኔል ጽ/ቤት ብቅ አልኩ።ሙስሊም መሆኔን አላወቁም ፤አክብረው ተቀበሉኝ ፣ ቡና መጣና ፉት እያልኩ ከሁለቱም ጎሳዎች ነፍሰ ገዳዩ እየተለቀመ ህጋዊ ፍርድ እየተሠጠ ከድሬዳዋ ጀምሮ እስከ ናዝሬት ባለው የዛፍ ግንድ ላይ አንድ መቶ ያህሉ ቢሰቀሉ ሰላምና ፀጥታ ይሰፍናል። ህዝቡም ሰልጥኖ ወደ ልማት ስራ ይገባል።
ለምን ይህ አይደረግም አልኳቸው? እርሳቸውም በጣም ደነገጡ። ፊታቸውን ኩምትር ጭምድድ አደረጉና ሌባ ጣታቸውን ቀስረው አፍንጫቸው እና አፋቸው ላይ አድርገው "ኡስ ኡስ "ብለው ከኔ ሌላ ሰው አደራ እንዳይሰማህ አሉኝ። ደነገጥ ብዬ ምነው አልኳቸው? እሳቸውም ከቀይ ባህር ጀምሮ በወሎና በመንዝ ተራራ ስር አልፎ እስከ ኬኒያ ባለው ምድረ በዳ እና ሜዳ ላይ የሠፈረው ህዝብ እስላም መሆኑን አታቅም? በኢትዮጵያ ዙሪያ ያለው አረብና እስላም መሆኑን አታቅም? እነዚህ ሁለት ብሔሮች ማለትም አፍርና ሶማሌ ተምረው ቢሰለጥኑና አንድ ቢሆኑ በአካባቢያቸው ካለው እስላምና አረብ እየተገናኙ ኢትዮጵያዊ ለሆነው የክርስቲያን ህዝብ ካባድ ችግር ይፈጥራሉና እንደዚህ ዘላን ሁነው "እየተገዳደሉ ይኑሩ" የሚል ጥናት ተደርጎ ከነገስታቶች የተሰጠ የበላይ መመሪያ መሆኑን ጋዜጠኛ ሁነህ እንዴት አታውቅም ሲሉኝ ደነግጨ ከቢሯቸው ወጣሁ ይላል። ወንድማችን
ይሄ ጉዳይ ግን በታላላቅ መሪዎቻችን መፍትሄ ያገኘ ይመስላል።
ስለዚህ ሙስሊሞች ሆይ በየጊዜው በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በብሄር እና በሰፈር እየተከፋፈልን እርስ በርሳችን ከምንገዳደል፣ ከምንናቆር እና ጀርባ ከምንሰጣጥ ይልቅ ቀርበን በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በአንድ ላይ ብንመክር፣ አንዳችን ለአንዳችን እየተረዳዳን እና እየተባበርን፣ በልዩነታችን ደግሞ ተከባብረን የጋራ ጠላቶቻችንን ድል የምናደርግበት ሁኔታዎች ቢፈጠሩ ባይ ነኝ።
ለማንኛውም አስቡበት!!
አጋቡኝ!
"አላህን ላጤ ሆኜ መገናኘት አልሻምና አጋቡኝ።"
(አል ኡም ሊሻፊዒይ 4/32)
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ረዲየላሁ ዐንሁ ሊሞቱ ሲል በጠና በታመሙበት ሕመማቸው ላይ ሆነው የተናገሩት
ከቤተሰቡ አንድ እንኳን አሰተዋይ እንዴት ይጠፋል??
አይይይ አባባ ታጁ (የሐሰን ታጁ አባት)
የአለጥላጭነት ሰንደቅ አውለብላቢዎች
~
ሷሊሕ ታጁ (የሐሰን ታጁ ወንድም) አፄዎቹን እያወደሰ ፅፏል። እሱም፣ ወንድሙም፣ መሰሎቻቸውም የአፄዎቹ አወዳሽ ካምፕ ዘንድ ለመወደድ ሲያሸረግዱ ማየት የተለመደ ነው። የለየለት አለጥላጭነት!! Trying to be more Catholic than the Pope አይነት ነገር።
1- አፄ ቴዎድሮስ ወሎ ላይ በርካታ ሙስሊሞችን ለማውራት በሚሰቀጥጥ መልኩ ጨፍጭፏል። ራስ ዐሊን ሲዋጋ የሙስሊምና የኦሮሞ ስሩን እያጣቀሰ ነበር የሚያብጠለጥለው። ራስ ዐሊ ግን ሙስሊምም አልነበረም፣ ኦሮምኛ ተናጋሪም አልነበረም። ወደ ኋላ ተመልሶ የአያቶቹን ዘር መዞ ነበር ቴዎድሮስ ይህን የሚያደርገው። አቅም አጥቶ እንጂ ኋላ በአፄ ዮሐንስ የተፈጸመው አስገድዶ ማጥመቅና የጅምላ ፍጅት የቴዎድሮስ ህልም ነበር።
2- አፄ ዮሐንስ አስገድዶ እምነት የማስለወጥ አዋጅ አውጆ በጊዜው ወሎ ላይ ገዥ የነበረውን አባ ዋጠውን አስጠምቆ ወደ ደጃች ኃይለ ማርያም፣ ሙሐመድ ዐሊን ደግሞ ወደ ራስ ሚካኤል አስቀይሮ ያስጠመቀ፣ እልፍ አእላፍ ሙስሊሞችን በግዳጅ እምነት ያስቀየረ፣ ከ20ሺ - 35ሺ የሚገመት ቁጥር የወሎ ሙስሊሞችን የጨረሰ፣ መጨረሻም በሱዳን ደርቡሾች የእጁን ያገኘ የሸይ ^ጧን ቁራጭ ነው።
3- አፄ ምኒልክ የወሎ ሙስሊሞችን በብዙ የገፋ መሆኑ የሚታወቅ ነው። የነ ጦለሐ ጀዕፈር ትግልኮ ከነ ምኒልክ ጋር ነበር። የጨለንቆ እልቂት በታሪክ ያለ ነው። ሐረር ላይ መስጂዶች ወደ ቤተ ክርስቲያን የተቀየሩበት ታሪክ ለነ ሷሊሕ ታጁ ቁም ነገር ሆኖ የሚወሳ አይደለም።
4- አፄ ኃይለ ሥላሴም ከሙስሊሞች አንፃር ከታዬ እጅግ መሰሪና አግላይ ነበር። አገሪቱ የሱ የግል ንብረት ነበረች። ሷሊሕ ታጁም ይሁን የሚያሸረግድላቸው አካላት ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ አዎንታዊ ውጤቶችን ለአፄዎቹ በመስጠት ላይ ሲጠመዱ የሚዘነጉት እውነት ቢኖር ሃገሪቱ ለገጠማት ኋላ ቀርነትና የእልቂት ታሪክ ተጠያቂዎቹ እነዚሁ አፄዎች መሆናቸውን ነው። ታሪክ እየተመረጠ አይፃፍም።
"አይ እሱ ያለው ከሃገር አንፃር ... " የሚሉ እንደሚኖሩ እጠብቃለሁ። ሙስሊም ነኝ የሚል ሰው ከሁሉ ነገር በፊት ቀዳሚ መለኪያው እምነቱ ነው። እነዚህ ግን አፄዎቹ በሙስሊሞች ላይ ያደረሱት በደል ሲወራ ከነሷራዎቹ በፊት ቀድሞ ይከፋቸዋል። ከሸረሪት ድር የደከመ መከላከያ ይደረድራሉ። ውሏቸው፣ መከላከላቸው፣ ፖስታቸው፣ ላይካቸው ከነዛ ጋር ነው። ዝንብን ያቆሸሻት ውሎዋ እንጂ ተፈጥሮዋኮ አይደለም። እነ ሷሊሕ ታጁ በኢትዮጵያ ሙስሊም ላይ የተለጠፉ መዥ ^ ገሮች ናቸው።
=
ኢብኑ ሙነወር
* ሃይማኖታዊ በዓላት፡
በዓላት ደግሞ የእምነት መገለጫዎች ናቸው። እያንዳንዱ እምነት የራሱ የሆነ የኢባዳ (አምልኮ) ስርአት አለው። በሌላ እምነት በዓል ላይ ተገኝቶ እንደ ባለቤት መሆን ወይም ያንን በዓል የሚያደምቁ ስራዎችን መስራት የራስን "አቂዳ" (እምነት) አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ነው።
3. ለወንድም እና እህቶች የቀረበ ምክር
ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን! አላህ ዘንድ ክብር ያለው የሙስሊም ማንነታችሁ ነው። በሌሎች ዘንድ ለመወደድ ወይም "ዘመናዊ" ለመምሰል ተብሎ የአላህን ህግ መጣስ መጨረሻው ኪሳራ ነው።
* ማንነታችሁን አትለጥጡ፦
ሙስሊምነታችሁን በኩራት ያዙ። ከሌሎች ጋር በሰላም ኑሩ ነገር ግን በዓላቶቻቸውን እና የአምልኮ ስርአቶቻቸውን አትጋሩ።
* አላህን ፍሩ፦
ማንኛውም የምናደርገው ተግባር አላህን ያስቆጣል ወይስ ያስደስታል? የሚለውን መመዘን አለብን። የሌሎችን በዓል ማድመቅ አላህ ዘንድ ተጠያቂነትን ያመጣል።
እውነተኛ አብሮነት ማለት አንዱ የሌላውን እምነት ድንበር አክብሮ፣ ሳይቀላቀልና ሳይመሳሰል በሰላም መኖር ማለት ነው። አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን፣ ማንነታችንንም የምንጠብቅ ያድርገን።
ምናለ መርህ ቢኖረን
በእስልምና እምነት መርህ መሰረት፣ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመልካም መኖር እና በደስታም ሆነ በሃዘን መረዳዳት የሚበረታታ ቢሆንም፣ በሃይማኖታዊ ስነስርዓቶች ላይ ግን የራስን ማንነት ጠብቆ መቆየት መሰረታዊ ጉዳይ ነው።
የእምነት ማንነትን መጠበቅና ከሌሎች ጋር ያለው ማህበራዊ ግንኙነት
ሙስሊም በምድራዊ ህይወቱ ከሰዎች ጋር በሚኖረው ግንኙነት "አሚን" (ታማኝ) እና ለሁሉም መልካም አሳቢ እንዲሆን ታዟል። ሆኖም ግን ይህ መልካም ግንኙነት የራሱን የእምነት መለያና ድንበር አሳልፎ እንዲሰጥ አያደርገውም።
በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ፣ በሌሎች እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውን ሃይማኖታዊ በዓላት (እንደ ጥምቀት ያሉ) ከእምነታችን መርህ ውጭ በሆነ መልኩ የመሳተፍ ዝንባሌዎች ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል።
1. "መመሳሰል" (ተሸቡህ) ምንድን ነው?
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ባስተማሩን ሀዲስ፡ "በአንድ ህዝቦች የተመሰለ እርሱ ከነርሱው ነው" ይላሉ። ይህ ማለት የአንድን እምነት ተከታዮች ልዩ መለያ የሆኑ መንፈሳዊ ተግባራትን፣ አለባበሶችን ወይም ስነስርዓቶችን መጋራት በእስልምና ዘንድ የተከለከለ ተግባር ነው። አላህን የሚያስቆጣውም የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ጥራቱን የጠበቀ የእውነት ጎዳና ትቶ ሌላን መንገድ ሲከተል ነው።
2. በማህበራዊ ጉዳይ እና በበዓል መካከል ያለው ልዩነት
ልብ ሊባል የሚገባው ታላቅ ነጥብ አለ፦
* ማህበራዊ ግንኙነት፡
በሰፈር ውስጥ የታመመን መጠየቅ፣ የተቸገረን መርዳት፣ በንግድ መተሳሰር እና በጋራ ሰላምን ማስፈን የሚበረታቱ ተግባራት ናቸው።
Repost from SadatKemal Abu Meryem
ሑዘይፋ ኢብኑል የማን መስጂድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000680622543
አቢሲንያ ባንክ: 115183818
አዋሽ ባንክ: 01437999853200
ሒጅራ ባንክ: 1000034780001
ዘምዘም ባንክ: 0054754710301
ዳሸን ባንክ: 2959082956711
+251 911 678 186
በወንጀልህ ተፀፀት ወደ አሏህም ተመለስ እንጂ በጭራሽ ተስፋ እንዳትቆርጥ ! ብቸኛው አምላካችን አሏህ አዛኝ ፣ ፀፀትን ተቀባይ እና ይቅር ባይ ነው
ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር
